አልሸሹም ዞር አሉ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አልሸሹም ዞር አሉ!

Postby ኳስሜዳ » Wed Jan 03, 2018 6:44 pm

ማእከላዊ እስር ቤት ከሚገኝበት የአራዳ ሰፈር ወደ ካሳንቺስ ዮርዳኖስ ሆቴል ስለተዘዋወረ ነው የተዘጋው ሌላ አዲስ ነገር የለውም፡፡

ኢሕአዴግ እስረኞችን እፈታለው ማለቱ መልካም ነው ፤ ሁኔታዎችን በጥሞናና በርጋታ መመልከት ያስፈልጋል ፤ ወያኔ የፖለቲካ አጀንዳዋን ለማስፈፀም የገፅታ ግንባታ እየሰራች ነው ፤ ለስር ነቀል ለውጥ የምንተጋ ወገኖች ሰከን ማለት ይጠበቅብናል ፤ ወያኔ ባንድ ጊዜ የተለያዩ ነገሮችን ተናግሮ እያመምታታ ነው ። ተግባራዊ ስራዎችን በማየት መጓዝ እንጂ የወያኔ የፕሮፓጋንዳ ሰለባ መሆን የለብንም ። ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው ፤ የዜጎች የመኖር ዋስትና ባልተረጋገጠበት አገር የፖለቲካ መተማመኛ ማግኘት አይቻልም ፡፡

ሌላው ማእከላዊ የማሰቃያ ጣቢያ የሕንፃ ቅያሬ አደረገ እንጂ ከነአካታው አልተዘጋም ፤ ከአራዳ ወደ ካዛንቺስ ተቀየረ ፤ ማእከላዊን አስመልክቶ ዛሬም ደርግ የሚባለው ነብሰ በላ ኢሕአዴግ በሚባለው ሰው በላ ደም መጣጭ እየተወነጀለ ነው ፤ የራሷ ቁስል እየለበለባት በከሰመ ቁስል የምትሳለቅ ኧረ ማነች ? ማእከላዊ የስቃይ ማእከል 26 አመታት ምን ሲሰራበት ነበር ? ባለጠባሳዎች ይናገሩ ።

ለቁጥር የሚታክቱ ድብቅ የደህንነት ሰቆቃ የማሰቃያ ማዕከላት ባሉበት አዲስ አበባ ውስጥ በይፋ የሚታወቀውን የማእከላዊ ማሰቃያ እስር ቤትን ዘጋን ማለት ለውጥ አይደለም ። ማእከላዊ እስር ቤት ከሚገኝበት የአራዳ ሰፈር ወደ ካሳንቺያ ዮርዳኖስ ሆቴል ስለተዘዋወረ ነው የተዘጋው ሌላ አዲስ ነገር የለውም ። ደርግን ወንጅሎ ሙዚየም ለማድረግ ወያኔ የሞራል ብቃት የለውም ።
ምንጭ፡ ምንሊክ ሳልሳዊ
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2149
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: አልሸሹም ዞር አሉ!

Postby ዞብል2 » Thu Jan 04, 2018 2:24 am

ደርግ ከደየመ 17ዓመት ሆነው .....ወያኔዎች ማዕከላዊን 26ዓመት ሙሉ ምን ሲያደርጉበት ነበር?አልቤርጎ?ወይስ የጌታቸው አሰፋና የደብረፅዮን ከረንቦላ ቤት?ቅቅቅቅቅቅ ይቺ ናት የወያኔዎች ጨዋታ!!
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2049
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: አልሸሹም ዞር አሉ!

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Jan 04, 2018 10:07 am

ማዕከላዊ በደርግ ግፈኞች ያለጎሳ ልዩነት የደርግ ተቃዋሚ የሆኑ ሁሉ ጥፍራቸው እይተነቀለ በሽቦ ገመድ እየተዘለዘሉ ይታረዱ ነበር፡፡በወያኔ ዘመን ደግሞ ማዕከላዊ የትግሬ ዘር የሌለባቸው ተቃዋሚዎች ጥፍር እየተነቀሉ በገማ ካልሲ አፋቸው እየታፈነ በብረት የሚቀጠቀጡበትና ብልታቸው ከጥቅም ውጭ እየሆነ የሚገደሉበት ስፍራ ነው፡፡

ዞብል2 wrote:ደርግ ከደየመ 17ዓመት ሆነው .....ወያኔዎች ማዕከላዊን 26ዓመት ሙሉ ምን ሲያደርጉበት ነበር?አልቤርጎ?ወይስ የጌታቸው አሰፋና የደብረፅዮን ከረንቦላ ቤት?ቅቅቅቅቅቅ ይቺ ናት የወያኔዎች ጨዋታ!!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1546
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests