ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !!!

Postby ቆቁ » Fri Jun 28, 2019 7:42 pm

ዋለልኝ ለምን ለምን ሞተ ? ማርታ ለምን ለምን ሞተች ?
ሆነብኝሳ ነገሩ ?
ያሳዝናል ፡ ግራ ያጋባል ?
ግራ የሚያጋባው ፈላስፋውን ብቻ ነው? ወይስ መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ፡ እነ ጠ/ሚኒስቴር ዓቢይንም ጭምር ?
ነፍስ ይማር እስከ ዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ ምድር
ኢትዮጵያዊ ሆናቻሁ ተወልዳችሁ ኢትዮጵያ ሆናችሁ ለተቀበራችሁ ወንድሞቼ እህቶቼ አባቶቼና እናቶቼ
እጅግ ያሳዝናል
እንደው ነገሩ ..... ?????
የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር !
የጎሳ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ መስመር አይደለም! አይሆንምም!!

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Tue Jul 02, 2019 5:31 pm

ስለ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የቆጥ የባጡ ተቀባጥሮአል
ስለ ቁዋንቁዋ እድገት ብዙ ተቀዶአል
ስለ ባህል እድገት በጣም ነው የተደሰኮረው
ስለ ሕገ መንግስቱ ብዙ ተለፍልፎአል
ስለ ፌዴሬላዚም ሁሉም እየተነሳ ጡሩምባ ነፍቶእል

ይህ ሁላ ቱሪናፋ በልሂቃን ሳይሆን በትምህርት ቤት ባለመሰጠቱ የሚገባው በጣም ጥቂቱ ነው ነገር ግን ለብዙሃኑ የሚያስተላልፈው
መልእክት ግን አስቀያሚ ነው
ስለ ዲሞክራሲ ማውራት የሚቻለው ዲሞክራሲን የተማረ ካለ ብቻ ነው
ስለ ባህል የሚወራው የባህላዊ ልዩነትንና ተቻችሎ መኖርን በትምህርት ገበታ ላይ የተማረ ካለ ብቻ ነው
ስለ ሕገ መንግስቱ የሚወራው ስለ ሕገ መንግስቱ ከሞላ ጎደል በትምህርት ቤት ተማሪው ግንዛቤ ሲኖረው ነው
ስለ ፌዴሬላዚም የሚወራው በየትምህርት ቤቱ ተማሪው ስለዚህ ጉዳይ እውቀት ሲኖረው ነው

ልሂቃን ፖለቲከኞች የሚደነቁዋቆሩበት ምክንያትም ይህ ነው ፡፡ እነሱ አዋቂዎች ተንታኖች ሌላው ግን መሐይምን ፡፡
ትምርስምስ ተፈጠረ ብሎ መደነቅ መገርምም የሚያስፈልግ አይሆንም ፡፡
አብዛኛው በትምህርት ቤት ያላለፈበትን ጉዳይ ልሂቃን ሲዘበራርቁበት ምን ይፈጠራል ብሎ መጠየቅ ትልቅ ችሎታ ነው ብሎ ፈላስፋው ያምናል ፡፡
የተማሪው ንቅናቄም እንደዚሁ ዓይነት ነበር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲቀባጥሩ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ኢትዮጵያ የሆነው ማለትም ያለቀው ግን ምንም የማያውቀው የሐይስኩል እና የኢለመንታሪ ተማሪ ነበር

ከላይ የጠቀስኩዋቸው ባህል ቁዋንቁዋ ሕገ መንግስት ፌዴራሊስም አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚባሉት በኢትዮጵያ የትምህርት ገበታ ላይ ተነበው ተሰተምተው የማያውቁ ነገሮች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ አለመተማመንን ፡ መጠራጠርን የፈጠሩ ይመስላሉ
ለዛም ነው
በፈስ ቡክ በዩቱቦ እና በመሳሰሉት ችግሩ እየጎላ የመጣው
ሌላው ደግሞ በሐገር ውስጥም የዚህ የፈስ ቡክ ጩሀት በሕዝባችን ላይ የነበረውን አለመተማመን ወደ ላይ እያጦዘው ለመሆኑ አንዳንድ ሁኔታዎች ያስረዳሉ
በአጠቃላይ የጎሳ የፌዴሬላዝም የመጨረሻው እጣ ግለሰብን ከግለሰብ ጋር ማጣረስ ፡ አለመተማመን ፡ መጠራጠር፡ ቅናትና ፡ ምቀኝነትት መፍጠር ይሆናል፡፡
ለዚህም ብዙ በሐገራችን ያሉትን ጠቅላላ ሁኔታውዎች በምሳሌ ማስቀመጥ ይቻላል
ለምሳሌ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ግለሰብ የሆቴል ዘበኛ ሆኖ ቢቀጠር ጥያቄ ሊቀርብ ይሆናል ማለት ነው ፡ ከየት ነው ?
ወይም መቀሌ ላይ አንድ ሆቴል ውስጥ አንድ ግለሰብ በሳህን አጣቢነት ቢቀጠር ጥያቄ ሊቀርብ ነው ማለት ይሆናል፡ ከየት ነው ?
ይህ ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ግለሰብን ወይም ቡድንን ወይም ብሄርተኛን ብቻ ሳይሆን ግራ የሚያጋባው መንግስታዊ አስተዳደር ውስጥ ላይ የሚገኙትን ሁላ የሚጠቀልል ነው፡፡

ስለሆነም ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ የብሄርተኝነት ፈደራሊዝም የሙከራ ጊዜ አክትሞእል ይላል ፈላስፋው
የጎሳ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አያስፈልግም
ልዩነታችን እና አንድነታችን ለዘላለም ይኖራል
ነፍስ ይማር !!
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Thu Jul 04, 2019 9:53 pm

የምርጫ ውይይት ተጡዋጡፎአል
ምርጫው መካሄድ የለበትም አለበት የሚለው አተካራ እየተካረረ ከመጣ ውሎ አድሮእል

ፈላስፋው ምርጫው በምን አጀንዳ ነው የሚካሄደው የሚለው ነገር ነው ያልገባው
በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ ወይም በላቲን አሜሪካም ሆነ በእስያ ምርጫ ሲካሄድ ከደህንነት ሌላ ብዙ አጀንዳዎች አሉት፡፡
ለምሳሌ
ስራን በምድር ላይ ብቻ ሳይሆን ጸሐይን በሚዞሩዋት ፕላኔቶች ላይ እንፈጥራለን
የትምህርት እድል ምድር ላይ ሳይሆን ማርስ ላይ እንፈጥራልን
ጡረተኞች የነጻ ቪላ ቤት እንዲያገኙ እናደርጋለን
የሕክምና አገልግሎት በሮቦት በየቤት እንዲዳረስ እናደርጋለን
የሕጻናት መዋያ በብዛት እንደ ባቄላ እሸት እንፈለፍለዋለን
መንገድ በሰማይም በምድር በባህርም እንሰራለን
ኢኮኖሚውን እናናጋዋለን ወይም እናጋንነዋለን
ገለመሌ ገለመሌ ፡ገለመሌ ገለመሌ የመሳሰሉት
የምርጫ አጀንዳው ምንድነው ?
የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ የነጻ አውጭ ድርጅት የሚባሉት የምርጫ አጀንዳቸው ምንድነው ?
በምን አጀንዳ ነው እኔ ፈላስፍው የምመርጠው
በጎሳ
በብሄርተኝነት
በያኔው በትራይባሊዝም ዘመን እንደነበረው ?
የብሄርተኝነት ፖለቲካ አለመተማመንን የሚፈጥር የተበለሻሸ የሕብረተሰብ ችግር ነው
የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
ነፍስ ይማር !!
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Fri Jul 05, 2019 8:49 pm

ምርጫው
እሺ ምርጫው ይካሄድ ብንል
ምርጫው ብሄር ተኮር ይሁን ማለት ይሆን?
ከዛስ መንግስታዊ መዋቅሩ ልክ እንደ 27 ዓመታቱ ብሄር ተኮል ይሁን ማለት ይሆን ?
በአጠቃላይ
የትግራይ ሕዝብ የትግራይ ተወላጅ
የኦሮሞ ሕዝብ የኦሮሞ ተወላጅ
የአማራ ህዝብ የአማራ ተወላጅ
በቃ እንደዚህ ነው ምርጫ ማለት ይሆን ? በዚህ ሁኔታ ስለአንድነት ማውራት ይቻል ይሆን ?

ሕገ መንግስቱ ይከበር ፡
አንድ ሕገመንግስት የሚከበረው ሕገመንግስቱ ሕዝባዊ ምርጫ ተካሂዶ በሕዝብ የተመረጡት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ያረቀቁት ህገመንግስት ብቻ ሲሆን ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ መወከል የሚችለው

ለመሆኑ እስከ ዛሬ ያለው ሕገመንግስት በየትኛው የሕዝብ ተመራጮት የተረቀቀ ሕግ ይሆን ?

ለዚህም ነው ሕገመንግስቱም ዲሞክራቲክ ያልሆነ የሚባለው

ስለዚህም ነው የብሄር ተኮር ፖለቲካ ዲሞክራቲክ ያልሆነ መጠራጠርን አለመተማመንን የሚፈጥር ስርዓት መሆኑን ዓለም የሚያስረዳው

ሕገመንግስቱ ይከበር ከማለት ደግሞ ሕገመንግስቱን ለማስከበር አብሮ መስራት ደግሞ ሌላ ነገር ነው ፡፡
መፍትሄ አብሮ መፈለግ ደግሞ ሌላው ትልቅ ነገር ነው ፡፡

ይህንን አብሮ መስራት ነው የብሄር ተኮር ፖለቲካ አራማጆች መስራት ያልቻሉት ምክንያቱም እንዴት እንደሚሰራ ስለማያውቁ

ራስንን በክልል ከልሎ ሕገመንግስቱ ይከበር ብሎ መጮህ ፋይዳ አያመጣም ፡፡
ነገር ግን ተባብሮ ሕገመንግስቱን ለማስከበር መስራት መታገል ግን ትልቅ ነገር ሆኖ ሳለ የሆነ ጥግ ይዞ ወይም ራስን ከልሎ በፌስ ቡክና በቲቪ " ሕገመንግስቱ ይከበር " ማለት ፋይዳ የሌለው የፖለቲካ አተላ ነው
ይህ አባባል እገሌ ወይም የክክልሉ አስተዳደር ሕገመንግስትቱ ይከበር አለ አሉ አለ አሉ አለ አለ አሉ ከማለት በስተቀር
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Sun Jul 07, 2019 4:49 pm

የከሸፈ ጭንቅላት እንጂ የከሸፈ መፈንቅለ መንግስት የለም
ጭንቅላት ሲከሽፍ የሆነ ያልሆነውን ይጽፋል የሆነ ያልሆነውም ይቀባጥራል፡፡
በሐገራችን የተደረጉት ትክክለኞቹ መፈንቅለ መንግስቶች ጊዜያቸውን ጠብቀው ለውጥ ወይም ነውጥ ለማምጣት በቅተዋል፡፡
ይህንን ሁኔታ ለጊዜ እንስጠውና እንለፈው

ዋናው የኢትዮጵያ ችግር የከሸፈ ጭንቅላት ነው ፡ የከሸፈ ጭንቅላት ስለዲሞክራሲ እያወራ የብሄርተኝነት ፖለቲካ እያራመደ ብሄር ከብሄርን የሚያጋጨው ክፍል ነው፡፡
በአንድ ሕብረ ብሄር በሚኖርበት ሐገር የብሄርተኝነት ፖለቲካ ለብሄርተኖቹ እንጂ ለሌላ ብሄርተኛ የዲሞክራሲ ወግም መንገድም ሊሆን እንደማይችል እያወቀ በከሸፈ ጭንቅላት ሕዝቦችን ለማሳመን የሚሞክር ብቻ ነው የከሸፈ ጭንቅላት ያለው ፡፡
ለምን የከሸፈ ጭንቅላት?
የጥንቱ አባቶቻችን ይህንን ችግር መጽሐፍ ሳያነቡ ፡ ትምህርት ቤት ሳይሄዱ፡ ዲግሪ ሳይኖራቸው ፡ ዶክትሬት ሳይኖራቸው ፡ፕሮፈሰር ሳይሆኑ በደመ ነፍስ ብቻ ይህ የጎሳ ፖለቲካ ከባድ የሰብዓዊ መብት ችግር መሆኑን ተረድተው ፡ ሰላምና ፍቅር እንደማያመጣ አውቀው ኢትዮጵያን ለኛ ትተው አልፈዋል ፡፡

የአሁኑ ዘመን ልሂቃን ዶክትሬትና ማስትሬት በኮሮጆ ታቅፈው ስለ ጎሳ ፖለቲካ ዲሞክራሲነት ሲያስረዱን የማይገርመን የከሸፈ ጭንቅላት በመሆኑ ነው ፡፡

ሌላው የከሸፈ ጭንቅላት ደግሞ በቁመና ያለበትን እና የእውነታውን ዓለም በመዘንጋት በዲጂታል ዓለም ውስጥ ራሱን ዘፍቆ የሚደናበርና በዚህ ድንብር ውስጥ እንኪያ ሰላምታ በመስጠት የሚጣለዘው ወገን ነው ፡፡
አክቲቪስት ነኝ ብሎ ሲዘባርቅ፡ ለዚህ ለዘባረቀው ዝብረቃ ደግሞ ተከታይና አጨብጫቢ ሲያገኝ፡ ከዛም በሐገር ውስጥ እሰጥ አገባ ውስጥ ሲገባ፡ የከሻሸፉ ጭንቅላቶች ራሳቸው ከሽፈው ሌላውን ለማክሸፍ ሲጣደፉ ዘመነ ክሽፈት ለመሆኑ ምንም መጽሐፍ መጻፍ ወይም ማንበብ አያስፈልግም፡፡
በዚህ በከሸፈ ጭንቅላት ሞባይላቸውን የሚጠቀጥቁትን የሐገሬ ዝምቦችና ትንኞሽ ይቁጠራቸው ፡፡
ሞባይሉን ወይም የሆነ ኮምፑተሩ ላይ አድፍጦ ዝምቦች እሽ እያለ በመተክተክ ጭንቅላቱን ለሚያከሽፈው ወገን አንድ የምለው ቢኖረኝ

የሚኪ ሾው አብጃለሁ የሚለውን እንዲከታተልና እጅና እግሩን ከሞባይልና ከኮምፑተር ላይ እንስቶ ወደ እውነተኛው ዓለም ራሱን አዙሮ ከክሽፈት የሚፈወሰበትን መንገድ ቢፈልግ መልካም ነው ይላል ፈላስፈው
የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኖራል
ብሄርተኛት የዲሞክራሲ መንገድ አይደለም፡፡
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ምክክር » Sun Jul 07, 2019 5:59 pm

መልካም ፍረጃ ነው፡፡
ሕዝበ አዳም ሲበጭጭ አንተ ጤነኛ ሆንክ፡፡
የሌላው ጤንነት ላንተ አይበጅ ይመስል!

አንድነታችንን ካናጉት ዉስጥ ምግባረ ብልሹነት አለበት፡፡ ያውም በዋናነት!
ያስተዳደጋችን ችግሮች እና እሱን ተከትሎ የህብረተሰቡ የሞራል ዝቅጠት ስልጡን እንዳንሆን አድርጎናል፡፡ ሰው ሞራል ከሌለው ለራሱም አይሆን፡፡ ገና ይቀረናል፡፡ አንድ የመጨረሻ ትንቅንቅ፡ ንትርክ ና ግጭት፡፡ በዚህ እሳት ዉሥጥ የሚወለድ ትውልድ ይሆናል የሚታደጋት-ኢትዮጵያን!
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Thu Jul 11, 2019 6:58 pm

ምክክር ያልከው ገብቶኛል
ልቀጥል ፡
1. የሳይኮሎጂካል ጦርነት
ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም ይባላል
2. የባዮሎጂካል ጦርነት
የእምቦጭ ወረርሽን በጣና ሐይቅ እና የበለስ ዛፍ መወረር ከፔሩ በገባ ትል ፡
3. የባቢሎን ግምቦች በአዲስ አበባ እና በከተሞቻችን
ምክክር ወደ አንተ፡
በሶስቱን ነገሮች ላይ ሌላ ጊዜ
ያልበጨጨ ፈላስፋ የለም አርኬሚዲክስ በለው ፓይታጎራስ ወይም አርስቶትል ወይም ፈላስፋው
ፈላስፋ የሚበጭጨው እውነት የመሰለውን ነገር ሲከተል ጅራቱ እንዳያመልጠው በህልሙም በውንም ስለሚሮጥ ነው
በጨጨ እና አበደ ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው
በጨጨ ሲልህ ሰውየው ከራሱ ጋር ማውራት ጀመረ ማለት ነው ቀዥበር አድርጎ ዘወር አለ እንደማለት ነው
አበደ ማለት ግን በስድብና እና በርግማን አተካራ ውስጥ ትገባና እስከ መጠራጠስ የምትደርስበት ሁኔታ ነው
ለዚህም ነው አብጃለሁ እና በጭጫለሁ ሁለት የተለያዩ ነገሮች የሚሆኑት
የበጨጨ ለመደባደብ አይሮጥም ያበደ ግን እንደምታውቀው ነው፡፡
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Fri Jul 12, 2019 8:28 pm

------------------
ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም፡፡ ይመስላል የሕወሃት መግለጫ
ጊዜ ያወጣዋል ብለን ጃምፕ እንበለው ይህንን ጉዳይ
-------------
እንደመር ፡ ተደመሩ ፡ የሚለው ነገር የማቲማቲካል ግድፈት ያለበት መሰለኝ ባልሳሳት ?
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሊደመሩ የኢሕአዲግ ጥምሮች ግን በመቀናነስ ላይ ይገኛሉ
ከዛም የሚገርመው ጊዜና ወቅት በመጠበቅ የኢሕአዲግ ጥምሮች ከመደመር በላይ በሌላ ስሌት እየተጉዋዙ ነው፡፡
higher matimatics በሚያስረዳው መሰረት እየተጉዋዙ ነው
ይህ higher matimatics የሚያስረዳው የማቲማቲካል ቀመር combination የሚባለው ነው

የኢሐዲግን ጥምረት combination በሚባለው የሂሳብ ስሌት ስናሰላው ነገሩ ሁላ የዞረ ፡ የጦዘ ድምር ሆኖ እናገኘዋለን
በዚህ ስሌት ሁሉም እንደ ድመት እና አይጥ ሆኖ ነው የሚጠባበቀው ምክንያቱም አንድ ነገር ብቻ ነው ይህም የብሄርተኝነት ፖለቲካ
የኢሐዲግ ፓርቲዎችን እና ሌሎች በዚህ የጎሳ ፌዴራሊዝም ፖለቲካ የተደራጁትን ድርጅቶች በዚህ combination በሚባለው የሂሳብ ስሌት መሰረት ለማዋሃድ ቢሞከር መልሱ ቀላል ነው፡፡ ግራ የሚያጋባ ግምባር ተፈጥሮ ኢለመንታሪ የሆነውን የመደመር ሕግ የሚያናጋ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Sun Jul 14, 2019 6:43 pm

የመደመሩ በኢሐዲግ መካከል ውስብስብ ያለ ነገር ለመሆኑ እስቲ በቀላል ምሳሌ እንረዳው
2+2 = 4
ወይም
1+1= 1
1+1 = 2
እያልን ብንደመር ትክክለኛው መደመርር ነው ይህ መደመር ነው ባለፈው እንደመር በሚለው መፈክር ስር የተካተተው

በጎሳ ፌዴራሊዝም ግን እንደመር ሌላ ስሌት ይዞ ነው የተገኘው
ይህ ደግሞ የ Vriables ስሌት የሚባለው ነው

x+y = what ?
a+b = what =
or x+y = 3 ከዛስ መልሱ ምንድነው
የመደመሩ ስሌት ትክክል ሆኖ
መልስ ያጣ መደመር ሳይሆን መልስ ያጣ ፌዴሬሊስም ነው ፡ የጎሳ ፌዴራሊዝም
የጎሳ ፌዴራሊዝም በምን ይተካ ?
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ምክክር » Mon Jul 15, 2019 12:47 am

መደመር አንድነት ነው፡፡ ቁጥር አይደለም፡፡ ለመደመር ደግሞ አንድ ጠንካራ ጎን በቂ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት፡፡ ያን ጠንካራ ጎን ያንቋሸሹብንን መጠራረግ ተገቢ ነው፡፡ ከላይ ጀምሮ፡፡ ለውጥ ማምጣቱን ባንክድም ዓብይም ቢሆን መምራት ካልቻለ ይወገዳል፡፡ የለውጥ ደጋፊዎች ከወያኔ አሽቃባጮች ለየት የሚያደርገን ይህ ነው፡፡ ለሰራ እጃችን ለጭብጨባ ላልሰራ ደግሞ እግራችን ለካልቾ ዝግጁ ነው፡፡

ፈላስፋው ወዳጄ ያነሣኸው ነጥብ ወሳኝ ነው፡፡
ትልቁ ሥራ የጎሳ ፌደራልዝም ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት መስራቱ ላይ፡፡ ያለውን መግራት ወይም መቀየር፡፡ ሁለቱም ሥርዓት፡ መግራቱም መቀየሩም ከባድ ስራ እንዲሆን ያደረጉትን የያኔ አናጢዎች ያሁን መናጢዎችን ማስወገድ የመጀመሪያ ሥራ ይሆናል፡፡ በውስጥህ ነቀርሳ ይዘህ እስከመቼ?
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Mon Jul 15, 2019 9:09 pm

ምክክር ወንድሜ መመካከር መልካም ነው እንቀጥል፡፡
ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ይባላል መሰለኝ
የፌዴራሊዝም ተቃዋሚ ያለ ይመስል በየጢሻው መሽገው ሲቀዱ ሰምቼ በጣም ነው የገረመኝ
ስለ ፌዴራሊዝም ለመስበክ የግድ የሆነ ጥግ ይዞ ነገም መግለጫ ተነገወዲያም መግለጫ ቢሰጡ ለፌዴራሊዝም መልስ የሚሆን አይመስለኝም ፡፡
ስለ ፌዴሬላዚም ለመስበክ የግድ የሆነ ጥግ ይዞ የሆነ ልሂቅ ጠርቶ መወያየትም ለፌዴራሊዝም መልስ አይሆንም ፡፡
ይህንን ለማለት ያበቃኝ
በሕዝቄል ጋቢሳ የተሰጠው ያልተመቻቸ ሌክቸርና ፡ የተጠየቀው ጥያቄና መልስ ነው

ይድረስ ለሕዝቄል ጋቢሳ
ፌዴራሊዝምን ስትተነትነው ሌሎችም ሲተነትኑት በጣም ነው የገረመኝ
የኢትዮጵያን ታሪክ ከ50 ዓመታት በፊት ያለውን ለመጥቀስ አለመፈለግህ ደግሞ በጣም ነው እጅግ የሚያስገርም ነው፡፡
coming together or hoding together በማለት ረቀቅ ያሉ የእንግሊዘኛ ቃላትን በመደርደር ስትወያዩ ሰምቼ በጣም ነው የገረመኝ ምንያቱም እነዚህ የየእንግሊዘኛ ቃላቶች ለፌዴራሊዝም መልስ ይሰጣሉ ብላችሁ ለማመናችሁ ምንም ማስረጃ አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም የምትወረውሩዋችው የልሂቃን ቃላት ናቸውና ፡ ልሂቃን በቃላት የተካኑ ናቸው እንደሚባለው ፡፡
አንተም ተጨማሪ የአንግሊዘኛ ተርሚኖሎጂ በመጠቀም አዳማጩን ለማስረዳት በሳቅና በፈገግታ ስትተነትን እጅጉን ነው ተገርሜ ያዘንኩት ፡፡

ፌዴራሊዝም Living together , working together, learning together ... የሚሉትንም ነገሮችን የሚያጠቃልል መስሎኝ ? ተሳስቼ ይሆን ?
ለመሆኑ coming together በሆኑት ሐገሮች (አንተ እንደጠቀስከው) ለምሳሌ በምትኖርባት ሐገር አሜሪካ እንዴት ነበር ፌዴራሊዝም የተመሰረተው? አሁንስ እንዴት ነው ፌዴራሊዝም
በጫና ፡ ወይስ በጡጫ ወይስ በርግጫ ? እስቲ ለማስረዳት የምትችል ባትሆንም ለማሰብ ጊዜ ይሰጥሃል በማለት ነው ፈላስፋው ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው
ለመሆኑ ፌዴራሊዝም በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ላይ ሲደረመስ Reconciliation የሚባል ነገር ተደርጎ ነበር ?
ለምን ያን ጊዜ Reconciliation አልተደረገም ? እንዲደረግስ አልሆነም ?
ከፌዴራሊዝም በፊት የሰው ልጅ መብት መከበር ነው ዋናው ትልቅ ነገር አይደለም እንዴ ?
የፖለቲካ ፓርቲ አባላትም በዚህ በሰው ልጅ መብት ማክበር ታጥነው እና ተጠምቀው ማለፍ የግድ ይሆንባቸዋል መሰለኝ ባልሳሳት
ስለሆነም የአሁኑ ሐገራችን ያለችበት ችግሩ ይታይህ ይሆን ?
እስቲ ሌላ ምሳሌ ልስጥህ በአሜሪካ ያለው ፌዴሬሽን ምን ዓይነት የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው ያሉት ?
Republican Party
Democratic Party


Minor parties
Party Ideology )
[6] State Legislators
Libertarian Party
Green Party
Constitution Party
Party for Socialism and Liberation
American Freedom Party
American Solidarity Party
Black Riders Liberation Party
Citizens Party of the United States
Communist Party USA
Freedom Socialist Party
Humane Party
Independent American Party Paleoconservatism
Justice Party Social democracy
Legal Marijuana Now Party
Modern Whig Party
Protectionism
National Socialist Movement
New Black Panther Party

ከዋኖቹ ፓርቲ ሌላ ተጨማሪ ጥርቅምቅም የሆኑ ትናንሽ ፓርቲዎችን አስቀምጬልሃለሁ
ምን ይታይህ ይሆን ? ምን ታዝበህ ይሆን ከነዚህ ፓርቲዎች ስም
ለመሆኑ በሐገራችን እንዴት ነው እንደዚህ ያለ ፓርቲ በዚህ ፌዴራሊዝም ስርዓት ለመመስረት የሚቻለው ?
እስቲ መንገዱን አሳየን ?
በትግራይ ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ የመድረክ ፓርቲ ፡ በኦሮሞ ክልል ውስጥ የኢዜማ ፓርቲ ወይም የቅንጅት ፓርቲ የመሳሰሉ መድበለ ፓርቲዎች የሐገሪቱን ፌዴሬሽን ፌዴሬሽን እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው የፖለቲካ ምህዳር በየብሄሩ አለ ?

(ማሳሳቢያ ፡ እኔ ፈላስፋው የማንም ፓርቲ ደጋፊ አይደለሁም ለምሳሌ ያህል ነው የጠቀስኩዋቸውን )
እዚህ ላይ ወደ መደመር ልምጣ

a+b+c+d = coming together or holding together ? እንዴት ?
a= ኦሮሚያ
b = ሱማሌያ
c = አማራ
d= ትግራይ
እነዚህ ምሳሌዎች ናቸው

coming or holding together , living together, working together , learning together ... ሁሉም መደመር ናቸው መሰለኝ ፡፡ አይደሉም እንዴ ?
ይቀጥላል አንተንም ይመችህ ነፍሱ !!
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Tue Jul 16, 2019 6:39 pm

ይድረስ ለሕዝቄል ጋቢሳ
በአሜሪካ ባለው የፌዴራል ስርዓት ውስጥ ዲሞክራት በለው ሪፐብሊካን በሁሉም ስቴት ውስጥ ይገኛሉ ብለን ብንገምት
በነዚህ ፓርቲዎች ውስጥ በጠቅላላው በአሜሪካ የሚገኘው ህዝብ ሙሉ በሙሉ ይካፈልበታል ፡ የኤርትራው ተወላጅ ለምርጫ የሚያደርገው ውድድር ምሳሌ ይሁንህ ?
ለመሆኑ በአሜሪካ ስንት ዓይነት ሕዝብ የስንት ሐገር ሕዝብ የስንት ብሄር ሕዝብ ይገኛል ?

ለመሆኑ አንድ የትግራይ ተወላጅ በኦሮሚያ ለምርጫ ለመወዳደር የሚያስችለው መስፈርት አለ ብለህ ትገምታለህ?
አንድ የኦሮሞ ተወላጅ በአማራ ለምርጫ ለመወዳደርር የሚያስችለው መስፈርት አለ ብለህ ትገምታለህ ?
አንድ የጉራጌ ተወላጅ በወላይታ ለምርጫ ለመወዳደር የሚያስችለው መስፈርት አለ ብለህ ትገምታለህ?
አንድ የሱማሌ ተወላጅ በአፋር ለምርጫ ለመወዳደር የሚያስችለው መስፈርት አለ ብለህ ትገምታለህ ?
እዚህ ላይ ነው ፈላስፋው አንተን ከመጠይቅ አልፎ ለማስረዳት የሚለፋው ፡፡
በአሜሪካ ግን አንድ ብሄሩ ሳይሆን የአሜሪካ ዜግነት ያለው ግለሰብ በዲሞክራቲክ ፓርቲ አባልነት የትም ተወዳድሮ ለመመረጥ መብት እንዳለው ማስረዳት ያስፈልግ ይሆን ?
የሰው ልጅ ሰብዓዊ መብቱ ከተከበረ ማለትም የአንተ ሰብዓዊ መብት በአሜሪካ እንደተከበረ ሁላ አማርኛ ኦሮምኛ ከዛም አልፎ እንግሊዘኛ እያቀላጠፍክ working together በማለት፡ በስራው ዓለም በአሜሪካ እየኖርክ ፡ከዛም በምርጫ እየተካፈልክ፡ ሲሻህ ዲምክራቶችን ሳይሻህ ሪፐብሊካኖችን እየመረጥክ መኖርህ የፌዴራሊዝም ስርዓት በአሜሪካ በመጀመሪያ የአንተን ሰብዓዊ መብት ስላከበረ፡ አንተን በሰውነትህ እንጂ በጎሳህ ሳይሆን ስላከበረ መሰለኝ ባልሳሳት ፡፡ ትክክል አይደለሁም እንዴ ?
እንግዲህ ጨዋታው እዚህ ላይ ነው ወደ ትውልድ ሐገርህ ስትመለስ እንዴት ነው ይህንን በተግባር የምትተረጉመው የሚለው ጥያቄ ነው የፈላስፋው ጥያቄ
የአንተ መልስ በእንግሊዘኛ ቁዋንቁዋ Dissolution እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ ፡ ምንያቱም ስለ ዩኒቨርሲቲ ሌክቸር አይደለም እዚህ ላይ የምናወራው ስለ አንድ ሐገር እለ ኢትዮጵያ ነው የምናወራው ስናወራ ደግሞ መፍትሄ ለመፈለግ መሆን ስለሚገባው ነው living together , working together , learning together , thinking together, coming together, or holding together በለው ሁሉም መደመር ነው

ለመደመር ሌላ ነገር አያስፈልግም ከላይ የተጠቀሱትን የእንግሊዘኛ ቃላቶች በተግባር ማዋል ነው ለዚህም ዋናው ነጥብ
ደመቀ መኮንን የኦርሚያ ፕሬዘዳንት
ሽመልስ አብዲሳ የትግራይ ፕሬዘዳንት
ደብረ ጽዮን የአማራ ፕሬዘዳንት
ሙስተፋ መሐመድ ኡመር የአማራ ፕሬዘዳንት
ሌሎችም እንደዚሁ ቦታ ተለዋውጠው ለሰው ልጆች የሚያሰቡበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ይላል ፈላስፋው
ከፌዴራሊዝም በፊት የሰው ልጅ መብት ይከበር
የጎሳ ፌዴራሊዝም ከምድረ ኢትዮጵያ ይጥፋ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ምክክር » Wed Jul 17, 2019 5:43 am

ከአሜሪካ ጋር ሚዛን ላይ ስንቀመጥ ምን ያህል ዓመታት ወደ ኋላ ቀርተናል፡፡ አስላውማ፡፡ እነሱ የዛሬ መቶ ምናምን ዓመታት ነው የጀመሩት፡፡ ቀደሞዉኑ የብሄር ፌደራላዊ ሥርዓት ትግራይን ምክንያታዊ አድርጎ ለመገንጠል እና ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ነበር፡፡ ከኤርትራ ጋር ያልጠብቁት ሢከሰት መፈናፈኛ ሲጠፋ ኢትዮጵያዊነትን ባልተቃኘ ድምፅ እየተናነቃቸው ለማዜም ሞከሩ፡፡ ዘፈን ቀይሩ፡ ሪትም ጠብቁ አይባል ነገር፡፡ ሲጀምር የሌለን የሃገር ፍቅር አሁን ቢያምጡት ከየት ይወለድ? ዉስጥ ተቀረቅሮ አልወለድም እያለ! እነዚህ ዝንተ ዓለም ሰላም አይሰጡንም፡፡ ኢትዮጵያን ሊኖሩባት እንጂ ሊኖሩላት አይሹም፡፡ እናም ወዳጄ ሆይ የብሄር ፖለቲካን ለመግራት ጉዞው ፈታኝ ነው፡፡ አንድ ትውልድ ይቀረናል፡፡ ለዚያ ትውልድ ግን ቢያንስ መንገዱን እንኳ እናበጃጀው፡፡ አረሙ ዳግም እንዳይበቅል ከነስሩ መንቀል፡፤ ተግባባን! ዋንስ ዶንኪ ኔቨር ሆርስ እንዳንሆን!
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Sun Jul 21, 2019 6:39 pm

አይ የጎሳ ፌዴሬሽን ?
በየዩኒቨርሲቲው በተደረገው ምረቃ የክልል አስተዳዳሪዎች ንግግር
1. የተናጋሪዎቹ ተመሳሳይነት
ሁሉም የዲግሪ ጋዋናቸውን መልበሳቸው
ሁሉም የተመረቁ መሆናቸው
ሁሉም የክልል መስተዳደር ሐላፊ መሆናቸው ከዓቢይ አህመድ በስተቀር

2. ልዩነታቸው ሁሉም ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ሲናገሩ፣ ተፈቃቅሮ ፣ተሳስቦ ለሐገር መስራትን ሲያበስሩ
አንዱ ግን ከሁሉም የተለየ ንግግር ማደረጉ ነው የሚገርመው
በንግግሩ መካከል ምሩቃኑ የተመረቁበት ክልል አምባሳደር በመሆን የክልሉን ደግነትና ጨዋነት ለመጡበት ወይም ወደፊት ለሚሰሩበት ክልል አንዲያስረዱ በማለት የደሰኮረው ነው ፈላስፋውን ያልገባው
ሰው በሐገሩ ለሐገሩ አምባሰደር ይሆናል አንዴ ብዬ በጠየቅሁት ነው ያሰነኝ
ቨርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ለሜኖሶታ ነዋሪዎች አምባሰደር በመሆን ስለ ቨርጂኒያ ይናገሩ እንደ ማለት ነው
ወይም የሜኖሶታ ተመራቂዎች ለቨርጂኒያ ነዋሪዎች አምባሰደር በመሆን ስለ ሜኖሶታ ይናገሩ እንደ ማለት ነው
ተማሪዎቹ ስለሐገራቸው አያውቁም አንደማለት ይሆን? ወይም ከጥንቱ ከጠዋቱ የትምህርቱ ካሪኩለም ባዶ ነው ማለት ይሆን?

አይገርምም?
ስለ ሐገር ታሪክ -፡ስለ ወንድማማችነት ፡ስለ ፍቅር፡ ሳይሆን የሐገራችን ወጣቶች ከአያት ከአባቶቻቸው እንዲሁም በአንደኛ ደረጃን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሩት ነገር ቢኖር የጎሳ ፌዴራሊዝም ? እንዴት ሐገር እንደ ዶሮ ብልት እንደሚገነጣጠል ማለት ይሆን ? ለዚህ ይሆን "አምባሳደር ለመጣችሁበት ክልል ሁኑ" የሚለው ቃል የወረደው
የጎሳ ክልል ይጥፋ ፡ የጥንታዊ የጋርዮሽ ስርዓት ነው
coming together and holding together ይቀጥላል
የስዊዘርላንድ የፖለቲካ ፓርቲዎችች አመሰራረት እንደ ምሳሌ ይጠቀሳል ስለ አሜሪካ የሚታወቅ ነው ዲሞራቶችና ሪፐብሊካኖች ስለሆነም በኢትዮጵያ
ደመቀ መኮንን የኦርሚያ ፕሬዘዳንት
ሽመልስ አብዲሳ የትግራይ ፕሬዘዳንት
ደብረ ጽዮን የአማራ ፕሬዘዳንት
ሙስተፋ መሐመድ ኡመር የአማራ ፕሬዘዳንት የሚለው የፈላስፋው መመሪያ ለሐገራችን ለኢትዮጵያ አስፈላጊ ነው
የመድበለ ፓርቲ ሲስተም በፌዴራል ኢትዮጵያ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Mon Jul 22, 2019 5:03 pm

Christian Democratic People's Party (CVP/PDC)
FDP.The Liberals (FDP/PRD)
Social Democratic Party (SPS/PSS)
Swiss People's Party (SVP/UDC)
Green Party (GPS/PES)
Green Liberal Party (GLP/VL)
Conservative Democratic Party (BDP/PBD)
Independent

እንግዲህ እዚህ ላይ ነው ጨዋታው የስዊዘርላንድ የፖለቲካል ፓርቲዎች ይህንን ይመስላሉ
ስዊዘርላንድ በፌዴሬሽን የተዋቀረች ሐገር ነች እናስ ምን ዓይነት ፓርቲዎች ይታያሉ ?
የጋርዮሽ ስርዓተ ማህበር ዓይነት የጎሳ ጥርቅም ፓርቲዎች ?
ለምን በኢትዮጵያ የጎሳ ጥርቅም ፓርቲዎች ?
ፌዴሬሽን ተቀባይነት ያለው አደረጃጀት ሲሆን ነገር ግን የፓርቲዎች አመሰራረት የመድበለ ፓርቲ አመሳሰረት ብቻ ሲሆን ሐገርህ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የምትሆነው
በጎሳ በተደራጀ የፖለቲካል ፓርቲ ሕገመንግስት የሚባል ነገር አይሰራም
መጠራጠር አለመተማመን ብቻ ነው በጎሳዎች መካከል የሚፈጠረው
ለዛም ነው በአሁኑ ሰዓት የምንሰማው የምናየው መጠራጠር እና አለመተማመን የመነጨው
ስለሆነም የጋርዮሽ የጎሳ የፖለቲካል ፓርቲ ከምድረ ኢትዮጵያ ሳይውል ሳያድር ይጥፋ እስከ ዛሬ የሆነው ሆኖ አልፎእል
ስለሆነም
ደመቀ መኮንን የኦርሚያ ፕሬዘዳንት
ሽመልስ አብዲሳ የትግራይ ፕሬዘዳንት
ደብረ ጽዮን የአማራ ፕሬዘዳንት
ሙስተፋ መሐመድ ኡመር የአማራ ፕሬዘዳንት የባህርዳር ከንቲባ የድሬደዋ ከንቲባ የድሬደዋው የደብረ ማርቆስ ...
ተመስገን ጥሩነህ የአፋር ፕሬዘዳንት የእፋሩ ፕሬዘዳንት የጎንደር ከተማ ከንቲባ
ጌታቸው ረዳ የአዋሳ ከንቲባ የእዋሳ ከንቲባ የአዲግራት ከንቲባ
ዳንኤል አሰፋ የስልጢ ወረድዳ አስተዳዳሪ የስልጢ ወረዳ አስተዳዳሪ የመቀሌ ከንቲባ

በቃ ሁሉም በመድበለ ፓርቲ ተሰልፎ ኢትዮጵያዊ የሚያስተዳድራት ሐገርና ከተማ፡ የትኛውም ኢትዮጵያዊ ያለ መታወቂያ እና ያለ ጥያቄ በሰወውነቱ ብቻ ታውቆ ፡ የትም ሄዶ የትም ኖሮ የሚሰራባት ፡የመረጠውን ቆንጆ የመረጠቸውን ቆንጆ የምታገባበት ፡ በፈለገው ቁዋንቁዋ፡ በአንድም ሆነ በሁለትም በሶስትም ሆነ በአራትም ቁዋንቁዋ ያለ ምንም ሕገ መንግስት በገዛ ፈቃዱ የሚማርባት የሚናገርባት የሚዋለድባት ውብ ሐገር ኢትዮጵያ ሲል ነው የሚፈላሰፍባት
የጥንታዊ የጋርዮሽ የፖለቲካ ፓርቲ ለተኩላዎች ነው ለሰው ልጆች አይሆንም
የጥንታዊ የጋርዮሽ የፖለቲካ ፓርቲ ለጅቦች ነው ለሰው ልጆች አይሆንም
የሰው ልጅ ጭችንቅላት ፡ ጭንቅላት ፡ ጭንቅላት ያለው ፍጡር ነው ለዛም ነው ከተኩላዎችና ከጅቦች የሚለየው

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4189
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests