የቅንጅት ምክር ቤት 8 ቅድመ ሁኔታዎች ካልተማሉ ፓርላማ እንደማይገቡ አስታወቁ::

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: እንኳን ደስ አለን...

Postby ሳም2 » Sun Oct 09, 2005 10:28 pm

KOMCHE_AMBAW wrote:ፈረንጆች እንደሚሉት...I have good news and a bad news, which one do you like to hear first?...አዎን እኔ እንኳን በለተ ሰንበት ቀርቶ ባዘቦቱም ቀን ቢሆን ጥሩ ዜና ነው መጀመሪያ መስማት የምፈልገው...ማን ያውቃል በትንሽ ማይክሮ ሰኮንድ ውስጥ ተአምር ሊፈጠር ይችላል ከሚል እምነት ነው...ቸር ወሬ ያሰማን :!:

ቆምጨ
ሰላም ቆምጨ

በአሁኑ ጊዜ የአገራችን የፖሊቲካ ሁናቴ እንኴን ለአንባቢ ለአገራችን ጋዜጠኞች ለመተንቢየት አስቸጋሪ ሆኖዋል ምክንያቱም በየጊዜው እየተለዋወጠ በሚመጣው ዜናዎች ሁላችንም ግራ አጋብቶናል

አሁን ደግሞ preconditions በማለት ተቀይሮዋል ታዲይ ይህ ጉዳይ ምንድ ነው የተገልፀ ነገር አለ ወይስ ከዚህ በፊት የተነጋገሩበትና ሊስማሙብት የሚችሉ ጉዳይ ነው ወይስ ቅንጅት ደጋፊውን ላለማስቀየም የመግቢያ ዘዴ ነው ባንቾክል ይሻላል ነገ ሌላ እዳንሰማ

ቆምጨ ምን ትላለህ
Last edited by ሳም2 on Sun Oct 09, 2005 10:31 pm, edited 1 time in total.
test
ሳም2
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Sat Aug 13, 2005 3:09 am
Location: ethiopia

ትግሉ ይቀጥላል...

Postby በቃ » Sun Oct 09, 2005 10:31 pm

ሰላም ወገኖቼ!
ቅንጅት ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጥ ይገባዋል:: ወያኔ በምንም መልኩ ባይገባውም አሁን ቅንጅት ንቅንቅ ማለት የለበትም:: የቅንጂት ቅድመ ሁኔታዎች ወሳኞች ቢሆኑም ትግሉ እንደገና ተጀመረ እንጂ ምኑም አልተነካ:: ስለዚህ እባካችሁ ወገኖቼ ደስ አለኝ ቀበርጥሴ ይቅር:: በትንሹ ደስታ ምንድነው? ትግሉ ይቀጥላል! የኢትዮጵያ ህዝብም የምንፈልገው ነፃነትን ነው:: ስለዚህ ቅንጅት እኛን በቆራጥነትና በብልሃት መምራት አለበት:: እኛ ለነፃነታችን ከቅንጂት ጎን ነን:: ቅንጂትም ከኛ ጋር ነው:: በቃ!
በቃ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 12
Joined: Mon Aug 29, 2005 9:57 pm
Location: ethiopia

በጣም አስደሳች ውሳኔ ነው! ዶ/ር ያቆብን ሰምቼ

Postby sheggaw » Sun Oct 09, 2005 10:59 pm

እኔም ትንሽ ተንፍሻለው:: ከዚህ ወዲያ ግን ቆራጥ የሆነ አመራር ያስፈልጋል አልፎም አስቸኳይ ጥሪ ለሕዝቡም ያስፈልጋል:: ሌላው ዜና ደግሞ ባለፉት 4-5 ቀናት ውስጥ አንዳንድ ረባሽ ዜና እንደ ዶ/ር ብርሃኑ ቅንጅትን ሊበትኑት ነው የሚባለውን ወሬ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ውሸት እንደሆነ የዛሬው ቴሌ ኮንፍረንስ ላይ ተገልጾልናል...
ባለንበት ሁሉ ይሚቻለንን ለማድረግ ሁላችንም መትጋት አለብን....
አሁንም ለሚመለከተን ዓለምም ድምጻችንን ማሰማት አለብን...
አንድ ኢትዮጵያ ለዘለዓለም!
sheggaw
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Sun May 15, 2005 10:43 pm
Location: azerbaijan

እንካን: ደስ: አለን:

Postby እለተ » Mon Oct 10, 2005 12:46 am

በእውነቱ: እዪን: ጭንቅ: ቀን: ሰንበት: ጥሩ: ወሪ: ስላሰማን: ለሰንበት: ሰንበት:: ይስተው:: በመሰረቱ: ውድ: ወገኖቺ: በመሪዎቻችን: የሰከነ: አመራር: እጅግ: እንደኮራችሁ: ይሰማኝአል:: ነገር: ግን if weyane didn' accept(decline) the preconditions, what's the next step should be?

ወገኖቺ: በመሰረቱ: መልሱ: እጅግ: ቀላል: ነው:: እና: ውድ: ወገኖቺ: ከአሁን: በሁዋላ: የመሪዎቻችንን: የሰከነ: አመራር: በንቃት: ትከታተል: ዘንድ: በዚህ: አጋታሚ: እገልጽልሀለው: ትግሉ: ተጀመረ: እንጂ: አላለቀም: ዋናው: ትግል: ያለው: ከአሁን: በሀላ: ያለው: ነው:: መሪዎችም: መዘናጋቱን: ትታችሁ: እዝቡን: ሀሳባችሁን: በአስቸኮአይ: ለህዝቡ: አሳውቁ:: በርቱ: ተበራቱ: እግዚአብሂር: ከእናንተ: ጋር: ይሁን: አሚን::
እለተ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Thu Feb 03, 2005 4:20 am
Location: united states

Re: እንካን: ደስ: አለን: የአነ መረራና በየነን ጉድ አዩ

Postby ጌንዶ » Mon Oct 10, 2005 1:22 am

የበየነና የመረራ ጉድ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Majority MPs registered for inaugural conference
Addis Ababa, October 09,2005 (WIC)- Registration of MPs who would attend the inaugural conference of the House of Peoples Representatives has reportedly been underway up until today.

According to the Information and Public Relations Department of the HPR, 44 members of the UEDF, including the leaders Dr. Beyene Petros and Dr. Merea Gudaina, and six CUD members were registered.

Also were registered 10 members of the Oromo Federalist Democratic Movement, it said.

It is to be recalled that the ruling party EPRDF has won 327 seats in the HPR, while the CUD secured 109 seats and UEDF 52. The Somali People Democratic Pary won 24 seats and OFDM 11 seats.እለተ wrote:በእውነቱ: እዪን: ጭንቅ: ቀን: ሰንበት: ጥሩ: ወሪ: ስላሰማን: ለሰንበት: ሰንበት:: ይስተው:: በመሰረቱ: ውድ: ወገኖቺ: በመሪዎቻችን: የሰከነ: አመራር: እጅግ: እንደኮራችሁ: ይሰማኝአል:: ነገር: ግን if weyane didn' accept(decline) the preconditions, what's the next step should be?

ወገኖቺ: በመሰረቱ: መልሱ: እጅግ: ቀላል: ነው:: እና: ውድ: ወገኖቺ: ከአሁን: በሁዋላ: የመሪዎቻችንን: የሰከነ: አመራር: በንቃት: ትከታተል: ዘንድ: በዚህ: አጋታሚ: እገልጽልሀለው: ትግሉ: ተጀመረ: እንጂ: አላለቀም: ዋናው: ትግል: ያለው: ከአሁን: በሀላ: ያለው: ነው:: መሪዎችም: መዘናጋቱን: ትታችሁ: እዝቡን: ሀሳባችሁን: በአስቸኮአይ: ለህዝቡ: አሳውቁ:: በርቱ: ተበራቱ: እግዚአብሂር: ከእናንተ: ጋር: ይሁን: አሚን::
ጌንዶ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Fri Dec 31, 2004 11:03 pm
Location: united states

Postby አባዊርቱ » Mon Oct 10, 2005 6:34 am

ሳም 2 ትልቅ ነጥብ ነው ያስቀመጥከው!

8 ቱን ፕረኮንዲሽኖች ለተመለከተ ወያኔ ቀና ብሎ የሚያስበውን መልስና ቃል ኪዳን ከገባ ሊገቡ ነው ማለት ነው?? ምኑ ነው 8ቱ ነጥቦች ትልቅ ቁምነገር የሆኑት?? ነገ ጉድ ይታያል......እልልል ባለ አፌ እወይይይይይ እንዳልል ነው የፈራሁት! ይቅርታ አድርጉልኝና ምኑም አላማረኝም.....ከዚህ ድራሼ ቢጠፋ ሌላው ቢቀር ለቤተሰቤ እሆን ይሆናል......

እግዜር ሁላቹንም ባላች ሁበት ይጠብቃቹ!
ጭራሹን አልመለስም ብዬ እራሴን አላታልልልም, የነገ ሰው ግን ይበለን!

ኤታማዦሩ ነኝ,
ሰሞኑን ናላው የዞረው!
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

ወንድም አባዊርቱ ተበራታ!

Postby moa » Mon Oct 10, 2005 10:47 am

[quote="አባዊርቱ"]ሳም 2 ትልቅ ነጥብ ነው ያስቀመጥከው!

8 ቱን ፕረኮንዲሽኖች ለተመለከተ ወያኔ ቀና ብሎ የሚያስበውን መልስና ቃል ኪዳን ከገባ ሊገቡ ነው ማለት ነው?? ምኑ ነው 8ቱ ነጥቦች ትልቅ ቁምነገር የሆኑት?? ነገ ጉድ ይታያል......እልልል ባለ አፌ እወይይይይይ እንዳልል ነው የፈራሁት! ይቅርታ አድርጉልኝና ምኑም አላማረኝም.....ከዚህ ድራሼ ቢጠፋ ሌላው ቢቀር ለቤተሰቤ እሆን ይሆናል......

ይገባኛል ጭንቀትህ!
እንገዲህ ምን ይደረጋል የቤታችንን ገበና እነደገና ፈትሸን በቀረችው ትንሽ ፍርፋሪ የቅንጅትን ወኔ ከማጠናከር ሌላ! በሰሞኑ ክርክር በቆራጥነት የታገሉትን የቅንጅት አባቶቻችንን እያጠናከርን አዳዲስ ኮብራ ለመንዳት የተራወጡትን ወጣት ቅንጀቶች ደግሞ መንፈላሰሻው ሜዳውም ሆነ አስፋልቱ የሚመቸው በህዝብ በታጀበ አጀብ እንጂ በወያኔ ጀሌዎች እንዳልሆነ አስረግጦ ከመናገር ሌላ የምንለው ሌላ ነገር የለም።

እኔ የሚያስፈራኝ አንድ ነገር ብቻ ነው! ይህ ትግል ከተኮላሸ ከእንግዲህ ይህን ወጣት ትውልድ ለሌላ ትግል ለማዘጋጀት ቢያንስ ሌላ 15 አመት ይፈጃል።

ዛሬ በሚከፈተው ፓርላማ ሁለቱን ዶክተሮች ጨምሮ ከቅንጅትም ስድስት ሰዎች ፓርላማ ለመግባት እንደተመዘገቡ ሰምተናል፡ ምናልባት የዶክተር መረራ ምክንያት ጊዜ ካሳየን ታክቲክ ሊሆን ይችላል፡ምክንያቱም በነ አልማዝ ሰይፉ ኩዴታዊ ፓርላማም እንደሚካሄድ ስለሚያውቁ ሊሆን ይችላል የዶክተር በየነ ግን የስልጣን ጥማት እንደሆን የተወቀ ነው፡ዶክተሩን በተለያየ አጋጣሚ አግኝቻቸው ተወያይተን እናውቃለን።ከአራት አመት በፊት ለምን የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች እርስ በርሳችሁ ትጠላለፋላችሁ ብዬ ብጠይቃቸው እኔ ካስር አመት በላይ ስታገል የነበርኩ ሰው ነኝ ትላንት ከመጣ ጎረምሳ ጋር የምነጋገርበት ምክንያት የለም ያሉኝን ሳስታውስ ሰውየው ምን እንደሆኑ ያኔ ነው ያወቅሁት፡ ጎረምሳ ያሉት ልደቱን መሆኑ ነው።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ፕሮፌሰር መስፍን፤ ዶክተር ያቆብ፤አቶ ሃይሉ ሻውል የሚሉትን እኔም ጎረምሶቹ ልበል የቅንጅት ወጣቶች ቢሰሙ ኖሮ እንደዚህ ያለ ቅሌት ውስጥ አይገባም ነበር።
አሁንም አልመሸም! ፓርላማ ለመግባት የሚቋምጡት ይግቡ የወላወሉ ሰአትና ጊዜ ይሰጣቸውን ቶሎ ይወስኑ- የፈረጠሙትን ይዘን ምን በቀጣይ እንደሚሠራ እየተመካከርን ትግሉ ይቀጥል።
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: እእንፌቃ and 6 guests