"" ዋርካ ዲቤት "" ቅንጅት የፓርላማው አካል ይሁን ወይስ ፓርላሜንታሪነቱን ይሰርዝ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

"" ዋርካ ዲቤት "" ቅንጅት የፓርላማው አካል ይሁን ወይስ ፓርላሜንታሪነቱን ይሰርዝ?

Postby ሳምቻው » Thu Oct 06, 2005 12:42 pm


እንደዚህ ባጭር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ባህል እንደ ዩክሬን እና ጆርጂያ ኣይነት ይሆናል ብሎ መገመት የዋህነት ይመስለኛል ::

የሌላው አለም የፖለቲካ አመራር, የህዝቦቹን የመምረጥ መብት በውል የተገነዘበ , በህዝቡ ሰብ-አዊ ነክ ጉዳዮች ላይ ሀላፊነቱን የሚውስድ , በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት ሲቆም አይኑን በጨው ማጠብ እንደማይችል የተገነዘበ እንዲሁም "" መንግስት "" ከሚባለው አካል ምን እንደሚጠበቅ ምን እንደማይጠበቅ ጠንቅቆ ከማወቁም በላይ በህግ የበላይነት የሚያምን ነው :: በመሆኑም በህግ ተጠያቂ የመሆን እድሉ በተለይ ለ'ሱ ከማንም በላይ የበረታ መሆኑን ይገነዘባል ....

በእንደዚህ አይነቱ ሀገር ውስጥ ብቻ ነው ህዝቡ ቤተመንግስት ደጃፍ ላይ እያደረ የመሪውን ሪዚግኔሽን ስፒች ሰምቶ ወደ ቤቱ በሰላም የሚመለሰው ::

ለመሆኑ የዚህ አይነቱ ሀገር አቀፍ የህዝብ አቋም አራት ኪሎ ቤተመንግስት ደጃፍ ላይ ተከማችቶ ቢታይ የጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ መንግስት ለሰልፈኛው ያለው አያያዝ እና ምላሽ እንደ ዩክሬን ,ጆርጂያ እና ሊባኖስ መንግስታቶች ይሆናልን ?

መልሱ ማሺን-ገን ከሆነ የመለስ ዜናዊን መንግስት በህግ የመጠየቅ እድሉ ምን ያህል ነው ? , የቀሪው አለም ምላሽስ ምን ሊመስል ይችላል ? ሌሎች የማይበርዱ የጎሳ-ማህበረዊ ቀውሶች ይከተሉ ይሆን , ድንበራችን ላይ አቆብቁቦ የሚጥብቅው የኢርትራ ሰራዊትስ ""እድሉን"" ለመጠቀም ይመቸው ይሆን ...?

ቀጥለን እናያለን

ሳም

Last edited by ሳምቻው on Thu Oct 06, 2005 2:04 pm, edited 6 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

ዋርካ ዲቤት ሩም

Postby ሳምቻው » Thu Oct 06, 2005 1:47 pm


"" ቅንጅት ወደ ፓርላማው ግብቶ ይታገል ወይስ ማይኖሪቲ ወንበሮቹን ጥሎ ሌላ የትግል ስትራቴጂ ይቀይስ"" የሚል ፐብሊክ ዲቤት ከፍተናል ::

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ , የፖለቲካ , የማህበራዊ እና ወታደራዊ ጠበብቶች በውይይቱ እንዲሳተፉ ባያሌው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ::

በዚህ ርእስ ዙርያ እንዲተነተኑ የሚጠበቁት ሀሳቦች:-

የኢትዮጵያ ህዝብ መሪዎቹን የመምረጥ ተፈጥሯዊ መብቶቹ እንተጠበቁ ሆነው ወደ ፓርላማ እንግባ/ አንግባ የሚለውን ሀሳብ ግን ልንዳስሰው የሚገባው ,የሀገሪቱን ወቅታዊ እና መጽአዊ እድሎች በመተንተን ነው :: ፓርላማ እንግባ/ አንግባ ስንል የሀገራችንን የፖለቲካ ባህል ያለበትን ደረጃ በመፈተሽ , የኢኮኖሚ ድቀታችንን በማስታወስ , ልባችንን ላይ ቆሞ ያለውን የድንበር እና ሉአላዊ ቀውሶቻችንን በመቃኘት ባጠቃላይ በጎሳ ክፍፍል ዙርያ ያለውን ተሰባሪ ሰላማችንን በማገናዘብ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል::

በዚህ ርእስ , የኢትዮጵያን አንድነት የሚያጣጥሉ ጽሁፎች በፍጱም ምላሽ ኣያገኙም :: ሁሉም ኢትዮጵዊ ለሀግሬ ይጠቅማል ብሎ የሚሰማውን ሀሳብ የመሰንዘር መብት አለው :: ሀሳቡን እንጂ የ ጸሀፊዉን/ ጸሀፊዋን ፕርሰናሊቲ መተቸት ግን ( irrelevant ) መሆኑ ብቻ ሳይሆን ምሁራኖች እንዳይሳተፉ የገፋፋል ::

ከሰላምታ ጋር

ሳም

Last edited by ሳምቻው on Fri Oct 07, 2005 11:23 am, edited 4 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby ወዲ ሰበርጉማ » Thu Oct 06, 2005 2:19 pm

ሳምቻዉ

ይህንን ጽሁፍ ብታነብ ላነሳኻዉ ጥያቄ በቂ መልስ የምታገኝ ይመስሎኛል::

http://www.ethiomedia.com/fastpress/andargachew.pdf

የሉአላዊነት ጉዳይ በእዉን የጊዜዉ አንገብጋቢ ጉዳይ ነዉ??? ሉአላዊነታችንን አሳልፈው ከሰጡት ጋር ያሎው ትግል የሚቀድም አይመስልህም???
ወዲ ሰበርጉማ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Thu Mar 17, 2005 4:10 pm
Location: united states

Postby ሳምቻው » Thu Oct 06, 2005 3:13 pm


ወዲ ሰበርጉማ

አታች ያደረከውን ፋይል ቀደም ሲል ያየሁት ቢሆንም ለተሰማህ "ሀላፊነት" ግን ስላመሰግን አላልፈም !!

ሉአላዊነት የወቅቱ ብቻ ሳይሆን በታሪካችን ውስጥ የምንግዜውም አንገብጋቢ ጉዳያችን ሆኖ ነው የኖረው :: የጦርነት እርፍት መች ወስደን እናውቃለን ስታስበው ?

አሁን በጉያችን የያዝነው ደግሞ ገደል አፋፍ ላይ የቆመ ማህበራዊ ሰላም እና በመንግስት የሚረዳ የ ጸረ አንድነት ፖሊሲ እና ተግባራቱ ነው :: እንቅልፍ ያስወስዳል ታድያ ??

ማምሻውን የከሰል ፍም የጨበጠች የአመት ከስድስት ወር ሴት ልጅህን ከፍሙ ሳታላቅቃት ዝም ብለሀት ወደ መኝታህ ብትሄድ የሚሰማህን መገመት አያቅተኝም :: መገመት የማልችለው ፍሙን እንደጨበጠች የምትጮሀዋን ህጻን እንዴት ልትቀረባት እንደምትችል ሳስብ ነው ::

አቀራረብህ( the way you conduct to the fire ) ያሳስበኛል ....

የሆነው ሆኖ የኢትዮጵያ እጆች የጨበጠውን ፍም ማስጣል የሚቻለው በሚንጫጩ ፖለቲከኞች ሳሆን ማስተዋል በሚችሉ በሳል አመራሮች ብቻ እንደሆነ የራሴ እምነት ነው :: ማንም ሰው ከዚህ የተለየ አቋም ቢይዝ መብቱ ነው !

ሳም
Last edited by ሳምቻው on Fri Oct 07, 2005 11:24 am, edited 1 time in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby ዞብልየ » Thu Oct 06, 2005 3:19 pm

ሳምቻው

ዱራ ሰንበት እንዳለው ይህ ዊብ ሳይት የብዙዎቻችንን ፍላጎት ያንጸባረቀ ምንባብ ነው;; ከዚህ ውጭ ያለ አስተያየት ካለህ ጽሁፉን አንብበህ ንገረን;; ቅስሚያ ትኩረት የሚሰጥእው ጉዳይ ቢታችንን ማጽዳቱ መሰለኝ;; የተያያዝነው የዲሞክራሲ ትግል ፈር ሳይዝ ወደ ሊላ አርስት መሂድ መዘናጋት ካልሆነ በስተቀር ምንም የሚፈይደው ነገር የለም;; ህገራችን ላይ ለሚታየው ችግሩ ሁሉ መልሱ የዲሞክራሲ ሂደትና መጎልበት ጋር የሚያያዝ ነው;; ወያነ የሰረቀው የህዝብ ምርጫ ወጥእት መከበሩ ነው የውቅቱ አንገብጋቢ ጥያቂ;; ይህ ሲከበር ሊላው በመልክ በመልኩ ጊዚ ተወስዶ መልስ ያገንኝኣል;;

በወያነና በሽአብያ የተደገሰልንን ሊላ የፖለቲካ ቁማር ብቅ እያለ መሆኑን አመላካች ሁኒታዎች ይታያሉ;; በህገር ስም እንደገና ለማንሰራራት የሚደረግ ደባ ስለሆነ የባድመ ጥያቂ አሁን ወቅታዊ አይደለም ባይ ነኝ

በቸር ያቆየን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ዞብልየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Thu Feb 24, 2005 7:22 pm

Postby ወዲ ሰበርጉማ » Thu Oct 06, 2005 3:50 pm

ሳምቻዉ

"ዳህላክ ላይ ......" የሚሎዉን የቴዲ አፍሮን ዘፈን ታዳምጥ ዘንድ ጋብዥሀሎሁ::
ወዲ ሰበርጉማ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Thu Mar 17, 2005 4:10 pm
Location: united states

ጉዳዩ ባድሜ ሳይሆን ኢትዮጵያ የሚል ነው

Postby ሳምቻው » Thu Oct 06, 2005 3:57 pm


ዞብል

አነሳሴ የባድሜ አቧራማ መንደር ሳይሆን , የኢትዮጵያ ደህንነት ከቅንቅጅት ወደ ፓርላማው የመግባት አለመግባት ጉዳይ ጋር የተያያዘ ነው !

የህዝብ ድምጽ መከበር በሚለው ሀሳብ ላይ ምንምን አይነት ኮንፊዎዥን አይኖረነም ::

ይህ መንግስት ሽንፈቱን የማይቀበል ከሆነ ቅንጅቱ ከፓርላማው እራሱን አግልሎ ሜዳ ላይ የሚጮህ ሰባራ ቁራ እንዳይሆን ነው የኔ ጥሪ :: አንዴ ፓራልይዝድ ከሆንክ ጌሙ ያበቃል !

ሁላችንም እንደምናውቀው ቅንጅት የታጠቀው የህዝብን ክንድ እንጂ የ ጦር መሳርያ አየደለም ::

ሁሉም ደግሞ ይህንን መንግስት እንገለብጣለን ብሎ ተስፋ ያደረገው ""በ ህዝባዊ አመጽ "" (public disobedience) በመታገዝ ነው በሚል አደገኛ ተስፋ ነው ::

የኔ ስጋት ይሄ እይነቱ የነውጥ ለውጥ እንደ ቀድሞዋ የሩስያ ሪፕሊኮች በቀላሉ ለኛ ይሳካልናል ወይ የሚለው ነው ?

በዚህ ግርግር ከላይ መቀርደድ የጀመረው ሉአላዊነት ሽርክትክቱ ቢወጣስ ? ልክ እንደሱማሊያ ጎሳ ለ ለ ጎሳ ተከፋፍሎ ትናንሽ መንግስቶች ያለፍላጎታችን ላለመታወጃቸው ምን ዋስትና ይኖረናል ? ምእራቡ አለም በራሱ ችግሮች ፋታ የሌለው ሆኗል !የቀሪው አለም ምላሽ ተስፋችን አይደለም ::

ልብ በል የ ወያኔ/ኢሀዲግ አመራሮች ይህንን ክራይስ ለማስቆም ከራሳቸው የግል ደህንነት አያልፍም ::ለሀገሪቱ ደህንነት ሀላፊነት የሚሰማው የታጠቀ አካልም የለንም ::

አሁንም ልብ በል ሀይለስላሴ ሥራት አልበኛውን ኢያሱን ሲገለብጡ ጦር ነበራቸው :: ደርግ የዘውዱን አገዛዝ ሲገረስስ ቤተመንግስቱን በታንክ እና መትረይስ ከቦ ነው :: በዲንጋይ እና በጨፈቃ ሳይሆን :: ሁሉም ግን አብዮቶች ነበሩ :: በተለይ ሁለተኛው ህዝባዊ አመጽ ነበረው !

ቅንጅቱ ፓርላማ ገብቶ ኢሀዲግን በማጋለጥ እና እርቃኑን በማስቀረት በሰላማዊ መንገድ ትግሉን ይቀጥል የሚል አቋም ነው ያለኝ ::

የህዝብ ድምጽ መስረቅ ብቻ ለመለስ ምንድነው ? መጥፎ መሆን ለመልስ ብርቁ እንዳይመስልህ :: ሲጀመር የመለስ መንግስት በሀገሪቱ ደህንነት ክፉኛ ተጫውቷል:: ሀገሪቱን ገድሏል :: እኔን የሚያስፈራኝ እኛው ራሳችን በስህተት እንዳንጨርሳት ነው ....

ሳም
Last edited by ሳምቻው on Fri Oct 07, 2005 12:28 pm, edited 4 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby ዞብልየ » Thu Oct 06, 2005 4:47 pm

ሳምቻው

በቅድሚያ አንድ ባንድ ሁኒታዎችን እንይ
1. ፓርላማ አትግቡ የሚለው ጥያቂ የህዝብ እንጅ የነ ወይም ያንተ ብቻ አይደለም;; ህዝቡ በተለያየ ጊዚ በህብረቱና በቅንጅት በተጥእራ ስብሰባ ላይ ውሳኒውን በማያሽማ መንገድ ገልጽዋል;
2. ፓርላማ ቢገባ ምን ለማድረግ ነው;; ወያነ ህጉን ለዋውጥኦታል;; ይህን ታውቀዋለህ;; የወያነ አጫፋሪ ከመሆን በስተቀር ዲሞክራሲ በዚህ መንነገድ ይጎለብታል ብለህ ካሰብህ ትልቅ የዋህነት ነው;; አጀንዳ ማስያዝ ካልቻሉ, በተያዘ አጀንዳ ላይ እንክዋን መንቀሳቀስ ካልቻሉ ጥቅሙ ምን ላይ ነው
3. ያንተ ትልቁ ፍርህት አገሪቱ ወደ ርስ በርስ ጥኦርነት ትገባለች. ይህ ፍርህት የኢትዮጵያን ህዝብ ባህርይንና ባህሉን በሚገባ ካለማወቅ የመጥአ ነው;; ህዝባችን በታሪኩ ውስጥ መቸ ነው ርስ በርሱ ተፋልሞ የሚያውቅ? ካለ አስረዳኝ;; ወያነ አዲስ አበባን በያዘበት ወቅት አካባቢ ቢሆን ሰጋኝ ነበር;; አሁን ህዝባችን የወያነን ደባ በሚገባ አውቆ ህብረቱ የጥእነከረበት ወቅት ነው;; ይህንንም በምርጫው አስመስክርዋል;; ይልቁንም የሚያስፈራው ወያነ ሊላ አምስት አመት ቢጨመርለት ምን ያህል ደባ ጥፋት እንደሚሰራ ነው;; ህዝባችን ጨዋ ነው;; ማ ማንን ይወጋል እስቲ ነገረን;; ሁላችንም የምንፈራው ወያነን ወይም ሽብያን እንጂ ሊላው የሚያስፈራ አይደለም;; ኦነግ ልትለኝ ትችል ይሆናል;; ኦነግ ከህዝቡ ማእበል ጋር እንደሚሂድ ግንጭ እያሳየ ነው;;
ሳምቻው አንዳንደ በራሳችን ውስጥ ችግር ፈጥረን የምናሳድግ ና አንችልም የምንል ከሆነ ምንም ነገር አይሳካልንም;;በቅድሚያም ትግሉ ውስጥ አለመግባት ይመረጥአል;; ያለ መስዋእትነት ድል የለም;;

በቸር ያቆየን
ድል ለህዝባችን
ዞብልየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Thu Feb 24, 2005 7:22 pm

ድንቄም ለኡአላዊነት

Postby moa » Thu Oct 06, 2005 5:45 pm

በመጀመርያ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚፈልገው ለደም ነው፤የኢትዮጵያ ሉአላዊነትን በመጀመርያ ያስደፈረው ወያኔ እንጂ ሻብያ አይደለም፡ ወዲ ሰበርጉማ ከተደበቅህበት ዋሻ የወጣኽው ያን አመድማ ስፍራ አጎቶችህ ዳግም ሊሸዋወዱበት ሲመጡ ብቅ ማለትህ ይህን መድረክ ለማምታታት መሆኑ ይገርማል፡

የኢትዮጵያ ሉዋላዊነት የተደፈረው ወያኔና ሻብያ በዚያች ቅድስት ምድረ ላይ ከተፈለፈሉ ወዲህ ነው፡
ለኢትዮጵያ ወደቧና ድንበሯ የነበረው ቀይ ባህር በወያኔ ሲሰጥ ነበር የሃገሪቱ ሉዋላዊነት የተደፈረው። ያ ሁሉ ወገናችን ያለቀበትን ሜዳ አጣጥሎ በህዝባችን ላይ የተሳለቀው መለስ ዜናዊ ዛሬ ባድመ ገለመሌ ቢለን ሁለቴ ማሰብ ያለብን ይመስለኛል።

ወገኖቼ እግዜር ያሳያችሁ! ከሻብያ ጋር ካልተደራደርን ምእራቡ አለም ማእቀብ ያደርግብናል እና እንደራደር ሲልና ከተቀዋሚዎች ይልቅ ላጎቱ ልጆች ልቡ የሚራራው የወያኔ ቅጥር በመሃል አዲስ አበባ እንደ ቅኝ ገዥ ጦር 42 ህጻናትን ግንባር ግንባራቸውን ሲነድል ዛሬ ባድመ ምናምን ቢለን ያው ነብሰባላውን አጋዚ ጦር እዚያው ወስዶ ይፈትሸው።ለዚያውስ ሻብያና ወያኔ ዛሬ የመጣባቸውን የህዝብ ሃይል ለማዳከም የወሰዱት የታክቲክ ዘዴ ቢሆንስ? ለትግራይ ህዝብ የሚቀርቡ በባህል፤በቋንቋ ፤የተጋቡ የተዋለዱ፤በደም የተሳሰሩ ኤርትራውያኖች ናቸው፡

ስልጣን ላይ ያሉትን እስቲ ፈትሹዋቸው? አባቱ ከዚህ ወይም ከዚያ ነው።መለስን፤በረከትን፤ሁሉንም ተመልከቱ ታድያ የሚቀርቡት፡ለወላይታው፤ለኦሮሞው፤ላማራው፤ለጉራጌው ነው? አንታለል፡

ይልቅስ ምርጫው የተጭበረበረበትን ቦታ እንደገና በነጻ ምርጫ ቦርድ ምርጫው እንዲደገም መታገልና መደራደር እንጂ ይህን አዘርፎ ወንበር ለሟሞቅ ፓርላማ መግባት በአርባ ሁለቱ የነጻነት ቀንዲሎች ደም ላይ ዋንጫ ማንሳት ነው፡
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

Postby የዘመኑ ልሳን » Thu Oct 06, 2005 6:25 pm

ሞአ ይህ እኮ የወያኔው ወዲ ሰበርጉማ አይደለም::እስቲ የተመዘገበበትን ቀን ተመልከት::

ወዲ ሰበርጉማ

Joined: 17 Mar 2005
Posts: 157
Location: united states

የወያኔውን ወዲ ሰበር ጉማ ዋርካዎች ከጌታ ያውቃል ጋር በአንድ ሰሞን Ban አድርገዋቸዋል::የወያኔው ወዲ አሁንም በተለያዩ ስም የየሾለከ ብቅ ይላል::አንድ ሰሞን ባካፋ ብሎ መከራችንን ሲያሳየን ነበር::እንደ ለግንዛቤ ቡዬ እንጂ ከእርሱ ጋር ምንም የሚያገናኘው የለም:
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

እንዴት ተብሎ ነው ከእዚህ አይነት መንግስት ጋር አብረው የሚሰሩት ?

Postby sheggaw » Thu Oct 06, 2005 6:43 pm

በመጀመሪያ ከዚህ አይነት መንግስት ጋር ሆኖ መስራት የማይቻልበትን ምክኒያቶች ብናይ ምናልባት ችግሩን አብጠርጥሮ መገንዘብ ይቻላል::
1. ሕገ መንግስት : ይህን ሕገ መንግስት እንደፈለገው እየተረጎመው ያልው መንግስት እንኳዋን እና ከትንሽ ጊዜ በኃላ ትናንት የነበሩት የሕዝብ 'ተመራጮች" ነን ያሉት እንደፈለጉት ህግ ሲደነግጉ እና ሲጠመዝዙት አይተናል:: ስለዚህ ሌላው ቀርቶ ፓርላማ ይግቡ የሚለው ጥያቄ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ? ምንስ ዋስትና አላቸው ምንም ላያደርጉዋቸው ? የሚሉትን እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ያስነሳል::
2. የገዢው ፓርቲ አለመታመን : ከታሪክ እንደተማርነው ይህ መንግስት ለውጥ ቢፈልግ ኖሮ ወይንም እውነተኛ ዲሞክራሲ ለህዝብ አሰጣልው ብሎ ቢፈልግ ኖሮ በብዙ እድሎች አጋጣሚ እያደረግ ይሻሻላል ብሎ የሚጠበቀውን ድርጊቶች አስመስክሮ በሕዝቡ ዘንድ እምነትን ያሳድር ነበር:: ነገር ግን እያደረ የዲክታተር ክምችት እንደሆነ በገሀድ እያስመሰከረ ነው::
3. ኢትዮጵያ እና ሉዓላዊነቷ : አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ቀይ ባሕር ነው:: ይህን ስል አፋር የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ተብሎ ተካሎ ሳለ መሬቱ ግን ለሌ መሰጠቱ እና ምንም አይነት መልስ ለተጠየቀው የባለቤትነት ጥያቄ መልስ ስላስጡ ከዚያም አልፎ ለሱዳን መሬት እየቦጨቁ የሚስጡ እስከሆኑ ድረስ ለሐገሪቷ ሉዓላዊነት ግድ የለሽ መሆናቸው አሁን በገሀድ አስመስክረዋል::
4. በኢትዮጵያዊያን ስም እና ደም መነገዳቸው : ሌላው ቢቀር 70,000 የኢትዮጵያ ጀግና ውታደሮች ሕይወታቸውን ሰውተው ከእንደገና መሬቱን ለማስረክብ የሰሩት ድራማ ከምንም የበለጠ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል::
ከዚይ በላይ ደግም በምርጫው ላይ የተደረገው ሴራ ደግም ሌላ ታሪክ ነው:: መለስ እኮ ያገኘው 99.9999% ውጤት ሳዳም ሁሴን እንኳዋን አላገኘውም...ሳዳም የለየለት ዲክታተር ነበር...መለስ በስውር ስራው ነው::
ስለዚይ ከሞላ ጎደል ባለፉት 14 ዓመታት የሰሩት ስራ ለሚቀጥለው 5 አይድለም ወር እንኳዋን አገሪቷዋን ለመምራት እድሉ ሊሰጣቸው አይገባም:: ከእነዚይ አይነቶች ጋር መስራቱም ሕዝብን መክዳት ማለት ነው::
sheggaw
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Sun May 15, 2005 10:43 pm
Location: azerbaijan

የኔ ሃሳብ!

Postby ትምህርት » Thu Oct 06, 2005 6:47 pm

ሰላም!

ይህንን መድረክ ለመወያያ በመክፈትህ ሳላመሰግንህ አላልፍም!

መቼም ያንተ ሃሳብ ምንድነው ብለህ ጠይቀሃል! እኔም ተቃዋሚዎች ያለ ምንም ማንገራገር ወደ ፓርላማ መግባት አለባቸው! ሆን ብዬ ነው ያሰመርኩት! ለምን? ይህ ጥሩ ጥያቄ ነው! መንግሥት በሚፈጥረው ጨዋታ መሳተፍ ትልቅ አዋቂነት ነው! ልብ በል ምርጫውን አንካፈልም ቢሉ ኖሮ አሁን ለማየት የበቃነውን ታሪክ ማየት እንችል ነበር?

ምክንያቶቼ:

1ኛ. እንደ ተቃዋሚነታቸው በድርጅትነታቸው እንዲቆዩ (survival)! መለስ እንደ ሙጋቤ አምባገነን እንዳይሆን ቀዳዳ አሳጡት ማለትም ነው!

2ኛ. ከሁለት አመት በኌላ የቀበሌ ምርጫ የሚደረግ ይመስለኛል! ስለዚህ ለዚህ ምርጫ ተዘጋጅተው በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ቢያንስ ከአዲስ አበባ ከሥሩ መንግለው ማስወጣት እንዲችሉ!

ማጠቃለያ: አሁን በሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ ከኢህአዴግ ጋ መደራደር ተገቢ ነው ብዬ በግሌ አላምንም:: ስለዚህ በተቃዋሚነታቸው (ማይኖሪቲ ሆነው) ወደ ፓርላማ መግባት አለባቸው! እዚያው እፓርላማ ሆነው ግን ኡኡታቸውን ማስነካት አለባቸው! አላሰራን አሉ! የአገር ገንዘብ ወደ እዚህ ተንቀሳቀሰ! ለዚህ አካባቢ የተመደበው በጀት ያላግባብ ነው! የዚህ ብሄረ-ሰብ አባላት አላግባብ ይህንን አገኙ ያንን አገኙ ወዘተ ዝርዝሩ አያልቅም!

ተቃዋሚ ሆኖ ተወዳጅ መሆን ቀላል ነው! በአንጻሩ ደግሞ በሥልጣን ላይ መቀመጥ በድምጽ አንጻር ሥልጣን ለያዘው ድርጅት(ያውም እኛ አገር) ጎጂ ነው! ለዚህ አይነት ነገር ምሳሌ ማቅረብ ከባድ አይመስለኝም:: ኦስትሪያው የሃይዳር ቀኝ አክራሪ ፓርቲ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው! ፓርቲው ሳይታሰብ በከፍተኛ ተስፋ ወደ ስልጣን መጣ! በሥልጣን ብዙ ጊዜ ሳይቆዩ እራሱን ዋንዋን ሰውየው ከዋና ሥልጣን አገለሉት! ያንን ፓርቲ ለአገር ሥልጣን ያደርሰ ሰው አሁን ባውራጃው እንኳን ተወዳጅ አይደለም::

ካገራችንም ቢሆን ምሳሌ መጥቀስ አያስቸግርም:: ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ በእማኝነት መጥራቱ በቂ ነው! ያሁኑን ጨምሮ ሦስት ጊዜ ተመርጠዋል:: አኚህ ሰው አሁንም ተወዳጅ(ቢያንስ በተመረጡበት አካባቢ) ናቸው! እሳቸውም ደግመው ደጋግመው የተመረጡት ላካባቢያቸው ልማት እና እድገት ስላስገኙ ነው? አይደለም! ጥሩ ጯሂ ስለነበሩ ነው! ተቃዋሚዎች ለጊዜው በመጮህ ተግባር ላይ መሰማራት አለባቸው! ለዚህ ደግሞ ጥሩ እና የተመቸ ቦታ ፓርላማ ነው! በመጮህ ስልጣን አለ!

እኤአ 1998 ይሁን 99 ረሳሁት! ያኔ መለስ ፕሬዚደንት ነበሩ! በዚህ አመት አካባቢ በአሜርካ ምክር ቤት ንግግር አድርገው ነበር:: ከንግግራቸውም ውስጥ 'ጠንካራ ተቃዋሚ ላገራችን ልማት እና እድገት ያስፈልጉናል:: ስለዚህ ለዚህ ጉዳይ የበኩላችንን ከማድረግ ወደ ኌላ አንልም' የሚለው ይገኝበት ነበር!! አሁን የልባቸው የተፈጸመ ይመስለኛል! ባሁኑ ወቅት ደግሞ ተቃዋሚዎች ፓርላማ እንዲገቡ ምኞት እንዳላቸው እናውቃለን:: ስለዚህ ተቃዋሚዎች ግቡ ግቡ እንዳሏቸው ፓርላማ ገብተው እኚህን ሰውዬ እንደ ሞጀሌ ነቅለው ማውጣት አለባቸው!

ዋናው ነገር ትዕግስት ነው!!! ባጭር ጊዜ ሁሉንም ላግኝ ማለት ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል ብዬ እገምታለሁ!

እስኪ የናንተን ልስማ! ሳትስደነግጡን ሃሳባችሁን ስጡ! ድንፋታ ዋጋ የለውም!

አክባሪያችሁ!
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

Postby ዶኑ » Thu Oct 06, 2005 7:07 pm

ወዲ ሰበርጉማ wrote:ሳምቻዉ

ይህንን ጽሁፍ ብታነብ ላነሳኻዉ ጥያቄ በቂ መልስ የምታገኝ ይመስሎኛል::

http://www.ethiomedia.com/fastpress/andargachew.pdf

የሉአላዊነት ጉዳይ በእዉን የጊዜዉ አንገብጋቢ ጉዳይ ነዉ??? ሉአላዊነታችንን አሳልፈው ከሰጡት ጋር ያሎው ትግል የሚቀድም አይመስልህም???

ወዲ ሰበርጉማ!

እውን አንተ ኦሪጅናሉ ወዲ ሰበርጉማ ነህ?.. ቅቅቅቅቅ.... መልስህ የሚያስቅ ብቻ ሳይሆን ማንነትህንም እንደገና እንዲናስብ የሚያደግ ነው ;;በመጀመሪያ ከሁሉ በፊት በቅድሚያ ወያኔን መፋለም የሚለው ሀሳብ ከሌላ ወገን ቢቀርብ የሚያስደንቅ ሊሆን አይችልም :: ካንተ ስንሰማ ግን ወዲ ሰበርጉማ ለምን እንደዚያ ሊል ቻለ ብለን መጠየቃችን ግድ ይሆናል;; ከእባብ እንቁላል እርግብ አይጠበቅምና ነው::


ደህና እንሰንብት
ዶኑ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 411
Joined: Fri Apr 01, 2005 5:31 am

Postby የዘመኑ ልሳን » Thu Oct 06, 2005 7:54 pm

እኔ የኔን አስተያየት ከመስጠቴ በፊት ከኔ በላይ የሳፈው ግለሰብ ሀሳብ ጥቂት አስታየት ልስጥ::

ትምህርት እንደጻፈችው wrote: አሁን በሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ ከኢህአዴግ ጋ መደራደር ተገቢ ነው ብዬ በግሌ አላምንም :: ስለዚህ በተቃዋሚነታቸው (ማይኖሪቲ ሆነው ) ወደ ፓርላማ መግባት አለባቸው ! እዚያው እፓርላማ ሆነው ግን ኡኡታቸውን ማስነካት አለባቸው ! አላሰራን አሉ ! የአገር ገንዘብ ወደ እዚህ ተንቀሳቀሰ ! ለዚህ አካባቢ የተመደበው በጀት ያላግባብ ነው ! የዚህ ብሄረ -ሰብ አባላት አላግባብ ይህንን አገኙ ያንን አገኙ ወዘተ ዝርዝሩ አያልቅም !


በመጀመርያ እኔ ብዙ ጊዜ ከምትሰጠው አስታየት አንተን ከወያኔ ጎራ አድርጌ ነው የማይህ::ሁል ጊዜ የወያኔን ሀሳብ ስታንጸባርቅ ስለምሰማ ነው::እኔ በዋርካ ላይ የተቋዋሚዎች ሀሳብ ብቻ ይሰማ የሚል አቋም ስለሌለኝ በግልጽነት የፈለከውን ሀሳብ ብትሰጥ ቅር አይለኝም::

ወደ ሀሳብህ ስመጣ ያንተን ሀሳብ የተረዳሁት ተቋዋሚዎች ፓርላማ የሚገቡት የመረጣቸው ህዝብ መብት ለማስከበር ሳይሆ ወያኔ ሲረግጠው እያዩ እንዲጮሁ ነው::የታጠረ ጊቢ ውስጥ ሆነው ቢጮሁ ማን እንዲሰማቸው ነው? ደግሞስ ለመጮህ ፓርላማ መግባት ያስፈልጋል::እቤታቸው ቁጭ ብለው ማንኛውንም ወያኔ የሚሰራውን ነገር እስካሁን ያደርጉት እንደነበረው ማጋልጥ ይችላሉ::እኔ እንደውም በዚህ ጉዳይ ላይ ፓርላማ ካሉት ይልቅ ነጻው ፕሬስ የበለጠ ሲሰራ አያለሁ::አብዛኛው ወያኔ በሀገራችን ላይ የሚሰራቸውን አሻጥሮች ሲያጋልጡ የማየው እነዚሁ የሀገራችን የቁርጥ ቀን ልጆች የነጻው ፐሬስ ጋዜጠኞች ናቸው::እዚህ ላይ ችግሮች የሉባቸውም ማለቴ ሳይሆን የተሻሉ ናቸው ለማለት ነው::

ሌላው ተቋዋሚዎች ከወያኔ ጋር ሳይደራደሩ ዝም ብለው ማይኖሪቲ ሆነው ፓርላማ ይግቡ ማለትህ መደራደሩ ምንም ጥቅም የለውም ማለትህ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ማይኖሪቲ ሆነው የሚለው አሁን የያዙትን ውቴትና ወያኔ ያወጣውን አጀንዳ ለማስያዝ 50% በላይ ፊርማ ያስፈልገዋል የሚለውን እንኳን ሳያስቀይሩ የወያኔን ፓርላማ ለማድመቅ ይግቡ ማለትህ መሆኑን ተረድተህዋል::ወያኔ የሰረቀው የህዝብ ድምጽስ? ያሁኑን እሺ ገቡ በሚቀጥለው ወያኔ እንደ ልማዱ ላለመስረቁ ምን ዋስትና አለ? ለማንኛውም Offend ካደረኩህ ይቅርታ::የተሰማኝን ለመግለጽ ነው እስቲ ደግሞ የኔን ልግለጽ::

እኔ ተቋዋሚዎች ቢገብና ባይገቡ ሊያገኙትና ሊያጡት የሚችሉትን ነገሮች ገምተው መወሰን አለባቸው እላለሁ::እስቲ ሁለቱንም ለየብቻ ሊያቸው::
 1. ፓርላማ ቢገቡ
  • ከወያኔ ጋር ያለውን ጊዚያዊ ፍጥጫ ለጊዜው ያረግባሉ::
  • በተወስነም መልኩ የመረጣቸውን ህዝብ ድምጽ በፓርላማው ቢያንስ ያሰማሉ
  • በድርድሩ አሳማኝ ምክንያት ያያገኙ ቢገቡ አብዛኛውን የሀገር እና የውጭ ያለ ህዝብ ድጋፍ ያጣሉ(በሚቀጥለው መመረጣቸው ጥያቄ ውስጥ ይገባል)
  • ከዚህ በላይ ለመሄድ በዚህ ድርድር ውጤትና በወያኔ ፈቃድ ላይ የተመረኮዘ ነው::
 2. ፓርላማ ባይገቡ
  • ማለቂያ የሌለው ከወያኔ ጋር ትግል ይገጥማሉ
  • ወያኔን ህዝቡ አንድ ካላለ እንደልብ እንዳይንቀሳቀሱ መሰናክል ሊፈጥርባቸው ይችላል
  • አሁን ያለው የህዝብ ድጋፍ አብራቸው ይቀጥላል::ይህም ወያኔ የሚያደርስባቸውን ጫና መቋቋም ያስችላቸዋል::

ይህን ከላይ ያሉትን ካገናዘቡ በኃላ እኔ በጣም ያሳሰበኝ ሀገራችን እስከመቼ ያለ ዲሞክራሲ ትሰቃያለች የሚለው ነገር ነው::እኔ ፓርላማ ቢገቡም ባይገቡም አሁን እንዳለው የአፍ ብቻ ዲሞክራሲ ሳይሆን ግልጽ የሆነ የተግባር የዲሞክራሳዊ አሰራር እንዲኖር መታገሉ ላይ ነው ቁምነገሬ::በሚቀጥሉት 5 አመታት ውስጥ
 • ነጻ ፕሬስ ያለገደብ እና ተጽህኖ በሬድዮና በቴሌቨዥን እንዲቋቋም ከተደረገ
 • በፍርድ ቤት አካባቢ ያለው አሰራር ግልጽ ከሆነ(ፍርድ ቤቶች ከፓርቲ ተጽህኖ ነጻ ከሆኑ)
 • ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ተደርጎ እንደገና ከተቋቋመ
 • ሚሊተሪው ሆነ ፖሊሱ ለፓርቲ ሳይሆን ህግን አስከባሪ ሆነው ከተቋቋሙ


ከሚቀጥለው አምስት አመት ውስጥ ወያኔ ታሪክ እንደሚሆን አልጠራጠርም::ስለሆነም ተቋዋሚዎች ፓርላማ እንግባ አንግባ የሚለው ጨዋታ ውስጥ ሳይሆን እነዚን አካላት እንዴት ነጻ ልናደርጋቸው እንችላለን የሚለው ላይ ቢያተኩሩ እመርጣለው::እነዚህ ነገሮች ሳይስተካለሉ ቢገባ የዛሬ አምስት አመትም አንድ አይነት ስለሚሆን አሁን እነዚን ነገሮች ፓርላማ ገብተው የሚያስተካክሉ መስሎ ከታያቸውና ካመኑበት እኔ በበኩሌ ተቋውሞ የለኝም::ነገር ግን ምንም ላይፈይዱ ከሆነ የሚቀጥለው አምስት አመት ላይ እንደገና ከምንጫጫ አሁን የተከፈለው መሰዋትነት ተከፍሎ ነገሮችን ማስተካከል አለባቸው::

እኔ ከድርድሩ ውጤት ሊኖር ይችላል ብዬ ስለምጠብቅ ይግቡም አይግቡም ለማለት የድርድሩን ውቴት እንጠብቅ እላለሁ:;
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

የመልስ መልስ

Postby ትምህርት » Thu Oct 06, 2005 9:02 pm

የዘመኑ ልሳን wrote:ወደ ሀሳብህ ስመጣ ያንተን ሀሳብ የተረዳሁት ተቋዋሚዎች ፓርላማ የሚገቡት የመረጣቸው ህዝብ መብት ለማስከበር ሳይሆ ወያኔ ሲረግጠው እያዩ እንዲጮሁ ነው ::የታጠረ ጊቢ ውስጥ ሆነው ቢጮሁ ማን እንዲሰማቸው ነው ? ደግሞስ ለመጮህ ፓርላማ መግባት ያስፈልጋል ::እቤታቸው ቁጭ ብለው ማንኛውንም ወያኔ የሚሰራውን ነገር እስካሁን ያደርጉት እንደነበረው ማጋልጥ ይችላሉ ::እኔ እንደውም በዚህ ጉዳይ ላይ ፓርላማ ካሉት ይልቅ ነጻው ፕሬስ የበለጠ ሲሰራ አያለሁ ::አብዛኛው ወያኔ በሀገራችን ላይ የሚሰራቸውን አሻጥሮች ሲያጋልጡ የማየው እነዚሁ የሀገራችን የቁርጥ ቀን ልጆች የነጻው ፐሬስ ጋዜጠኞች ናቸው ::እዚህ ላይ ችግሮች የሉባቸውም ማለቴ ሳይሆን የተሻሉ ናቸው ለማለት ነው ::


ሰላም!(እኔ ሰላም ብየሃለሁ! አንተም ሰላም ብለህ ጀምር)

አንተም ከወያኔ ጎራ እንደሆንክ እኔ አውቃለሁ! ይህንን ነገር ያስቀመጥኩት ሁላችንም ይህንን ማለት እንደምንችል ለማሳየት ነው! ስም መለጠፍ ቀላል ነው! እንደገባህ እገምታለሁ! በዚህ ብዙ የመቀጠል ዓላማ የለኝም! ላንተ ለለመድከው ትቼልሃለሁ! እኔን የትም ብትመድበኝ አይከፋኝም!! የበሰልኩ ሰው ነኝ!

በእኔ ሃሳብ ላይ ስለሰጠኸው ሃሳብ የመልስ ሃሳብ ላቅርብ! ወንድሜ በዚህ አሁንም ሆነ ወደፊት ተቃዋሚዎች ከመንግሥት(ልብ በል ሃሳቤን ለመግለፅ መሳደብ አያስፈልገኝም:: አንተም ከእኔ ተማር::) ጋ በሚያደርጉት ድርድር የሚገኝ ነገር እንደሌለ ሰሞኑን ተቃዋሚዎች ያወጡትን የመግለጫ ተለዋዋጭነት መመልከቱ የሚረዳ ይምስለኛል:: ይህ ያሁኑን ድርድር መጀመሪያ ተቃዋሚዎች በመንግሥት የተጠየቀ እንደሆነ ገልጸው ነበር:: ጥቂት ሳይቆዩ ይህን መግለጫቸውን እንዲቀይሩ መንግሥት ግፊት አደረገባቸው! መንግሥት የመወያየት ዓላማ ቢኖረው ይህን ተጽእኖ ማድረግ ነበረበት ብየ አላስብም:: ነገር ግን ከእንደዚህ አይነት ስብሰባ መንግስት ለመጠቀም የተቻለውን ያደርጋል ብየ ከልቤ አምናለሁ! ስለዚህ ከድርድሩ ባለደል ሆኖ የሚወጣው ሁልጊዜ የመሳሪያ ሃይል ያለው አካል ነው!

ሌላው በተቃዋሚነት መቆየትን በሚመለከተው አንተ የተናገርከው የማይረባ ነገር እንደሆነ ለመግለጽ እወዳለሁ! እቤታቸው ተቀምጠው ምን ማድረግ እንደሚችሉ አንተ ብቻ ነህ የምታውቀው! ሰሞኑን በየትኛውም ሆቴል መግለጫ እንዳይሰጡ መታገዳቸውን አልሰማህ ይሆን! ቤታቸውም ለመንግሥት ይርቀው ይሆን! እነ ዶ/ር ብርሃኑ በሰላም እንደልባቸው የሚንቀሳቀሱ ይመስልሀል? አሁንም ማለቴ ነው! ወጋየሁ ምን እንዳደረጉት አልሰማህም! በእኔ እምነት እነዚህ ሰዎች ጨዋታቸውን ካላሳመሩ እንኳን ሰው ሊቀሰቅሱ ቀርቶ የራሳቸው ህይወት አደጋ ውስጥ ይገባል::

ምነው እንዳንተ አይነት ይህን መንግሥት የማመን ልብ ቢኖረኝ! አንተ እድለኛ ነህ! በእንደዚህ አይነት ሰዎች እቀናለሁ! የነጻ ጋዜጦች ህልውና ከተቃዋሚዎች ህልውና የሚለይ አይመስለኝም! ነገውኑ መንግሥት እንዲጠፉ አያደርግም ብየ አላምንም! ከፍተኛ ስጋት አለኝ! ከዚህ ሥጋቴ የተነሳ እነዚህ ሰዎች እዚያው አገር ቤት በኅቡዕ የሚተላለፍ ራዲዮ እንዲከፍቱ እመኛለሁ! እንግዲህ ሥጋቴን ያስረዳሁ ይመስለኛል! አይ ነጻ ጋዜጦች ሊጠፉ አይችሉም ካልክ በልዩነት እንይዘዋለን! ይህ አያጣላንም!

ሌላው የፓርላማ መግባታቸው ጉዳይ ነው! ወንድሜ የወቀቱን የአውሮፓ ፓርላማን የምትከታተል ከሆነ እላይ እኔ ያልኩት ነገር ሊገባህ ይችላል:: Austria's Freedom Party እና የJoerg Haidar ታሪክ በምሳሌነት አቅርቤ ነበር:: እንዲሁም በዴንማርክ: በኔዘርላንድ: በኖርዌይ: በቤልጂግ: በፈረንሳይ የFrench National Front leader Jean-Marie Le Pen ታሪክ ከተከታተልክ እኔ ያልኩህ ነገር ሊገባህ ይችላል:: እነዚህ ፓርቲዎች ፖፑላር ፓርቲዎች ይባላሉ:: ተወዳጅ የሆኑት በተቃዋሚነታቸው ነው! ስለዚህ የእኔ አባባል ተቃዋሚዎች ወደ ፓርላማ የሚገቡት ይበልጥ ተወዳጅ እንዲሆኑ ስለሚረዳቸው ነው! አገር ቤት ያለው ሰው ተቃዋሚዎች ወደ ፓርላማ እንዲገቡ አይፈልግም! ይህ የእኔ ግምት ነው! ስለዚህ ከዚህ መንግሥት ጋ በተደራደሩ ቁጥር መራጩ በእነሱ ላይ ያለው መተማመን እየቀነሰ ይመጣል የሚል ሥጋት አለኝ! ይህም መንግሥት ይህንን ነገር የሚያጣው አይመስለኝም!

ፓርላማ ገብተው ድምጽ መስጠት ስለማይችሉ ፓርላም ገብተው መስራት ስለማይችሉ መግባት የለባቸውም የሚባለው ሃሳብ አይገባኝም:: ዶ/ር በየን ምን ሰሩ? ሃሳባቸው በውሳኔ ካልጸቀ እንደገና ደግሞ በተግባር ካልዋለ ሃሳብ ብቻ ማቅረቡ ምን ጥቅም አለው? ልብ በል አስፈጻሚዎቹ: የካቢኔ አባላት በሙሉ: ኢህአዴጎች ናቸው:: የአዲስ አበባ ምክር ቤትን ከምርጫው ማግሥት ስልጣኑን እንደገፈፉት አላስተዋልክም:: እና ያንተ አመለካከት ፓርላማ ገብተው ሃሳብ መስጠት አለባችው የሚለው ዋጋ እንደሌለው እዚህ ያሳየሁ ይመስለኛል!

እንግዲህ እኔ ያልኩት እነዚህ ተቃዋሚዎች በህልውናቸው እንደተጠበቀ(መቶ በመቶ እርግጠኛ አይደለሁም) እዚያው ፓርላማ ገብተው ቢንቀሳቀሱ ይሻላል:: ምናልባት ላገኙት ድምጽ የሚመጥን ወይም የሚያንስ በመንግሥት መገኛኛ ብዙሃን የመጠቀም እድል ያገኙ ይሆናል:: ያገኙትን የህዝብ ድምጽ እንደያዙ! ይኸ መንግሥት አሁን አገኘሁት ከሚለው መቀመጫ ለተቃዋሚዎች አንድ ባርጩማ ይሰጣል ብየ አላምንም!!! በዚህ መንገድ የተቃውሞ ሥራቸውን ቢቀጥሉ ይሻላል ብየ እገምታለሁ! ከዚያም ለቀበሌ ምርጫ ከሁለት አመት በሁዋላ ይህ መንግሥት ቢያንስ ከአዲስ አበባ ይወገዳል ማለት ነው!! ይህን ነገር ስናገር ግን እውስጡ ብዙ ምኞት አስገብቼ ነው!

ከሰላምታ ጋር!
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests