"" ዋርካ ዲቤት "" ቅንጅት የፓርላማው አካል ይሁን ወይስ ፓርላሜንታሪነቱን ይሰርዝ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ፓርላማ ወይስ ኢትዮጵያ !?

Postby እንድሪያስ » Wed Oct 12, 2005 7:15 pm

ወንድሜ ሳምቻው አሁንስ በተቀመጡ ሰዎች ፊት የሚያረገርግ ባለሜሲንቆ አዝማሪ መሰልከኝ ::
ለቅሶን(ሀዘንን) በዜማ መስማት ከዘፈን የበለጠ የሚያዝናናውቸው ታዳሚዎች እንደሚበዙ ማወቅህ ራሱ ብልጥነት ነው ::
ጫን ወሬ ቅንጣት ፍሬ.....ይላል ድንቅየው ያገሬ ሰው ::
<.......ሰባራ ወንበር ተሰረቀ ብየ........> ይህን ስንኝ አስምሬበታለሁ ::

ለማንኛውም ለሌሎቻችሁ ( የሊቀ መኳስ ግጥም አቀባዮች)........:-
ዴሞክራሲ ማለት በፍትህ በእኩልነትና በነጻነት መርሆዎች ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ሂደት እንጂ የአንድን አናሳ ብሄረሰብ ጥቅም ብቻ የሚያስከብር አይደለም ::
ህገ መንግስቱ..... የፍትህ አካላቱ .... የአገሪቱ የዜናና የመገናኛ አውታሮች በሙሉ...... ህግ አውጪና ህግ አስፈጻሚው ....የመከላከያ ኃይሉ ....በኢኮኖሚው ረገድ ያለው የአሰራር ሁኔታ ሁሉም ለአንድ ብሄርሰብ የቆሙና የእሱን ጥቅም አስጠባቂዎች የሆኑበት አገር ውስጥ ያለው ዴሞክራሲ ዴሞክራሲ አይባልም ::
ለዛች አገር አንድነትና ሉአላዊነት ደማቸውን ያፈሰሱላትና አጥንታቸውን የከሰከሱላት የአገሪቱ ዜጎች ልጆቻቸው ዛሬ በገዛ አገራቸው ባይታወር ሆነው መኖር ብቻ ሳይሆን በአገር ውስጥም ሆነ ተሰደው በሚኖሩበት በጎረቤት አገር በየጊዜው እየታደኑና እየታፈኑ በመገደል ላይ ናቸው::
እናንተ የምትሉት ... እነሱ ይሙቱ.... ለእነሱ ነጻነት አያሻም ....ዋናው ከሀዲዎቹና ዘረኞቹ ስልጣን ላይ ይቆዩ.......ለዘብተኞችና ወላዋዮች ደግሞ ሲጠብቅ እያላሉ ...ፍርፋሬያቸውን ሲለቅሙ ይኑሩ ነው ::
ዞሮ ዞሮ ወያኔም ሆነ እነሱ ስውር አጀንዳቸው አንድ ነው ::
ይብቃኝ

ሳምቻው wrote:ሰሞኑን በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ተንጠልጥሎ የቀረው ደመና "" ኢትዮጵያ ወይስ ፓርላማ !?"" የሚል ይመስላል ...!!

በኛ ኃገር ፖለቲካ መሰረት "" ሀገሪቱ ፓርላማ ውስጥ የለችም :: ፓርላማው ግን ከነ-ግሳንግሱ እሷ ውስጥ ይኖራል "" ግን ግን ለረዥም አመታት የተጠማነውን ህዝባዊ ፓርላማ ለማግኘት ስንል ሀገራችንን በመያዣነት መድበን ለተኩስ እንወጣለን ወይ ???

ልብ ያለው ልብ ይበልና :ኢሀድግን እልህ እንጋባ ክላልን በቀር ዛሬ እውነተኛው የኢትዮጵያ ጠረን ያለው በ'ያንዳንዳችን ልብ ውስጥ እንጂ ፓርላማ ውስጥ እንዳልሆነ ውስጣችን ይነግረናል !

ጎጠኞቹ የኢሀዲግ ከባድ-መስመረኞች በሚከተሉት የተዛባ አሰራርም ሆነ የፖለቲካው ባህላችን አሁን ካለበት ደርጃ አንጻር ሲታይ(የጥምር መንግስትም ቢቋቋም) የኢትዮጵያ ፍልጎት እንዲህ ባጭር ጊዜ ውስጥ ፓርላማ ውሳጥ ይንጸባረቃል ብዬ አልገምትም :: እየጎለበተ በሚሄድ ዲሞክራሲ ግን አምናለሁ ::

ባጭሩ የተሰመረበትን አብይ አረፍተ-ነገር ከፓርላማ ወደ ኢትዮጵያ ትቅደም! (Ethiopia before all ) ወደሚለው እንመልሰው ዘንድ ህሊናችንን እንፈትሽው ::

ብዙዎች ዛሬ ; ኢሀዲግን ለመጣል ህዝባዊ አመጽን እንደ ፍቱን ዘዴ አድርገው የሚገፋፉት "" የኢትዮጵያን ህዝብ አብሮ የመኖር ባህል'ና ጨዋነት" በመጥቀስ እንዲሁም ሊነሳ የሚችለውን የርስ በርስ ጦርነት በማጣጣል'ና ትናንሽ መንግስቶች ሊፈጠሩ መቻላቸውን በመቃወም ነው:: ለዚህ የሚያቀርቡት ዋስትና አሁንም የህዝቡ ""ጨዋነት"" ሆኖ እናገኘዋለን :: ( ዞብልዬ ካንተ የመንደርደሪያ ሀሳብ ዋቢ በማድረግ )

ይህ ግን ለኔ ፍጹም አደገኛ የሆነ ታሪካዊ ሥህተት ይሆናል :: የኢትዮጵያን ህዝብ ጨዋነት አምናለሁ ዞብል :: ሆኖም ይህ'ና ያ ለ'የቅል ነው ::

የሀገር አንድነት'ና ሉአላዊነትን የሚያክል ግዙፍ ቅርስ ,"" በ40ቀን እድሌ "" ላይ በመተማመን ሪስክ ለማድረግ አልደፍርም :: የሚጠብቀኝ ኪሳራ የ'ንዋይ ሳይሆን የ ኃገር ነው :: ላስብብት የግድ ይለኛል !!

ዞብል

በያንዳንዳችን ደጅ ላይ የቆመው የኢትዮጵያ ማህበርዊ'ና ፖለቲካዊ ቀውስ ከቤት እስክወጣለት ድረስ አይን አይኔን አፍጥጦ እያየኝ ; እዛ አንድ አዳራሽ ውስጥ አምስት አመት እድሜ ያሌላቸው ገዳዳ ወንበሮች ተሰረቁ ብየ ውድ ሓገሬን በሰብ-አዊ ጋሻነት ተሽክሚያት ለዘመቻ አልወጣም !
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1784
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

Re: ለእንድርያስ

Postby ትምህርት » Wed Oct 12, 2005 7:25 pm

ቃኘው wrote:አስተሳሰብህን አደንቃለሁ:: ነገር ግን የህብረቱም ሆኑ የቅንጅቱ ወደ ወያኔ ህወኃት ፓርላማ ያለመግባታቸውን ነበር የምደግፈው::'

ለምን ብትለኝ የ 299 ወረዳዎች የምርጫውን ኮሮጆ ተሠርቀዋልና:: ያነው:: ዛሬ ወያኔ ያለው ቁጥር እንዲያውም ባብላጫው መያዝ የነበረባቸውና መንግሥትንም ማቓቓም የሚቺሉት እነሱ ነበሩ::


ሰላም ቃኘው!

ለጥያቄየ መልስ ስለሰጠኸኝ በጣም አመሰግናለሁ! አገራችን ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ እንዳለች ይገባናል:: ለዚህ ነገር ሁላችንም የተሰማንን ሃሳብ መግለፅ ጥሩ ነው:: ከችግሩ ውስብስብነት የተነሳ ሁላችንም የምናቀርበው የመፍትሄ ሃሳብ አስፈላጊ የሆነበት ወቅት ላይ እንገኛለኝ:: እኔ የእኔ ሃሳብ ብቻ ለዚህ ውስብስብ ችግር መፍትሄ ይሆናል ብየ አላምንም:: ሌላም ሰው እንደዚህ ቢለኝ ለመቀበል ይቸግረኛል:: ስለዚህ ሁላችንም አቅማችን የሚፈቅድልንን ያህል መወርወራችን አግባብ አለው!

ጠቅላላ ሀተታየን እዚህ ላቁም እና ወደ ጭብጡ ልመለስ:: የአገራችን ምርጫ ውጤት መጭበርበሩ አለም ያወቀው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው:: ይህ በገለልተኛ አካሎች ማረጋገጫ የቀርበበት እውነታ የሚክደው በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ብቻ ነው! ስለዚህ ይህን በሚመለከት ካንተ ጋ እስማማለሁ:: የተነጠቁትን ወንበሮች ለማስመለስ ተቃዋሚዎች እስከ መጨረሻ ማድረግ የሚገባቸውን ትግል አድርገዋል ብየ እገምታለሁ:: አሁን እናስመልሰዋለን ከሚሉት የፓርላማ መቀመጫ አልፎ አደጋ በህልውናቸው ላይ አንዣብቧል:: ስለዚህ ተቃዋሚዎች ፓርላማ ውስጥ በመግባት ለጊዜው ሰላም ሊያገኙ ይችላሉ ብየ አምናለሁ:: ይህ ማለት እዚያ ተቀምጠው የተነጠቁትን መቀመጫ ለማስመለስ ትግላቸውን ይቀጥላሉ ማለት ነው:: ተቃዋሚዎች ወደ ፓርላም ሳይገቡ ሊያደርጉ የሚችሉትን ነገሮች ሁሉ ፓርላም ከገቡ በኌላ ለማድረግ ይችላሉ ብየ እስባለሁ:: የመቀመጫው መሰረቅ ለተቃዋሚዎች ቋሚ ክስ በመሆን ያገለግላል:: ይህንን ነገር ችላ ማለት አይገባቸውም::

አንዳንድ ሰዎች ተቃዋሚዎች ፓርላማ ከገቡ ለመንግሥት/ለፓርላማው ሀጋዊነት ይሰጡታል ሲሉ ይሰማሉ:: በዛሬው የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ይህን የምንለውን እውቅና ለማግኘት አስቸጋሪ አይመስለኝም:: ለዚህ ምሳሌ የፓኪስታኑን President: Pervez Musharraf መንግስትን መጥቀስ ይቻላል:: እኚህ ጄኔራል እኤአ በ1999 በዲሞክራሲ የተመረጠውን መንግስት በመገልበጥ ሥልጣን በእጃቸው ውስጥ ያስገቡ ናቸው:: ዛሬ የሳቸውን መንግሥት እውቅና የማይሰጥ የምዕራብ መንግሥት አይገኝም:: እና ለማጠቃለል ያህል ዛሬ እውቅና ማግኘት ከምንም ነገር የቀለለ ሳይሆን ይቀራል:: ስለዚህ የተቃዋሚዎች ፓርላማ መግባት/አለመግባት ብዙ ተጽእኖ ይኖረዋል ብየ አላምንም::

በተረፈ ስለ ኦነግ ያነሳሁት በተቃዋሚዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመጠቆም ያህል ነበር:: እንጂ ኦነግን በሚመለከት ዝርዝር ውስጥ ለመግባት ፈልጌ አልነበረም::

ከሰላምት ጋር!
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

ሳም

Postby mengistu H/Mariam » Thu Oct 13, 2005 8:42 am

ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ ሳም
ፖለቲከኞች ተወናብደው ስላወናበዱን ብቻ ተወናብደን ቀረን እንጂ ከመወናበዳችን በፊት ማወናበድ እየተካሄደ እንዳለና እኛም ከመወናበዱ ወጥተን ቢቻል የሚወናበደውን ህዝብ ማዳንና የሚያወናብዱትን ሁሉ መታገል ከተቻለ ደግሞ እኛም እንዲሁ እንደነሱ የማወናበዱ ተግባር ላይ ተሰማርተን ማወናበድን በማወናበድ ካንስል አውት ማድረግ ይገባን ነበረ የሚል አመለካከት ነበር የነበረኝ::
ፓርላማ መግባትና አለመግባት ጥያቄ ውስጥ ሊገባ አይገባውም በሚል አንድንድ አርቆ አሳቢ ተቃዋሚዎች ሲያስደምጡን ስለነበረ እነኝህን ዜጎች አምላክ ሀገርን ለማዳን እንደመና ከሰማይ እንደጣለልን አድርጌ ቆጥሬ ነበረ:: አልሆነምና እናም እንደነሱ ስናቦካ ስናወጣ ስናወርድ ሰንብተን ከነሱም በበለጠ ማመን አቅቶን ውሳኔውን ጠበቅን እንደምንፈልገውም ባይሆን የምንፈልገውን አገኘን:: በአጠቃላይም የህዝብ ጥያቄ እውነተኛ ምላሽ አገኘ:: አንገባም በሚል::
እንዳው እንደፈሪና እንደ አድርባይ ከሁላ ደርሼ አስተያየት ሰጪ አልባል እንጂ ሳራምድ የነበረውም አቋሜ ይኸው ነው::
የኢትዮጵያ ህዝብ ከፓርላማ ተለይቶ 14 አመታትን አስቆጥሯል:: የተወሰኑትንም ፓርላማ ውስጥ አስገብቶ ሞክሮታል:: ምን ሲካሄድ እንደነበረ: ተቃዋሚዎችስ ቁጥራቸው ቢበዛም ምን ሲሉ ተደምጠው ነበር? የሚል ጥያቄ ብናነሳ መልሱ ምንም ነው የሚሆነው::
ክፉ ተናገርክ አልባል እንጂ ለሁሉም ተቃዋሚ የሚበጀው ፓርላማ መግባት አለመግባት ላይ እንደትላንቱ መከራከር ሳይሆን ምርጫውም ውስጥ ራሱ አለመሳተፍና ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዲሰፍን: ነጻ አሰመራጭ አካል እንዲደራጅ:ደህንነቱና የፍትህ አካሉ ነጻነቱ እንዲስተካከል:የመገናኛ ብዙሀንን በጋራ የመጠቀምን ወዘተ ጥያቄዎች ህገ መንግስቱ በሰጣቸው መብት ተጠቅመው መግለጽ ይችሉ ነበረ:: ያ አልሆነም:: ጥያቄዎቹ ሁሉ ግልጽ: በጎና ቅን ለመሆናቸው ገና 16 አመት የሆነው ለአቅመ አዳምና አቅመ ፖለቲካ ያልደረሰ ወጣት ሊረዳው የሚችለው ነው::
ለዛ ደግሞ ህልሙም ሆነ ፍላጎቱ ብሎም ዝግጅቱ ያልነበረው አምባገነን ስርአት የወሰዳቸውን የቅርብ ኢሰብአዊ እርምጃዎች ግምት ውስጥ ማስገባቱ የግድ ይሆናል::
በኔ አመለካከት ከዚህ በኌላ ስርአቱን ማጋለጥና መታገል የሚቻለው ከፓርላማው ውጭ ሆኖ ህዝብን በማስተባበር የማያቋርጥና ጠንከር ያለ ተቃውሞ በማሰማት ህገ ወጡ ፓርላማ ሊዘጋ የሚችልበትን መንገድ ማመቻቸት ነው::
ሰላማዊሰልፍ : የስራ ማቆም አድማ: ለመንግስት አለመታዘዝ ወዘተ በየደረጃው አድገው የሁሉንም ቀልብ ለመሳብ ከቻሉ ትግሉን በአጭር ጊዜ ጫፍ ያደርሱታል:: ለውጪውም ሆነ ለሀገሪቱ ህዝብ ጥሪው እንዲሰማ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ:: 14 አመት ሙሉ ብርዥ ጥርዥ ይል በነበረው ለዴሞክራሲ መብት ተጋድሎ ያለፈውን የሰው ህይወት ብንመለከተው ቀላል አይደለም:: ይህ የሆነበት ምክንያትም የኢትዮጵያ ህዝብ "ልበ ቢስ" ወኔ ቢስ በሚል በጠላቶቹ በመፈረጁ ነው::
የስከዛሬውም ትግል መሪ አልባ ለመሆኑ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርካች ነው::
ከዚህ በኌላ የህዝብን ትግል እየለኮሱ መተው የበለጠ የፈሪ በትር ምን ጉዳት ሊያመጣ እንደሚችል ልብ እንላለን::
ለሰላማዊ ሰልፍ የተጠራው ህዝብ ከቢእት ሆኖ ተቃውሞውን እንዲገልፅ ሲጠራ ፈቃስደኝነቱን ማሳየቱ ምስክር አላሻውም:: ባለስልጣን ተብዬውም ምን ያህል ቀውስ መውደቁ እንዲረዳ እንዳደረገውም እንደዚሁ::
ግና መቀጠል ሲገባው በሰላም ፈላጊነት ስም መሪዎቹ ውሀ ቸለሱበት!
የመረጣቸውን ህዝብ ወደ የስፍራው በመሄድ በማይገባው አማርኛና ርዕስ ሰብስበው አነጋገሩት:: ህዝቡ ግን ሳይጠይቁት ድምጼን ሳታስከብሩና መብቴ ሳይከበር ፓርላማ የሚባል ስፍራ አትደርሱም የሚል መመሪያ ሰጣቸው::
መቼም ፖለቲከኛ መልስ አይጠፋውም ሁሉም ሆኖ ዛሬ እዚህ ደርሰናል::
ዋነኛው ጥያቄ የድምጽ ቆጠራው በአግባቡ ስላልተከናወነ እንደገና ይጣራልን ነው:: ዛሬ ለዚህ ያልታገሉ ከ አምስት አመት በኌላ ምን ተአምር ሊፈጠር ይችላል ተብሎ ይጠበቃል::
ለዴሞክራሲ ተገዥ የሆነ መንግስት ቢሆን ኖሮ 14 አመት ሙሉ ዴሞክራሲን ሊለመን ባልተፈለገ ነበረ:: በየዩኒቨርሲቲው: በየፒያሳና መርካቶው አያሌ ዜጎች በጥይት እንዲደበደቡ ባልሆነ ነበረ::
ሁሉም ነገር የሚከናወነው በስልጣን ላይ ባለው ቡድን መልካም ፈቃድና ፍላጎት የሚከናወን ከሆነ ያን መልካም ፈቃድና ፍላጎቱን ያሟላ ዘንድ ህዝቡን ሙጥኝ ብሎ ትግሉን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ማድረሱና የህዝብን ስቃይና መከራ በአጭር መቅጨቱ የተገባ ይሆናል የሚለው የራሴው አመለካከት ነው::
የህዝብ ስቃይና መከሪ እስካሁንም መስዋዕትነት ተከፍሎበታል:: የሚያዋጣው ነገር ቢኖር ያን የተከፈለ መስዋዕትነት ልክ አላግባብ እንደተከፈለ መስዋዕትነት ከመቁጠር ይልቅ ሙታንና የተሰቃዩትን እያሰቡ የነሱን አርአያ በመከተል ለሀገር መዳን የራስን አስተዋጽኦ ማበርከቱ ከፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎቻችን የሚጠበቅ ነው እላለሁ::
ያ ካልሆነ እስካሁን የተደረገው ሁሉ ስህተት ነበረ:: ከዚህ ወዲያ ለሚደረግ ጥሪም ህዝብ ምላሽ ሊሰጥ እንደማይወድ ሊታውቅ ይገባል::በስልጣን ላይ ያለውም ስብስብ ባደረገው "ታጋይነት" ተኩራርቶ ለሚቀጥለው ወሰኛ ፍልሚያ ቼ ፈረሴ ብሎ በህዝባችን ላይ ይወጣበታል::
በስልጣን ላይ ያለውን ቡድን በአጭር ጊዜ ውስጥ አቁስለን ጉዳት እንዳደረስንበት ሁሉ ትግሉን አሁንም በማካሄድ የህዝብ ድምጽ እንዲመለስና ከዚህ በኌላ በጠመንጃ ተማምኖ የህዝብን ህይወት ሊቀጥፍ ለማይቻለው ስርአት ይሰፍን ዘንድ ሁላችንም መጣር ይኖርብናል::
በስልጣን ላይ ያለው ስብስብ በሁሉም ሰላምና ዴሞክራሲን ወዳድ የሀገር ውስጥና የውጭው ህብረተሰብ ዘንድ ተጋልጧል:: ፓርላማ ተገብቶ የማጋለጥ ዘመቻ በተቃዋሚዎች የሚካሄደው ለነማን ለማጋለጥ ነው:: ወይስ በየአምስት አመቱ የማጋለጥ ዘመቻ ቢካሄድ ጠቃሚ ነው በሚል የዋህ ፍላጎት?
ወንድሜ እንዳው ሰኞ ማክሰኞ አደረኩት መልእክቴን::
እንግዲህ ለዛሬ ይኸው ነው በቸር እንቆይ::

አክባሪህ
መንግስቱ ሀ/ማርያም
mengistu H/Mariam
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 67
Joined: Sun Nov 02, 2003 3:20 am

Re: ባይገቡ ወይም ቢገቡ ምን ሊከሰት ይችላል?

Postby ቃኘው » Thu Oct 13, 2005 10:29 am

ከዚህም ከዚያም!!!!!!
በበኩሌ ሁላች ሁም በዚህ ጉዳይ ላይ ሃሳባች ሁን ያቀረባች ሁትን ሁሉ አደንቃለሁ:: ትንቢያቺሁን ጭምር::

እውነቱ ግን አፈ-ጉባኤ የሰጠው ይመስለኛል:: ታለፈ ታሪክና አሁን ታለው ጋራ በማጣመር ብሎታል:: ጥሩ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ገምጋሚና በነዚያም ላይ ያቀረበው የማስረጃ ኃሣቦቹ ይጥማሉ::

1ኛ: የፓኪስታኑ ጄኔራልን ምሣሌ ብንወስድ:: ዛሬ ፓኪስታን በራሷ ጥረት ብቻ ሳይሆን እየተስተዳደረች ያለችው በነማን የዶላር ውርጂብኝ እያደረጉላት ያስፈለጋቸውን እያደረጉ ይገኛሉ በቴሬሪስት ስም::

በኛጋ ብንሔድ በተለያዩ ቡድኖች ማለትም:: በኦነግ/በሶማሌ የውጋዴኑ ነጻነት ግንባር የሚባለው:: ከዚያም ከሞቅዲሾ ተነስቶ በምሥራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ይንቀሳቀሳል በሚባለው የዕስላሚክ ጅኃድ ቡድን ምክንያት:: የአቶ: መለሰ ዜናዊ ህወኃትና ወያኔው አመራር ያለምንም ቺሎታው ህዝብን ዕየሰነጣጠቀ በሚያስገርምም ሁኔታ ከ70 ዓመት በኌላ የፋሺስቱ ገዥ የሩዶሩፍ ግራሲያኒኒን ዕቅድ መሥርቶ እንደፈለገው ህዝብን በአደባባይ እየገደለ እንዲኖር አድርገውንታል::

በሌላ በኩል ስንመለከት ዕርግጥ ነው ቅንጂቱ ና ህብረቱ ምርጫውን በሚገባ አሸንፈዋል:: ግን እነሱ ውስጥ ያሉት ብዙዎቹ በዘር ይደራጁ እንጂ ማለትም ህብረቱ ውስጥ ያሉትን ለመጠቆም ነው:: ከኢትዮጵያዊነት ሌላ መንፈስ እስካሁን አላደረባቸውም:: ያን አውቆ ህዝቡ መርጧቸዋል::

ቅንጅቶቹ ደግሞ እንዳሉ ፍጹም የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው:: በዚያም ምክንያት ይመስለኛል:: ስንጥር በኪሳቸው ሳይኖር እያሰቃያቸው ወያኔው የሚገኘው:: ስለኢትዮጵያ በግልጽ የሚያስብ ለአቶ መለሰ ህወኃት ልባዊ ጠላቱ ነው::

አቶ መለሰ ደግሞ በታሪክ በባህል በተፈጥሮ ስለኢትዮጵያ ኩራት እንዳይኖር የሚከላከልና እያጠፋም የሚገኝ አጋጠመኝ መሪ ነው:: ታሁን በፊት በህዝባዊም ሆነ በራሱ ስብሰባ ላይ ብቻውን እንደ ትልቅ ኤክስፕርት ሁኖ ማንም የሱ ንግግሮች ውስጥ ጣልቃ ሳይገባ ስብሰባው ከ5 ሰዓት በኌላ ተፈጸመ::

ያም ስብሰባ መለሰ ሲዘጋው የተናገራትን ንግግር እስካሁን ትዝ ይለኛል:: "ምን ታሪክ ታሪክ ትላላቺሁ የምትበሉት የሌላቺሁ የዓለም ድኃ (ሽጭራ) የሆናቺሁ ስለታሪክ ሳይሆን ስለ ድሕነታቺን ብቻ በማሰብ ሌሎቹም ደሃ መሆናቺንን እንዲያውቁልን ራሳችንን እያዋረድን መሻሻል እንድናመጣ ታሪክ ጫሪነትን እንተወው እንርሳው ብሏል::

ይህ አስተሳሰቡ የተራቀቀ ኃሣብ ነው:: መለሰ ዜናዊ ኢትዮጵያ አንድ ሐገር ሆና ሰፊ ግዛት እንዲኖራት አይሻም:: የላኩትም እንደሱ ነው እያሰቡ ያሉት:: በቀላሉ ለመናገር ብሞክር! "ኢትዮጵያ የኃይማኖት ቺግር ያለባት ይመስል ከ160 በላይ የርዳታ አቅራቢ አገሮች ከዕርዳታው ጋራ የየአገራቸውን ስብከት በመጀመር ለነሱም ካድሬ የሚሆኑ የኃይማኖቸው ሰባኪዎቺን አገራቸው ድረስ ወስደው በማሰልጠን ገንዘብና የተከለሰ በዕጃቸው በአሁኑ ወቅት የጻፉትን መጽሐፍ ቅዱስ አስታቅፎ በመመለስ አገራቺን ውስጥ ቢስተዋል ስንት ዓይነት ኃይማኖት እንዲኖር አድርገዋል:: ይህ ሁሉ ጫና ይፈጥርብናል:: አንዱ ሌላውን ገምሎት ያልፈዋል:: ባናስተውለው ነው እንጂ ትላንት 2 ኃይማኖቶች ብቻ ነበሩ በአገሪቱ 3ኛዋ የሮማዋ ካቶሊክ ብቻ ነበሩ:: ዛሬስ? ቤቱ ይቁጠረው:: ህዝቡም ቺግር ስላለበት እነኛ የሚሉትን እየሰማ ሲሰግርላቸው ይገኛል::

ከላይ የሰጠሁት ምሳሌን እንዳጠናቅቀው ያህል:: በነዚያ አገሮች ግን ቤተክርስቲያኖቻቸውን ለሱፐር ማርኬትነትና ታላላቅ የምሺት መጨፈሪያ ናይትክለቦች:: ከዚያም እየተከራዩ የስብሰባ አዳራሾች የሾው መታያዎች የሞዴሎች መሽከርከሪያዎች እንዲሁም የፉናፉንቶች መዳለቂያ መተዋወቂያ ፕሮግራማቸውን ማስታወቂያና መብታቺንን ዕወቁልን የሚሉበት ተሆነ ከመቆየቱ አንስቶ::

መጽሐፍ ቅዱስ ከብዙ ሺህ ዘመኖች ጀምሮ መጻፉና ማንም ሳይሰርዘው ማንም ሳይጨምርበትና ሳይቀንሰው የኖረን ዛሬ እሱ እየተሰረዘ (በኢትዮጵያ ስም ፋንታ ሱዳን) የሚሉና ብዙ ነገሮችንም ያካተተ ሁኔታዎች ጽፈውበታል:: ያን ማየቱና መስማቱ ለልብ ምን ያህል ጽር ዕንደሆነም ይታወቃል:: ይህን የሚሰሩ ሰዎች" እስላሙም ሆነ ክርስቲያኑ" ፍጹም ዕምነት የነበረባትን ቦታ እነሱ ስለ ሃይማኖት ሊሰብኩን ከመምጣታቸው ይሊቅ ሃይማኖቶቻቺንን ሊማሩ እንዲማሩ መምጣት የነበረባቸው እነሱ ነበሩ::

እንግዲህ መከፋፈላቺን ከዚያ እንደሚጀምር ማሰብ ይገባናል እላለሁ:: ያም ሁኖ ስለ ህወኃት አንድ የመሰለኝን እንድል ቢፈቀድልኝ!!!
ህወሀት ወይም ወያኔ! የትግራይ ተገንጣይ ቡዱኑ ህወኃት እገነጠላለሁ ይለናል:: ሃቁ ግን አይደለም ነው የኔ መልስ:: እንዴት? አዎ ህወኃት ይህቺን ዜዴ አፍልቆ ንቅናቄውን በተጨማሪ ሲቀጥል የውጪ መንግሥታት ድጋፋቸውን በ100% ነው የጨመሩለት ለርሻቢያውም እንደዚያው:: ለምን?

ወደ ኢትዮጵያ በ18ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የገቡት ሚሺነሪዎች ከሱዳን በወለጋ በኩልና በመሰዋ በኩል በዮቦኪ (ጂቡቲ) በኩል ነው የገንቡት:: እነኛ ሰዎች አንድን ድንቅ ክርስቲያን ድንቅ የሙስሊሞች አገር የሆነቺን ደሴት ለማስተማር ሳይሆን ሀይማኖትን ምክንይያት በማድረግ ገብተው ኢትዮጵያን የመንደር የጉልቻ መንግሥት ለማቓቓም የረጅምና 100 ዓመት የሚጠይቅ ሥራ ለማከናወን የነኛ አገሮች ያስለላና የሌላውን ሕዝብ የመለያያ ስትራተጂ ሊያጠኑ ነበር የመጡት ያም ተሳካላቸው::

እንግዲህ ህወሃት ያንን ጥሩ አድርጎ ያውቃል ወያኔዎቹም ጭምር ተነግሯቸዋል የገዛ አገራቸውን ወግተው እንዲያፈርሱና የደከመቺ ጭንቅ የበዛባትን አገር ከመሬት ተነስተው ያለምንም ቺሎታ ሊገዟት እንደሚቺሉ ተነግሯቸዋል::

ያነው ሚስጢሩ:: ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያሉ ዕድሜያቸውን ልክ በውጪም በግቢም ትግል ያደረጉ የት ናቸው ዛሬስ? ለምን? ምክንያቱም እነሱ በነኛ ሚሺነሪዎች አይን ዕይታና ፕሮግራም ሆነው የትም ቢሄዱ አገራቸውም ቢገቡ ተንገብግበው ተቃጥለው ያልፏታል እንጂ በምንም አይነት ኃሣባቸው እንዲፈጸም አይደረግም:: ለምን ቢባል እየጎተቱ የንሚወስዷቸው ከወፍ አዕዋፋት እስከ አልማዝና ወርቅ የመድኃኒት ቅጠላቅጠሎቺና የነጠሩ ነገሮች ሌላም በዚያ ቦታ የነሱን ኃሣብ የሚያስጠብቁ እንደ ህወኃት መሪ የመሳሰሉን ማስቀመጣቸው ህዝቡንም አመናቃቕሮ ላልተጠበቀ ሁኔታ እንዲያመቻቺላቸው አውቀው ያደረጉት ከመሆኑም በላይ ይህም የ100መቶ አመትን ዕቅዳቸውን ለማጠናቀቅ ትንሽ እንደቀራቸው ይነገራል::

ህዋኃት ብልጡ እየሰራ ያለው የብት ሥራው ያንን ይስላል ለማለት ነው:: ይህ ቡድንና የኤርትራው ሻቢያው የሰሩት ጥፋት እስካሁን ደግሞ ለጦርነት ማግዶ ከወዲያና ከወዲህ የሚገኙት ወንድማማች ህዝብ ለሌላ ጦርነት ተሰልፈዋል:: ይህንም አጣብቂኝ ይፈልጉታል የላኳቸው ምክንያቱም እንደዚያ ታልሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ ዕድገት ምን እንደሚሆን ያውቁታልና:: ህዝቡ አገሩን ይወዳታል:: እንደሌላው ለጦርነቶቹ የወጡትን ነዋይ የሚያህል እንኳን ለልማት ቢውልና ለህዝቡ ክብካቤ ቢደረግለት የመሥሪያም መሣሪያዎች ቢቀርቡለት በዕልህ ማታና ጠዋት ሰርቶ በመሠረቱ ካሉበት አስቀያሚ የሆኑ ችግሮቹ ሊላቀቅ እንደሚቺል በማወቃቸው ያህዝብና ያቺ አገር ከቺግራቸው ውስጥ እንዲኖሩ አድርጓቸዋል::

ለኤርትራም ሆነ ለናቷ ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ሰላም አልሰጥ ብለው በዚህ የሰለጠነው ዓለም ውስጥ ነን በሚባልበት ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ግን 18 ሚሊዮን ህዝxብ ለህራብ ተጋልጧል ካልደረሳቺሁልን ግን እናልቃለን ተጠያቂም አይደለንም የሚል መሪ አጋጥሞናል::

እነሱ ደግሞ ቃላቸውን ለማክበር አገሪቷንና ህዝቧንም አዋርዶ በነሱ መሐል እጅ ላይ ስላቀረበላቸው ወዲያው ሳይውሉ ሳያድሩ ይደርሱለታል:: በሌላ አስተያየት ሳስበው ደግሞ "የጥንት የፋሽስት ሥርዓት አራማጅ የነበሩ የልጅ ልጆች ዛሬ በአሜሪካ በአውሮጳና በአውስትራሊያ በካናዳም ጭምር በሳይንቲስትነት በፖለቲከኛነት በአገር መሪነት ላይ መሆናቸውንም መዘንጋት አይኖርብንም:: እንግዲህ መለሰ ዜናዊ የተናገረውም ታሪክ ታሪክ ምኒልክ ምኒልክ አትበሉ የሚልበትም ለዚያው ነው:: ከኦጋዴኑ እስከ ኦነጉም ድረስ ያሉት ምኒልክ እንዲህ ሰራ እንዲህ አደረግም እያሉ ልብ ወለቃ ውስጥ የገቡት ከህወኃት ጥቅም ስለአገኘበት ሰምተው ነቅተው ነው:: እንደዚያ ታላሉ እንደ ኢትዮጵያዊማ ኢትዮጵያ ትቅደም ብለው ቢጽፉ በአንድ ቀን ይወድቃሉ::

ለዚያም ማስረጃው! ቅንጂቱ አሸንፏል::ከ 26 ሚሊዮን የተመዘገበ መራጭ ውስጥ 23 ሚሊዮኑ ህዝብ የመረጠው ቅንጅቶቹንና ህብረቱን ነበር:: ያን ግን በስራ እንዳይመዘገብ ዜሮ እንዲገባ ያደረገው ምናልባት አንዱ የሶላቶ ፋሺስት የልጅ ልጅ ቂሙን ለመመለስ ያቺን አገር ካስጠፋ በኌላ ስላሰበ ይመስለኛል ያቺንም ፊደል አስባቺሁ ድረሱባት(3ቱ) ፊደሎቺን::

እና አፈ-ጉባኤ የሰጠኸው ሃሣብ ላይ ለማከል ያድረኩት ጥረት ብዙ አስባለኝ:: ለማንኛውም!

*ቀይ ባህር ዳር ድነበራቺን ነው*

አክባሪያቺሁ

ቃኘው
ከ(ሰሐሊን)

ጊዜ ሣገኝ ይቀጥላል ይህ የማገናዘቢያ መልክቴ!
አፈ-ጉባኤ wrote:ወደ ፓርላማ ባይገቡ ወያኔ እሚፈልጋቸውን ከመሀላቸው እየነጠለ ለእስር ይዳርጋል:: ህዝቡ ምን ያደርጋል? ባብዛኛው ምንም:: ከፕሮፌሰር አስራት እስር መማር ይቻላል:: ከዚያም ባሻገር ወዳጆቻችንን ገድለው ሬሳ የቸበቸቡልንን ደርጋውያንንም ጉያችን ውስጥ አቅፈን አስራ አምስት አመታት ኖረናል:: ከነኚም ጋር እንኖር ይሆናል:: ቅንጅት የኢህአፓን ያህል በህዝብ ልብ ውስጥ የገባ ድርጅት አይደለም:: ኢህአፓ እንኳን ሲፈረካከስ ህዝቡ አላስጣለም::

ህዝባዊ አመጽ ቢቀሰቀስ አገር ልትበተን ትችላለች? ትችላለች:: ኦነግ ሻእቢያና ኦብነግን የመሳሰሉት ነቀዞች ቅርጫ ያሰገቧታል:: ሻእቢያ በ66ቱ የመንግስት ለውጥ ወቅት ነበር በቀናት ውስጥ ሰፊ ቦታዎችን የተቆጣጠረው:: ብዙዎቹን ቦታዎች ሳናስመልስ ነው የተገነጣጠልነው::

ፓርላማ ባይገቡና በውጭ ያለ (ይስሙላ) ህግ ከለላ ይታገሉ ብለን ብንል ምን ያህል ሊፈይዱልን ይችላሉ? ያማራጭ ሀይሎች ምክር ቤት በተቃዋሚነት አመታት አስቆጥሯል ምንድን ፈይዷል እስካሁን? እማውቀው የረባ ነገር የለም:: ቅንጅትም እሚፈይደው ትልቅ ነገር ይኖረዋል ብዬ አልጠብቅም:: የህዝቡ ትኩሳት እንደሆነ ካሁኑ የበረደ ይመስለኛል:: ውጭ ያለነው ደግሞ ሰልፍ ከመውጣት የተሻለ ብዙም እርባና ያለን አይመስልም:: መስዋእትነቱ ኪሳችን እንኳን እንዲገባ አንፈቅድለትም::

ባለመግባታቸው (ከህግ ውጭ ወይም በህጉ መሰረት) ወያኔ ያዲስ አበባንና ሌሎች ከተሞችን አስተዳደር በጁ ያስገባና ብቀላውን ወይም የተለመደ ህዝብ ያስመረረ ግዞቱን ይቀጥላል:: ሌላ ብግነት!

ቢገቡስ?

ቢያንስ ለራሳቸው ይሻላቸዋል:: ፓርላማውን ማወክ ይችላሉ ከፈለጉ:: በመንጋ አጨብጫቢ መሳለቅ: በነገር ማሳረር ይችላሉ:: አማራጭ ሀሳቦችን ያካፍላሉ:: ኢህአዴጋውያኑ ብቃት የለሾችና ስግብግቦች እንጂ ጸረ ሀገሮች ስላልሆኑ የተቃዋሚዎች አስተያየት ገንቢ አስተዋጾ ይኖረዋል:: የተሻለ ቀን እስኪመጣ የያዙትን ይዘው ይከርማሉ:: እኛም ያመራር ብቃታቸውን በትንሹ እንይ:: ካመንናቸው በትልቁ እንሾማቸዋለን:: አለመግባታቸው ብቻውን የሟቾችን ደም የሰማእትነት ክብር አይሰጠውም:: ደማቸው ይበልጥ እሚረክሰው እፍረተ ቢሶቹ ወያላዎቻቸውን በምትካቸው አስመርጠው በትእቢት ድራማቸው ሲቀጥሉ ነው:: ነገ ሌላ ቀን ነው:: እግዜሩ ለወያኔ መገዝገዣ ባድመን ስላዘጋጀ እንታገስ:: በኔ እይታ መግባቱ ይሻላል::

ከወገናዊ ሰላምታ ጋር
አፈ-ጉባኤ
tank you
ቃኘው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Thu Oct 23, 2003 11:35 pm
Location: Man

ሰላም ለሁላችን !!!!

Postby Fesame » Thu Oct 13, 2005 11:16 am

ከመሳተፌ በፊት አስተያየቶችንሁኝ አነበብኩኝ ! ምንም ግን እኔ የሚያረካ መልስ አላገኘሁም !!!

ቅንጅት ወደ ፓርላማ ይግባ ወይስ አይግባ ?

ጥያቄው ይህ ነው መስለኝ ባልሳሳት? ሰለዚህ ወደ ፓርላማ የማይገቡበት ምክንያት እንዲሁም መግባት ያለባቸውን ምክንያት እየገለጸን ጥሩ የሆነ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን በተላበስ አሳባችሁን ብታስተላልፉ ጥሩ ይሆናል ብዬ አስብ ነበር ! ለማንኛውም, ማንም የመውቀስ መብትም ሆነ የመቃወም ፍላጉት የለኝም የሰዎችን መብት አከብራለሁኝ !!

እኔ በዚህ እርስ ላይ ማስተላለፍ የምፈልግው ነገር ቢኖር ብዙ የፓለቲካ እውቀት አለ የምትሉ ሰዎች ስለምትገቡ ! ለምን የበስ ለሀገር ለወገን የሚጥቅም ነገር አታበረክቱም !!! እንዴት በሉኝ ! እነመለስ እና በረከት እንደኛው ከአፈር የተስሩ ሰዎች ናቸው:: ሆኖም አንዳድ ደካማ በሆን ስዎች አስተሳሰብ እየበለጡን ይህው እንደፈለጉ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ይጨፍራሉ !!

ብልጠት ስል :- የፓለቲካው አካሂድ አሳምረን ሰላልተረዳነው ነው :: ለምሳሌ ወደ ፓርላሜት ይግቡ ወይስ አይግቡ ለሚለው ጥያቄ ! ብዙን በውጭ ሀገር የምንገኝ ኢትዮጵያዊያኖች አይግቡ እንላለን ጥሩ ግን ከዛስ ? .....................ብዙን ሲባል የሰማሁት ነገር አለ ሰላማዊ ትግል ! እንዴት አይነት እረ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል::

እንዲስመርልኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር እነመለስ እና በረከት ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ተፈላጊነት የለውም, አንድ ቀንም እንዲኖሩ አይሹም ግን የህዝቡን ፈላጎት ከአረመኔው መለስ እንዴት ማላቀቅ ይቻላል ? ብዙ ምንገድ አለ..... እዚህ ላይ ማውራት እንቺላለን ለምን ብዙ ሀሳቦች ሊፈልቁ ይችላሉ እና .............

በተረፈ የቲትዮጵያ ህዝብ እነመለስን እና በረከትን ሲያባርር ሌላ ስይጣን እንዲመጣ ማየትን አልሻም !!! ወያኔ ወያኔ እያለ የጻፈ ሁሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስባል ማለት እንዳለሆነ ህዝብ እንዲገነዘበው እወዳለሁኝ::


ኢትዮጵያን ከገዳዮች እና ካስገዳዮች ይሰውራት ! ለመወዳት ሀገሬ ንጹህ አየር ከንጹህ ፍቅር ጋራ እመኝላታለሁኝ !!

ይግቡ አይግቡ ወደሚለው የእኔ አመለካከት ወደ በኍላ እመለስበታለሁኝ ::


ቸር ሁኑ
Fesame
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Fri Sep 03, 2004 11:15 pm
Location: united states

ክቡራትና ክቡራን

Postby ሳምቻው » Thu Oct 13, 2005 1:32 pm

ዞብል

ሰኞ ኣካባቢ የሀገሪቱን አስከፊ የመከፋፋል ምልክቶች ከስር ለብቻ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ :: ተከታተለኝ'ማ !

ትምህርት

የተቃዋሚው ሀይል ወደ ፓርላማው ዘልቆ በመግባት < የሕዝብ ድምጽ ማጭበርበር > በሚለው ፖፑላር ክሱ ሊገፋበት ይችላል ያለከውን ሁለቴ አስምሬበታለሁ ::ያውም በተጣናከረ ሁኔታ ክሱ ፍትሀዊ መልስ እስኪገኝ አልመለስም ብሎ ሊገፋበት ይችላል ::

ይህም በቀጣዩን የ 5አመት ምርጫ ላይ ከፍተኛ አለም አቀፍ እና ሀግረዊ ተጸኖ አሳድሮ ያልፍና ኢሀዲግን ለመጣል ለሚደረጋው የፖለቲካ ቻሌንጅ የማይረሳ መሰረት ይጥላል :: ( ማለት በተውሰነ ድረጃ : ውናው አላማው ፍትህ ማገኘት ሆኖ እግረ-መንግዱን ቀጣዩ ምርጫ ለመንግስት ፍራስትሬሽን መባባስ ተጨማሪ ተጸእኖ እንዲያሳድር ይረዳል )

ልጁ ነኝ

እርሶ ያሉት የትግል ስልቶችን ጨምሮ ሌሎች በርካቶች ይኖራሉ:: ሲስተም (ፓርላማ) ውስጥ ሲገባ ደግሞ ሁኔታዎች በራሳቸ የሚያስተምሩት የትግል ስልት እንዲሁ ወደር የሌለው ይሆናል ::

እንድርያስ

እምልልኃለሁ ጮርቃ ፖለቲከኛ ለመሆንህ ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለኝም ::

አንተ የጠቀስከው "" ጁዲሽሪ , ህግ መሰውሰኛ ;ሕግ አስፈጻሚ - የጸጥታ'ና የመከላከያ ሀይሎች በሙሉ አንተ እንዳልከው በቅርጻቸው እንጂ በይዘታቸው ሙሉ በሙሉ የገዢውን ፓርቲ ፍላጎት የሚያራምዱ ናቸው :: ባጭሩ አንተ ለማለት የፈለከውን ባንድ መስመር ላጠቃልልህ'ና ኢሀዲግ ዲክታተር እና ጸረ-ኢትዮጵያ አቋም ያለው መንግስት ነው :: ስለዚህ ፓርላማ መግባት አያስፈልግም :: ቅቅቅቅቅ... ቅ ! ነው ልጅ እንድርያስ ነው :: ምንም ጥርጥር የለውም:: ይህንን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ምና'ልባትም አልፎ አልፎ ከ 18 አመት በታች ያለውም አሳምሮ ያውቀዋል :: አሁን አንገብጋቢው ነገር ያንን አውቆ መናገሩ ሳይሆን ይህ ዲክታተር ጸረ-ህዝብ መንግስት ሲወድቅ ከራሱ በላይ ይዞ እንዳይሂድ መስጋታችን ነው :: ያልካቸውን ነገሮች በግራ አይንህ እያየህ ፈዘህ ቀርተሀል :: በቀኝ አይንህ ማየት ከቻልክ ደግሞ ሀገርህ ገደል አፋፍ ላይ ተሰባሪ በሆነ ስስ አለት ላይ ተቀምጣ ትገኛለች ::

መጀመርያ የቱን ልታድን ትሄዳለህ አያ እንድርያስ ? እስቲ በደንብ ማየት እንድትችል የሪንግንሱን ብዛት ከሳጥን ወደ ጣርሙስ ቀነስ አድርገው :: አጠገቤ የተቀረመጠው ጎደኘዬ << ብዥ እንዳይልብህ ይረደሀል >> ይለሀል :: በመጨረሻም ፈጣሪ አቅል ይስጥህ :: አሚን !!


ወንድሜ ጋሽ መንግስቱ

እንደምን ከርመሀል :: በዚህ ርእስ የተለያየ አመለካከት አለን ማለት ነው :: ጠቅለል አድርጌ ባንድ ርእስ እመጣለሀለሁ :: ሆኖም መጨረሻ ላይ ቮት ከማድረጋችን በፊት ያንተን ድምጽ ፍለጋ ፕራይቬት ሩምህ ድረስ ሳላንኳኳ አልቀረም :: በኔ ሞት እንዳታሳፍረኝ በደጅህ......

ሳም
Last edited by ሳምቻው on Fri Oct 14, 2005 8:22 pm, edited 12 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

የተለመደው የመለስ < የማርጅናላይዜሽን> ጫወታ

Postby ሳምቻው » Fri Oct 14, 2005 10:37 am


የሀገሪቱ መሰረታዊ የፖለቲካ ጥያቄ
-ፓርላማ መግባት እና አለምግባቱ ላይ ከሮ መቆየቱ ምን አይነት የፖለቲካ መልክ ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ዳሰስ ላድርግ :-
ፓርላማ የፖለቲካን ልዩነት ለመፍታት የምንገልገልበት ኢንስቲቲዩት ከመሆኑ ይልቅ ፖለቲካው"" ፓርልማውን እይተወያየ ይገኛል ::

በፕሮሴጀር ጉዳይ ተቃቃሮ መፋጨት ከዚያ ብርቱ ተቃውሚን ከጫወታው እንደ ውሀ እያጫወቱ እዳር ማድረስ'ና ማግለል :: የ ""ፖለቲካል ማርጅናላያዜሽን"" ጫወታ ለመለስ ቀላል የገበጣ ጫወታ ምናልባትም ጥርሱን የነቀለበት ልማድ ማለቱ ይቀላል :: ያ'ባት የ'ናቱ ውቃቢ እንደዚያ አይቀናውም ባጭሩ ::

ጫካ እያሉ ከተራ ኩከርነት'ና ውሀ ቀጅነት ወደ ፖለቲካ መምህርነት ቀስ እያለ የተሻጋገረው መለስ ቀደምት ታሪኩ ምን ይመስላል ? ከተጣባባቂ የሴንትራል ኮሚቴ አባልነት ወደ ሙሉ አባልነት ብሎም የ ማሌሊት ሊቀመንበር እና የህወሀት ሊቀመንበር (ተራ በተራ )ለመሆን የበቃው መለስ እንዴት ነው ?? የግል-ምህደሩን ስትፈትሹ መልሱ < ተቃዋሚዎቹን እያሳሳቀ ዳግም በማያንሰራሩበት ሁኔታ ድባቅ መምታት በመቻሉ ነው>>

መጀመርያ ጫካ እያሉ :-

የአረጋዊ-ግደይ ዘርአ-ጽዮንን ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር ቡድን ( ኮሚኒዝም ወይስ ካፒታሊዝም ) በሚል የማሌሌት ፍትጊያ ውስጥ አዘናግቶ በመጨመር በ'ስበኃት ነጋ እና ቀደም ተብሎ በተቀረጹ ካድሬዎቹ እየታገዘ ካስወገዳቸው በኁላ በኤርትራ ጉዳይ ጽኑ አቋም ይዞ የቆየውን ሀገር ወዳዱን ተክሉ ሀዋዝን እስከዛሬም ሚስጥር ሆኖ በቆየው ሁኔታ ገደሉት :: ጀግናው ተኩሉ ሀዋዝ የአረጋዊ በርሄን እና የ ግደይ ዘርአ-ጽዮንን ከአመራሩ መወገድ ካየ በኅዋላ ወድያው አንገቱን አቀራሮ'ና ተክዞ እንደንበር ይሰማል :: ተክሉ ሞት ሲመጣ እያየ ነበር ...

በቅርቡ ከኢትዮ-ኢርትራ ጦርነት በኅላ ደግሞ :-

የነ ስዪ- ተወልደ- ገብሩን ቡድን ( የሀገሪቱ ቀዳሚ ችግር ---ሀገር መሽጥ ነው------: በሚል እና ----የለም ይሀገሪቱ ቀዳሚ ችግር ኮራፕሽን ነው ------- በሚሉ ቡድኖች ) ለሁለት ተከፍሎ ድርጅቱ በተተራመሰበት ወቅት መለስ እነ ሰየ አብረሀን ካጫወታው ያስወገደበት የ "ቦን'አፓርቲዝም" የማዘናጊያ ታክቲክ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው :: አቶ መለስ ባለ 700 ገጽ የቦን አፓርቲዝም ቲዎሪውን ለ'ነስዬ በ 3ወር ጊዜ ውስጥ አንብበው እንዲመለሱ በማዘዝ :: ናሽናሊስቶቹ ባዶ ቲዎሪ ተሽከመው ወደቤታቸው እንደሄዱ አፍቃሪ-ኤርትራው መለስ የብረት መዶሻውን በሰዎቹ ላህ ወድያው አነሳ :: በተገኘው ትንፋሽም ቡርቦራውን አጠናቆ ለመጨረስ የቻለ ሰው ነው ::

እነሆ ዛሬ ደግሞ ህብረት እና ቅንጅት በተለመደው የመለስ የማርጂናላይዜሽን በትር ተዘናግተው ሊመቱ ቀለበቱ ዙርያ እይተሽከረከሩለት ነው ( ፕርላማ እንግባ ወይስ አንግባ ) የመለስ ጥሩ አጋጣሚ !!

THE SHOW IS GOING O...N
Last edited by ሳምቻው on Fri Oct 14, 2005 1:01 pm, edited 13 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

ፓርላማ ከዚያ ፖለቲካ :: ወይስ ፖለቲካ ከዚያ ፓርላማ ?

Postby ሳምቻው » Fri Oct 14, 2005 10:40 am

የመለሳውያን ሰለባዎች በሚያስገርም ሁኔታ ተመሳሳይነት አላቸው :: በመዘናጋት እና ታክቲክ ባለመቀየር የተመቱ ናቸው ሁሉም :: ተመሳሳይነታቸው እንዲሁ --ትግሉን ሳይጀምሩ በውይይት ቀደም ተከተል / ፕሮሴጄር/ ላይ በመወዛገብ ነገር ተፈልገው እዛው ካሉቡት ሳይነቀሳቀሱ ከስመው እንዲቀሩ መደረጋቸው ነው ::

በዚህ ውስጥ የመለስ ተደጋጋሚ የሚባሉት ዘዴዎች :- የሚሰነዝረውን ዱላ ህግዊ የሚያደርግለት ህግ አስቀደሞ ማውጣት :: ከዚያ ታማኝ ካድሬዎች ማሰማራት'ና ደጋፊ ማብዛት :: የሴንትራል ኮሚቴው አባላትን በግል; በስብሰባ : በስልክ እንዲሁም በየስብስባው እረፍት ላይ ሳይቀር ከሎቢ ሎቢ እይተሯሯጠ በነገር መጠዝጠዝ ና መጠምዘዝ ናቸው ::

ከዚያ አስተማማኝ ሓይል በዙሪያው መኖሩን ካረጋገጠ በኅላ'ና ግራዎንዱ ስላም መሆኑን ካየ በኅላ በመረጠው ወቅት ስብሰባ ጠርቶ በህጉ መሰረት እና በድምጽ ብልጫ ተቀናቃኞቹን እስከመጨረሻው ከጫወታው ማግለል ነው ::

ለመሆኑ ---------------------

ከምርጫው ጋር ተከትሎ የመጣውን ብሄራዊ ቀውስ ለመፍታት ተቃዋሚዎች ጣታቸውን ገና እግራቸውን ወዳላስገቡበት ፓርላማ ላይ ቀስረው የቀሩት ለምንድነው ?? ::

እነዚህ ሰዎች ለህግ መወሰኛው ምክር ቤት ተመርጠው ማንዴቱን ያገኙት በራሱ በህዝቡ በቀታ ተሰይመው ነው :: ወንበሮቹን ኢሀዲግ እንዳልሰጣቸው ይታወቃል :: ከህዝብ የተገኙትን ኮንፈርምድ ሲትስ ( በኢሀዲግ ሳቦተጅ የተቀነሰውን ትተን ) ይዘው መግፋት እንዳለባቸው ይሰማናል :: በነዚህ በኢሀዲግ በጎ ፍቃድ ባልተገኙ ወንበሮች እጣ ላይ ከምንግስት ጋር መደራደሩ አይወደድም ::ወንበሮቹ ቢያንስ ከሕብ የተገኙ ናቸው :: ይህ ግልጽ ነው ::

እነዚህን ወንበሮች እንደያዙ'ና ለድርድር ሳያቀርቧቸ ነው የጅመሩትን እልህ አስጨራሽ ትግል መቀጠል ያለባቸው :: አሁንም አልረፈደም :: ጥይቱን ወዲያ ጥለን ጠበ'ንጃውን ብቻ ተሽከመን እንደ በቂ ነገር መንቀሳቀስ አያዋጣም !!

ተቃዋሚው ሀይል እና ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ ደጋፊ ዛሬ ፓርላማ መግባቱን ያስተዋለው ትግሉ እንደቆመ አድርጎ ነው :: ስህተት ነው ይሄ !!

ህጋዊ ሰውነታቸው ሳይረግፍ - የፓርላማ ሀይል እና የመንግስት ህጋዊ ተቅናቃኞች- ሆነው ሳለ ነው ክሳቸውን እና ጩህታቸው በማካረር ጣሪያ ማድረስ ያለባቸው :: ድርጅት የሌለው ቡድን በየቤቱ ቁጭ ብሎ መንግስትን ቻሌንጅ ላድርግ ቢል ጉዳዩ የህግ እና የፖሊስ ነው :: ወደዚህ ደረጃ ዝቅ ሲሉ ማየት የለብንም :: ፓርልማ ገባችሁ : ብሎ ህዝቡም ፊት ሊነሳቸው አይገባም ::

ሌሎች ደግሞ ፓርላማ መግባቱን -ለአቶ መለስስ ዜናዊ ህገ-ወጥ ፓርላማ እውቅና እንደመስጠት ነው - የሚሉ አሉ:: "እውቅና መስጠት " የሚባለውለው አሰራር ብዙ ጊዜ ገለልተኛ ወገን ሲኖር ይመሰለኛል :: ተቃውሚው ሀይል የዚህ ፕርላማ አካል እንጂ ገለልተኛ ኣይደለም ::የሆነው ሆኖ በድምጽ ማጭምበርበር የተጀመርውን ክስ ይዞ ጉዳዩን ሳይለቅ ፓርላማ ከገባ ለመንግስትን ማጆሪቲ ወንበሮች እውቅና እንዳልሰጠ በውስጥ ታዋቂነት እንረዳዋለን ::

ልብ እናድርግ እነዚያ ተንጕለው ተንጓለው የደርሱን ወንበሮች የህዝብ ሀብቶች እንጂ ኢሀዲግ በማናቸውም መልኩ እንዲጠቀምባቸው እድል የሚሰጣቸው አይደሉም :: ኢሀዲግ በወንበሮቹ ላይ ለመደራደርም ይሁን ,በሌላ ሊተካበት በነዚያ ወንበሮች እድል መሰጠ ኣያስፈልግም :: ብልጥ ልጅ የሰጡትን ይዞ ያለቅሳል ይባልል ::

መጠቀምያ ወንበሮች ለአቶ መለስ ጥለንላቸው የወጣን ጊዘ ወይ ፖለቲካ ማለት "ኩርፊያ ነው ብለን አምነናል " ማለት ነው :: ከውጭ ሆኘ ባኮርፍ ይሻለኛል ከሆነ አካሄዳችን ፓርላማው የህዝብ ነው ብሎ ዩንቨርሳሊ መታመኑ ቀርቷል ማለት ነው ::

የኢሀዲግ የግል መኖሪያ ቤት አይደለም ፓርላማው:: በይዘቱ እንደዚያ መሆኑን ብናውቅም ባደባባይ አምነን መቀበል ግን የለበንም ::

ይተቃዋሚው ሀይል ዛሬ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል :: ባንድ በኩል የመረጠውን ህዝብ ፍላጎት ለማራመድ ይገደዳል :: ቤሌላ በኩል የሀገሪቱን ሶሺዮ-ፖለቲካል -ኢኮኖሚ ሁኔታዎችን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ አመራር መሥጠት ይፈልጋል :: ባንድ መልኩም የኢሀዲግን ያልተገራ የፖለቲክ እርግጫ ይሽከማል ...

ይህንን ሽጉጥ ሳይታጠቅ ደረቱን ለጥይት የሰጠ የቁርጥ ቀን የህዝብ ሀይል ከጎኑ ሆነን በሀሳብ ልርረዳው እና አመራሩን ልንቀበል ይገባል :: ግራ ልናጋባው እና ልናዋክበው አይበገባም ::

በነገራችን ላይ "" ህዝቡ ፓርላማ አትግቡ "" ብሏል የሚለውን ኃሳብ አፋችንን ሞልተን ባደባባይ ባንናገረው ጥሩ ነው :: ህዝብ ስንል የምናወራው ስለ 70 ሚሊዮን ህዝብ ከሆነ , አቋሙን ለመለየት ገለልተኛ 'ና ትክክለኛ በሆነ መረጃ የተሰበሰበ /objective and independent data/ የለንም ::

ሳም
Last edited by ሳምቻው on Fri Oct 14, 2005 8:41 pm, edited 2 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

የወቅቱ የኢትዮጵያ እንቆቅልሽ

Postby ሳምቻው » Fri Oct 14, 2005 2:04 pm

በጥንት ጊዜ አንድ እራሱን'ና ቤተሰቡን ለምለም በሆነ መሬት ላይ እያረስ የሚያስተዳድር ገበሬ ነበር :: ይህ ገበሬ በጣም የሚወዳት ለማዳ እርግብ በግቢው ውስጥ ነበረችው ::እርግቧን እሱና ቤተሰቦቹ ልክ እንደ እስትንፋሳቸው ይሳሱላት ነበር ::
በዚያ ግቢ ውስጥ ከገበሬው እጅ ያገኙትን ሁሉ መብላት የለመዱ ተናዳፊ እባቦች ግቢውን ተቆጣጥረውት ነበር :: መጀመርያ አካባቢ ገበሬው ያሰበው ግቢውን እና እርግቧን ከወራሪ አውሬ ይጠብቁልኛል ብሎ በማሰብ ነበር ለእባቦቹ ፍቃድ የሰጠው ::

እባቦቹ የገበሬውን ጎተራ ከመገልበጥ ውጭ የሚፈይዱለት አንዳችም ጠቃሜታ አልነበረም ::በአካባቢው አውሬም ሆን ብለው ተጠብቆ የኖረውን ግቢ ያስጠቁት ጀመር ::

ይህንን ገበሬው እና ልጆቹ ቶሎ የተርዱም ቢሆን እባቦቹን የሚቋቋሙበት ሀይል ስላልነበራቸው አቅም እስኪያገኙ ከጊቢው ሳያስወጧቸው በትእግስት ቆዩ ::

የገበሬው ቤት ጎተራ ተመዝብሮ እንዳለቀ ቤተሰቡ እባቦቹን የሚያበላው ጥሪት እያጣ መጣ:: ከዚያ እባቦቹን ከግቢው ለማስወጣት ይህ ቤተሰብ ባንድ ልቡ ወሰነ :: ይህንን ይተረዱት እባቦች ከሚቦጠቡጡት መልካም ግቢ ላለመውጣት የሞት-ሽረት ዘዴ ፈለጉ ::

ማምሻውን ገበሬው እባቦቹን ሰብስቦ ከመላው በተሰቡ ጋር በመሆን እባቦቹን የሚሽከምበት አቅም ከአሁን በኅላ እንዴለው በጨዋ ደንብ ይነግራቸውና ወደ ሚሄዱበት እንዲሄዱ ቁርጥ ኣድርጎ በምስክሮች ፊት ይነግራቸዋል ::

እባቦቹ ትቢተኛና ቂመኞች ነበሩና ገበሬውና ቤተሰቡ ጥዋት ማልደው ሳይነሱ እንደ እስትንፋሳቸው የሚወዷትን እርግብ ከበዋት ያድራሉ ::

ንጋት ላይ ይህንን ያስተዋለው ገብሬው እና ቤተሰቦቹ እስትንፋሳቸው አደጋ ላይ መውደቁን በሀዘን ያያሉ:: እልህም በያሌው ይይዛቸዋል ::

የገበሬዎቹ ልጆች እይናቸውን እያጉረጠረጡ በቁጣ ድምጽ ፎከሩ ::ትርሳቸው በቁጣ ተንቀጫቀጨ:: በያዙትም ቆንጨራ እባቦቹን ሊጨፈጭፉ ባንድ ላይ ተንቀሳቀሱ :: ምራቁን ዋጥ ያደረገው ገበሬ ግን የእባቦቹን ባህሪ አሳምሮ ያውቅ ነበር'ና ልጆቹን ከዚህ እርምጃ አከላከለ :: ህልውናቸው የሆነችውን እርግብ ማዳን ግዴታ እንዳለባቸው ግን ያምኑ ሁሉም ነበር ::

አስተዋለ ገበሬው በትእግስት ሊመረምር ነገሩን ::
ከቅርብ ሆኖ ከልጆቹ ጋር ነገሩን በአንክሮ ያስተውል ገባ ......

መርዘኛዉዎቹ እባቦች በባህሪ የተለያዩ ሆነው አገኛቸው :: ሁሉም ምግብ እና ሀያልነት ይፈልጋሉ :: ይህንን በዚያ ግቢ ዳግም ካላገኙ ኣንዱ ወገን የእርግቧን ክንፎች ሊገነጣጥል:: ሌላው አካሏን እየመጠጠ ሊኖር ቀሪው ደግሞ ነድፎ ሊገላት ሆነ ....

ገበሬው እና መለው ልጆቹ እባቦቹን ጨፍጭፈው ለመፍጀት የሚወስድባቸው ጊዜ 30 ሰከንድ ብቻ ሲሆን እባቦቹ ደግሞ እይተጨፈጨፉም ቢሆን እርግቧን በገዳይ መርዛቸው ሊዘነጥሏት የሚወስድባቸው ጊዜ 15 ሰከንድ ብቻ መሆኑን አጤነ ::


እንቆቅልሽ መሆኑን አዩ :-

እባቦቹን በግቢው ለማኖር በቂ ሀብት ጠፋ :: የገበሬ ውም እርሻ እነሱ ባሉበት አላድግ አለ ::

እርግቧን ማጣት ማለት ደግሞ እስትንፋሳቸውን ማጣት ሆነባቸው ::

ገበሬው እና ልጆቹ ከዚህ ፈተና ለመውጣት ምን ማድረግ አለባቸው ?
Last edited by ሳምቻው on Fri Oct 14, 2005 8:34 pm, edited 3 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby ዞብልየ » Fri Oct 14, 2005 2:29 pm

ሳምቻው: አሁንም ለጥያቂዎቸ መልስህን እየጥእብቅሁ ነው
ዞብልየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Thu Feb 24, 2005 7:22 pm

Re: ፓርላማ ከዚያ ፖለቲካ :: ወይስ ፖለቲካ ከዚያ ፓርላማ ?

Postby ትምህርት » Fri Oct 14, 2005 7:23 pm

ሳምቻው wrote:
በነገራችን ላይ "" ህዝቡ ፓርላማ አትግቡ "" ብሏል የሚለውን ሀሳብ አፋችንን ሞልተን ባ'ደባባይ ባንናገረው ጥሩ ነው :: ህዝብ ስንል የምናወራው ስለ 70 ሚሊዮን ህዝብ ከሆነ , አቋሙን ለመለየት ገለልተኛ 'ና ትክክለኛ በሆነ መረጃ ይተሰበሰበ /objective and independent data/ የለንም ::


ሰላም ሳም!

ለትንታኔህ ምስጋናዬ ይድረስህ! እዚህ ላይ ያልከውን ነገር ባሰምርበት እወዳለሁ! ባሁኑ ወቅት ሁሉም ወገን በየትኛውም አቅጣጫ ህዝቡ ይደግፈኛል ብሎ ሊያወራ ይችላል:: አንዱም ወገን ትክክል ለመሆኑ/ላለመሆኑ ማረጋገጫ የለም!! ከዚህም በላይ አንተ እንዳልከው 77 ሚሊዮን (ትናንት የወጣው የUNDP ሪፖርት የኢትዮጵያን ህዝብ ቁጥር 77.4 ሚሊዮን ህዝብ እንደሆነ አሳውቋል) http://www.unfpa.org/swp/2005/english/ch1/index.htm ህዝብ ይህን ወይም ያንን ፖለቲካ ፓርቲ ይደግፋል ብለን ብንናገር ሊያምነን የሚችል ሰው ማግኘት አስቸጋሪ ነው!!

ለዚህ ውይይታችን ይጥቀም አይጥቀም አላውቅም እንጂ የአውሮፓ ህዝብን የፖለቲካ አመለካከት የሚያሳይ በያዘነው ኦክበር ይፋ የወጣ የጥናት ውጤት ይኸው!

Image
ምንጭ The European Social Survey
ከሰንጠረዡ መረዳት እንደምንችለው ከህዝቡ ወደ 60% የሚጠጋው አውሮጳዊ ፖለቲካ ያንገሸግሸዋል:: የኛን እንግዲህ በዚህ ልንገምተው እንችል ይሆን?

ማጠናከሪያዬን ጨርሻለሁ!
አክባሪህ!
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

Re: ክቡራትና ክቡራን

Postby እንድሪያስ » Fri Oct 14, 2005 10:51 pm

ክቡር ሳምቻው እንደምን አለህ ?
እንዳው ሲያቀብጠኝ....ቅቅቅቅቅ አንሸራቶኝ ክቡራትና ክቡራንን በጋበዝክበት መድረክ ገብቼ ቤተክርስቲያን እንደገባች ውሻ አዋከብከኝ እኮ !!
በነገራችን ላይ ትናንትና ዛሬ ፖስት ያደረካቸውን ጽሁፎች አንደኛውን 12 ጊዜ ሁለተኛውን ደግሞ 13 ጊዜ edit አድርገሀል ::
በዋርካ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ....... እርግጠኛ ነኝ ይሄ ክብረወሰን እንደተጠበቀ ይኖራል :: ምናልባት አንተው ራስህ ከአልበጠስከው በስተቀር::
የሚገርመው 12 እና 13 ጊዜ ድክመህም .....ለውጥ አለመኖሩ ነው ::
ሌላው አንተ ተነክረህበት በምትውለው ቢራም በራስህ መብት ልትዘፍቀኝ ትፈልጋለህ ::
አለቃ ሳምቻው ..... የተሳሳተ ግምትና መላምት ነው :: "ቢራና ትንባሆ እርም የሆነበት ባህል ነው ያሳደገኝ ::
በተረፈ ከታች ኮት አድርጌ ስለአቀረብኩት ጭዋታህ .....ሌላም የምለው ነበረኝ ......በአግባቡም ለመመለስ ብቃቱ አለኝ ግን ይቅር እስኪ ::ሳምቻው wrote:.......................


እንድርያስ

እምልልኃለሁ ጮርቃ ፖለቲከኛ ለመሆንህ ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለኝም ::

አንተ የጠቀስከው "" ጁዲሽሪ , ህግ መሰውሰኛ ;ሕግ አስፈጻሚ - የጸጥታ'ና የመከላከያ ሀይሎች በሙሉ አንተ እንዳልከው በቅርጻቸው እንጂ በይዘታቸው ሙሉ በሙሉ የገዢውን ፓርቲ ፍላጎት የሚያራምዱ ናቸው :: ባጭሩ አንተ ለማለት የፈለከውን ባንድ መስመር ላጠቃልልህ'ና ኢሀዲግ ዲክታተር እና ጸረ-ኢትዮጵያ አቋም ያለው መንግስት ነው :: ስለዚህ ፓርላማ መግባት አያስፈልግም :: ቅቅቅቅቅ... ቅ ! ነው ልጅ እንድርያስ ነው :: ምንም ጥርጥር የለውም:: ይህንን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ምና'ልባትም አልፎ አልፎ ከ 18 አመት በታች ያለውም አሳምሮ ያውቀዋል :: አሁን አንገብጋቢው ነገር ያንን አውቆ መናገሩ ሳይሆን ይህ ዲክታተር ጸረ-ህዝብ መንግስት ሲወድቅ ከራሱ በላይ ይዞ እንዳይሂድ መስጋታችን ነው :: ያልካቸውን ነገሮች በግራ አይንህ እያየህ ፈዘህ ቀርተሀል :: በቀኝ አይንህ ማየት ከቻልክ ደግሞ ሀገርህ ገደል አፋፍ ላይ ተሰባሪ በሆነ ስስ አለት ላይ ተቀምጣ ትገኛለች ::

መጀመርያ የቱን ልታድን ትሄዳለህ አያ እንድርያስ ? እስቲ በደንብ ማየት እንድትችል የሪንግንሱን ብዛት ከሳጥን ወደ ጣርሙስ ቀነስ አድርገው :: አጠገቤ የተቀረመጠው ጎደኘዬ << ብዥ እንዳይልብህ ይረደሀል >> ይለሀል :: በመጨረሻም ፈጣሪ አቅል ይስጥህ :: አሚን !! ...................ሳም[/b]
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1784
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

ለ ዞብል እና ለ መንግስቱ

Postby ሳምቻው » Mon Oct 17, 2005 1:11 pm

ውድ መንግስቱ ;ትምህርት እና ዞብል
ውድ የዋርካ ዲቤት እድምተኞች

ውስብስቡን የአቶ መለስ ዜናዊ መንግስት; የኢትዮጵያ አንድነት አደጋ ላይ በማይወድቅበት ሁኔታ ከስልጣን ሊወገድ የሚችለባቸውን ጥቂት አማራጮች በሌላ ጊዜ ይዤ ብቅ እላለሁ ::

ለዛሬ:-.....

ለተቃዋሚው ሀይል በዚህ ባዲሱ ፓርላማ አለመጠቃለል ማለት ( የፖለቲካውን ተጽ'እኖ ወደ ጎን ትተን) ከህግ አንጻር ብቻ ሊመጣ የሚችለውን ውጤት ቀጥለን እንይ :-

1. ተቃዋሚው ሀይል ፓርላማ አልገባም ካለ : ቀጥሎ የሚመጣው አዲስ ነገር የድርጅቶቹ ህልውና ማብቃት ( ኮላፕስ ) ማድረግ ይሆናል :: ምክንያቱም ሰዎቹ --/ ""ወደ ፖለቲካ ስልጣን የሚያመራውን ፓርላማዊ መንገድ በመተው አቋራጭ( ሾርት ከት) ፍልጋ ላይ እንዳሉ ጸረ-መንግስት ቡድኖች ስለሚፈረጁ "" ነው / (በቀላሉ) ::

በማናቸውም አሰራር ማናቸውም መንግስት ይህንን "" ሾርት ከት "" ለማናቸውም ማይኖሪቲ ፓርቲ በታሪክ አይቀበልም :. ኢሀዲግም "ህጋዊ" ስልጣን ለማስረከብ ሁዋላ በር አይጠብቃቸውም :: የመለስን የ ጓሯ በር ሲዞሩት እንዲያመሹም የሚፈቅድላቸው አይመሰለኝም ::

2. ብዙ ዝርዝር ውሥጥ ሳልገባ : "ፓርላማ አንገባም" ካሉ በምርጫ-ቦርድ የተመዘገበ የድርጅቶቻቸውን ህልውና (ላይሰንሱን) ተገደው እንዲመለሱ ኢሀዲጎቹ ያደርጓ'ቸዋል:: የፖለቲካው ጫና ደግሞ የህጉን ተፈጻሚነት ያፋጥነዋል::
Last edited by ሳምቻው on Mon Oct 17, 2005 1:47 pm, edited 12 times in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

የቀጠለ....

Postby ሳምቻው » Mon Oct 17, 2005 1:12 pm

3.ድርጅቶቹ ኮላፕስ አድረጉ ማለት ደግሞ : መሰብሰብ አይችሉም የሚለውን አስቡ :: ኦፊስ አይኖራቸውም :: ይህም ግልጽ ነው :: በድርጅቶቹ ስም የሚደረግ ማናቸውም ውል ,ውክልና ,ድርድር በገሀድ ያከትማል :: የድርጅት ስም ይከስምና በራሳቸው የየግል ስም መጣራት ይጀምራሉ :: ድርጅቱ ስከሰመ በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ህዝቡን ማነጋገር አይችሉም:: ድርጅቶቹን ወክለው ከሌላ ሀገር መንገግስት ጋርም ስለ ኢትዮጵያ
አይነጋገሩም:: ዲፕሎማቶችንም በግልጽ ይሁን በሚስጥር አያነጋግሩም :: ባጭሩ በሀገሪቱ ብሄርዊ አጀንዳዎች(ፖሊሲዎች) ላይ ያለቸው ህጋዊ እንቅስቃሴ ኦፊሻል አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን """ ጉዳዩ የማይመለከታቸው "" ሆነው ይቆጠራሉ :: ከፕሬስ ያለፈ ተሳትፎ አይኖራቸውም :: ምክንያቱም የፓርላማ ሀይል አለመሆናቸው ብቻ ሳይሆን ድርጅታዊ ህልውናው ያበቃ የሰዎች ስብስብ በቅርብ በመከሰቱ ነው ::

አሁን አቶ መለስ ለተቃዋሚው ነገሮችን እየያመቻቹ ያሉት( ጥርሱን የተነቀለ አንበሳ ወደ ፓርላማው መጋበዝ ወይም ጥርሶቹን እንደያዘ ወደ እስር ቤት የሚያመራን ኣውሬ ማባበል ) ናቸው ::

in the poltics of truth , የ አቶ መለስ አስተዳደር ተቃዋሚው ኃይል ፓርላማ እንዲገባ አይፈልግም :: ከገባም እጅ እና እግር የሌለው በድን ሆኖ መመጣቱን አረጋግትትጦ ነው :: ለዚህ አላማው

ተፈጻሚነት እንዲሆን ; ፓርልማውን ለተቃዋሚው ወገን ምቹ ያለሆነ ስፍራ """ አን-ኮንፈርተብል ፕሌስ "" አድርጎታል :: "" እንቢ ! "" ሲል ደግሞ , ህገ-ወጥ ቡድን ተብሎ ፍቃዱን ይቀማል :: ፍቃዱን የተቀማው ተቃዋሚ ቡድን ወደ ህዝብ ዞሮ ሳይጣራ ያለማመንታት ይታፈሳል :: ከዚህ ክራይስ ለመውጣት የመለስ አልቲሜት የፖለቲካ ግብ ለጊዝው ይህንን ይመስላል ::

ልብ በሉ ፓርላማ ቢገቡም ""handless"" ተደርገዋል :: መለስን አያሰጉትም :: ከፓርላማው ቢወጡም "" የድርጅት ህልውና የሌለው "" powerless"" የሰዎች ቡድን ናቸው :: እዚህም አያሰጉትም :: ይህ ኦፕሬሽ ሪስክ-አልባ ነው ባይባልም አቶ መለሰ ሊነሳ ለሚችለውን የህዝብ አመጽ ለመግታት የሚያስችል ሌላ ""ትሬት -ፓኬጅ"" ሳይነድፉ አይቀሩም ---!! እኒህ ሰው ሌላ ስራ ይሰራሉ ትላላችሁ ?


ፓርላማ ከገቡ ግን , የሚጠበቅባቸውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያስችል ጉልበታቸው ሽባ የተደርገም ቢሆን ድርጅቶቹ ግን አሉ ::ይንቀሳቀሳሉ :: በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ይንቀሳቀሳሉ :: /ቢያንስ በህይወታቸው ላይ የሚደርስ አደጋ እና እስር አይኖርም ) የኢሀዲግን እርግጫ እየቻሉ : እነሱም ቻሌንጅ እያደረጉት ትግሉን ሊቀጥሉ ይችላሉ :: .......[b]
Last edited by ሳምቻው on Mon Oct 17, 2005 1:33 pm, edited 1 time in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

የቀጠለ....

Postby ሳምቻው » Mon Oct 17, 2005 1:31 pm

""" ፓርላማ አንገባም !"" ህዝብ በአመጽ ና ቀውስ የራሱን ስር ነቀል እርምጃ ይውሰድ "" ከተባለስ ......?

እርግጥ ነው የህዝብ አመጽ ኢሀዲግን ሊስይስፈራው የሚችል ዋናው እና ትልቁ አደጋ ነው :: የህዝብ አመጽ ኢሀዲግን በፍጥነት ይጥላል :: ሆኖም የህዝብ አመጽ ሉአልውዊነቷ የሳሳውን ሀገር ህልውናም እያንገላታ ወስዶ ሊጥል የሚችል ከባድ ማእበል ነው .... !!


ለመሆኑ የኃገሪቱ አንድነት እና ሉአላዊነት ከ'አካባቢው የጸጥታ ሁኔታ ጋር ሲታይ የህዝብን አመጽ ሊሽከም የሚችል የሰከነ ጉልበት አለውን ??

ይቀጥላል ... .....!
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: ብልሀት and 3 guests