ለሳይበር ኢትዮጵያ አስተዳዳሪወች

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ለሳይበር ኢትዮጵያ አስተዳዳሪወች

Postby ሱልጣን » Wed Oct 05, 2005 8:49 am

ለሳይበር ኢትዮጵያ እና ዋርካ አስተዳዳሪወች

--------------------------------------------------------------------------------

ለሳይበር ኢትዮጵያ እና ለዋርካ አስተዳዳሪወች እንዲሁም ለ ሳይበር ፖስታቤት አዘጋጅ ...ጉዳዩ ይመለከተኛል ለሚል ቅን አሳቢ ኢትዮጵያውያን ሁሉ

እንደሚታወቀው ሐገራችን ኢትዮጵያ የሁሉም ሀይማኖት የጋራ መገለጫ እና እናት እንደመሆኗ ሁሉም እንደ ባህሉ ሀይማኖታዊ ባእሉን ሲገልጽ ይስተዋላል ::
ሙስሊሞች ለረመዳን (ኢደል ፈጥር )እና ለአረፋ -ኢድ አል አድሀ በአል በአለም አቀፍ ደረጃ ሲያከብሩ ሙስሊም ያልሆኑትም የሀይማኖት ባእላቸውን ሲያከብሩ ይስተዋላል ::
እዚህ ጋ መጠቆም የፈልግኩት ነበር የ ሳይበር ኢትዮጵያ ማኔጅመንት ለበአላት የመልካም መግለጫ መልእክት ለህዝበ ክርስቲያኑ አመቱን እየጠበቀ የመልካም መግለጫ መልእክት እያስተላለፈ ይስተዋላል :!: ታዲያ ምነው ከጠቅላላ የኢትዮጵያ ህዝብ ከግማሽ በላይ ይወክላሉ ለሚባሉ ኢትዮጵያን ሙስሊሞች ለኢድ አልፈጥር ረመዳን እና የአረፋ በአል የመልካም መግለጫ መልእክት አይተላለፍልንም :?: :?: :?:
ሳይበር ፖስታ ቤት በ እያንዳንዱ የዋርካ ፎረም ተጠቃሚ ኢሜል ለሙስሊሙም ሆነ ለክርስቲያኑ እንኳን ለመስቀል አደረሳችሁ እያለ ኢ ሜል ሲልክ እና ለተለያዩ ባእላት የሚሆን ፖስት ካርድ ለህዝበ ክርስቲያኑ ሲያዘጋጅ ምነው ለሙስሊሞች አላዘጋጀም :?: :?:
ይህን መጣጥፍ መድረክ ላይ ከማውጣቴ በፊት ለሳይበር ማኔጅመንት ኢ ሜል አድርጌ መልስ ስላጣሁ ነው :!: ስለዚህ ሳይበር ይህን በተመለከተ ምን እንደሚል መልሱን እጠብቃለሁ ::


ሱልጣን
ሱልጣን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 261
Joined: Wed Sep 03, 2003 11:38 am

ለ ወንድም ሱልጣን

Postby ሞልጨው » Wed Oct 05, 2005 9:11 am

ጥያቄህ አግባብ ያለውና ትክክልም ነው! እንዳልከው የክርስቲያን በአሎች ሲከበሩ ሳይበርም ይሁን ዋርካ ላይ የ እንኳን አደረሳችሁ መልክቶች ከ አዘጋጆቹ ይተላለፍ ከነበረ (ልብ ብዬ አላውቅም) እና የሙስሊም በአል ሲከበር ግን ያ መሆን ካልቻለ አድሚቶቹ ባፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጡህ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ!!

የምፈራው ግን ደጉ ወደዚህ አምድ ብቅ ያለ እንደሆን ነው!! ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
selam le sew lijoch hulu
ሞልጨው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Fri Feb 11, 2005 10:36 am
Location: finland

ውድ ወንድም ሱልጣን

Postby ልጁነኝ1 » Thu Oct 06, 2005 7:50 am

እንኳን ለበዓሉ (ዐውደ ዓመቱ) አንተንና ቤተሰቦች ህን እንዲሁም ያገሬን የሙስሊሙ ህብረተሰብ ሁሉ አደረሳችሁ:: እያልኩ ወገናዊ ሰላምታዬን አቀርባለሁ::

ይህም የረመዳን አብይ ጾምና ጽድቅ ለተሰራበት ያደረጋችሁት ሠደቃ አላህ ብድሩን ይክፈላችሁ::

በአገራችሁም ሠላም እንዲያመጣ በጸሎቶቻቺሁ ጊዜ በማቅረብ ተጨንቃችሁ የምትለምኑትንም ሰምቶ ምላሹን አኬሩን ለአገራችን አላህ ያውርድልን::

ወንድሜ ብቻቺሁን አይደላሁም ክርስቲያኑና ከዚያም ሃይማኖት አልባ የሆኑት ሁሉ ደስ ብሏቸዋል ረመዳንን በጤናና በፍቅር ተሳስራችሁ በትጋትና በመደጋገፍ የሌላቸውን በማሰብ እነሱንም በመንከባከብ ያሳለፋችሁትን ሁሉ ሁላችን እናውቃለን እናስባለንም:: ቢያንስ በረመዳን ወሮች ውስጥ የሚራብ የለም በሐገራችን ሙስሊሙ ወገን በሚያቀርበው ሰደቃ የሌላቸው የተራቆቱት ሳይቀሩ አዲስ የሚለብሱበት መሆኑን ጭምር::

ሣሂቤ (ዘመዴ) አላህ ብሎ የከርሞ ሰው ታደረገን ቀድሜ እንደምጽፍ ቃል ዕገባልኃለሁ የወቅቱ ችግር ይዞን እንጂ ሣይታሰብ ቀርቶ ያለመሆኑን በመላዋ ሣይበር ሥም እንኳን ብናገር ማንም ቅር የሚለው እንደሌለ እንድትገነዘበው:: ያጋጣሚ ጉዳይ እንጂ::

"ሣሂቤ ወሳሂቤ ወሰሊም ተስሊም አላሁ መሰሌ አለም ነቢ" አሜን!!!

ዘወትር አክባሪህ

ልጁነኝ1
ከ(ሰሐሊን)
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states

Postby CyberEthiopia » Thu Oct 06, 2005 11:11 am

ሰላም ሱልጣን

ይህን ጥያቄ ከዚህ በፊት በEmail ጠይቀሕን መላሽ ሰጥተንሀል ::

በጣም ተገቢ እና ትክክል ጥያቄ ነው ::

1) የፖስታ ቤት ካርዶቹን በሚመለከት ያሉህን ካርዶች ብትልክለን እናስገባቸዋለን :: ከኛ በኩል ትብብር ካስፈለገም ወደ ኌላ አንልም :: በContact us ላይ ሄደህ ጻፍልን ::

2) የእስላም በዓሎችን ማስተወውቅን በሚመለከትም አስቀድመህ መልዕክት ብትልክልን በሚገባ እናስተዋውቃለን ::
Last edited by CyberEthiopia on Sat Oct 08, 2005 5:19 pm, edited 1 time in total.
CyberEthiopia
የዋርካ አስተዳዳሪ/Admin
የዋርካ አስተዳዳሪ/Admin
 
Posts: 17
Joined: Mon Jul 21, 2003 6:27 pm

Postby ሳም2 » Thu Oct 06, 2005 6:25 pm

በመጀመሪይ እንኴንም ለረመዳን በሰላም አደረሰን እያልኩ በዛሬው እለት ለሳይበር ካርድ የረመዳንን በሚያስመለክት islam.com ዌብ ያገኘሁትን ልኬአለሁኝ ተስፋ አደርጋለሁኝ እንደሚያወጡት ለኢድ አስታውሼ እልካለሁኝ

ሰላሙን ለአገራችን ይሁን
test
ሳም2
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Sat Aug 13, 2005 3:09 am
Location: ethiopia

ምስጋና

Postby ሱልጣን » Sat Oct 08, 2005 1:35 pm

ለሳይበር ኢትዮጵያ አድሚን እና በዚህ ፎረም ላይ በቅን ልቦና ለተሳተፋችሁ ሁሉ

ከሳይበር በኩል ለተሰጠኝ መልካም ምላሽ ለሳይበር አድሚን እና ገንቢ ሀሳብ በማቅረብ ለተባበራችሁ ሁሉ በሙስሊም ጓደኞቸ ስም ምስጋናየን ሳቀርብላችሁ መልካሙን ሁሉ በመመኘት ነው:: Image
ሱልጣን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 261
Joined: Wed Sep 03, 2003 11:38 am

መልካም ረመዳን

Postby ሙስሊም » Sun Oct 09, 2005 11:55 pm

ሰላም

መልካም ረመዳን ይሁንልን::

Image
ሙስሊም
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Thu May 20, 2004 6:18 pm
Location: ethiopia

Postby ሙስሊም » Mon Oct 10, 2005 12:07 am

Image
Image
ሙስሊም
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Thu May 20, 2004 6:18 pm
Location: ethiopia

ለዋርካ አድሚን

Postby ሱልጣን » Tue Oct 11, 2005 8:11 am

ሰላም
ለ ሳይበር ፖስታ ለኢድ አልፈጥር እና ለ ኢድ አል አድሀ(አረፋ)በአል የሚሆኑ ፖስትካርዶችን ልከናል በገባችሁልን ቃል መሰረት
ተግባራዊ ምላሹን እየጠበቅን ነው
Thank You In advance
ሱልጣን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 261
Joined: Wed Sep 03, 2003 11:38 am

መልካም:ረመዳን!!

Postby SAY-NO-TO-HATRED » Tue Oct 11, 2005 8:20 am

ውድ:የሙስሊም:ሀይማኖት:ተከታይ:ወገኖቼ:በያላችሁበት:መልካም:ረመዳን:ከልብ:
እመኝላችኍለሁ!!ውድ:ሀገራችንና:ሰላም:አፍቃሪ:ሕዝባችንን:በጾም:በጸሎታችሁ:አስታውሱልኝ:
እባካችሁ:እያልኩ:እለምላናለሁ!!


ሁሌም:እህታችሁና:አክባሪያችሁ:

እምቢ:ለጥላቻ:

ነኝ
WE ARE NOW AMBASSADORS FOR OUR BELOVED COUNTRY AND ONE DAY WE WILL BE CITIZENS IN ETHIOPIA, ONCE AGAIN!!
SAY-NO-TO-HATRED
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1354
Joined: Sat Mar 12, 2005 8:29 pm
Location: united states


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests