እውነትም ስልጣን ሱስ ያስይዛል!!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

እውነትም ስልጣን ሱስ ያስይዛል!!!

Postby ጥልቁ1 » Sun Oct 09, 2005 7:17 am

የካሊፎርኒያ አገረ-ገዥ የነበሩት Governor Davis ፣ ስለስልጣን የሚከተለውን ብለው ነበር:: ‘ከልጅነቴ ጀምሮ ፣ የተለያዩ የሱስ አይነቶች ተፈራርቀውብኛል ፤ ነገር ገን ፣ በስትርጅና የያዘኝ የስልጣን ሱስ ከሁሉም ይበልጣል። ይሄው ጊዜየን ጨርሸ ስወጣ ፣ በቢሮየ ላይ እጠቀምባቸው የነበሩ መገልገያወቸ ሁሉ ፣ ወደ የእቃ ማጓጓዣው መኪና በሰዎች ሲንቀሳቀሱ ፣ እጅግ ያስጨንቀኛል። በጣምም ያበሳጨኛል” ነበር ያሉት።

ቢል ክሊንተንም ፣ ስልጣናቸውን ጨርሰው ከመውጣታቸው በፊት ፣ 60-minute በተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ፣ ጋዜጠኛው “ከዚህ ከኋይት ሃውስ ምን ይናፍቀዎት ይሆን?” ብሎ ሲጠይቅ ፣ በአጭር አገላለጽ “ስልጣኔን!” ነበር ያሉት።

እኔ የምለው ፣ ይሄ ስልጣን የሚባለው ነገር ፣ የሚከብድ ሃላፊነት ፣ ህዝብ የሚገለገልበት እና ፣ የሚያስጨንቅ የታሪክ መጸሃፍ አይደለም እንዴ?!
እስኪ አሁንም ፣ እጅግ ወደማከብራቸው ፖለቲከኛ ቢል ክሊንተን ቃል ልመለስ…
በዚሁ የቴሌቪዥን ዝፍጅት ላይ ፣ “ልጅወት ለፖለቲካ ስልጣን የምትወዳደር ይመስለዎታል?” ተብለው ሲጠየቁ ፣ “ስለ የወደፊት ምርጫዋ እርግጠኛ ሆኘ መናገር አልችልም ፤ ነገር ግን ፣ የህዝብ ስቃይ ያስጨንቃታል ፣ ህዝብን የማገልገል ፍላጎት እንዳላት አምናለሁ።” ነበር መልሳቸው።

እንግዲህ ፣ ፖለቲካን እያንዳንዱ የራሱ የሆነ ትርጓሜም ቢያስይዘው ፣ ከላይ ከተቀመጠው የክሊንተን አነጋገር ፣ ፖለቲከኛ መሆን ማለት ፣ ህዝብ የሚገለገልበት ነው ማለት ነው። ታዲያ ህዝብ የሚገለገልበት መሆኑ ቀርቶ ፣ አብርሃም ሊንከን “ሰውን ላስተዳደር ከማለትህ በፊት ፣ እራስህን በቅጡ አስተዳደር” ወደሚለው ተቀየረ እንዴ?! አብርሃም ሊንከንም ቢሆን ፣ ሊሉ የፈለጉት ፣ እራስ ከሌለ ያ እራስ ለሌላ መቆም አይችልም ማለት ይመስለኛል። እራስ መኖሩ የሚታወቀው ግን ፣ የፓርላማ ገንዘብ በመልቀም ፣ ለፓርላማ ገንዘብ ከፋዩ ህዝብ ልጩህለት ማለት ነው ብየ አላምንም። አዎ! Malcom X ለአፍሪካ አሜሪካዊያን ነጻነት እታገላለሁ ሲል ፣ በመጀመሪያ ፣ በመጠጥ ፣ በድራግ እና በዋልጌነት ጠፍቶ የነበረው ራሱን ፣ በእስልምና እምነት ፈልጎ አግኝቶት ነው ለህዝቡ አራርአያ መሆን የጀመረው። እንግዲህ ከMalcom X የምናገኘው “እራስ” ፣ በገንዘብ እራስን መቻል ሳይሆን ፣ በአመለካከት እራስን መቻል ነው ማለት ነው። በጣም የሚያሳዝነው “እራስ” ግን ፣ በአመለካከት የበሰለ ሆኖ ተገኝቶ ሳለ ፣ በግብዝነት ሲጠፋ ነው።

አዎን! ትላንት በአፋችን ምራቅ ያስሞሉት ፣ አንደበተ-ርትኡ የጊዜው ፖለቲከኞች ፣ ዛሬ እንዲህ በስልጣን ግብዝነት እልም ብለው ሲጠፉ ፣ ከማንም በላይ የሚያሳዝኑት ታሪክን ብቻ ነው። እንጅ እኛማ! እኛ ተስፋ የጣልንባቸውማ! እኛ ያጨበጨብንላቸውማ! እኛ በአደባባይ የአሞገስናቸውማ! እኛም ለስልጣን ስንበቃ ይቅር እንላቸዋለን!

አንዳንዴ እንዴውም ፣ እኔ እነሱን ሆኘ ሳስበው ፣ እውን ፓርላማ የመመረጥ እድሉን ባገኝ ፣ መለስ ዜናዊ አለቃየ ሆኖ ፣ በረከት ስሞንም ጋር “ችርስ” እየተባባልን ስንጠጣ አይነምናቤ ሲያሳየኝ ፣ ያ የመረጠኝ ህዝብ ማሽሟጠጡን እንኳ ቢያያዘው ፣ እድሜ ለጠባቂዎቸ እንጅ የት አይቻቸው የት ሰምቻቸው ፣ በማለት እጽናናለሁ። እንደ እነ ዶ/ር ያእቆብ ሃይለማሪያም እና “ኢንጂንየር” ሃይሉ ሻወል ያሉ “ብክድህ ታሪክ ይክዳኝ!” የሚሉ ሰዎችን ለመሆን ፣ በመጀመሪያ ተለቅ ያለ ስልጣንን በልጅነት ዘመን መቋደስ ግድ ይላል። አዎን! መለስ የአድዋን ህዝብ ወክሎ ፓርላማ ከመግባቱ በፊት ፣ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ነበረ። ስለዚህ ፣ አሁን ወረድ ብሎ ፣ የፓርላማ መቀመጫ በመያዝ ፣ ተቃዋሚ መሆን ብቻ ሳይሆን ፣ ፓርላማ ከሚያሳልፈው ጊዜ ይልቅ ፣ ለፈጸማቸው ወንጀሎች ፍርድ ቤት የሚመላለስበትን ቀን ሲያስብ ፣ ለምን አንድ አውሮፕላን እስኪቀር ለስልጣኑ አይሟገት?!

የሰው ስም መጥራት ነውር ሆነ እንጅ ፣ ዶ/ር ብርሃኑስ ከንቲባነታቸው ምራቅ አያስውጥም ብሎ ማሰብ ይቻላል?! ግፋ ቢል ፣ አርከበን የደመራ እለት አላናግርም ያለው የአዲስ አበባ ነዋሪ እሳቸውን አላናግርም እንደሚል ስለሚያውቁ ፣ የንብ ምስል ያለባትን ቲሸርት ገልብጠው ለብሰው ፣ ወያኔንም ኢትዮጵያዊያንንም ለአለማስቀየም መሞከር። ደሞስ ፣ እሳቸው ምን መስቀል አደባባይ አስኬዳቸው?! ሬዲዮኑ እና ቴሌቪዡኑን አዝዝበታለሁ ብለው አይደል?! ብቻ ፍቅረ-በረከት አይለያቸው ነው የሚባለው።

እግዜኦ! ሰው እንደዚህ ይገለበጣል? እኔ እራሴ ትላንት “እባካችሁን ፣ የተቃዋሚ መሪወችን ስም አናንሳ” በአልሁበት አፌ ፣ ዛሬ እንዲህ ከራሴ ላፈንግጥ?! ለነገሩ ፣ በፖለቲካ አምድ ላይ መፈነጋገጥ እራሱን የቻለ ውበት አይደል?! አቶ ደምስ ፣ ይህንን ጽሁፍ ከአነበቡ ፣ እሳቸውም ምራቃቸውን ቢለድፉብኝ ከኤልያስ ጋር ተረዳድተን እናጸዳዋለን እንጅ ፣ እሳቸውንስ አልፈርድባቸውም።

በነገራችን ላይ ግን ፣ አንድ ጥሩ የፍልስፍና ቃል አለች የምወዳት። አንድን ሰው ከልብ ከጠሉት ፣ ያንን ሰው በግንባር ሄዶ ፣ ‘በጣም እጠላህ ነበር ይቅርታ አድርግልኝ ። ነገር ግን ለወደፊቱም እጠላሃለሁ እና ይቅርታ አድርግልኝ ማለት ፣ ለተጠይውም ለጠይውም ጥሩ ነው’። እኔም ፣ ዛሬ ተገልብጫለሁ እና ይቅርታ ፣ ነገም ግን እገለበጣለሁ። ከዚህ በተሻሻለ መልኩ ፣ የተዋረዳችሁ ፓርላመኞችም ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ “ዛሬ ከድተንሃል እና ይቅርታ አድርግልን ፣ ነገ ግን እንክድህም” ትሉት ዘንድ እመክራለሁ! ምክንያቱም ፣ ከዚህ በኋላ ደግማችሁ የምትመረጡት ፣ እናንተም አጭበርብራችሁ ብቻ ስለሚሆን ፣ ነገ የመክዳት ሃቅሙ አይኖራችሁም።

ዛሬ ዛሬ ፣ ፖለቲካን እንዲናገሩ እንጅ እንዲያዝዙ የተፈቀደላቸው ጥቂቶቹ ቢሆኑም ፤ ሃቅሙ ያለኝ ይመስል አንድ ነገር ግን ይጸጽተኛል። የአዲስ አበባው የስልጣን ክፍፍል ባይደረግ ኖሮ እና ስልጣን ተጋሪዎችን ምራቅ ከማስዋጥም አልፍ “አንተ ስራ አይሰጥህም ፣ አንተ ይሰጥሃል” ከማባብላቸው በፊት እና ፣ ፓርላማ የመግባት አለመግባቱ ውሳኔ ፣ እንዲህ ለፓርላማ መከፈቻው ቀን አፍንጫ ድረስ ባይቀርብ ኖሮ …

የልጣን ጠአሙ እየጠፋ ፣
የህዝብ ፍቅር እየፋፋ ፣
የታሪክ ምእራፍ እየሰፋ ፣
የዶክተሮችም ስም ሳይጠፋ ፣
ፕሮፌሰር መስፍንንም ሳናስከፋ ፣
የመለስ ተንኮል እየከረፋ ፣
በፈካ ነበር የኢትዮጵያ ተስፋ።

“ነበር?” ቱፍ ቱፍ!!!

እግዚያብሄር ይመስገን አልን አንዴ እዚህ ብንደርስ
ከዚህ ወደ ቁልቁል ማን እኛን ሊመልስ?
የካዱትም ይክዱ ወርቅ ይሁን መንገዱ
የድል መራመጃው ድሮም ደም ነው ልምዱ።
ልግባ ልውጣ ብሎ አሁን ያወላዳ
በቃ ቀረሁ ቢልም ነገ በማለዳ
ክህደትን ማሰብ ነው የታሪክ ይሁዳ!
በብእሬ አርጀህ ገፋፊህ እኔ ነኝ
ልክ እንደምንሊክ ብምርህ አይማረኝ።


ኢትዮጵያ ትቅደም!

ጥልቁ ዘብሄረ-ኢትዮጵያ
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

እውነትም:የስልጣን:ሱስ: ..እጅግ:ይገርማል...

Postby SAY-NO-TO-HATRED » Sun Oct 09, 2005 7:51 am

ውድ:የተከበርክ:ወንድሜ:ጥልቁ:የእግዚአብሔር:ሰላምታዬ:ይድረስህ!!

የፖለቲካ:background ዱ:የለኝም::ከአገርና:ከሕዝብ:ፍቅር:የተነሳ:ረሴን:በተቻለኝ:መጠን: በአገራችን:ላይ:የሚደረገውን:የሕዝብ:ትግል:እጅጉን:በቅርብ:እየተከታተልኩ:
እገኛለሁ:: ቅንጅቱ:እንደዚህ:አይነት:ፓርላማ:እንግባ:አንግባ:የሚል:debate ላይ:ፈጽሞ:ይደርሳል:ብዬ:ጠብቄም:አላውቅም:ነበር::አሁን:እጅጉን:
በጣም:ከገረማቸው:አንዷ:ነኝ::እጅጉንም:አዝኛለሁ!! ነገ:ለድሀው:ሕዝባችን:ትልቅ:ቀን:ነው:: ከሁሉ:የሚያሳዝነኝ:ይህን:ድሀ:ሕዝብ:አንዳንዶች:በሚያደርጉት:ከህሊና:ይልቅ:
ሆዳቸውን:በመከተል:የሚያደርጉት:ክፉ:ውሳኔ:ነው::እስቲ:ገና:ውሳኔውን:አላሳለፉምና:
ከዚህ:በኍላ:የቀረን:የጸሎት:ሀይል:ብቻ:ነውና: በእሱ:መትጋት:ነው::

አምላክ:ለእዛ:ድሀ;ሕዝብ:ሲል:የህዝቡን:ድምጽ:የሚያስከብር:
ውሳኔ:ለማሳለፍ:ያብቃቸው::

አክባሪህ:

እምቢ:ለጥላቻ:

ነኝ
WE ARE NOW AMBASSADORS FOR OUR BELOVED COUNTRY AND ONE DAY WE WILL BE CITIZENS IN ETHIOPIA, ONCE AGAIN!!
SAY-NO-TO-HATRED
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1354
Joined: Sat Mar 12, 2005 8:29 pm
Location: united states

Postby አባዊርቱ » Sun Oct 09, 2005 7:03 pm

የናንተን አላውቅም እንጂ, እኔ ልፈነዳ ነው....ባለፉት 24 ሰአታት ወደ 16 ታየኖል ወስጃለሁ....ስለ እውነት እላቹዋለሁ ሰው ወዶ አይደለም ለካ እየወሰደ እራሱን የሚያፈነዳው....ፍልስጤሞቹን ማለቴ ነው! የዛሬን አይኑር እንጂ በቅርብ አመት, ያገራችን ሁኔታ መልኩ ካልተለወጠ ይህ አይፈጸምም ብሎ የሚጠብቅ ይኖራል ትላላቹ??? ምን ማድረግ እንደምችል አይገባኝም...አይምሮዬን እንዳልስትና ቤተሰቤን በትኜ አንዳልቀር እሰጋለሁ...ስለ እውነት እላች ሁዋለሁ ወገኖቼ.....በጣም, በጣም የሚያሳዝን ወቅት ላይ ነው ያለነው......እባክህ አምላኬ አገራችንን አንድ በላት.....ብቻ ይቅር...

አገር ወዳድ ወገኖቼ, ምን ለማለት እንደፈለኩኝ ይገባች ሁዋል!!! እንደኔው እርርርር ያላቹ...እግዜር ይርዳን!! አምላክ በምህረቱ ይጎብኘን.....ያን መከረኛ ህዝብ አለሁልህ ይበለው...

አቤት!!!!!!!!
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests