ምን ነው ዶ/ር መራራ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ምን ነው ዶ/ር መራራ!

Postby KOMCHE_AMBAW » Sat Oct 08, 2005 4:52 pm

ሰላምታዬ ይድረሶት..
(ፍ.እ.እ ነኝ)...

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ..በስልክ ላገኞት ሞከርኩ..ሆኖም አልተሳካም! ከዛም በ "ጆ" በኩል መልክት ሁሉ አስቀመጥኩኝ..ምንም ግልፅ የሆነ መልስ ግን ማግኘት አልቻልኩም:: ታዲያ ምንም በአሁኑ ሰአት ወደዋርካ ሊያስመጣኝ የሚችል ነገር ባያጋጥመኝም..አልፎ..አልፎ በረፍቶ እርሶም ብቅ እያሉ አንዳንድ በዋርካ ፖለቲካ ስር የሚወጡትን ፅሁፎች ስለሚያነቡ... የኔንም ብሶት እንደሌሎቹ ወገኖቼ ሊይነቡት ይችሉ ይሆናል ብዬ በመገመት ይችን ፅሁፍ ለመፃፍ ተገደድኩ...

አንድ ታሪክ ልንገሮት...ነገሩ እንደዚህ ነው..በድሮ ጊዜ በፈረንሳይ አገር ሲኖር የነበረ አንድ ንጉስ..በአንድ ወቅት ላት በጣም ታማኙ የነበረው ጄኔራል ይከዳዋል:: ታዲያ ንጉሱ አስቀድሞ ጉዳዩን ደርሶበት ጄኔራሉን ወደ ቤተ መንግስት ባስቸኳይ እንዲመጣ ያዝና ቁጭ ብለው መነጋገር ይጀምራሉ:: ንጉሱ ለጄኔራሉ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ አለና..የሚከተልውን ጥያቄ አቀረበለት..
አንድ ከአፍ ጠበብ ያለና..ከወደመቀመጫው ዘርጠጥ ያለ ጠርሙስ በወተት ተሞልቶ ቁጭ ብሏል:: አንድ ውሀ የተጠማ እባብ ቀስ ብሎ ወደ ጠርሙሱ በመጠጋት አንገቱን ወደታች አቆልቁሎ ወተቱን እሲያልቅ ድረስ ግጥም አድርጎ ጠጣ..ጣሙን ቆርጦ..ለመዝናናት ለመውጣት ሲሞክር ሌላው ሰውነቱ ከመጀመሪያ በበለጠ ተነፋፍቶ ስለነበር መውጣት አልቻለም..ስለሆነም የንጉሱ ጥያቄ ለከዳተኛው ጄኔራል..እባቡ እንዴት መውጣት ይችላል ነበር

መልሱ ሁለት ነው...አንድም ጠርሙሱን የሚሰብርለት ሰው እስኪያገኝ መጠበቅ (ከሌላ..ከውጭ ሰው ማለት ነው) ውይም የጠጣውን ወተት በሙሉ መትፋት አለበት (እራሱ ማድረግ የሚችለው ማለት ነው)..

እንግዲህ ዶ/ር ምንም አማርኛ ሁለተኛ ቋንቋዎ ቢሆንም አባባሌን ሊረዱልኝ እንደሚችሉ ቅንጣት የምታክል ጥርጣሬ የለኝም..

የገቡበት የፖለቲካ አጣብቂኝ ግልፅ ብሎ ይታየኛል..የርሶም መወላወል ከዚሁ የመነጨ ነው..ለርሶ በጣም ቅርበት ያለው ሰው እንዳጫወተኝ..ወያኔ ሁለት ምርጫ በሚስጥር እንዳቀረበሎት ነው..አንዱ ያለምንም ማንገራገር ወደ ፓርላማ እንዲገቡ ሲሆን ሌላው ደግሞ ላለመግባት ከወሰኑ..ለነወ/ሮ አልማዝ ሰይፉ እውቅና ሰጥቶ እርሶን ከፓለቲካ ጨዋታ ውጭ ማድረግ ብሎም በኢሰፓነት ወንጅሎ ወደ ዘብጥያ ማውረድ ሲሆን ይህ ሲባል በውጭ አምባሳደሮች ያለውን ግፊት ሳይጨምር ነው.. :!:

አዎን ያሉበት ጭንቀት ይገባኛል.." አንድ ሰው በቅሎ ላይ ሆኖ በቅሎዋ እየዘለለች ልታፈርጠ ስትታገል..ጉዳዩን በፅሞና የሚከታተሉት ሰዎች..አንዱ ልጓሟን ጎትት ሲል..አንዱ ትንሽ አሰግራት ሲል..በጭንቀት ያለው ሰውየ ምን እንዳለ ያውቃሉ..." አይ መሬት ያለሰው" አለ ይባላል.. :lol:

ታዲያ እዚህ ለስራ ወደ ሰሜን አሜሪካ ብቅ ባሉበት ጊዜ የተናገሯቸውን ማለትም "ፓርላማ በመግባትና ባለመግባት" መካከል እርሶም አይረሱትም እኛም እንደዛው! እንዳውም በቀላል አባባል በጭራሽ አይታሰብም ነበር ያሉት..አስታወሱ :!:

እናም ወደ መጀመሪያው ታሪክ ልመልሶ..ማለትም ወደ ንጉሱና ጄኔራሉ..እርሶም ልክ እንደ እባቡ..ካሎት አጣብቂኝ ለመላቀቅ ከህዝቡ የተሰጦትን አደራ መልሰው ማስረከብ ሲጠበቅቦት..ያ ሳይሆን ሲቀር ግን ከውጭ ያለው ሀይል ወያኔም ይበሉት..እራሱን ኦብኮ ብለ የሰየመው የነወ/ሮ አልማዝ ሰይፍ ድርጅት ጠርሙሷን ሰባብሮ እርሶንም ጭንቅል..ጭንቅላቶትን ብሎ ከጤና ውጭ እንደሚያደርጎት ሳይታለም የተፈታ ነው::

ታዲያ ያን ያህል ክብርና የህዝብ ፍቅር እንዳልነበሮት ሁሉ..አያድርስቦትና.. ይህ ሁኔታ ቢፈጠር..ወያኔ ደስታውን አይችለውም! እንዲሆም ወ/ሮ አልማዝ..ታዲያ ሌላው ወገኑ የሞተበት የህብረቱ አባላት የሚያዝኑሎት ይመስሎታል...ደግመው ያስቡብበት :!: ከህብረቱ ከ 23 አባላቱ በላይ ተገድለዋል..በጣም ብዙ ታሰረው ከንብረቱ የተፈናቀለውን ቤቱ ይቁጠረው..ታዲያ ያንን ሁሉ እያዩ ከረባቶን አድርገው መንግስት በሚሰጦት መኪናና ቪላ መቀመጡና የወያኔን ኦና ቤት ማሞቁ እውነት ምን ያህል የህሊና ደስታ የሰጠኛ ብለው ገምተው ነው.. :?:

ለኔ.. እንኳን የርሶ ፓርላማ መግባት ሳይሆን... ማሰቡ ጭራሽ በርሶ ላይ የነበረኝ ልዩ ፍቅር..ክብር ከህሊናዬ ሙሉ በሙሉ እንዲፋቅ አድርጎታል..ላለመግባትም ቢወስኑ..ውሳኔዎትን ሳደንቅ..በርሶላይ የሚኖረኝን እምነት ግን በጭራሽ ከእንግዲህ በኋላ ሊያስለውጠው አይችልም..

ይልቅ የህዝብን አደራ ተቀብለው የመረጦትን ህዝብ ባያሳፍሩና የህዝቡን ሞራል ባይገድሉት..በህይወቶ እንኳን ባይሆንም በሌላው አለም የሰላም ዳግም ህይወት ይኖሮታል..ወደፖለቲካው አለም ሲመጡ..ሁሉንም ያውቁታል..ቀላል የፖለቲካ መንገድ የለም.. በግል ለስጣን ከመሮጥ በስተቀር..በመሆኑም በክብር መሞት..ለህዝብ ድል ሲሉ መታሰር..መሞት..ፍፁም ታሪክ የማይረሳው የዘላለም ህይወት ነው.. :!:

እግዚያብሄር ለሚወስኑት ውሳኔ ሁሉ የህዝብን መንገድ እንዲያሳዮት የዘወትር ምኞቴም ፀሎቴም ነው :!:

ቆምጨ አምባው (ፍ.እ.እ)
I am only one, but still I am one. I cannot do everything, but still I can do something; and because I cannot do everything, I will not refuse to do something I can do

Edward Everett Hale
KOMCHE_AMBAW
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 229
Joined: Tue Feb 10, 2004 3:20 pm
Location: ethiopia

Postby እንድሪያስ » Sat Oct 08, 2005 5:36 pm

Code: Select all
<<ለኔ.. እንኳን የርሶ ፓርላማ መግባት ሳይሆን... ማሰቡ ጭራሽ በርሶ ላይ የነበረኝ ልዩ ፍቅር..ክብር ከህሊናዬ ሙሉ በሙሉ እንዲፋቅ አድርጎታል..ላለመግባትም ቢወስኑ..ውሳኔዎትን ሳደንቅ..በርሶላይ የሚኖረኝን እምነት ግን በጭራሽ ከእንግዲህ በኋላ ሊያስለውጠው አይችልም..........>>

ይልቅ የህዝብን አደራ ተቀብለው የመረጦትን ህዝብ ባያሳፍሩና የህዝቡን ሞራል ባይገድሉት..በህይወቶ .............ወደፖለቲካው አለም ሲመጡ..ሁሉንም ያውቁታል..ቀላል የፖለቲካ መንገድ የለም.. በግል ለስጣን ከመሮጥ በስተቀር..በመሆኑም በክብር መሞት..ለህዝብ ድል ሲሉ መታሰር..መሞት..ፍፁም ታሪክ የማይረሳው የዘላለም ህይወት ነው.. :!:


ውድ ቆምጨ .....ምንም የምጨምረው ወይም የምለው ነገር ኖሮ አይደለም የገባሁት ....እንዲሁ አክብሮቴን (የተለመደውን) ልገጽልህ ፈልጌ ነው ::
ምንጊዜም አክባሪህ::
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1784
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

ምን ያህል ዕውነት ነው????

Postby ጣሰው ገ » Sat Oct 08, 2005 6:37 pm

ሠላም ቆምጮ:
ከላይ ያስቅምጥከው አስትያይት ምን ያህል ዕውነት ነው ወገኔ? ወያኔና ቱልቱላዎቹ በአሁኑ ስዓት ብዙ ብዙ ያስወራሉና አንተ ስታሰበው መራራ ፓርላማ ይገባል ብለህ በሙሉ ልብህ አምንነህ ተቅብለኸዋል ማለት ነው ወይስ ከተጨባጭ አካባቢ ነው የሰማኸው? እንዲያው እኔስ ተባራሪ ወሬ እንዳይሆን ብዬ እጠራጠራለሁ:: በእውነቱ እስቲ ለጊዜው ስክን እንበል ከቅንጅቱም ከኅብረቱ መግለጫ እስከንሰማ ድረስ:: መግልጫዎች ከሁለቱም ጎራ ሰኞ ገደማ ይውጣል ይባላል እና ያቺን መከራኛ ሰኞ በናፍቆትና በተስፋ እንጠብቃት::
አንቸኩል!!!!!!

ትንሣኤዋ ተቃርቧል!
ጣሰው ገ
ጣሰው ገ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 39
Joined: Sat Dec 20, 2003 3:22 am

Re: ምን ያህል ዕውነት ነው????

Postby maki » Sat Oct 08, 2005 6:56 pm

እሺ ፓርላማ አይግቡ እንበልና, ባይገቡ በምን መንገድ ነው ውያኔን መጣል የምንችለው???
maki
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Sun May 02, 2004 1:12 am

Postby አባዊርቱ » Sat Oct 08, 2005 6:59 pm

ውድ ወንድሜ ቆምጨ!
ስጋትህ ይገባኛል, እኔማ ሰሞኑን ህሊናዬንም ወደመሳት ደርሼ ነበር.....ይልቁን አንድ በርግጠኝነት (መቼውንስ እስካሁን ካየሁትና ከሰማሁት) ስለ ዶር መረራ መናገር የምችለው ቆራጥና ምንንም እንደማይፈራና ባለው የሚረጋ ሰው ነው....እንዲህ አይነቱን ክህደትም በለው ወለወልቱነት ያረገዋል ብዬም በህልሜም አልጠብቅም....ግን ምን ይታወቃል ስጋ ለባሽ ነውና ካደረገው በተለይ እሱ በበኩሌ ያኔ ጎዝጉዤ ሀዘን ነው የምቀመጠው...ግን አያሳፍረኝም ወንድም መረራ...በተለይ እሱ ከመጣበት አካባቢ (አምቦ) የሚፈልቁ ልጆች ጀግኖችና ቆራጦች መሆናቸውን ስለምሰማ አያደርጋትም ባይ ነኝ!
ይልቁኑ ወንድም ቆምጬ እነ በየነና ብርሀኑን ፍራልኝ...በአንድ ጀምበር ብዙ ችሎት የሚቀመጡትን!

እግዚአብሄር የወገናችንን ለቅሶ መና አያስቀረው!

ከሁሉ ከሁሉ ልብ የሚሰብረው, መግባታቸው ላይቀር (ነገ የሚወስኑ ከሆነ) እስካሁን ልምምጣቸውና ደጅ ጥናታቸው ነው ቅጥል የሚያረገው..ለዚያውም የዚያ የአሞራ በረከት ፊት እየገረፋቸው....ቱፍ!!....ከዚህ በፊት ብዬዋለሁ...የገዛ አውራጣትን ቆርጦ እንደመጣል ስለሆነ እስቲ ግፋ ቢል ሁለት ቀን ስለሆነች ት እግስቱን ይስጠን!

ኤታማዦሩ!
እስከመጨረሻው የዶ/ር መረራ አድናቂ!
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

Postby maki » Sat Oct 08, 2005 7:07 pm

በጣም እኮ ይገርማል እኛ እዚህ ውጭ አገር ተቀምጠን "'ፓርላማ አይግቡ"" እንላለን? ብባይገቡ ለኛ በምን መንገድ የጠቅመናል??? ወያኔን በመሳርያ እንዳንጥለው መሳርያ የለን, እንዴ! ምን ይሁን, ምን ይደረግ ነው የምትሉት??? ፓርላማ ካልተገባ, ዲሞክራሲ ከማያውቅ ወያኔ ጋር እኮ ነው ጥሉ.......ፓርላም ባይገቡ በርግጠኝነት ለቅመው ነው የሚያስሩዋቸው, ትግሉንም ያግቱታል, አረ እናስብ!!!!!!!
maki
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Sun May 02, 2004 1:12 am

Postby የዘመኑ ልሳን » Sat Oct 08, 2005 7:20 pm

የግለሰቦች ስም መጥቀስ አስፈላጊ አይመስለኝም::አንድ ግለሰብ ብቻሁን ምንም ሊያደርግ አይችልም::እኔ ቅንጅትና ህብረት ተነጣጥለው ወይም ከሁለቱም የተወሰነው ገብቶ የተወሰነው ከሚቀር ሁሉም በአንድነት ፓርላማ ቢገቡ ወይም በአንድነት ባይገቡ እመርጣለሁ::የተወሰኑ ሰዎች ስም እያነሳን ባንናገር መልካም ነው::የሚባለው ወሬ እውነት ከሆነ የቅንጅት ምክርቤት አብዛኛው ፓርላማ መግባትን ይፈልጋል::እነዚህ ሰዎች የወያኔ ፓርላማ መግባት ደሞዙን ስለፈለጉት ነው ለማለት ይከብዳል::የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ እንደ ተጭበረበረ ያውቋሉ ነገር ግን ወደፊት ይህ ነገር እንዳይፈጠር እንዴት ብንታገል ይሻላል በሚለው እነሱ አሳማኝ እና አዋጪ መንገድ መስሎ የታያቸው ፓርላማ በመግባት ሊሆን ይችላል::የተወሰኑ ሰዎችን ስም እየጠራን የሰዎችን ህሊና ከምናደክም አብዛኛው ሰው የተሳሳተ ይሁን ትክክለኛ የተስማማበትን ልንቀበል ይገባል::
የቅንጅት ምክር ቤት እውነት በ2/3 ድምጽ በላይ ለመግባትም ይሁን ላለመግባት ከወሰነ ሌሎቻችን የማንስማማበትን ምክንያት አይገባኝም::ለኛ እኔንም ጨምሮ ማለቴ ነው የመግባቱ ጉዳይ ላይታየን ይችላል::ነገር ግን እሳቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች የተሻለ የመታገያ መንገድ አድርገው ካዩት የማንስማማበት ምክንያት አይታየኝም::
ዲሞክራሲ ማለት በተመረጡ ሰዎች አብዛኛው ድምጽ የሚወሰነውን መቀበል አይደል? Please ሁላችንም ልንቀበለው የሚከብድ ሀሳብ ነው ነገር ግን ቅንጅት ይሁን ህብረት ፓርላማ ለመግባት ሆነ ላለመግባት በአብዛኛው ድምጽ ከተወሰነ ለመቀበል ዝግጁዎች ልንሆን ይገባል::
እስቲ እስከመቼረሻው በትህግስት እንጠባበቅ::
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

ሰላም

Postby ትምህርት » Sat Oct 08, 2005 7:36 pm

maki wrote:በጣም እኮ ይገርማል እኛ እዚህ ውጭ አገር ተቀምጠን "'ፓርላማ አይግቡ"" እንላለን? ብባይገቡ ለኛ በምን መንገድ የጠቅመናል??? ወያኔን በመሳርያ እንዳንጥለው መሳርያ የለን, እንዴ! ምን ይሁን, ምን ይደረግ ነው የምትሉት??? ፓርላማ ካልተገባ, ዲሞክራሲ ከማያውቅ ወያኔ ጋር እኮ ነው ጥሉ.......ፓርላም ባይገቡ በርግጠኝነት ለቅመው ነው የሚያስሩዋቸው, ትግሉንም ያግቱታል, አረ እናስብ!!!!!!!


ሰላም!

ተቃዋሚዎች ወደ ፓርላማ መግባት አለባቸው የምትለውን ሃሳብ እኔ እደግፋለሁ! ተቃዋሚዎች ረጅሙ ትግላቸው ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ፓርላማ መግባት ጥሩ አማራጭ ይመስለኛል! በእኔ አመለካከት ባሁኑ ወቅት ትግሉ በአሸናፊነት እንዲጠናቀቅ ከዚህ የተሻለ ምሽግ ያላቸው አይመስለኝም:: ከዚህ ተቋረጠ ከተባለው ድርድር ምንም ውጤት ሊገኝ እንደማይችል ቀደም ብየ ተናግሬ ነበር:: ስለዚህ የተቃዋሚዎች ጊዜና ጉልበት መዋል ያለበት መልእክታቸውን ለህዝቡ እንዲደርስ ለማድረግ ብቻ ይመስለኛል:: ከዚህ መንግሥት ጋ ተወያይተን የሆነ ውሳኔ ላይ እንደርሳለን የሚለውን ስሜታቸውን መታገል እና ማሸነፍ ያለባቸው ይመስለኛል::

ከሁለት አጭር አመታት በኌላ የሚደረገውን የቀበሌ ምርጫም አስታውሱ! ትክክለኛውን መንገድ መምረጥ እንድትችሉ አምላካችሁ ይርዳችሁ! አሜን!
ከስላምታ ጋር
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

Postby KOMCHE_AMBAW » Sat Oct 08, 2005 8:58 pm

ሰላም የዘመኑ ልሳን...

አስተያዬትህን እንደግል አስተያዬት ብወስድም..የኔንም በዚያው መልኩ እንድታይልኝ..
የግለሰቦች ስም መጥቀስ አስፈላጊ አይመስለኝም::

መሪዎች ታቦት አይደሉም...ታዲያ እነሱ እየተገለባበጡ ማንን ነው ማንሳት የነበረብን :?:ለማንስ ነው ብሶታችንን ማሰማት የነበረብን :?: ሰው የሚከበረው በስራው ነው :!: ያውም ህዝብ አደራ ያለውን ሀላፊነት ሲጠብቅ..ብሎም በቃል-ኪዳኑ ሲገኝ..ለማውራትማ ይሄው እኛስ እድሜ ለዋርካ ብዙ እናወራ የለም :!: ወያኔን ብቻ ስለምንጠላ "አትናገሯቸው" ማለት አግባብ አይደለም...የስከዛሬው ይበቃል :!: በግል ዶ/ር መራራን እወዳቸዋለሁ...ከላይ ያስቀመጥኩት እየተንጋደደ የመጣውን የፖለቲካ መንገድ ምናልባት ትንሽ ቆም ብለው ቢያዩት ከሚል ነው..ፍቅሩም ስላለኝ ነው ምርር ብዬ የተናገርኩት..እንጂ ዝም ብሎ መቀመጡን አጥቼው አይደለም...አዎን ዛሬም..ነገም..የማየውን ስህተት ከመናገር ወደኋላ አልልም :!:


እኔ ቅንጅትና ህብረት ተነጣጥለው ወይም ከሁለቱም የተወሰነው ገብቶ የተወሰነው ከሚቀር ሁሉም በአንድነት ፓርላማ ቢገቡ ወይም በአንድነት ባይገቡ እመርጣለሁ::


ትክክል :!: ዶ/ር መራራም ከዚህ በፊት የህብረቱ አመታዊ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ሁላችንም ያስደሰተን ይሄው አባባላቸው ነበር :!:

<<<.....እነዚህ ሰዎች የወያኔ ፓርላማ መግባት ደሞዙን ስለፈለጉት ነው ለማለት ይከብዳል....>>>>
ታዲያ ምን ፈልገው..የማንንስ ጥቅም ሊያስከብሩ ነው መግባት የፈለጉት? እስቲ አንተው እንደገባህ መልስልኝ :?:

የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ እንደ ተጭበረበረ ያውቋሉ ነገር ግን ወደፊት ይህ ነገር እንዳይፈጠር እንዴት ብንታገል ይሻላል

አንድ ያበው አነጋገር አስታወሰኝ..." እህል የሚደርሰው በፍልሰታ..እኔ የምሞተው ዛሬ ማታ" :!:


የቅንጅት ምክር ቤት እውነት በ2/3 ድምጽ በላይ ለመግባትም ይሁን ላለመግባት ከወሰነ ሌሎቻችን የማንስማማበትን ምክንያት አይገባኝም:
:

ወንድሜ ሆይ..ያ የግል አመለካከትህ ነው..እኔን አይመለከተኝም :!: የኢትዮጲያ ህዝብ ህልውና የሚወሰነው በፓርቲዎች ባለባቸው ጫና ሳይሆን ለህዝቡ ቃል የገቡለትን የተሰረቀውን ድምፅ ሲያስመልሱለት ብቻ ነው...ያ ሳይሆን ግን እነሱን ተማምኖ ደረቱን ለጥይት በሰጠው ዜጋ ላይ መቀለድ ይሆናል...

ዲሞክራሲ ማለት በተመረጡ ሰዎች አብዛኛው ድምጽ የሚወሰነውን መቀበል አይደል?


አዎን...ለዚህም ነው የተሰረቀው ድምፅ መመለስ ያለበት... በስም ብቻ የምናቃትን "ዲሞክራሲ" በተግባር እንድናያት..እንጂ የውጭ ጫናና..የወያኔን መርገምት ለማለፍ የሚደረግ ምርጫ አይደለም :!:

ወደ ፓርላማው መግባት ወይም አለመግባትን የሚወስኑት እኛን ለማስደሰት አይደለም..ማለቴ እኔንና አንተን የመሰሉትን ማለቴ ነው..ውሳኔያቸው የህዝብን ጥያቄ ይመልሳል ወይ ነው :?: በዛ ላይ መልስህ "አዎን" ከሆነ...በመጭዎቹ ሳምንታቶች እንደገና ተመልሰን ጉዳዩን እናየዋለን..አንድ መርሳት የሌለብህ ጉዳይ ቢኖር...የህዝብ አመኔታ ማጣት ትልቅ የፖለቲካ ክስረት መሆኑን ነው..! አንድ ፖለቲከኛም..በቃላቱ ወይም ንግግር አዋቂ በመሆኑ ሳይሆን..መለኪያው እሱ ራሱ ለተናገረው መርህ ወይም ፕሮግራም ተገዢ ሲሆን ብቻ ነው..(የግል እምነቴ ነው)

ቆምጨ አምባው
Last edited by KOMCHE_AMBAW on Sat Oct 08, 2005 9:02 pm, edited 1 time in total.
I am only one, but still I am one. I cannot do everything, but still I can do something; and because I cannot do everything, I will not refuse to do something I can do

Edward Everett Hale
KOMCHE_AMBAW
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 229
Joined: Tue Feb 10, 2004 3:20 pm
Location: ethiopia

ቀደም ብለው!

Postby ወርቅሰው1 » Sat Oct 08, 2005 8:59 pm

ውድ ኮምጬአምባው!

ድንቅ የሆነ የንጉሡንና የጀነራሉን ምሣሌ በቓንቓህ በማቅረብህ ያለህን ልቦና ከሚያደንቁት ወገኖችህ አንዱ ነኝ::

ሰተት ብሎ የሚሰራጭ ነው በመንፈሳችን ውስጥ ለምናነብህ:: ጥሩ አባባል ነው::

ኮምጬ ካሁን በፊት ወይዘሮ አልማዝ ታሰረች ተብሎ በተሰማ ጊዜ ወዲያው በዚሁ በዋርካ ፖለቲካ ላይ ከጻፉት ሰዎች አንዱ ነኝ:: በማግስቱ ደግሞ ተፈታች ተባለ ደስ አለኝ:: ሴትዮዋን በአንድ ራዲዮ ጥያቄ ቀርቦላት ያንን መልስ ስጸጥ ስሰማት ነው ያደነቅኌት::

ታዲያ ያች ሴት ከብርሃንና ሰላማ ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት የህወኃት ታጣቂዎች ወሰዷት ተብሎ ነው ዜናው የተናፈሰው:: ተዚያም በዚያ ምክንያት ከድርጅቱ ተሰናበተች በወሳኝ ነገሮች ላይ የነበረን ሰው ወይ በምክር ካልሆነም በተግሳጽ መታለፍ ነበረባት::

ያየእልህ ነገር አሁን ለደረሰ የድርጅቱ የርስበርስ መሰባጠር ያውም በክፍትና በሻጥር የታጀለ ሆኗል:: 2 አብኮዎች ተፈጥረዋል:: ወያኔ እንደዚህ መፍጠር ዘወትር ይጥራል::ያንን አውቆ ከሱ በልጦ ማሰብ ነበረበት:: እኔም ልክ እንደቆምጬው በዚያን ቀን በጻፍኳት ላይ የጀኔራሉን ዓይነት ነገር ጽፌ ነበር::

"አንድ ጀነራል ጦሩ በውጊያ ወረዳ ውስጥ እያለ" ጥሎ ወደ ቤቱ ወይም ለስብሰባ ብሎ ወደ አዲስ አበባ መሄድ አይኖርበትም በግንኙነት መሣሪያዎች ከስብሰባው ጋር ቀጥታ ግንኙነት ብቻ መፍጠር ይኖርበት ነበር:: የድርጅት መሪዎች አገሪቱ እዚህ ትኩሣት ላይ እያለች ለደቂቃ ታህል ከህዝባቸው መለየት አይኖርባቸውም ነበር::

አንድ የፖሊስ ተራ ወታደር ነው ግልበታውን በአብኮ ላይ ያደረገው:: ያሳዝናል:: ከዚያም አኩራፊዋን ወ/ት: አግኝቶ ከወያኔው ጉያ እንድትገባ አደረጋት መለት ነው:: ይህቺ ሰው ከዶክተር መረራ ያላነሰ በህዝቡ ትታወቃለች ለዓላማዋ በከፍተኛ ደረጃ ታጋይ ነች ንግግሮቿ ደግሞ ቀጥተኛና ያለፍርኃት የምትናገራቸውን የምታውቅ ነች:: ከቀድሞው ያሁኑ እንዳይደርስ ቢታሰብበት ኑሮ ጥሩ ነበር ለማለት ነው::

እርግጥ ዶ/ሩ: በሚገባ ከማደንቃቸው ሰው አንዱ ነኝ:: በዚያው ልክ በውጪ የድርጅታቸውና የህብረቱ በየአገሩ ተወካዮች አሏቸው ለምን አሜሪካ ድረስ በዚያ ወቅት ሊሄዱ ፈለጉ አማካሪዎቹስ ምን ዓይነት ምክር አማክረዋቸው ነበር:: ይህና ያንን የመሰለ ያሰራር ቴኪኒኮች መመልከት አለብን:: ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንፁ ብቻ ማለቱ እስከመቼ መቀጠል እንደሚኖርበት አላውቅም::

ይህ የሰላም ድርድር:: የፓርላማ አለመግባት:: የሽግግር ብሔራዊ አንድነት መንግሥት እንዲሁም አንዱን ጥሎ ሌላው መግባት እነኝህ ራሳቸው የቴክኒካዊ አሰራርን የሚመለከቱ ናቸው:: ሁሉም ድርጅቶች ከመሪዎቹ ኃላ ብቻ ሣይሆን ከኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ጎን መቆም ይኖርባቸዋል::

አቶ: መለሰ ባለፈው ሣምንት የሰጡትን የቴሌቪዥን ጥያቄ ዛሬ ተመለከትሁት:: የሰውዬው አነጋገር ፈረንጆች እንደሚሉ 11ኛው ሰዓት ላይ ነኝ ይላሉ 1 ሰዓት ነው የቀራቸው ለ12 ሰዓቷና ለግድያው ለማሰሩና ለማሰቃዬቱ ማለት ነው::

እንጊዲህ እኝህ ሰው የሚናገሩት ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ የዲሞክራሲ ፍላጎት የሚያከሽፍ የአነጋገርን ስልት ነው:: ባጠቃላይም ማስፈራራት ነው:: ባለፈው የቀይ ሽብርና የፍየል ወጤጤን መዝሙር በመስማት ያትውልድ የቱን ያህል እንደከሸፈብን ይታወቃል:: አሁን ደግሞ መጪውን መንግሥት እንኳን ተቃውሞ ለማድረግ እንዳያስደርግ የመጨረሻ ትዛዝ የሚእባበቅ ኃይልና ሁኔታዎች አሉን ሲሉ ነው::

የሚያሳዝነኝ ግን በተለይ ውጪ ያለነው ሌላ አማራጪ ስትራተጂ ያለመነደፉ ነው:: እስከዛሬ ዘንባባ ተይዞ ይለመናል:: ከዚያስ ግድያውንና እስሩን ሲጀምርስ? ከዚያ ቴሌቪዢኑ ላይ! በትግሪኛው ፕሮግራም ጊዜ አሜሪካ መተው ሳለ ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ያደረጉትን በየመድረኩ ውይይታቸውን በፊልም ያሳያል:: የቀድሞ የሶቬት ክላሽንኮቮቺ ጥይቶች መትረየሶች መገናኛ ራዲዮኖች እንዲሁም የጅቦንቦችን ያሳያል:: ይቀጥልና አቶ ኃይሉ ሻውል ከቀድሞው የመከላከያ ኃይል መኮንንኖች ጋርና ከደርግ ኢሠፓ ባለስልጣኖች ጋር ተሰብስበው በገንዘብ ረድተዋቸዋል ይላል:: ይህ ሁሉ የወያኔ/የህወኃት የክስ መመሪያን ይመስላል::

ለመናገር የፈለግሁት የኢትዮጵያ ህዝብ በትንሣኤ ራዲዮ አማካኝነት ከመሪዎቹ አንዱ ወይም ህዝብ የመረጣቸው ላይ አደጋ ማለትም መታሰር መታፈን መገደል ቢፈጸም ቢደርስባቸው ቅሌን ጨርቔን ሳይል የውኃትን አስተዳደር በሠላም ከዚያ ቦታ እንዲነሳ በማድረግ አገሪቱ ውስጥ ምንም ዓይነት አናርኪ ሳይፈጠር ሁሉንም እንዲያስተካክል ጥሪ እንዲቀርብለት ነው::

"ደርሶ ከመጨነቅ አስቀድሞ ስለዚያ ነገር ማሰብ መዘጋጀት መደራጀት መወያዬት"

አመሰግናለሁ::

*ቀይ ባህር ዳር ድንበራቺን ነው*

አክባሪህ

ወርቅሰው1
ከ(ሰሐሊን)
ወርቅሰው1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4075
Joined: Wed Nov 05, 2003 9:49 pm
Location: Sehalin

Postby የዘመኑ ልሳን » Sat Oct 08, 2005 9:41 pm

ቆምጬው እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙም የተለየ ሀሳብ ኖሮኝ አይደለም::ህብረቱና ቅንጅቱ በሚኖራቸው እለት ተለት እንቅስቃሴ ላይ አስታየት መስጠት መልካም ነው::ምን ለማለት እንደፈለኩ ግልጽ ለማድረግ አንድ ግለሰብም ያንሳው ይሁን የተወሰነ ግሩፐ ያ ሀሳብ በአብዛኛው እስከተደገፈ ድረስ የሌሎቻችንን በጠቅላላው የተወሰነውን ሌሎቻችን መቋወም የምንችል ቢሆንም ከተስማሙት ውስጥ የተወሰኑት ላይ ብቻ ባናተኩር ለማለት ነው ግለሰቦች ላይ ያልኩት::

አንተ ባለፈው እንደጻፍከው ፓርላማ ብንገባ እንኳን ከቅንጅት ጋር ተማክረን እንጂ ለብቻችንም አናደርገውም ብለዋል ያልክ መሰለኝ::ስለሆነም ከቅንጅት ጋር በጋራ የሆነ መግለጫ እስኪሰጡ ብንታገስ ብዬ ነው::

አስታየቴ ቅር ያለው ካለ እኔን ሳይሆን ያቀረብኩትን ሀሳብ ቻሌንጅ ቢያደርግ ምንም ቅር አይለኝም::
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

Postby KOMCHE_AMBAW » Sat Oct 08, 2005 9:56 pm

አንተ ባለፈው እንደጻፍከው ፓርላማ ብንገባ እንኳን ከቅንጅት ጋር ተማክረን እንጂ ለብቻችንም አናደርገውም ብለዋል ያልክ መሰለኝ::ስለሆነም ከቅንጅት ጋር በጋራ የሆነ መግለጫ እስኪሰጡ ብንታገስ ብዬ ነው::


የዘመኑ ልሳን..
አዎን ብያለሁ...አሁንም በዚሁ ርእስ ላይ ደግሜዋለሁ.. "ብንገባ እንኳን" ማለት እንገባለን ማለት አይደለም..ሆኖም ግን The worst-case scenario..ቢሆንም እንኳን..የትግል አጋርንነታችንን እናሳያለን ለማለት ያህል ነው.."ቡዳ በወዳጁ ይፀናል" ይባላል...ለዶ/ር በግል ባላውቃቸውና ከልብ የምተማመንባቸው ባይሆኑ ኖሮ...ሂሴን በሌሎቹ በጀመርኩ ነበር..
በተረፈ እድሜ ይስጠን..እንክርዳዱ የሚለይበት ቀን ሩቅ አይደለም..ሌላው... እኔ አንተን ሳይሆን ሀሳብህን ብቻ ነው የተቃወምኩት :!:
I am only one, but still I am one. I cannot do everything, but still I can do something; and because I cannot do everything, I will not refuse to do something I can do

Edward Everett Hale
KOMCHE_AMBAW
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 229
Joined: Tue Feb 10, 2004 3:20 pm
Location: ethiopia

Re: ምን ያህል ዕውነት ነው????

Postby ዘማች » Sat Oct 08, 2005 10:35 pm

ሰላም አቶ ጣሰው.... ይቺ አስተያየትህ ጥማኛለች:: የረጋ ወተት... ነውና እስቲ ወደ ሰኞ ተሻግረን እውኑን እንይ:: ወዳጄ ቆምጬው በመረጃ አሰባሰብ ረገድ ጠንካራ ሰው መሆኑን ባውቅም ይህ የዶ/ር መረራ ጉዳይ ግን ከቶም ሊዋጥልኝ አልቻለምና ትርፉን እንግልቱ ባሰኝ:: ስሜትህን ብጋራም ጭንቀትህን በውስጤ ባዳምጥም, እንዲያው መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ በቂ ጊዜና ዋቤ ያጠጠን ይምስለኛልና ጉዳዩን በይደር ማበራየቱን መረጥኩት.... ቆምጬው:: አንድዬ ቸር እንደሚያሰማንና መረራን በእምዬ ጉያ ስር በጽናት እንደሚያቆይልን እምነቴ ነው እያልኩ ተዚህ ተገበታህ ልለይ :(

አክባሪያችሁ
ዘማች

ጣሰው ገ wrote:ሠላም ቆምጮ:
ከላይ ያስቅምጥከው አስትያይት ምን ያህል ዕውነት ነው ወገኔ? ወያኔና ቱልቱላዎቹ በአሁኑ ስዓት ብዙ ብዙ ያስወራሉና አንተ ስታሰበው መራራ ፓርላማ ይገባል ብለህ በሙሉ ልብህ አምንነህ ተቅብለኸዋል ማለት ነው ወይስ ከተጨባጭ አካባቢ ነው የሰማኸው? እንዲያው እኔስ ተባራሪ ወሬ እንዳይሆን ብዬ እጠራጠራለሁ:: በእውነቱ እስቲ ለጊዜው ስክን እንበል ከቅንጅቱም ከኅብረቱ መግለጫ እስከንሰማ ድረስ:: መግልጫዎች ከሁለቱም ጎራ ሰኞ ገደማ ይውጣል ይባላል እና ያቺን መከራኛ ሰኞ በናፍቆትና በተስፋ እንጠብቃት::
አንቸኩል!!!!!!

ትንሣኤዋ ተቃርቧል!
ጣሰው ገ
ዘማች
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 88
Joined: Wed Aug 18, 2004 7:02 pm
Location: ethiopia

Re: ምን ነው ዶ/ር መራራ!

Postby SAY-NO-TO-HATRED » Sat Oct 08, 2005 11:41 pm

ውድ: KOMCHE_AMBAW:: የእግዚአብሔር:ሰላምታዬ:ይድረስህ!!

በዚህ:አለም:ላይ:እውነተኞችን:እንደማየት:የሚያስደስተኝ:ነገር:የለም::
ለእውነት:የቆመ:ሰው:አይኑ:የሚያተኩረው:ያቺው:እውነት:ላይ:ነው:
እንጅ:ሰው:እውነቱን:ብናገር:ምን:ይለኛል:የሚለው:ነጥብ:
ላይ:አይደለም::

ውድ:በእግዚአብሔር:ፊት:የተከበርክ:ወንድሜ:KOMCHE_ABMAW:
የእውነት:ምንጭና:ህይል:የሆነው:አምላካችን:አንተና:ቤተሰቦችህን:አገራችንና:ሕዝባችንን:
ይባርክልን!!! የስው:ልጅ:ህይወት:አጭር:ነው::ስህተትን:ማረም:አንዳንዴ:
ህይወት:አጭር:ከመሆንዋ:የተንሳ:አይቻል:ይሆናል::ስለዚህም:
አውቆ:የሚሰራን:ስህተት:የሰው:ልጅ:ብልህ:ከሆነ:ቢያርም:
ለርሱ:ይበጀዋል::

ውድ:እጅጉን:የማከብርህ:ወንድሜ:KOMCHE_AMBAW: በወቅቱ:ማድረግ:ያለብህን:ግዴታ:ተወጥተሀል::ዛረ:ስህተትም:ይሁን:
ትክክል:እውነት:ነው:ብሎ:ያሉትን:አለመፍራት:አውጥቶ:መናገር:
ትልቅነት:ነው::ነገ:ነገር:ሁሉ:ካለቀ:በሁዋላ:ያዙኝ:ልቀቁኝ:ከማለት::
የእኛ:የአፍ:ስህተት:ቀላል:ነው:ከተቃዋሚዎች:ሊሰሩት:ካሉት:ስህተት::

ውድ:ወንድሜ:አሁንም:እጅጉን:ኮርቸብሀለሁ::ይህ:ነው:እኔ:የማውቀው:
ኢትዮጲያውነት::አምላካችን:ይባርክልኝ!!


አምላካችን:ሕዝባችንና:አገራችንን:ይጠብቅልን!!
አምላካችን:ተቃዋሚዎችን:ድህውን:ሕዝብ:ብቻ:ተመልክተው:
ውሳኔያቸውን:ለመስጠት:እንዲችሉ:ያብቃልን!!
ደህንነታቸውንም: ይጠብቅልን!!
WE ARE NOW AMBASSADORS FOR OUR BELOVED COUNTRY AND ONE DAY WE WILL BE CITIZENS IN ETHIOPIA, ONCE AGAIN!!
SAY-NO-TO-HATRED
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1354
Joined: Sat Mar 12, 2005 8:29 pm
Location: united states

ሰላም ኮምጬ:-

Postby ሊቃውንት » Sun Oct 09, 2005 8:02 am

ከላይ ያሰፈርከውን ፅሁፍ ሳነብ አንተው እንዳለከው በአንድ ወቅት ዶክተሩ"" ፓርላማ መግባት በሰማይም በምድርም የማይታለም ነው::""በማለት የተናገሩትን በርግጥም ማንም አይረሳውም::

ግን እንዲህ ባሉበት አንደበታቸው በርግጥም ፓርላማ ለመግባት መወሰን አይደለም ማሰባቸውም ከህዝብ ጉሮሮ አስነቅሮ የሚያሰተፋ ተግባር ነው የሚሆነው::

አንተ ምን ያህል እርግጠኛ እንደሆንክ ባላውቅም ከላይ አንድ ወገን እንዳለው ወያኔዎች ወደቀ ሲሉ ተሰበረ ስለሆነ ወሬያቸው በጥንቃቄ ማስተዋሉ ሊመጣ ከሚችለው ስህተት እና ፀፀት መዳን ነው::


በተቀረ ግን በዚህ ሁኔታ ፓርላማ መግባት ማለት ሊፈጥረው የሚችለው የፖለቲካ ኪሳራ ወደር የማይገኝለት ነው::

በመጨረሻም በተቻለ መጠን ጥረት በማድረግ ዶክተሩ ለዚህ አፋታኝ ምላሽ እንዲሰጡ በምታውቀው መንገድ ሁሉ ጥረት ማድረግ ይገባሀል:; ከፅሁፍህ እንደተረዳሁት ቅርበት ያለህ ስለመሰለኝ :!:
The truth is out there.
ሊቃውንት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 10, 2004 9:21 am
Location: Far_east

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 5 guests