በኤርትራ ቅኝ መገዛት የጀመረችው የቀድሞዋ ኢትይዮጵያ እንደ ድመት የራሷን ልጆች መብላት ከጀመረች እነሆ 3ኛ ዓመቷን አከበረች፡፡ ይህ በአለም ለመጀመሪያ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስቴር ግራኝ አብዮት አህመድ ጋባዥነት በኤርትራ ቅኝ የወደቀችው ኢትዮጵያ፤ የደህንነት ተቋሟ፤ የውትድርና ማእከሏ፤ ብሎም የባንኪግ አሰራሯዋ ለኤርትራውያን አሳልፋ በመስጠት ልትወጣው የማትችልበት አጣብቂኝ ዉስጥ ገብታለች፡፡ የውርደት ሸማን የተከናነበችው የቀድሞዋ ኢትዮጵያ፤ በየትኛውም የውጭ ግንኙነት መድረክ ላይ ወዳጆቿን ትታ ከአፍሪካው ሰሜን ኮሪያ (ኤርትራ) ጋር በመወዳጅዋ አይንሽ ላፈር ተብላ ተሸማቃ ትገኛለች፡፡ የሃምሳ ዓመት እድሜ ያላስቆጠረችው ጅቡቲ እንኳን ሳትቀር የአዋሽ ወንዝ ላይ የይገባኛል ጥያቄ አቅርባለች፡፡ ቢሆንም ዳሩ: ከጂቡቲ በእድሜ የምታንሰው ኤርትራ ኢትዮጵያን ቅኝ ስታደርግ በማየቷ፤ እኔም ወጉ ይድረሰኝ ብላ በኦሮሞ ምድር ላይ ተወልዶ አፋር ክልል ላይ ግብአተ መሬቱ የሚፈጸመውን አዋሽ ወንዝ ኢትይጵያ ለዘመናት ተጠቅማበታለችና አሁን ተራው የኔ ነው በማልት የይገባኛል ጥያቄዋን ያቀረበችው፡፡ ጌታውን ካልናቁ አጥሩን አነቀንቁ አለ አማራ፡፡ ከዚህ በላይ ውርደት ታዲያ ከየት ይመጣል? ምናልባትም የ150 ዓመት ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ እዚህ ላይ እንዳበቃላት የሚያሳዩ ማረጋገጫዎች ናቸውን??? እዚህ ላይ መልሱን ለአንባቢዬ እተወዋለሁ፡፡
የሚቀጥለው ምዕራፍ የ3000 ዓመት ባለታሪኳ፤ አባይ ትግራይ ተብላ የድሮዋን ላእልና ተመልሳ ትይዛለች፡፡ ባሕረ ነጋሽና መረብ ምላሽ ተብላ ትጠራበት የነበረውን ጊዜ፡፡
ኦሪት ዘ-ፍጥረት ምዕራፍ 11 ቁጥር 4 ላይ እንዲህ ይላል፡፡ እንዲህም፤ ኑ ለኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንስራ፤ በምድር ላይ ሳንበትንም ስማችንን እናስጠራው አሉ፡፡
የአለምም ሕብረተሰብ ለአባይ ትግራይ ምን ያህል እውቅና እንደሰጠ በአራቱም ማእዘናት የተሰራጨውን የሰሞኑን ዜና ማየት ይበቃል፡፡
ዓወት ንሐፋሽ!