"" ዋርካ ዲቤት "" ቅንጅት የፓርላማው አካል ይሁን ወይስ ፓርላሜንታሪነቱን ይሰርዝ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ከኛ ወድያ ፉጨት አፍን ማሞጥሞጥ ነው ...

Postby ሞንክ » Sun Oct 09, 2005 6:27 pm

ትምህርት wrote:
ፓርላም ገብተው ::
ዶ/ር በየንምን ሰሩ?

በህልውናቸው እንደተጠበቀ!ሳም

ብታይ እኮ በሳቅ ነው የፈነዳሁት! ስስቅ ብታምንም ባታምንም ሄንከን ቢር ኪቦርዴ ላይ ፈሷል ..ቦርዴ ነው የመሰለው አረፋው !

የኛ የእንግሊዘኛ ችሎታ በክሪስ ማስ ሆል ትራፊ ጭምር አልፎ ይሄዳል ተብሎ የተሰበከበት ዘመን አልፎ አሁን እንዲህ ስሰማ ከምር ጡረታ የወጣሁኮ ነው የሚመስለኝ !

እርግጠኛ ነኝ ኪሊዮ ፓት ሳታስታውስ አትቀርም! , ማን ነበር ዲያሎ ብርሀነን ታስታውሰዋለህ አይደል ? 4ኪሎዎች ላይ ሲነጀብ አንዴ ያለውን , የካንፓሱን ኣጥር ታከው የሚኖሩት የመንን ጋንጎች የአራት ኪሎን ተማሪ ኢንግሊሽ በወረፋ ያስጠናሉ .... ቅቅቅቅቅ !

ትምህርት አማርኛ ሳይችል እንግሊዘኛ ለማረም የሚኮላተፍ መሆኑ ይሆናል ብዙዎቹን የሚገርመው ይሄኔ ድሮ ባማርኛ ፔሬድ ቂጡ ተገልቦ አርባ የተገርፈበት ጠባሳው እስክሁን ከቂጡ ላይ እንዳልጠፋ እንደሆንስ ማን ያውቃል ጎበዝ !

ሳም ፕሊስ ፐብሊክ ሌክቸሩን ቀጥል ....
ፖዲየሙ ላይ ሰናይትን አስቀምጥልሀለሁ ! ቂቂቂቂ

በል አሴ ቤት እንገናኝ ! ፍርፍር አለሀለሁ

ሞንክ / ዩንቨርስቲ ፓላስ
ሞንክ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 287
Joined: Thu Feb 17, 2005 8:02 pm
Location: france

አመሰግናለሁ!

Postby ትምህርት » Sun Oct 09, 2005 6:49 pm

ሰላም!

ስለ እርማቱ በጣም አመሰግናለሁ! እግዜር ይስጥልኝ! ወደፊት ለማስተካከል እሞክራለሁ! እንደዚህ የተናድዳችሁት ምን ጥፋት ተገኝቶብኝ ይሆን! ለማንኛውም ይችን ተመልከታት!

ሰውን ላለማሰልቸት ንግግሬን ጨርሻለሁ! ሌሎቻችሁን ይቅርታ ጠይቄያለሁ!

አክባሪህ!
Last edited by ትምህርት on Sun Oct 09, 2005 7:34 pm, edited 1 time in total.
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

Postby እንድሪያስ » Sun Oct 09, 2005 6:50 pm

ሳምቻው wrote:እንዚያን ቃላቶች ለመረዳት ዲክሽነሪ ላይ ተኝታችሁ ከምታድሩ 4ኛ ክፍል የሚማር ታናሽ ወንድማችሁን ለ ""context meaning"" እርዳታ ብትጠይቁት ይቀላችሁ ነበር :: ጠቅለል አድርጌ ስጽፍላችሁ ይዘቱ ይገባችሁዋል ብየ እንጂ አዲስ እንደተቀጠረች ቀዥቃዣ ሴክሬተሪ proof reading ለማገዝ ትጣደፋላችሁ በማሰብ አልነበረም :: ለካ speling error ለይቶ ማውጣት ""ያራዳ"" መሆን ጀምሯልና !! ወቅታዊ ጉዳይ በመሆኑ ይህንንም በአጀንዳነት እንይዘዋለን ቅቅቅቅቅቅ !!


የምን ቡራከረዩ ነው ጌታው ?
አስተካክለህ አቅርበው የሚል ገንቢ ሀሳብ ሲቀርብልህ ማመስገንና ያለውን ስህተትና ግድፈትም ማረም ሲገባህ አስፈላጊ ያልሆነ ስድብና ሌላ ታዕብ ታበዛለህ ::ሳምቻው wrote:ቃቢል የወንድሙን የአቢልን ሬሳ ምን እንደሚያደርገው ግራ ገብቶት ሬሳውን ተሽክሞ ለቀናት ጢሻ ለጢሻ ይዞ ሲዞር የነበረውን ታሪክ አስታውስኩ !!

ተመልከት እዚህ ጋ ........ ቃቤል(ቃየን+አቤል= ቃቤል)ቅቅቅቅቅቅ ልክ... smoke+fog= smog ወይም motor+hotel= motel..... በዚህ አይነት ሁለት ቃላትን በማጋጨት አንድ ቃል እንደሚፈጥሩት..... አንተም ቃላትን እያዳቀልክ ነው መሰለኝ :: ሌላው ደግሞ " ቃየን የአቤልን ሬሳ ተሸክሞ ለቀናት ሲዞር ነበር " ያልከው ታሪክ ከየት እንዳነበብከው እግዚአብሄር ይወቀው ::
የቃየንና አቤል ታሪክ Genesis 4:1-24 ላይ ተጀምሮ ያልቃል :: እና ፈጥረህ ከማውራት መጽሀፍ ቅዱስ ገለጥ አድረግህ ተመልከት .....ትንሽ እንኳን ግንዛቤ እንዲኖርህ ::
ብዙ የአለም የፖለቲካ አዋቂዎች (ፖለቲካል ኣናሊስትስ ) ሲወያዩ መሰረታዊ ልይነታቸው በስትራቴጂ እንጂ በፕሮሴጀር አይደለም /ብዙ ግዜ/ :: የኣሜሪካንን ኮንግረስ ፓርቲ አባላት እንኳ ብንወስድ ልየነታቸው የስትራቴጂ ና የሚሽን እንጂ የዲሲፕሊን እና የአሰራር አይለም :: common knowlege ወይም proceger ላይ መወዛገብ ያልተለመደ ነገር ነው ::የኛ የሶስተኛው አለም ፖለቲሺያኖች ባህል ደግሞ በተነሱት ርእሶች ላይ መሰርታዊ ግንዛቤ(basical analises) ማጣት ነው :: በመሆኑም በቅጡ ያልጨበጥነውን "" subject" በውይይት ልንፈታው ቀርቶ ,ልናስተምረው ቀርቶ በራሱ ተመልሶ ቻሌንጅ ያደርገናል :: ደህና ! ይህን መለወጥ ግን ይቻላል ::

እዚህ ላይ ቅቅቅቅቅ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም እንዲሉ የቃላት ግድፈት ላይ ነው ልብህ የቆመው ...እኔ ግን ባይገርምህ እሱን ግምት ውስጥ አላስገባሁትም ::
ለእኔ.... ለማስተላለፍ የፈለከው መልዕክትና መግለጽ የፈለከው ሀሳብ ራሱ ምን እንደሆነ አልገባኝም ::
ለዚህም ነው እንደገና አብራርተህ አቅርብልን ያልኩህ ::

ለሞተ ፍጡር የተሻለ እጣ ""መቅበር"" ብቻ ነው :: ሲምፕሊ ጉድጓድ ቆፈር ቆፈር አድርጎ መቅበር !! ቃቢል ይህን እንኳ አያውቅም ነበር ምክንያቱም ሰለያዘው የወንድሙ ሬሳ ምንነት አሁን አልገባ ብሎታል :: ከአምላኩ የተላከ ቁራ ነው መሬት እየጫረ ቀብርን ያስተማረው !


ሰው ሲሞት መቅበር "" ኮመን ኖውሌጅ " ነው ::
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ድንቅ አገላለጽ.........

ኢትዮጵያውያን የ parliamentary democracy አሰራር ምን እንደሚመስል ለናውቅ ይገባል :: ፓርላማ (ህግ መወሰኛው ምክር ቤት ) ምን እንደሚሰራ , ምን እንደማይሰራ ለይቶ ማወቅ , ማይኖሪቲ ፓርቲ ምን አይነት ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችል ማወቅ, እንዲሁም የመንግስትን ባህሪን እና ፈንክሽን , የህግ እና የ ሲቪክ አካላት በመሳሰሉት ላይ አንድ ተመሳሳይ እውቀት ልንይዝ ይገባል :: በሂሳብ ህግ 2+2 ምንጊዜም 4 ነው :: በዚህ ስሌት ስንስማማ የሀገራችንን ተጨባጭ እና ነባራዊ ሁኔታዎች በውል እያገናዘብን በወቅቱ ባለው መንግስት የሶሽዮ-ፖለቲካል-ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ላይ ልንወያይ እንችላለን ::መጀመርያ ምሰሶውን አልያዝንም ለውይይት ....
ፓርላሜንታሪ ዴሞክራሲን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል......አንተንም ያስተምርሀል ከፈለክ :: አንተ ነህ ይልቅ በቂ ግንዛቤ ሳይኖርህ ግልብና ባዶ አንተነትህን ይዘህ ገብተህ የህዝብን ማንነት ከአለበት ደረጃ ለማሳነስ የምትጥር ::
ለህዝብ ክብር ሳይሆን ለራሳቸውን ጥቅምና ስውር አላማ ለሚሯሯጡት ለዘብተኛ ፖለቲከኛ ተብየዎች እያጨበጨብክ መሆንክን አንተ ብቻ የምታውቅ መስሎህ ይሆን ? ቀስተ ደመና ማለት የቃል ኪዳን ምልክት ነው .....በህዝብ ፊት ለህዝብ የተገባ ቃል እንጂ ህዝብን ለመስዋዕት እያቀረቡ የግልን ጥቅምና ፍላጎት ማሟላት አይደለም ::

በሀገራችን የፓርላማ አሰራር ላይ እና የፖለቲካ ኃቆች ላይ ( parliamentary procegers and poletical facts ) ላይ የተለያየ እውቀት ካለን መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደተጣለው ህጻን ( the child lost on the cros road ) አይነት መሆናችን ነው :: ከየት እንደመጣን እና የት እንዳለን ካላወቅን ወደየት እንደምንሄድ አናውቅም !

ሳምቻው ወንድሜ መጨረሻ የምመክርህ .....አእምሮህን በደንብ ለማሰራት ሞክር እና ለማለት የምትፈልገውን በደንብ ለማብራራት ጥረት ይኑርህ::
በተረፈ መድረክ የራስህ ነውና ታዳሚዎችን በስርዐት ለማስተናገድ ሞክር ቅቅቅቅቅቅቅ እኔንም ጭምር ማለት ነው ::
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1784
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

U NEED A DOCTOR HELP !

Postby ሳምቻው » Sun Oct 09, 2005 7:26 pm

እንድርያስ

ምነው ዛሬ ልቃምክም መሰለኝ !

አና ሶልበርግን ይዘዝብህና የአረብኛው ስክሪፕቸር
አቤልን አቢል ቃዬልን ደግሞ ቃቢል ብሎ ነው የሚጠራው! ባጋጣሚ ሆኖ እኔ ታሪኩን የማውቀው ካረብኛው የተወሰደውን ስክሪፕት በማንበብ ነው . !የእንግሊዘኛው ደግሞ የራሱን ይሰጣቸዋል! አሁን ችግሩ አንተ በዚህ ሰፊ ዩንቨርስ ውሥጥ እራስህን በትንሽ ሳጥን ውስጥ ማግኘትህ ይመስለኛል. ከፈልክ ድንቅ አባባል አይሁን !!

ግን ለምን የማያገባህ እና ያልኮረኮረህ ነገር ውስጥ ሁሉ ገብተህ ትፈትፍታለህ ..?የሚከታተልንን ሰው አስበው ! አብሬህ ማፈሪያ ልሆን ከዚህ በኅላ ዝግጁ አይደለሁም !

በተረፈ አንተም ሆናችሁ ትምህርት በትህትና /ስህተትህን አርም / ሳይሆን ያላችሁኝ ስህተቴን ነው አድምቃችሁ የሰጣችሁኝ . እና ደስተኛ ትመስሉ ነበር . የሱዋሂሊኛ ዲክሽነሪ አዲስ የተፈበረኩ ቃላቶች ብላ ብላ ፓፓ ፓፓ ,ፒፒፒ.ፒ

ለመሆኑ ግን .........እናንተ ሁለታችሁን በዚህ ሩም ውስጥ ልክ እንደሌላችሁ ያህል ብረሳችሁ ምን አለብኝ ...??
Last edited by ሳምቻው on Mon Oct 10, 2005 12:33 pm, edited 1 time in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

ከሰላምታ ጋር

Postby ትምህርት » Sun Oct 09, 2005 7:41 pm

ሰላም ሳም!

ሁልጊዜ ስጽፍ ሳም ማለቴን ልብ ብለሃል? እኔ እንደዚህ አላሰብኩም ነበር!! ይቅርታ ታደርግልኝ ዘንድ በማክበር እጠይቃለሁ! ውይይቱን እንቀጥል!

አክባሪህ!
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

ስማ እንድርያስ

Postby ሞንክ » Sun Oct 09, 2005 7:53 pm

ማነህ እንድርያስ ..

ሀሳብ ካለህ በተጀመረው ርእስ ላይ ሀሳብህን አካፍለን !! ከሌለህ ሌሎች የሚሉትን በስረአቱ ተከታተል ! አባክህ አትረብሽን !! እንለምንህ.

መጥረግ ብቻ ነው ትልቁ የሕወትህ ይዞታ ? ማንም ሰው የተሰማውን ኃሳብ በነጻ መግለጽ እንደሚችል ከምትኖበት ሀገር አለመማርህ ያሳዝነኛል!

በጥላቻ የተሞሉት አስተያየቶችሕ በፍጹም ገና ምንም ነገር እንዳልገባህ ያረጋግጣሉ . ይህንን ከፈለክ አትመን ! ግን ሰላም ስጠን .

ሞንክ / ከ ልኡለ ገነት ፓላስ
for all of you ,

pls use the new Google tool bar , to make the POPUPS OKAY . if u have installed the pop up blocker , u can not open the clips . thanks !
ሞንክ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 287
Joined: Thu Feb 17, 2005 8:02 pm
Location: france

Re: ስማ እንድርያስ

Postby ትምህርት » Sun Oct 09, 2005 8:04 pm

ሞንክ wrote:
ትልቁ የሕወትህ ይዞታ ?.... እንደሚችል ከምትኖበት ሀገር

ሞኒካ /


ሰላም!

በል በዚሁ ቀጥል:: አጻጻፍህ ደስ ይላል! እንዳትቀየር! እዚችም ተጫን እንዳታመልጥህ!

ምንጊዜም አክባሪህ!
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

ሀሳቡን ብቻ እንወያይ whatever the argument is

Postby ሳምቻው » Sun Oct 09, 2005 8:35 pm

ሰላም ትምህርት

በቀሪው አለም የፓርላሜንተሪ ዲሞክራሲ ልምድ ላይ በመንተራስ ከሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ጋር አዛምደህ ያቀረብከው አርጊዩመንት ቀልቤን እንደሳበው ነው ! እኔም ውስጥ ያለ ነገር ቢኖር ይኽው ነው ! እንደምገምተው የብዙዎቹ የ ቅንጅት ጠንካራ ፖለቲሺያኖች አቋምም ይሄው ይመስለኛል ! በተለይም በማእከላዊው ኮሚቴው የአመራር አባላት አካባቢ ያሉት ባብዛኛው .ሁለት ሶስተኛ ድምጽ ያገኛል የሚለውን ግን አሁን እርግጠኛ ሆኘ መናገር ይከብደኛል !

የብረሀኑ እና የልደቱ አቋምም ይሄው ነው! ኦፖዚሽኑ ፓርላማ እንዲገባ የአሜሪካን ግፊት አላባራም . የሀገሪቱ ደህንነት ሀላፊነቱ በመንግስት ትከሻ ላይ ብቻ የተጣለ የማይመስልበት ደረጃ ላይ የተደረሰ ይመስላል handle with care ነው ነገሩ !!

ፓርላማ አንገባም ስንል , በሀገሪቱ ተሰባሪ ሰላም መኖሩን , የደቀቀ ኢኮኖሚ መኖሩን በመንግስት የሚመራ ክራክ ያደረገ ሉአላዊነት መርፈዱን እና ሌሎችም ተመሳሳይ አደጋዎች ሁሉ ተነጥለው ሊሰመሩበት እና ሊያወያዩን ይገባል . ህዝባዊ አመጹ እራሷ ኢትዮጵያን ዋጋ እንዳያስከፍለን ነው የኔ ስጋት .

አሁን ወደ መኝታዬ እንድሄድ ፍቀድልኝ እና ጥዋት ላይ ጥሩ አድርጌ ቀልብህን አስበዋለሁ .

ሳም
Last edited by ሳምቻው on Mon Oct 10, 2005 1:31 pm, edited 1 time in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

እስካሁን እዛው ላይ ናችሁ?

Postby ላህ » Mon Oct 10, 2005 10:27 am

ወይ ጉድ ምናለ ጊዜያችንን ለሚረባ ነገር ብንጠቀምበት እኔ ብዙ ለማወቅ ካለችኝ ጊዜ አሯሩጨ ብገባ እስካሁን ልክ እንደኛ ሰፈር ሴት አዳሪወች ጠብ እዛው ላይ ናችሁ!? ዋው ከሞን ጋይስ እንወያይማ በተለይ ዛሬ ያ የተረገመ ኢኮኖሚክስ ስለ ፖቨርቲ ነበር አቦ አሰለቸኝ ነው የሚባለው ቆዳየ ነው ያለቀው ....እናም እባካችሁ ስለ ፓርሊያመንት አወቃቀራችንና ስለኢኮኖሚ መርሀችን ትንሽ አሳውቁኝ....ግን ግን አልዋሻችሁም ኢኮኖሚክስ ያጠና ኢትዮጵያዊ ምንኛ ተበድሏል...እያወቁ...መሞት...ፈውስ የሌለው በሽታ ብየዋለሁ ለማንኛውም ባለቢራወችም ሆናችሁ ባለ ፊደል ተቆጣጣሪወች ወይም የመጽሀፍ ቅዱስ ሰባኪወች እባካችሁ ልዩነት ዉበት ነውና ተከባብረን እንማማር.......
ከአክብሮት ጋር
ላህ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 151
Joined: Fri Oct 29, 2004 2:03 am
Location: ethiopia

ፓርላማ የመግባቱ አስፈላጊነት

Postby ሳምቻው » Mon Oct 10, 2005 12:26 pm


እርግጥ ነው ማይኖሪቲ ወንበር ይዞ ፓርላማ መግባቱ
የኢሀዲግ ፖሊሲዎችን ከመጽደቅ አያድናቸውም ::

ሆኖም ኢትዮጵያን ከማዳኑ አንጻር ፓርላማ የመግባቱ ትልቁ ምክንያት በሶስት አበይት ምክንያቶች የሚታይ ይሆናል :-

1.የኢሀዲግ ፖሊሲዎች የለየለት ጸረ-ኢትዮጵያ ኢንተረስት ሆኖው ሲመጡ የምክር ቤቱን ትኩርት በሚስብ መልኩ ዲፌንድ በማድረግ ለህዝብ ማጋለጥ እና የማይበርድ ቻለሌጅ ለገዢው ፓርቲ በመስጠት አመራሩን ፍራስትሬት ለማድረግ

2. ተቃዋሚዎች ፓርላማ አንገባም የሚል ኦፊሻል አቋም ሲይዙ, እንደዚያ ብለው ባወጁበት ደቂቃ ውስጥ የተመዘገበ ህጋዊ ሰውነታቸውን (legal personality) በግልጽ አጡ ማለት ይሆናል :: ይህ ደግሞ ከዚህ በኅላ በድርጅቶቹ ስም የሚደረግ ማናቸውም መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ውሎች እና እንቅስቃሴዎች በህግ ማድረግ አይችሉም ማለት ነው ::ይሔ የህግ ጉዳይ እንጂ የፖለቲካ አይደለም :: ምክንያቱም ድርጅቶቹ በፍቃዳቸው ተርሚኔት ዞን ገቡ ወይም ኮላፕስ አደረገ ማለት ነው :: የህግ ሰዎች ይህንን በይበልጥ ሊገልጹት ይችላሉ::

3. የተጀመረውን ሰላማዊ ህዝባዊ ትግል ለማካሄድ ፓርላማ ( የኢትዮጵውን ሁኔታ ለጊዜው ትተን) በጣም የተሻለ ስፍራ ከመሆኑም በላይ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ""ግዙፍ የፖለቲካ ኢንስቲቲዩቶች ቀዳሚው ነው "" ወይም ነው ብለን ተስፋ ስለምናደርግ ::

ይቀጥላል
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

ፓርላማ ያለመግባት ጦስ

Postby ሳምቻው » Mon Oct 10, 2005 1:03 pm

ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ; "" ፓርላማ አልገባም!"" ብሎ በኩርፊያ እና በዛቻ ወደ ቤቱ የሚመለሰውን የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሀይል እጣ የሚያስቡት , ህዝባዊው ፓርቲ እንደ ድሮው ቢሮው ተመልሶ በህጋዊ ሽፋን እየተንቀሳቀሰ እንደ ለት-ተለት ተግባሩ ህዝቡን በግልጽ ከተማ ቁጭ ብሎ ለትግል ማነሳሳት የሚችል አድርገው በማሰብ ነው !!

ሆኖም የተቃዋሚው ሀይል "" ፓርላማ አልገባም "" ብሎ ኦፊሻሊ አቋሙን ያስታወቀ ጊዜ የገዢውን ፓርቲ ፖለቲካዊ ተጽእኖ ትተን , በህግ ደረጃ ብቻ ህጋዊ ሰውነቱ የሞተ እና ሀይሉ ወደ ግለሰቦች ስብስብነት ወድያውኑ ይለወጣል !!

ፓርላማ አንገባም በለን ስንወስን የምናልመውን የመንግስት ለውጥ ለጊዜው ትተን ; የሀገሪቱ የፖለቲካ ቀውስ እና ህግ ሁኔታውን እንዴት ይመለከተዋል የሚለውን በመተንተን ነው ...

ቀጥሎ ይቀርባል
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

ሳሚ

Postby Alisa » Mon Oct 10, 2005 3:35 pm

ደህና ነህ ወይ? ምነው ተበሳጨህ? እነሱን ተዋቸው የማይሉት የለም:: አንተ ቁምነገር ነው የጀመርክው እስቲ ቀጥል:: ብስጭቱ ሽበት ያስወጣብሀል እረጋ በል::
Alisa
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Thu Jan 06, 2005 7:25 pm
Location: united states

Re: ስማ እንድርያስ

Postby እንድሪያስ » Mon Oct 10, 2005 7:24 pm

ሳምቻው ወንድሜ ለእንደአንተ አይነት ሰዎች ማዘን ከአቆምኩ ቆይቻለሁ ቅቅቅቅቅቅቅ ከልቤ ነው ::
እዚህ ፎረም የገባሁ ሰሞን ሰዎች በከንቱ ሲደክሙና ራሳቸውን ሲያታልሉ ....በራሳቸው ላይ ሲጫወቱ ሳይ ያሳዝኑኝ ነበር ::
በተረፈ "በተጀመረው ርዕስ ላይ ሀሳብህን አካፍለን" ላልከው መልሴ " ከርዕሱ አልወጣሁም " ነው :: ባቀረብከው አጭር ጽሁፍ ላይ የሰጠኸው ትንታኔ ጭራሽ ስለአልገባኝ " እንደገና ግልጽ አድርገህ አቅርበው " አልኩህ ::
አንተ ግን መሰረት የያዘ እውቀትና ግንዛቤ ስለሌለህ ብሎም በራስህ ስለማትተማመን አግባብ ያለው መልስ ከመስጠት ይልቅ ስድብ መልሰህልኛል :: ስድብህንም (ከላይ እንዳልኩት) ከመጤፍ አልቆጠርኩትም ......አንተነትህን አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን በመገንዘብ....... ስቄ አልፌዋለሁ ::
ለምሳሌ :- " ~የአለም ፖለቲካ አዋቂዎች ሲወያዩ መሰረታዊ ልዩነታቸው በስትራቴጂ እንጅ በፕሮሲጀር አይደለም.::........... የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት እንኳን ልዩነታቸው የስትራቴጂና የሚሽን እንጂ የአሰራርና የዲሲፕሊን አይደለም ...........common knowledge ወይም procedure ላይ መወዛገብ ያልተለመደ ነገር ነው :: የእኛ በሶስተኛው አለም ፖለቲሽያኖች ባህል ደግሞ በተነሱት ርዕሶች ላይ መሰረታዊ ግንዛቤ() ማጣት ነው:........ "
እዚህ ጋ ምን ለማለት እንደፈለክ ግልጽ አይደለም (ለእኔ) እና እንደገና ማብራሪያ ያስፈልገዋል ስትባል "እንደንፍጣም ህጻን ተረማምጀብህ አልፌያለሁ ምናምን .......::
ሌላው :- "ቅንጂት ፓርላማ ገብቶ ኢህአዴግን በማጋላጥ ዕርቃኑን ለማስቀረት በሰላማዊ መንገድ ትግሉን ይቀጥል የሚል አቋም አለኝ:: "
አቋምክን ባልደግፈውም አከብረዋለሁ በዚህ ምንም ችግር የለብኝም የዴሞክራሲ ውበት የሚገለጸው የሰውን መብት... ሀሳብና አቋም በማስተናገድ ነውና :: ሆኖም ዝቅ ብለህ ተመሳሳይ (ያንተን ሀሳብ የሚደግፍ) ሀሳብ ያቀረበውን ግለሰብ አጥብቀህ በመቃወም ከላይ ቆርጨ ያስቀምጥኩትን ግራ የሚያጋባ ጽሁፍ ፖስት አደረክ :: ሁለተኛ ወዲ ሰበርጉማ ለግንዛቤ ቢረዳህ ብሎ የአንዳርጋቸው ጽጌን ጽሁፍ ሲያቀርብልህ " ከአሁን በፊት አይቸዋለሁ በማለትና በማጣጣል አለፍከው :: በጣም አስቀኸኛል ..ምክንያቱም ጽሁፉ እንደወጣ ነው ልጁ ፖስት ያደረገልህ .......::
አይ ሳምቻው ቅቅቅቅቅ Business correspondent!!.......አህ ይቅርታ Finance Analyst (finnance analist :? ) ነህ ለካ::
ለማንኛውም ስለቅንጂት ፓርላማ መግባትና አለመግባት የግሌ አቋም ከአንተ የተለየ ነው ::
በህዝብ ደም.... በግፍና በዝርፊያ በተቋቋመ ፓርላማ ውስጥ ዘው ብሎ የሚገባ የግል ጥቅም ያስከረውና .....ራዕይ የራቀው ብቻ ነው::
"ዕርቃኑን ማስቀረት" የሚለው ስንኝ ራሱ ከአገርና ከህዝብ በአካል ብቻ ሳይሆን በመንፈስም ማራቅህን የሚያሳይ ነው:: ወያኔ በእየለቱ የሚያወጣውን ውልና ድንጋጌ ለማያውቅ ይህን ለማለት አይከብደውም ::
ለሁሉም ይብቃኝ ግን አንድ ነገር ልንገርህ ስራ ክቡር ነው ጠርጎም ቢሆን ራስን ችሎና ወገንን ረድቶ መኖር ነውር አይደለም :: በጣም ደካማ ነህ ...ከምር :: እኔ እንኳን ምስጋና ለፈጣሬየ ጠረጋን ነክቸው አላውቅም ቢሆንም ስራ ነውና አልንቅም:: በል ሰላም እደር ነገ ደግሞ በ "ኪሊፓት" ብቅ ስትል መልስ እሰጥሀለሁ :lol:


ሞንክ wrote:ማነህ እንድርያስ ..

ሀሳብ ካለህ በተጀመረው ርእስ ላይ ሀሳብህን አካፍለን !! ከሌለህ ሌሎች የሚሉትን በስረአቱ ተከታተል ! አባክህ አትረብሽን !! እንለምንህ.

መጥረግ ብቻ ነው ትልቁ የሕወትህ ይዞታ ? ማንም ሰው የተሰማውን ኃሳብ በነጻ መግለጽ እንደሚችል ከምትኖበት ሀገር አለመማርህ ያሳዝነኛል!

በጥላቻ የተሞሉት አስተያየቶችሕ በፍጹም ገና ምንም ነገር እንዳልገባህ ያረጋግጣሉ . ይህንን ከፈለክ አትመን ! ግን ሰላም ስጠን .

ሞንክ / ከ ልኡለ ገነት ፓላስ
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1784
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

ፓርላማ ካለመግባት ጋር ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎች

Postby ሳምቻው » Mon Oct 10, 2005 9:07 pm

የኢትዮጵያ ህዝብ በመረጠው መንግስት የመተዳደር መብቱን ሳንረሳ;ተሰባሪ ሰላም የያዘችውን የወቅቷን ኢትዮጵያ ሁኔታ ስንቃኝ ደግሞ ጉዳዩ ወደ ፓርላማ ከለመጋባት ባሻገር አሳሳቢ'ና አደገኛ ሆኖ እናገኘዋለን ::

ተቃዋሚዎች ፓርላማ ባይገቡ , በሀገሪቱ ሊነሱ የሚችሉ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶች በሚቻል ሁኔታ; እንደሚከተለው ይሆናሉ ተብሎ ሊፈራ ይችላል ::

1.የተቃዋሚዎች ሀይል በህግ ፊት ተርምኔት በማድረጉ , ምሁራኑ ድርጅት የሌለው የሰዎች ቡድን ተብለው መጠራት ይጀምራሉ :: ይሁንና ከዚህ በኃላ ለመሰብሰብም ሆነ ህዝብ ለማታገል አለምቻለቸው በህግ የሚያስገርም ባይሆንም , የከፋው ነገር ግን የፖለቲካ ሰለባ መሆን መጀመራቸው ይሆናል:: ህዝቡም የመሪዎቹ ደህንነት ከምን እንደደረሰ ሚስጥር ሆኖበት ይኖራል :: (ኢሀዲግ የጎደለውን ማይኖሪቲ የፓርላማ ወንበር በዳግም ምርጫ በሌሎች መተካቱ ሳይረሳ )

መንግስት ለተባለው አካል የተቃዋሚዎችን እጣ ቀጥሎ የሚያየው ወደ ምንግስት ስልጣን ለመምጣት "" ካፕርላማ ውጭ የተሻለ ምክኑ'አዊ ቦታ አለኝ "" ብሎ እነሚያስብ ጸረ-መንግስት የከተማ ውስጥ ንቅናቄ ነው ::

ሌሎች ዝርዝር ምክንያቶች ይቀጥላሉ !
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Re: "" ዋርካ ዲቤት "" ቅንጅት የፓርላማው አካል ይሁን ወይስ ፓርላሜንታሪነቱን ይሰርዝ?

Postby ኤኬ47 » Mon Oct 10, 2005 11:38 pm

ሳምቻው wrote: ቅንጅት የፓርላማው አካል ይሁን ወይስ ፓርላሜንታሪነቱን ይሰርዝ?


በድምጽ ብልጫ ከሆነ ጣቴን አንስቻለሁ የፓርላማ አካል ይሁን:: :lol: :lol:
ኤኬ47
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Sat Dec 11, 2004 6:22 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests