ለብርቅየው ቴዲ አፍሮ ይድረስልን

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ለብርቅየው ቴዲ አፍሮ ይድረስልን

Postby moa » Sun Oct 09, 2005 11:54 am

ሃገራችን ካፈራቻቸው ምርጥና ተደናቂ ዘፋኞቻችን መሀከል አንዱ ቴዲ አፍሮ ነው። ቴዲ ለውዲት እናት ሃገሩ ሳንቲምና ሽንገላ ሳያሸንፈው ላመነበትና ለናት ሃገሩም ደህንነትና ትንሳኤ ሲል ያዜመውን ዜማ በናት ሃገሩ ለህዝቡ እንዳያዜም በመከልከሉ ገንዘባችህ ይቅርብኝ በሚል ወኔ ከእናት ሀገሩ ለሥራ ጉዳይ መውጣቱን ሠምተናል።

ይህ ብርቅና ውድ አርቲስታችን ለሥራ ጉዳይ በወጣበት ጊዜ የወያኔ አጫፋሪዎችና አክቲቭ ሰዎች በዚህም በዚያ ብለው ኮንተራት በመዋዋል በኖርዌ ሊያዘፍኑት እንደጨረሱና ልዩ ልዩ ፖስተሮችም እነደለጠፉ ሰምተናል።

ቴዲ ለኛ ዋልያችን ነው! ቴዲ ለኛ የነጻ አውጪ መዝሙር ደራስያችን ነው ! ቴዲ በእጅ አዙር የወያኔ ሰዎች እጅ በኖርዌ ወያኔዎች ሳያውቅ መጠለፉ ስላሳሰበን ኮንትራቱን የተፈራረመችው ሴት ቀንደኛ የህውሃት አቀንቃኝ ስትሆን በተደጋጋሚ ኖርዌ ላይ በተደረጉት ሠላማዊ ሠልፎች ላይ ሰው እንዳይወጣ ስትቀሰቅስ የነበረች ሰው ስለሆነች ቴዲ ቸግረ ውስጥ እንዳይገባ ወዳጅ ዘመድ የሆናችሁ ሁሉ ይህን ካልሰማ እንድታስታውቁት በዚህ አጋጣሚ እናሳስባለን።
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

ሳይቃጠል...

Postby ዘማች » Sun Oct 09, 2005 1:29 pm

ሰላም moa ይህ ያቀረብከው ጥሪ ወቅታዊና በጊዜ መታረም ያለበት ነው.... በቴዲ አፍሮ ዘንድ:: አዎን እሱ እመቤትን አያውቅም.... እንዲያውም አገናኝ ደላሎቹን ጭምር ላያውቅ ይችላል:: እናም አሱ በሚያቀርበው consert የሚገባው ገቢ የሕወሀት የገቢ ማግኛ አንድ ምንጭ አድርጋ ልትጠቀምበት መዘጋጀትዋን ሰምተናል:: የሚያሳዝን ነው!... እንዲያውም እሾህን በሾህ ተብሎም መተረቱን, ወግ መደረሱንም ሹክ ተብለናልና በዚያም አለ በዚህ ቴዲ ለወያኔ እርቦ ሰፋሪ አይሆንምና የሚቀርቡት ሁሉ, ይህንን የmoaን ማሳሰቢያ እንዲይሳውቁት አጥብቀን እንሳስባለን::

moa ጉዳዩ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲባል በወቅቱ በማሳሰብህ ወገናዊ ምስጋናዬ ይድረስህ.............

አክባሪህ
ዘማች
ዘማች
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 88
Joined: Wed Aug 18, 2004 7:02 pm
Location: ethiopia

Postby ራስ ንጉስ » Mon Oct 10, 2005 10:15 am

ከላይ የተሰጠው መረጃ ትክክልነቱን እኔም አረጋግጣለሁ ቴዲ አፍሮ ኦስሎ November 5,2005 ተጋብዞ የሚመጣው በTPLF ገንዘብና እዚህ ኦስሎ ባለችው የ TPLF አሽቃባጭ እመቤት(ቂጦ) በተባለች አይን አውጣ ብልጣብልጥ ስለሆነ ይህንን ድርጊት ማሳወቅ የኢትዮጵያዊነት ግዴታየ ነው ውሳኔው የራሳችሁ ነው

ተጬማሪ ማብራርያ እንዳስፈላጊነቱ ላቀርብ እችላለሁ
Etiopia Tikdem!
ራስ ንጉስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 376
Joined: Mon Dec 08, 2003 8:10 pm
Location: Jupiter

እረ በዛ አሁንስ

Postby ሞልጨው » Mon Oct 10, 2005 10:22 am

ብላችሁ ብላችሁ ደግሞ ልጁ በሙያውም ሰርቶ እንዳይበላ ላንደበቱ ሪሞት ኮንትሮል ማዘጋጀት አማራችሁ? እንዴ ቴዲ እኮ እንደናንተ አወኩ አወኩ ስላላ እንጂ ምን ማድረግ እንዳለበት የሚነገረው ሰው አይደለም! የሚያደርገውን ሁሉ ጠንቅቆ የሚያቅ ብልህ ነው! ""ኖርዌ መጥቶ የሚያሳየው የወያኔ ደጋፊ የሆነች ግለሰብ ጠርታው ነው"" እና ወያኔ ሆነ ማለት ነው? ነው እሷን ደገፈ? ነው ገቢው ለወያኔ መሆኑን በግልጽ ነግረውት ያንን አውቆ ነው የተፈራረመው ልትሉን ነው? እረ ዝም ብሎ ቅንጭብ ወሬ ይዞ ሰውን ጠልቶ ማጥላላት ባህላችን አታድርጉት! ቴዲ ምን ማድረግ እንዳለበት እሱ ያውቃል!!
selam le sew lijoch hulu
ሞልጨው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Fri Feb 11, 2005 10:36 am
Location: finland

Postby በቃ » Mon Oct 10, 2005 2:14 pm

ስማ ወንድሜ ሞልጨው... ይህ እኮ የክብር ጉዳይ ነው:: ቴዲ ያለው ሌላ አገር: እንዲዘፍን የተጠራው ወደ ሌላ አገር:: እሱ በማን እንደተጋበዘ ቢያውቅ ኖሮ ስምምነት አያደርግም ነበር:: የጋባዡ አካል ማን እንደሆነና ለማን እንደቆመ ሁኔታውን የሚያውቁት በጋሃድ በማውጣታቸው ሊመሰገኑ ይገባቸዋል እንጂ ነውር አይደለም::
በቃ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 12
Joined: Mon Aug 29, 2005 9:57 pm
Location: ethiopia

Postby ደምመላሽ » Mon Oct 10, 2005 2:36 pm

ቴዲ አፍሮ ተታለለ ማላት ወያኔ ሆነ ማለታችን አይደለም:: ነገር ግን በእርግጥ ሳያውቀው በኖርዌይ ወያኔዎች ማታለሉን በተጨባጭ ተደርሶበታል:: ቴዲ አፍሮ ራሱን ለገንዘብ የማይለውጥ መሆኑን እናውቃለን:: ሥለዚህም የኖርዌዩ ኮንሰርት ባስቸክዋይ እንደሰርዝ በአክብሮት እንጠይቃለን:: የኢትዮጵያ ደመኞች በሆኑ ግለሰቦች ወንድማችን ሲታለል እያየን ዝም ማለት አይገባንም:: ቴዲ አፍሮ እነዚህ ያአገር ጠላቶች ሲጋብዙህ እምቢ በል:: የቁርጥ ቀን ልጆች ከኖርዌይ
thank yiou for the possibility you gave us to express our views and reveal the enemies of Etiopia.
ደምመላሽ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Oct 10, 2005 1:35 pm
Location: norway

Postby አደቆርሳ » Mon Oct 10, 2005 3:03 pm

ምናልባት አባባላችሁ ያቺ እመቤት ቂጦ
የወያኔ እጅ ስለሆነች እሱዋ እንዳትሰራ ወይም ኮንሰርት እንዳታዘጋጅ መቃወም ከሆነ ትክክል ሊሆን ይችላል :ይህ ከሆነ ደሞ ቴዲ ተሸወደ ማለት
አይደለም ::በአውሮፓ የቴዲ ኮንሰርት መዘጋጀት ራሱ
ለወያኔ ራሱን የቻለ ራስ ምታት እንጂ ለቴዲ ጎጂ ጎን ያለው አይመስለኝም::
kibremengist
Image
kibremengist
አደቆርሳ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 977
Joined: Wed Aug 03, 2005 5:50 pm
Location: ethiopia

Postby በቃ » Mon Oct 10, 2005 3:27 pm

ውድ ቴዲ አጣብቂኝ ውስጥ እንዳይገባብን በቀጥታ ለግሉ መንገር ይቻል ነበር ይመስለኛል. የታዋቂ ተዋንያን አድራሻ ማግኘትም መክበድ የለበትም. ከዛም እራሱ መወሰን ይችላል. ምናልባት ይህ ጉዳይ አደባባይ ላይ ባይወጣ ይመረጥ ነበር.....
በቃ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 12
Joined: Mon Aug 29, 2005 9:57 pm
Location: ethiopia

Postby moa » Mon Oct 10, 2005 3:45 pm

አደቆርሳ wrote:ምናልባት አባባላችሁ ያቺ እመቤት ቂጦ
የወያኔ እጅ ስለሆነች እሱዋ እንዳትሰራ ወይም ኮንሰርት እንዳታዘጋጅ መቃወም ከሆነ ትክክል ሊሆን ይችላል :ይህ ከሆነ ደሞ ቴዲ ተሸወደ ማለት
አይደለም ::በአውሮፓ የቴዲ ኮንሰርት መዘጋጀት ራሱ
ለወያኔ ራሱን የቻለ ራስ ምታት እንጂ ለቴዲ ጎጂ ጎን ያለው አይመስለኝም::
kibremengist


በመጀመርያ የተቃወምነው ግለሰቧ ለማደግ በመጣጣሯ አይደለም። ይህን መቃወም የሚቻልም አይመስለኝም ። ዋናው ተቃውሞ አርቲስቱ ለሥራ በሚወጣበት ጊዜ ማን ኮንትራት እንደሰጠው በቅደሚያ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በማሰብ እንጂ የግለሰቧን የማደግ ጥረት ለማክሰም አይደለም።

ግለሰቧ ቁርኝቷ ከማን ጋር ነው? እስከዛሬ ከወያኔ ጋር ያደረገችው ጉዞ በህውሃት ወርቅ ቀለም የተጻፈላት ስለሆነች ብርቅዬ አርቲስታችንን የማዳን የዜግነት ግዴታ ስላለብን ነው ማስጠንቀቂያ ደውል የደወልነው።

ከእንግዲህ ደግሞ ዳግም ሞት መሞት ያለብን አይመስለኝም። በረቀቀ ዘዴ ተቃዋሚዎችን አዋክቦ
እየከፋፈለን ያለ መንግስትን የሚረዱ የወያኔ ውላጆችን ቦይኮት ማስደረግና በማናቸውም እንቅስቃሴያቸው ውስጥ አለመሳተፍ የጊዜው የትግል ስልት መሆን አለበት።

ቴዲ አውሮፓ መጥቶ መጫወቱ ያስደስተናል፤ያበረታታናልም! በዚህ ላይ ምንም ጥያቄ የለውም- ባስራሰባት መርፌ የጠቆመው ቁምጣ ገና ሲባል አዘፋኟ ችግር እንድታስደርስበት ስለማንፈልግ ጭምር ነው።
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

Postby የሰውልጅ » Mon Oct 10, 2005 7:36 pm

መቀባዠር ቢቀርባችሁ ምናለ!!!
እኛ የምንፈልገው የተወዳጁን ወንድማችን አርቲስታችንን ድምጽ መሥማት ነው: ደግሞስ ልጅትዋ እንክዋንስ ወያኔ ልትሆን ቀርቶ ስምዋን በደምብ ታውቀዋለች? እኔ እንደሚመሥለኝ ብር አሳዳጅ ነች እና ተዉና እንዝናናበት:
የሰውልጅ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Oct 10, 2005 12:46 pm
Location: ethiopia

ፍየል ከመድረስዋ.....

Postby ዘማች » Mon Oct 10, 2005 8:06 pm

ቅቅቅቅቅ!... ማነህ ደሞ አንተ ያዛኝ ቅቤ አንጉዋቹ?... ስትሮጥ መጥተህ የመጀመሪያ ፖስትህን ለዚህ ወያኔያዊ ፕሮጄክት መስዋእት አደረከው?... ያው የእሙዬ ደንገጡር ብትሆን እንጂ ጤናማ አእምሮ ያለህ ብትሆን ኖሮ በቴዲ የሀቅ እምባ "...እንዝናናበት!.." አትልም ነበር:: :twisted:

አዎን ወያኔያዊ ተልኮአችሁን ለማሳካት የማትፈነቅሉት ድንጋይ የለም:: ግን ግን ያምስት ዓመቱን አዲሱን የግፍና የባርነት ዘመናችሁን በቴዲ አፍሮ concert ለማክበር መቋመጣችሁ የሕልም እሩጫ ሆኖ እንደሚቀር ግን እንዳትጠራጠር!... ሱሚ ነው - በአንጡራው ኢትዮጵያዊ በቴዲ አቅንቃኝነት መደነሳችሁና የውስኪ ቅርሻታችሁን በሕዝብ ላይ ማዝረብረባችሁ!.... እናም መላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ነቅቶ ቴዲን ከናንተ አፈላማነት ይታደጋል!... ወይ ኖርዌይ... ትናንት ያንን ደም መጣጭ አለቃችሁን ሸለመች ... ዛሬ ደሞ የወያኔን ኪስ ለመሙላት ቴዲ አፍሮን አጠመደች!.... ዘይገርም አሉ ሰውዬው.... ጉድ ነው ዘንድሮ.... እነmoa በርትታችሁ ታገሉ!.... ikke gir opp i heltat!...

አባዱላ
ካገር ፍቅር ግምባር

የሰውልጅ wrote:መቀባዠር ቢቀርባችሁ ምናለ!!!
እኛ የምንፈልገው የተወዳጁን ወንድማችን አርቲስታችንን ድምጽ መሥማት ነው: ደግሞስ ልጅትዋ እንክዋንስ ወያኔ ልትሆን ቀርቶ ስምዋን በደምብ ታውቀዋለች? እኔ እንደሚመሥለኝ ብር አሳዳጅ ነች እና ተዉና እንዝናናበት:
ዘማች
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 88
Joined: Wed Aug 18, 2004 7:02 pm
Location: ethiopia

Postby አቡየ » Mon Oct 10, 2005 8:21 pm

ቴዲ ወያኔን እያሞገሰ ነው የሚዘፍነው ወይስ ያንኑ ያስተሰርያል ነው? ሲመስለኝ The sponsor has a lot of enemy to come to this website and talk nonsense here. Why don't you solve your issue there and don't bother us with your problem.
አቡየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 90
Joined: Tue Mar 15, 2005 10:17 pm
Location: united states

Postby ራስ ንጉስ » Mon Oct 10, 2005 8:36 pm

የሰው ልጅ(ጉድ)
ሴትየዋ ብዙ ሎሌዎች አሏት አንተ አንዱ ነህ በርግጠኝነት!እመቤት ቂጦ የሚገዛህ ካገኘች አንተንም አሽጣለች እመቤት የወንዟ ልጅ መለስ የያራን ጉቦ ለመቀበል እዚህ Oslo Grand Hotel አርፎ እያለ አንጣፊ ጋራጁ እንደነበርች የቅርብ ቀን ታሪክ ነው አሁን ደግሞ ቴዲ አፍሮን?
Etiopia Tikdem!
ራስ ንጉስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 376
Joined: Mon Dec 08, 2003 8:10 pm
Location: Jupiter

Postby የሰውልጅ » Mon Oct 10, 2005 8:51 pm

በለው :D !!!!!!!!!!!
ይሄውነው እንግዲህ የነ ዘራፍ ሙያ
በምታወሩበት ምላሳችሁ ብትሰሩበት ምናለ? ደሞስ ወያኔ ቅንጅት,...... እዛው ተነከሩበት
የሰውልጅ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Oct 10, 2005 12:46 pm
Location: ethiopia

አልገባኝም.....

Postby እምአእላፍ » Mon Oct 10, 2005 9:42 pm

አቶ አቡዬ አጠያየቅህ ስላልገባኝ ነው... ጎራ ማለቴ:: ከላይ አስተያየታቸውን ያስቀመጡት ወገኖች በሙሉ ስለ ግል ችግራቸው ( ከስፖንሰሯ ጋር) ሲያወሩ አላነበብኩም:: አንተ የትጋ አንብበህ እንዲህ ያለ ትጥቅ አስፈቺ አስተያየት ለመስጠት እንዳበቃህ ብትጠቁመኝ መልካም ነው:: እያሉ ያሉት ቴዲ አፍሮን የወያኔ የገቢ ማግኛ ምንጭ አድርገው ሊጠቀሙበት አይገባም መስሎኝ!.... 8)

እምአእላፍ
ከምድረ ከብድ

አቡየ wrote:ቴዲ ወያኔን እያሞገሰ ነው የሚዘፍነው ወይስ ያንኑ ያስተሰርያል ነው? ሲመስለኝ The sponsor has a lot of enemy to come to this website and talk nonsense here. Why don't you solve your issue there and don't bother us with your problem.
እምአእላፍ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 19
Joined: Mon Oct 25, 2004 4:12 pm
Location: united arab emirates

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 6 guests