የዩፎው ቅይጥ መለስ በኦስሎ ግራንድ ሆቴል

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የዩፎው ቅይጥ መለስ በኦስሎ ግራንድ ሆቴል

Postby moa » Thu Sep 01, 2005 4:26 pm

ውነትም የዮፎ ቅይጥ[/i]ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን በሰሞኑ ግጥማቸው ነው እኝህን ሰው እንዲህ ሲሉ የገለጹዋቸው።
እስከመቼ ነው እንዲህ እንደ ቆቅ እየበረገጉ የሚኖሩት? ቃየል የሆነ ሰው ግብሩም ሆነ ሥራው ስለሚከተለው ዘላለም እንዲህ እየበረገገ ይኖራል።
ውጭ ሃገርም ቢሆን ነጻነት አይሰማውም።
ዜናው እንዲህ ነው! መለስ ዜናዊ ኦስሎ ሲመጡ የሚያርፉበት ሆቴል በመሃል ኦስሎ ካርል ዮሃን ተብሎ ከሚጠራው ዋናው አውራ ጎዳና ላይ ከሚገኝ""ግራንድ "" ሆቴል ከሚባል ስፍራ ነው።
በጣም የሚገርመው በዚህ ሆቴል ውስጥ ቁጥራቸው የበዛ ኤርትራውያንና፤ኢትዮጵያውያን፤እንዲሁም ያህጉራችን ሰዎች የሆኑት አፍሪካውያን የሚሠሩበት ስፍራ ነው። ዛሬ ባጠቃላይ ላፍሪካውያን ሠራተኞች በተለየ ሁኔታ ከሆቴሉ ባለስልጣኖች የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ማንኛውም አፍሪካዊ የሆቴሉ ሠራተኛ መለስ በሚያርፉበት ክፍል ዙርያ በሥራ ላይ እንዳይገኝ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ሲሆን መለስ ወደ ሃገራቸው እስኪሰናበቱ ድረስ ወደ ሌላ ዲፓርትመንት አፍሪካውያኑ ሠራተኞች እንደተመደቡ ታውቋል።
አይ አቶ መለስ ለካ የነአቶ ግደይና አቶ አረጋዊ ፍራቻ አሁንም ድረስ አለቀቀሆትም?
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

አልጋው ሲያቃዠው ታየኝ......

Postby ተድባበ » Thu Sep 01, 2005 9:29 pm

ቅቅቅቅቅቅቅቅ.... ቦቅቧቃው መለስ! :lol: :lol: :lol: ምስኪኖች በስደት ተረጋግተው ሰርተው እንዳይኖሩ በጉሮሯቸው ገቡባችው?......... ያሳዝናል :oops: በድቡሽት ላይ የተሰራ መንግስታቸው ይሄው በየሄዱበት ይናዳል:: ገና በቁማቸው ይለቁታል... በርቱ እዚያ ያላችሁ ወገኖቻችን..... እኛም በእለቱ እዚህ በኖርዌይ ኤምባሲ ደጅ ተገኝተን ተቃውሟችንን ልናሰማ ተዘጋጅተናል :D :D :D

በነገራችን ላይ ይሄ ነፍሰ ገዳዩ መለስ የሚያርፍበት ሆቴል, ከዚህ ቀደም ጀግናው የመምህራን ማህበር መሪ ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት ኖርዌይን በጎበኙበት ወቅት, በታላቅ ክብር አርፈውበት የነበረና የተስተናገዱበት መሆናቸው በወቅቱ ከደረስን ዜና እናስታውሰዋለን!...... ዛሬ ይህ ከሀዲ ሲያርፍበት የሚተኛበት አልጋ እራሱ ምን ያህል ይጠየፈው?...... እሱም እራሱ የዶ/ር ታዬ ምስል እየመጣበት ምን ይህል በቅዠት ይሸበር ይሆን? :evil: :evil: :evil:

ተድባበ ማርያም
ተድባበ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Wed Feb 16, 2005 7:06 pm
Location: ireland

አስፈሪው ፎቶ

Postby ፈተና » Wed Oct 12, 2005 9:35 pm

የዛሬው VOኤ እንዲሁም ሲኤንኤን ዜና ላይ ያገኘሁት የቅርብ ጊዜ ፎቶ አስደነገጠኝ:: ምነው ምነው ምንስ ቢሆን መሪያችን አይደሉ እንዴ? ይሄን ያህል? Image
Image
http://www.voanews.com/english/2005-10-12-voa30.cfm
http://i.a.cnn.net/cnn/2005/WORLD/afric ... awi.ap.jpg
.
ፈተና
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 38
Joined: Thu Mar 10, 2005 11:54 pm
Location: united states


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests