ዶክተር መራራ በህዝብ ደም ቀለዱ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ዶክተር መራራ በህዝብ ደም ቀለዱ

Postby ናይክ » Sun Oct 09, 2005 8:51 pm

ትላንት የፈሰሰው የወንድሞቻችን ደም ሳይደርቅ ዶክተር መራራ ለ ወያኔ የፓርላማ አሻንጉሊት ለመሆን ብሎም ከወያኔ የስልጣን ፍርፋሪ ይወድቅልኛል ብለው በማሰብ የደረሱበት ውሳኔ የታሪክ ቅሌታም ያሰኛቸዋል ብሎም ያስጠይቃቸዋል::

ዶክተሩ በወንድሞቻችን ደም ቀለዱበት::

አሳዘኝ ትልቅ የታሪክ ቅሌት !!!!!!!!

ብራቮ ቅንጅት!!!
Senef Gebere Be sene yemotal !!!!
ናይክ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Sep 23, 2004 6:11 pm
Location: united states

Postby ዳንዲ » Sun Oct 09, 2005 10:16 pm

ሰዎች አትሳሳቱ ነገሩ ፖለቲካ መሆኑን አንርሳ::
የሚያዋጣውን ደግሞ ሰው ገምቶ አስልቶ ብወስን ዬቱ ጋ ነው አጥያት::
ዳንዲ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Sat Sep 04, 2004 12:32 am
Location: united states

ወገኖች ዝም ብላችሁ አትፍረዱ ዶ/ር መራራ በጭቃ እሾኮችና ከሀዲዎች ተከበዋል!

Postby ዲጎኔ » Sun Oct 09, 2005 10:54 pm

እባካችሁ ወገኖች በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ አትፍረዱ አብዛኛው የድርጅታቸው አባላት ከሀዲና የቅውስጥ እሾክ ስለሆኑባቸው የድርጅቱን ህልውና ለመወሰን መግባታቸው ታክቲክ ነው ይህ ደግሞ ከወያኔጋር ማበር አይደለም::

እንኩዋን የአንድ ዘርና ጎሳ ተወካይ ነኝ በሚል ድርጅት ቀርቶ ህብረብሄራዊና ኢትዮጵያዊ ስያሜ ያለው የቅንጅትም ግማሽ ያህል አባላትኮ ፓርላማ መግባቱን መርጠው ነበር ግን በኢንጂነር ሀይሉ የበሰለ ቆራጥ አመራራ ከሽፏል::

ኦብኮ ግን እንደ አልማዝ ሰይፉ ተስፋዬ ቶሎስና ሌሎች ለስልጣን የቆመጡ ስብስብ በጠባባ የጎሳ አመለካከት የታወሩ ስላሉበት ዶ/ር መራራ ብቻቸውን አልገባም ቢሉ ወያኔ ሰራሽ የሆነው የኦብኮ ኩዴታ ተግባራዊ ይሆን ነበር::ለሁሉም ነገን አይተን ግምገማችንን እናቅርብ::

ድል ለኢትዮጵያዊያን የዲሞክራሲና የአንድነት ትግል!
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

የዶክተር መረራ ነገር ያሳዝናል ግን......

Postby ብሔረ አራዳ » Mon Oct 10, 2005 11:46 am

ወንድሞቼና እህቶቼ የብዙዎቻችሁ ቆሽት እንደደበነ የሚያረጋግጥ ሐኪም አያሽም:: ግልጽ ነውና:: ዶክተር መረራ ያሉበት አጣብቂኝ እጅግ ከባድ ነው:: ባይገቡስ? ባይገቡ ድርጅታቸው (ኦብኮ) ለወያኔ አሻንጉሊቶች ሊሰጥባቸው ሆነ:: ይሁን ብለው የሚተውትም ጉዳይ አይደለም:: ካለፓርቲ ሊቀሩ ሆነ:: ያ ደግሞ ለብዙ የወያኔ ጥቃት ያጋልጣቸዋልና ቀላል ጉዳይ አይደለም የገጠማቸውና አለመፍረድ ነው ባይ ነኝ:: ይልቁንም የፓርላሜንት ዓባል መብት (ኢምውኒቲ) ከሠራ ወጣ ገባ እያሉ ገንቢ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉና ሳያስቡበት የቀሩ አይመስለኝም:: ሳያስገርም የሚገርመኝ የዚያኛው ዶክተር ነገር ነው:: የበየነ ጴጥሮስን ማለቴ ነው:: ካወቅኩት ጀምሮ እንዲሁ ጅራቱን እንደቆላ ቀሎ መኖሩ ነው:: ምን ሆንኩ ሊል ይሆን? የኢትዮጵያ አምላክ ቅንጅትን ስለሰጠን ተመስገን እያልን እነሱ እፍልሚያው ግንባር (ቀጠና) ላይ መሆናቸውን ተረድተን የምንችለውን ሁሉ ከቁሳቁስ እስከ ሞራል ድጋፍ ማቀበል እንዳለብን ልንዘነጋው አይገባም:: ደስ አለን ስንል ያንን ደስታ በሆነ ነገር አጀብ አድርገን እነሱም ወገን አለን እንዲሉ ማድረግ ይጠበቅብናል:: ሌላ ግን ያልገባኝን ነገር ሳልጠይቅ መሰናበት አልሻምና የምታውቁ እስቲ አንድ በሉ:: ህብረቱ እንግባና አንግባ በሚለው ቡድን መካከል ክርክር ተደርጎ አንግባ የሚለው 7 ለ 6 አሸነፈ ተብሏል:: ታድያ የተሸነፈው የስድስቶቹ ድምጽ ለምን ተቀባይነት አገኘ? ወይስ ደንቡ (simple majority) ሳይሆን the winner takes it all የሚሉት ነገር ነው? ተሸናፊው አሸናፊ ሆኖ የሚገባበት ስልት የወያኔ ብቻ መስሎኝ ነበር ተሳስቻለሁ ማለት ነው? ዉይ!! እንኳን የሕብረቱ ደጋፊ አልሆንኩ:: ደግሞ ህብረት ይባልልኛል:: እየዋለ ሳስበው ከመግባታቸው ይልቅ የአናሳዎቹ ድምጽ ክብደት ማግኘቱ ደነቀኝ:: ከ13ቱ (14 ነን ሲሉ ነበር!) የፓርላማ ድምጽ ያገኙት በሙሉ እንግባ ብለው ገብተዋል:: ምንም ድምጽ ያላገኙት እንደ ኢሕአፓ አይነቶቹ አንገባም ብለዋል ማለት ነው::
ሠላምና ብልጽግና በቅንጅት ይገኛል!
ሰላም ሁኑ
ብሔረ አራዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 39
Joined: Wed May 04, 2005 5:43 am
Location: ethiopia

Postby አቡዬ » Mon Oct 10, 2005 9:46 pm

ወገኖች እስኪ እንረጋጋ ዶ/ር መራራ እራሳቸው ናቸው ፓርላማ አንገባም ሲሉ የነበሩት አይደል አሁን ሊገቡ የተገደዱበት ምክንያት ሊኖራቸው ይችላልና በግብታዊነት ከምንፈርጃቸው ለምንና እንዴት እንደሆነ እስከምናውቅ ድረስ እንረጋጋ ወያኔ አንጃ ከራሳቸው ከኦፕኮ የፈጠረው ምናልባት ወደፓርላማ እንዲገቡ ለማስገደድ ሳይሆን አይቀርም ስለዚህ አይዞን ትግሉ እንደሆነ የቀዘቀዘ ቢመስልም የተዳፈነ እሳት እንጂየጠፋ አይደለም
አቡዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 240
Joined: Tue Jan 06, 2004 6:17 pm
Location: united states

ዶ/ር: መረራ ጉዲና ወደ ፓርላሜንት

Postby ልጁነኝ1 » Mon Oct 10, 2005 10:05 pm

አዎ: ዶክተሩ ውጪ ማለትም አሜሪካ ባይሄዱ ኖሮ በዚያን ወቅት ድርጅታቸውን ሩ አድርገው መምከር ማበርታትና በመሪነት መሰለፍ ይችሉ ነበር::

ነገር ቢበዛ ዋጋ የለውም:: ለወደፊቱስ በምን ሁኔታ ነው ፓርቲያቸው ሊጠናከር የሚችለው? ዶክተሩ ጥሩ የህግ አማካሪዎች ያሏቸው ይመስለኛል:: እነኛን ሊያዳምጡ ይገባል እላለሁ::

አንዴ ገብተዋል ይቀጥሉ ግን ብቻቸውን ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ መወሰን አይኖርባቸውም:: አሁንም ሳይገቡ ያሉትን ተቃዋሚዎችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብን በመንፈሳቸው ሊያስቡ ይገባል::

ወያኔ ህወኃት አጤ በጉልበቱ መለሠ ዜናዊም በብልጥነቱ ዙፋኑን ለ5 ዓመት ጫንኩ ብሏል:: ትክክል ወይም ትክክል ያለመሆኑን የሱን መንፈስ የሚወዳደር አዲስና የረቀቀ ትግል በፓርቲዎቹ ደረጃ ሳይሆን በህዝብ ፍላጎት ይቀጥላል:: ይህም የሚሆነው በባለ 5 ነጥቡ የአይጋና የኢሮብ ቀጥሎም የዛለአንበሣ ዙሪያና የመከረኛዋ የባድመ ሶስት አቅጣጫ ያላት ቦታን ለሻቢያ የሚሰጠውን ህግ አርቆ ምክር ቤት ሲያመጣ!!!

የወያኔው ተመራጭ ጭምር በመለሰ መላጣው ጭንቅላት ላይ ዘለው እንደነብር ይገሸልጡታል:: ይህም አንድ ምሣሌ ለመስጠት እሞክራለሁ ይቅርታ ይደረግልኝና:: " ወንድ አታውቂ ገልበሽ ታላዬሽ" ይባላል:: በተለይ ከትግራይ ህዝብ ጋራ የሚኖረው ግብ ግብ ከዚያች ሰዓት ጀምሮ የሚያታይ ይሆናል::

መለሰ እንዲህ ያልተዝናናቺብን ያህል ቁፍ ያለች ዶሮ ትመስልና የምትሄድበት የምትበርበት መላው ይጠፋትና በአንድ ባልታሰበ ወንድ ወይም ሴት ትማረካለች በቃ ኃይሏና ሥልጣኗ አይነጥላዋ ሁላ በረረ:: አከተመም:: ከዚያም የወያኔ ሳይሆን የህወኃት አመራር አሁንም ገዳይ ኮማንዶ ወደ ትግራይ ከደቡብ ወይም ከኦሮምያ እያነሳ ትግሪኛ መናገር የማይቺሉትን ወታደሮቹን ይልክባቸዋል::

በዚህ መኃከል ሻቢያዋ ደግሞ በተራዋ ለ2ኛ ጊዜ ያነሳኌቸውን መንደሮች ሁሉ ትወራለች:: በቃ አለቀ ደቀቀ ነገሮች እንዲያ እያሉ ይቀጥላሉ:: መቸስ ሲመጣ እንደዘበት ስለሆነ ጉድ ፈላ "የሰሎሞንን ዘፈን ያኔ መስማት ማዳመጥ ብቻ ይሆናል" ለዛሬው ግን ማንም ተነስቶ ሰራንላቸው እያለ ሊያሾፍ ይቺላል:: በመሐልና ደቡብና ምሥራቅ ም ዕራብ ኢትዮጵያ በሙሉ ከህወሃት ለመላቀቅ ታላቅና እስከዛሬም ተደርጎ የማያውቅ ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ መዓበል ይካሄዳሉ::

በመቀጠልም ዳር እስከ ዳር ቢያንስ የ3ሣምንት የሚዘልቅ ሥራ ላለመሥራት ት/ቤትም ላለመሔድ ሁሉም ርጭ ያለች ደሴት ይመስላል:: ባጠቃላይ ጉድ ፈላ በቃ ሻቢያ መጣ ትግራይ ራሷ አመጸች ወይንና ህወኃት ምን ይውጣቸዋል:: ነገሩ እንዲያው ዝም እንዲያው ዝም ብቻ ይሆናል::

በዚያን ወቅት ግን ሻቢያ እድል አገኘሁ ብላ ጉራዋን ነፍታ ብትመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ህዝባዊ መዓበሉን ከጥሩ ወንድነትና ጀግና ሴት እህቶችቹና ልጆቹ ጋር ሆኖ አር ባዕተ አስድመራ ከገዛ ባንዳጢሊያን ጀምሮ በቁጥጥሩ ስር ማድረግና ምጽዋ አሰብ አዶሊስን በመዳፉ ተደርገው ከውጪ እንደራደር ብለው ለሚጠይቁ የሻቢያ ምንደኞች ምናልባት በጉዳይ አስፈጻሚዎች በኩል በውጪ የሚገኙት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ጋራ ውይይት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፈቅዳል::

እስከዚያ እንግዲህ ኢትዮጵያ ከአሰብ እስከ ቃሩራና ብሎም እስከ አሊጊ´ኢርና ተላታአሸር -ከተላታ አሸር እስከ ሞያሌና ሩዶርፍ ሐይቅ ድረስ ከዚያም ሁምመራን ይዘህ እስከ ፌርፌርና ዶሎ ያለውን ወሰኑን ከማስጠበቁም በላይ ዳህላክ ላይ ፈጣን የሔሊኮፕተርና ፈጣን ጄቶች ይመድብና የተሰደዱትን የባህር ኃይሎች በ48 ሰዓታት ውስጥ ከቴክሳስ ከዩጋንዳና ጅቡቲ እንዲሁም የመን ከሌላውም አገርች ያስመጣቸዋል ማዕረጋቸውን አጥልቀው በተገኘው የባህር ኃይሉ ጀልባዎች ድንበራቸውን ያስከብራሉ:: ዋና መምሪያቸውንም አሰብ ላይ ያደርጋሉ::

ያንን ይመስላል የመለሰ ዜናዊ ከኢትዮጵያ ጭንቅላት ላይ መወገድ የሚሰጠው ተስፋ ኤርትራ ወላ እንደዚህ የሚባል የለም አንድ ህዝብና አንድም ደምና ዓላማ ያለን ህዝብ ነን ማንም የበላይ ማንም የበታች አይኖርም ሁሉም በቺሎታው ሰርቶ እንደ እውቀቱ የሚያድር ይሆናል:: ከዚያ በኌላ በኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ ሌላውን ወንድሙን አይገልም:: ታላቅ የሆነ የመማማር ጉባኤ በሁሉም አቅጣጫ ይካሄዳል:: ተግለሰብ ነጻነት እስከ ህዋሳቶቾና የዱር የቤት አራዊቶቿ ድረስ መብታቸው የሚጠበቅባት አገረ ኢትዮጵያ የሁላቺንም ሁና በደስታ እየሰራን እኖራለን::

*ቀይ ባህር ዳር ድንበራቺን ነው*

ኢትዮጵያ ትቅደም::

ጠላቶቿ ሁሉ ይውደሙ:: አሜን...አሜን...አሜን::

ልጁነኝ1
ከ(ሰሐሊን)
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states

መፍረድ ጥሩ አልመስለኝም

Postby ayelgn » Mon Oct 10, 2005 10:36 pm

በመጀመሪያ ዶከተሩ በሌሉበት ድርጅታቸውን ዘረፉቸው:: ያላቸው Alternative ገብተው በዘዴ ማስመለስ ይመስለኛል::
In the mean time የቅንጅት ፓርላማ አለመግባት በጣም ያስደስታል:: በድርድሩ ያጠፉትን አካክሰዋል::

አየልኝ
ayelgn
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Mon Oct 10, 2005 9:33 pm
Location: ethiopia

በዶክተሩ አትፍረዱ!!

Postby Temamen » Wed Oct 12, 2005 9:40 am

አልማዝን በመሰለች ከሀዲና ያጉቦ ገቢው የቀጠነበት ትራፊክ በመሰሉ "ሆድአደሮች" ተከቦ ድርጅቱን ከኩዴታ ለመታደግ ምን ያድርግ?

"የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ" ፖለቲካ ውስጥ አይሰራም:: ያልተያዘ ግልግል ያውቃል ነዉ ነገሩ::

ቅንጅትን ግን ብራቮ ልንለው ይገባል:: ህብረት ከሰሞኑ የፖለቲካ ክስተት ጥሩ ትምህርት እንደቀሰመ ተስፋ አደርጋለሁ::

ቸር ያሰማን!!
Temamen
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Tue Oct 04, 2005 9:13 am
Location: ethiopia

Postby ናይክ » Fri Oct 14, 2005 4:42 pm

እድሜ ልካቸውን ከወያኔ መንግስት የስልጣን ፍርፋሪ በሰላም ለመቀበል ሲደክሙ ሳያቸው እነ ዶ/ር በየነን በጣም ይገርመኛል::

እንዴት የሰውልጅ ካለፉት አመታቶች የወያኔን ማንነት መረዳት እና ማወቅ ያቅተዋል???

ዶ/ር መራራም ሆኑ ዶ/ር በየነ ምን ጥሩ ነገር ጠብቀው ነበር ወደ ወያኔ ፓርላማ ዘው ብለው የገቡት ??? ወርቅ አንጥፎ ወይንስ አልማዝ ???

እንደነ መለስ አይነት ነብሰገዳይ አረመኔዎች ስልጣን በጉልበት ይዘው በተፈናጠጡበት አገር ላይ ፓርላማ ገብቶ በቲቪ መስኮት ሲያዛጉ ከመታየት ብሎም ባገሪቱዋላይ ለሚፈሰው ደም አብሮ ተጠያቂ ከመሆን እንደ ቅንጅት መሪዎች አርቆ አስተዋይ መሆን ይበጃል::

Mእልካሙን ለናንተ!!!

ሞት ለወያኔ ባንዳ ነብሰ ገዳዬች !!
Senef Gebere Be sene yemotal !!!!
ናይክ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Sep 23, 2004 6:11 pm
Location: united states


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests