የተቃዋሚ ድርጅት መሪወችን በቁጥር መጨመር የግድ ይሆናል :

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የተቃዋሚ ድርጅት መሪወችን በቁጥር መጨመር የግድ ይሆናል :

Postby ይገርማል » Mon Oct 10, 2005 7:29 pm

እጅግ ብዙወቻችን በሁኔታወች በጣም እያዝን ነው ግን መሆን የለበትም ::
ይልቁንም ይህን መከረኛ ህዝብ በበለጠ ለመርዳትና በተቻለም መጠን የተጣለበትን ቀንበር ለማንሳት ከመቸውም የበለጠ ባንድነት ቆርጠን የምንንሰባት ወቅት አሁን ብቻ ነው ::
ይህ ካልሆነ አሁንም የሚጠቀመው ያው ሻቢያ - ወያኔ ነው ::

ባሁኑ ወቅት ወያኔ በተቃዋሚ መሪወች ላይ የማሰር ተግባሩን ሊፈጽም ተዘጋጅቶ ጨርሷል :
በዚህ ወቅት የግድ መሆን ያለበት የተቃዋሚ መሪወችን በደረጃ እጅግ ጠለቅ ያለና በጣም የተወሳሰበ የስልጣን አዋርድ ያስፈልጋል ይህ ካልሆነ ወያኔ ነገ እነዚህን የህዝብ ተስፋወች አስሮ ድላችንን በተልይም እነሱ እዚህ ያደረሱትን ድል ማስቀማት ነው ::
ይህ ማለት ወያኔ መሪወቹን ሲያስር በስራቸው መሪ መከተል ያስፈልጋል ::
ትግሉ እጅግ በጠነከረ መልኩ መቀጠል አለበት አሁን በውጩ አለምም ይህን የሚያጠናክር ሂደት እየትካሄድ ሊሆን ይገባል : አስፈላጋሚ ሲሆን በውጭ የምንገኝ ሰወች እነዚህ ሰወች ሲታሰሩ እነሱን ለመተካት ባንችል አብረን ለመታሰር ወደ ሀገራችን ማምራት የግድ ይሆንብናል ::
ለዚህ ደግሞ ማንም ምክንያት መፈለግ የለበትም ::

በተጨማሪም ባሁኑ ስአት በዛሬው ምሽት በአያልሰው ጎበዜ ታዛዥነት ወጣቶች ባስቸኴይ እይታፍሱና እንዲታሰሩ በጎንደር : በጎጃም : በወሎ አስቸኴ ትዛዝ ደርሶታል :

በተጨማሪም በነዚህ አካባቢ የተመረጡት ተመራጮች በሙሉ ወደ እስር ቤት ባስቸኴይ እንዲገቡ ታዝዟል ::

ውድ ኢትዮጵያውያን እስከ አሁን እንደተነጋገርነው ይህን የህዝብ አመጽ ባሁኑ ወቅት በተቻለን አቅም መርዳትና መታገል ብሎም ለድል ማብቃት አለብን ::
አለባልዚያ ግን በዚች ባንድ አመት ውስጥ ባገራች የወጣት ዘር ቀርቶ ህዝባችንን ጨርሰን እምናጣበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው ::

ሰላሙን ላገራችንና ለድሀ ህዝባችን እመኛለሁ !!
ይገርማል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Thu Nov 13, 2003 12:10 pm

Postby ETLOVE » Tue Oct 11, 2005 2:21 am

ባንድነት ቆርጠን የሚለው አማርኛ መች ሰራ ::

በአመጽ የሚመጣ መንግስት አይጠቅመንም በዚህ እንስማማ ስለዚህ ያለውን ደሞክራሲ እየተተቀምን
እያስተካከልነው አገራችንን እናሳድግ::

አሁን እየሰራን ያለነው ላረጁት ላፈጁት የደርግ ሰው በላ ሽማግለዎች ነውግን መስራት ያለብን ነገ ለሚመጣው ትውልድ መሆን አለበት::

የምንፈልገው እጁ ከደም የነጻ ወጣት ትውልድ ነው እንጅ ለደርግ ሽማግለዎች መሆን የለበትም::

ኢህአደግንም ማውረድ ያስፈለገበት ምክንያት እነዚህኑ ግለሰቦች ከመሞታቸው በፊት ስልጣን ለማስያዝ ነው ይታሰብበት::

ለአገር የሚጠቅመው የሰናፍጭ ቅንጣት የምታክለዋንም ዲሞክራሲ በአግባቡ መጠቀም ነው::

ሰላም ኢትዮጵያ አገራችን

መለስ ዘናዊ እንካን ደስ አለህ
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

Postby አባዊርቱ » Tue Oct 11, 2005 4:43 am

[quote="ETLOVE"]ባንድነት ቆርጠን የሚለው አማርኛ መች ሰራ ::


==========================
የለም, ባንዳነት የሚለው ትግርኛ ወይም ኤርትሮስኛ ነው ታዲያ የሚሰራው?? እረ ዋርካዎች, ይህንን መረን የተለቀቀ ውሻ ያዙልን!
ለጥቂት ቀናት አዘን እንጂ, አንተ ገንቦ እራስ እንደጠበከው የሞትን መስሎሀል! ተልካሻ ዱር አዳሪ ሁላ! መስሎሻል ገባጢት አሉ! ለጊዜው ጨፍር, ግድ የለም,,,, ይህ ከበሮ መደለቅ ለነገ አይመችም,,,ይህንን ደግሞ ጻፈው....ለነገሩ ጽህፈት ብትችል አይደል! ለጉዱ ይህን ያህል ዲቤ የሚያስደልቅ ነገር ምን ተገኘ?? ትግሉ እኮ አልሞተም,,,ማን ይሙት ኢትዮጵያዊ አንጀቱ እንዲህ እንዳረረ ቁጭ ብሎ አገር ስትበተንና ስትመነዘር ቁጭ ብሎ ያያል ከሆነ በጣም ተሳስተሀል.......አይ ነገን አለማወቅ!!
አይ ኢትዮላቭ አያ! ተሰምቶልኛል.....እውነቱን ተናግረህ እመሸበት ብታድር ጥሩ ነበር....ኤርትሮላቭ እያልክ!!

ውዳቂ ወያኔ
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

Postby ይገርማል » Tue Oct 11, 2005 10:14 am

ETLOVE wrote::

መልከ ጥፉን በስም ምን ይሉ ነው ይላሉ ያገሬ ሰወች ::

----
ወንድሜ አባዊርቱ ምናለበት እንዚህን የድብቅ አጥሮች መልስ መስጠታችሁን ትታችሁ በቁም ነገር ላይ ሀሳብ ብትሰጡ::

----------------------------
ባሁኑ ወቅት የህዝባችን ትግል እጅግ ከመቸውም በበለጠ ተጋግሎ ይገኛል:
ህዝባችን አንድ ጊዜ ቆርጦ እስከሚነሳ ብዙ ማስብና ማገናዘን የሚያውቅ ታላቅ ህዝብ ነው ይሁን እንጂ ከተነሳ ደግሞ የሻቢያ - ወያኔ አፈሙዝ ቀርቶ የባዳን መርዝ ወደ ኌላ አልመለሰውም ይህም ነው ለሻቢያ - ወያኔ አለቆችና ለነሱም እንቅልፍ ነስቶ እያሰቃያቸው የሚገኘው :
ቀደም ብየ እንደተናገርኩት ይህ ታላቅ ህዝባችን የማነንም ጥሪ ና ውጣ ተሰለፍ ና አልቅስ የሚለው አያስፈልገውም ይሁን እንጂ እራሱ የመረጣቸው በፊቱ ተሰልፈው ታግለን እናታግልህ ሲሉት ግን ያምናል ይከተላልም : ይህን የሚያደርግ ከሌለ ደግሞ በራሱ አነሳሽነት ተነስቶ የፈለገውን ውስኔ መውሰድ የሚችል ታላቅ ህዝብ መሆኑን ማንም ሊያውቅ ይገባል ::
ሻቢያ - ወያኔን አለቆቻቸው ወደ ስልጣን ሲአመጡአቸው የመከላከያ ሀይሉን በትነው ዝም በመባላቸው የህዝባችንን ድክመት ሳይሆን የህዝባችን አርቆ አሳቢነት ብቻ ሰላም እንዳደረገው ማንም ሊገነዘብ ይገባል ::
ይህ መከረኛ ህዝባችን በየትኛውም አለም እንደሚታየው የሚበረከክ ህዝብ እንዳልሆነም የሩቅ ጠላቶቻችን ሊገነዘቡት ይገባል ብየ አምናለሁ ::
የህዝባችን ጥሪ አንድ ብቻ ነው በዛሬው እለት በዚህ ወሮበላ ካድሪ የሚደርስበት ድብደባና በወጣቶቹ ላይ የሚደርሰው ግፍ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊቆም ይገባል :
ወያኔ የሰበሰበው እድር የህዝባችን እድር አይደለም በዚህም መሰረት በዚህ እድር ውስጥ ያለ ሁሉ የህዝብ ውክልና ሳይሆን ያለው የወያኔ ካድሪነት ነው ይህን ቀደም ብሎም ያወቀው ይመስለኛል:
ይሁን እንጂ አሁንም እኔ በበኩሌ እንደ ረዳት ፕሮፌሰር መራራ ያሉ ሰወች ቢአንስ ለተወሰኑ ቀናት ልንታገሳቸውና የሚደርሱበትን ውሳኔ ልናይ ይገባናል የሚል ነው : ይህ ማለት በዚህ እድር ላይ የመናገር እድሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያገኙ የሚሉትን መስማት ያስፈልጋል ብየ አምናለሁ : ከዚህያች ደቂቃ ጀመሮ ሰውየው ውሳኔውን ያሳውቃል የሚልም ጽኑ እመነት አለኝ ::


ሰላሙን ላገራችንና ለድሀ ህዝባችን እመኛለሁ !!
ይገርማል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Thu Nov 13, 2003 12:10 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests