የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ፍቅር ሊወርህ ነው
ሰላም ሐገርህን ሊወር ነው
ሰላምና ፍቅር ተባብረው በአበባ በእንድሽድሽ ከዛም አልፎ በቡና ሐገርህህን ሊወር አበባየሆይ እያለ ነው ሆያ ሆየ እያለ ነው
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ .....
ሰላምና ፍቅር ድምበርህ፡ ተወረው ዛሬ ሰላምና ፍቅር ድምበሮችህ ድምበሮችህ ሊሁኑ ነው
የመጣው ጦር ፍቅር ስለሆነ አደገኛ ነው ሲል BBC ፡ CNN ዘግቦታል በሆነ ነገር አዳምጠው
ጦሩ አደገኛ በመሆኑ የአበባ ቦምብ ይበትናል የቄጤማ ፈንጂ ይጎዘጉዋዝል ቡና እንደ ውሃ ይረጫል ይህንን ጉዳይ የተባበሩት መንግስታት ስለተመለተው በጣም ገርሞት ፍቅር ያሸንፋል በማለት ዘሎታል
ጦሩ በጣም አደገኛ በመሆኑ እየዘመረ ነው በአሁኑ ሰዓት የሚገኘው ከዛም እንድሽድሽ ይበትናል
እንድሽድሽኑን የእቶሚክ ኤጀንሲ የሚደንቅ ነው በማለት የአቶሚክ ኤጄንሲ እየለቃቀመ ሲበላ ታይቶእል ከዛም መጣፈጡን ተናግሮአል በማለት በየሚዲያው እየተነገረ ነው
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ
እንድሽድሹን ብሉ ሰላምና ፍቅር እንዲገባችሁ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ
ዶሮ ይታረዳል ፡በግም ይታረዳል ፡በሬም ይታረዳል ከዛም በፍቅር ምሳ ይበላል ራትም ይደገማል
ቁርስ ላይ ሙልሙል ዳቦ ወይም አምባሻ በሻይ በቡና ይቀርባል
ከዛስ
ከዛማ
አበባየሆይ
ለምለም
ባልንጀሮቼ
ለምለም
ግቡ በተራ
ለምለም
እንጨት ሰብሬ
ለምለም
ከዛስ
ሆያ ሆዬ
ሆ
እዛ ማዶ
ሆ
አጋፈሪ
ሆ
ይደግሳል
ሆ
ዘመን ከዘመን ተሸጋግሮ
ተገለባብጦ ተዙዋዙሮ
ጦርነትን ላለፈው ዓመት ወርውሮ
መከፋፈልን ላለፈው ዘመን አሽቀንጥሮ
ይጉዋዝ ጀመረ ተደማምሮ
ይነጉድ ጀመረ ተፈቃቅሮ
መልካም ዘመን ለሁላችንም
ፈላስፋው