ዶር መረራ እና ዶር በየነ ; ፓርላማ ረግጠው ወጡ! እና ምን?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ዶር መረራ እና ዶር በየነ ; ፓርላማ ረግጠው ወጡ! እና ምን?

Postby ጥልቁ1 » Tue Oct 11, 2005 2:10 pm

በመለስ መሪነት ; ዛሬ ፣ ህገ-ወጡ ፓርላማ ፣ በቅንጅቱ ተመራጮች ላይ አንድ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በሚወያይ ሰአት ፣ ዶር መረራ እና ዶር በየነ ፓርላማ እረግጠው ወጡ! ባልሳሳት እነሱ ከወጡም በኋላ ፣ መለስ የፈለገውን ውሳኔ በድምጽ አስጸድቋል።

ይሄ ዜና ያስደስታል? ከአሰደሰተስ ምኑ?

በመጀመሪያ ደረጃ ፣ ዶር በየነን ማመን ጉም መጨበጥ ለመሆኑ ፣ የኢትዮጵያን የአስር አመት የፖለቲካ ሂደት ዞር ብሎ መቃኘት በቂ ነው። የዶር መረራም ፣ ምንም እንኳ እሳቸው ብዙ ተናግረው ብዙ ተስፋ እንድንጥልባቸው ቢያደርጉም ፣ የጣልንባቸው ተስፋ ግን ፣ ባልቻ አባ ነፍሶ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ የምንጥልባቸውን ተስፋ ያህል ከባድ ስለሆነ ፣ ያንን ከቋጥኝ የሚከብድ ተስፋ ተሸክመው ከሚሄዱ ፣ መሬት ላይ ቁጭ አድርገውት መንቀሳቀስን መርጠዋል።

ወደ አይነተኛው ጉዳይ ስመለስ ፣ ዛሬ እነኝህ ሁሉት ዶ/ሮች ስብሰባ እረግጠው መውጣታቸው ፣ እየኖረ ባለው የወያኔ መንግስት ላይ ምን አይነት ጫና ሊፈጥር ይችላል? ለእኔ ‘ምንም’ ነው መልሱ። የሚመሩትን ፓርቲም የመሪነትን ቁንጮ የተቆናጠጡ ቢሆንም ፣ ፓርላማውን ጥለው ሲወጡ ምን ያህሉ ተከተሏቸው? ማንም። እነዚህ ሰዎች ፓርላማውን ዛሬ ጥለው መውጣታቸው ማለት ፣ በቃን ከዛሬ ጀምሮ ማለታቸው ነው? አይደለም።

ታዲያ ከዚህ አንጻር ሲታይ ፣ ዬሁለቱ ፓርላማውን ጥለው መውጣት ፣ ከቀቢጽ-ደስታ የራቀ ነገር ጥሎልን ያለፍን ሰዎች ካለን ፣ የነገንውን እውነታ ማየት ያልፍለግን ይመስለኛል።እኔ ከምንም በላይ የሚያሳፍረኝ ፣ ለዚህ ውሳኒያቸው ፣ ጋዜጠኞቻችን ሲያቆለማምጧቸው ከሰማሁ ነው።

ለእኔ ሃቁ እንዲህ ነው። እነኝህ ግለሰቦች ፓርላማ ሲገቡ ፣ ወያኔን ተቀብለን አቢዮታዊ ዴሞክራሲን እናራምዳለን ብለው አይደለም። ከቅንጅቱም ጋር የነበራቸውን ፣ የአንድነት ቃል ሲያፈርሱ ፣ ብቻችንን መቆም እንችላለን ብለው አይደለም። የልቁንስ ፣ ከሚመሩት የህብረት ድርጅት ይልቅ ፣ የተመረጡት ታጋዮቻቸው ስለሚጠነክሩ ነው። አዎ! ሁለቱ ዶ/ሮች ህብረቱ ፓርላማ ላለመግባት ወስኗል እያሉን ፣ የተመረጡት ሁሉ (እራሳቸውንም ጨምሮ) ፣ ፓርላማ ይገባሉ ሲሉም ፣ ፖለቲካውን እቃቃ ጨዋታ ቢያስመስሉትም ቅሉ ፣ እውነታው ግን ፣ ህብረቱ ከስራው ይልቅ ስሙ እንደሚበልጥ ያሳያል።

ቅንጅቱ በጽናት እና በብቃ ተመራጮችን ማዘዝ ሲችል ፣ ህብረቱ እንዴት ተመራጮችን የመቆጣጠር ሃይል አጣ? መልሱ ቀላል ነው…በህብረቱ ውስጥ ምርጫውን ያሸነፉት ሁሉ በአገር ቤት ያሉት ፓርቲዎች ሲሆኑ ፣ ፓርላማ የመግባት እና አለመግባት ውሳኔው ግን ፣ ህብረቱ ውስጥ አለን በሚሉ የውጫ አገር አቀንቃኞችም ጭምር ነው። ቅንጅቱ ግን ፣ ሁለመናው ያለው እዛው አገር ቤት ነው። ከዚህም የምንማረው የፖለቲካ ተሞክሮ ቢኖር ፣ በውጭ አገር ተቀምጨ የፖለቲካ ፓርቲ እመራለሁ ማለት ምን ያህል ትርጉም-አልባ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ፣ የአገር ቤቱንም ትግል እንደሚያዳክም ያሳያል።

ዛሬ ዛሬ ፣ በውጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያዊያን የምናደርገው የፖለቲካ ድጋፍ እና ንቅፈቶች ፣ ዜናን ተከትለን ብቻ ሆኗል ይመስለኛል። ይህንንም እንድል የሚያደርገኝ ፣ አንድ ዜና ስናይ ፣ ዬእንኳን ደስ ያለህ መግለጫ ስንለዋወጥ ፣ ሌላ ዜና ስናይ ብርድ ብርድ ሲለን ይታያል። መቸ ነው የዜና ህይወታችን የሚያቆመው? ወያኔ አገር ለማጥፋት የቆመ የበአድ ፍሬ እንደሆነ ፣ እለታዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴውን ማወቅ ያለብን አይመስለኝም። እለታዊ እንቅስቃሴ የማይለውጣቸው የአዲስ አበባ ታክሲ ነጅዎች ፣ ያለባቸው እዳም በተሰረዘ በማግስቱ ፣ መንግስትን ከመንቀፍ ወደ ኋላ አላሉም። ምክንያቱም ፣ ወያኔን በዜና ሳይሆን በታሪክ ነው የሚገምቱት። ተቃዋሚዎቻችንንም ፣ ማየት የምንፈልገውን ያህል አይተናቸዋል። ማን እስከመጨረሻ ከህዝቡ ጋር እንደቆመ እና ማን ደሞ ለስጋው እንደሚሳሳ አይተናል።

የዛሬውም የሁለቱ ዶ/ሮች ፓርላማ ረግጦ መውጣት ፣ ከውስጣቸው ያለውን ለህዝብ መብት ከመቆም አኳያ የሚያሳይ ነው ብለን ከማመን እና ወያኔ በሚወስነው ውሳኔ ላይም የተቃውሞ እጅ አወጡ ብለን እራሳችንን ከንቱ ከምናታልለው ፣ እረግጦ በመውጣትም ሆነ በመቃዎማቸው ህገ-ወጡን ፓርላማ ህጋዊ ሽፋን መስጠታቸውን ልናውቅ ይገባል። እንደዛ ከሆነማ ፣ ታዲያ ለምን መጀመሪያውንስ ፓርላማ አትግቡ አልናቸው?!

ወያኔ ፓርላማ በማይገቡት ላይ እርምጃ እውሰዳለሁ የሚለው እንዴውም ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ወደ ተሻለ አቅጣጫ ይመራዋል እና ዬእነሱ ፓርላማ እረግጦ መውጣት እና ሃስቡን መቃዎም ፣ ለእኔ ፋይዳ-ቢስ የሁለት ቢላዋ ጨዋታ ነው። የህዝቡንም ድጋፍ እንዳያጡ ፣ የፓርላማው መቀመጫም እንዳያመልጥ መሆኑ ነው። የልቁንስ እነሱ እዛ ህገ-ወጥ ፓርላማ ላይ ፣ ትላንትም ዛሬም አንዲት ነገር ለመትንፈስ ተከልክለው መታየታቸው ፣ ትክክለኛ የዛን የቅሌት ፓርላማ መልክ ስለሚያሳይ ፣ በlitmus paperነታቸው እናመሰግናቸዋለን። ከዚህ በኋላ ግን ፣ እንኳንስ በሚወስዱት የፖለቲካ አቋም ልደሰት ቀርቶ ፣ …ብቻ ሆድ ይፍጀው!

የወደዱትን ቢያጡ የጠሉት ይቀላውጡ!
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

Postby ማራናታ » Tue Oct 11, 2005 2:51 pm

እውነት ነው?ከየት ነው ? የሰማህው?
ማራናታ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 30
Joined: Fri Aug 12, 2005 10:12 am
Location: norway

ወንድሜ ጥልቁ1

Postby ማንትሩ » Tue Oct 11, 2005 5:10 pm

ከላይ ያሰፈርከውን ለመቃወም አይደለም ጥሩ ብለሀል ግን እነዚህ ዶክተሮች ጥለው መውጣታቸው የሚደገፍ ነው የመለስን ምንም እነት አሳይተዋል አንባ ገነንነቱ ዋጋ እንደማያስገኘው ባቅማቸው አሳይተውታል እረግጠውም ከወጡ በሁዋላ አውሬው ውሳኔውን አጽድቆዋል አይገርምም ምክንያቱም አራት ሚሊዮን ህዝብ ያለባትን አዲስ አበባን ካለህዝብ ፍላጎት ካለስተዳደርኩ ብሎ ሙጥኝ ያለ መዥገር መንግስት ነው አይተሀል ውስኔው ላይ አጫፋሪዎቹ ያን ሽባ እጃጀውን ሲመዙ ነገ ባያፍሩበት ነበር ጥሩ ዶክተሮቹ ከነዚህ አለመፈረጃቸው ጎበዞች አያስብልም ወንድሜ?ያለፈውን ታሪካቸውን ሊያስረሳ ባይችልም የዛሬው ድርጊታቸው ጎሽ በርቱ ያሰኛል'''
ግን ይሄ የመልስ መንግስት በሌላው አፍሪካ ሀገር ቢሆን ኖሮ አልቆለት ነበር ድሮ እድል ሲያድለው ፈሪያ እግዜር ያለበት የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሆነና ጊዜ አገኘ እሱም መሰለው አንባ ገነን የሆነ አይ አለማውቅ ነገን አይተን ብቻ የኛ ህዝብ እንባ የት ያደርሰው????ያሳየን

ቸር ያሳየን
ማንትሩ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 58
Joined: Mon May 16, 2005 9:45 pm
Location: united states

Postby የዘመኑ ልሳን » Tue Oct 11, 2005 5:14 pm

ማራናታ wrote:እውነት ነው?ከየት ነው ? የሰማህው?


ትንሽ ቢረዳህ ብዬ ነው::ይህን አንብብ

ETHIOPIA: Opposition MPs stripped of parliamentary immunity


[ This report does not necessarily reflect the views of the United Nations]


ADDIS ABABA, 11 Oct 2005 (IRIN) - Opposition members of parliament in Ethiopia could face prosecution after their immunity was lifted following a boycott of the opening session of the legislature, MPs loyal to the government decided on Tuesday.

The decision sparked a mass walkout by around 40 opposition law makers who had taken up their seats despite an increasingly hostile stand-off between the ruling Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front and the largest opposition party, the Coalition for Unity and Democracy (CUD).

Prime Minister Meles Zenawi told parliament the CUD had committed "serious crimes" by threatening to take power through street demonstrations and insurrection during bitterly contested May elections dogged by allegations of fraud and vote rigging.

"If they take illegal actions then this government has to see to it the constitution is protected," Meles told parliament on its second day.

"They want to use immunity to crash the constitution," he added. "Immunity is used to defend the constitution, not dismantle it, so this immunity must be removed for the sake of peace and stability in the country."

Some 334 MPs voted in favour of the motion stripping the opposition MPs of their immunity, while 35 opposed it and two abstained.

The new law, according to government officials, means charges could be brought against boycotting CUD members found to have been behind post-election disturbances or found to be planning any disturbances.

They cannot, however, be prosecuted for not attending parliament.

Opposition parties have been protesting since the May polls that voting had been rigged in favour of the ruling party. Violent clashes with security forces left 42 protesters dead.

The chairman of the opposition United Ethiopian Democratic Forces, Beyene Petros, said the move was unconstitutional before walking out with his party members.


"This House can remove immunity if they are caught red-handed committing crimes. They have not done that. This is a political issue and bad for the country," he said.

Hailu Shawel, leader of the CUD, insisted their boycott would continue. "We are prisoners here," he said after watching the debate on state-run television. "This means that we are going to be herded into jail. They will concoct charges against us."

Former youth sport and culture minister Teshome Toga, who is now speaker of the House of People's Representatives, told the 443 MPs who attended the house that the decision would only apply to those boycotting parliament.

"This concerns only those who did not join parliament. The immunity works only if the party accepts the mandate of the people and come to sit in this house," he said.

Meles also announced a major reshuffle of his cabinet, increasing the number of posts from 18 to 20.

Senior ministers who lost their positions included education minister Genet Zewdie, health minister Kebede Tadesse and information minister Bereket Simon.

The standoff over the disputed polls has also left the capital city, Addis Ababa, - home to four million people and the headquarters of the African Union - without an administration.

The CUD has refused to take up their seats on the council and parliament voted for a transitional former city government - voted out in May's election - to continue running affairs.

Opposition parties won just 12 seats during the last elections in 2000, but now hold 176 seats, constituting 32 percent of the parliament.
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

ይታረም

Postby ጉዋንጉል » Tue Oct 11, 2005 7:55 pm

አንደኛ ነገር በየነ የወያኔ እግር እሾክ በመሆን አላራምድ ብሎ ሲያደናቅፋቸው የቆየ የዘመናችን አርበኛ ነው::

ሲያሻቸው ውይኒ አልያም በእንጀራው እና በቤተሰቡ እየመጡ ቁም ስቕሉን ቢያሳዩትም : ወያኔ ክገባበት ሳምንት ጀምሮ በትግል ላይ የቆየ ታላቅ ኢትዮዽያዊ ነው!

ሁለተኛ..... ስብስባውን ረግጦ በወጣ ግዜ ወደ 40 የሚሆኑ አባላት ተክትለውት ወጥትዋል.

እንግዲ ስም ክማጥፋት በፊት ነገርን አጢኖ ማየት...እላለሁ!!
ጉዋንጉል
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 7
Joined: Wed Sep 14, 2005 2:22 am
Location: ethiopia

Postby አንፌቃ » Tue Oct 11, 2005 8:46 pm

ዶ/ር መራራ ወጡ የሚል እስካሁን አላነበብኩም!
አንፌቃ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2109
Joined: Wed Dec 08, 2004 2:02 pm
Location: united states

ትክክለኛ እርምጃ ነው!

Postby ትምህርት » Tue Oct 11, 2005 9:09 pm

ሰላም!

አናሳ ተቃዋሚዎች አሁን አደርጉ የተባለው ነገር ትክክለኛ እና አስፈላጊ ነው! የብሪታኒያን ፓርላማ (House of Commons) የተከታተለ ሰው ጩኸት እና ሁካታ ዋናው የተቃዋሚዎች መሳሪያ እንደሆነ ይረዳል::
Image

ተቃዋሚዎች ፓርላማውን ረግጠው ሲወጡ መጀመሪያ አትግቡ ብለናቸው ነበር ወይም መቼ አጣናው አይነት ነገር ሰዎች እዚህ ሲጽፉ ይታያል:: አናሳ ተቃዋሚ ፓርቲ(ዎች) ፓርላማ ውስጥ ገብተው ከመቃወም ውጭ ምን እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል? ከፍተኛ ተቃውሞ!! በቃ ይኸው ነው!

ከምርጫ በፊትም ሆነ ከዚያ ወዲህ እንዲህ ብለው ነበር!!!! አሁን ግን ቃላቸውን አጠፉ የሚል ክስ ይሰማል:: ይህ ቃል ሰበራ የኛዎቹ የተማሩት ከሰለጠኑት አገሮች ፓርቲዎች እንጂ እራሳቸው የፈጠሩት ደባ አይደለም:: የትኛው ፓርቲ ነው ለምርጫ አደርጋለሁ ብሎ ቃል የገባውን በሙሉ የፈጸመው? እስኪ የፓርቲ ስም ጥሩ ልስማችሁ!!

አሁን ተቃዋሚዎች ፓርላማ ጥለው ወጡ ሲባል እልልልልል ነው ያልኩት:: ሥራቸውን በሚገባ ማከናወናቸውን ከጅምሩ በመረዳቴ!! ቀጥሉ! ብራቮ!!

ከሰላምታ ጋር!
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

Postby ጉማ » Wed Oct 12, 2005 5:52 am

አሁን ያለንበት ቀውስ አይናችንን ከሰው ላይ አንስተን ትልቁን ስዕል አንድናይና ከየራሳችን ሆደ ባሻነት ይልቅ ለህዘባችን ድል የሚበጀውን ማሰቡ ትልቅነት ይመስልኛል::
የዶ/ር መረራ ፓርላማ መግባት ያናደደኝን ያህል መውጣታቸውም ያስደስትኛል:: እንኳንስ ዶ/ር መረራ እነ አባ ዱላም ፓርላማ ረግጠው ቢወጡ : አጨበጭባልሁ:: ለምን ብትሉኝ ማንም ይሁን ማን እራሱን ከወያኔ ባራቀ ቁጥር ህዝባችን የታገለለትን የነፃነት ቀን ያቀርበዋልና::[/b]:[b]
ቸር ወሬ ያሰማን
Tesfa Z Guma
ጉማ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Wed Oct 12, 2005 4:59 am
Location: united states

Postby ጥልቁ1 » Wed Oct 12, 2005 7:19 am

አንድ ቁምነገርኮ ስታችኋል!
እነኝህ ሰዎች ; ነገ በጠኋት ፓርላማው ሳይከፈት በር ላይ የሚገኙት እነሱው ናቸው:: በሉ ነገ ደሞ ለመናደድ ተዘጋጁ::

እዛ ፓርላማ ቁጭ ብለው ተቃወመው ወይም ረግጠው ሲወጡ የሚያስደስታችሁ ከሆነ ; በሉ እንዳሰኛችሁ::

ለእኔ ግን ; ያንን ፓርላማ ከረገጡ ጅምሮ ተለያይተናል:: በሉ በነካ አፋችሁ ; ትላንት ቅንጅት እና ህብረቱን ሲሳደቡ የነበሩትን አቶ ቡልቻንም አመስግኗቸው::

ፖለቲካ ማለት የአቋም ውሳኔ ሲኖር እንጅ ; ከነፈሰበት ጋር መንፈስ አይመስለኝም::

ጥያቄው ያለው የፓርላማው ህጋዊነት ላይ ብቻ ነው::

ቸር እንቆይ!
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

ተቃዋሞ ማለት

Postby ትምህርት » Wed Oct 12, 2005 8:29 am

ጥልቁ1 wrote:አንድ ቁምነገርኮ ስታችኋል!
እነኝህ ሰዎች ; ነገ በጠኋት ፓርላማው ሳይከፈት በር ላይ የሚገኙት እነሱው ናቸው:: በሉ ነገ ደሞ ለመናደድ ተዘጋጁ::
እዛ ፓርላማ ቁጭ ብለው ተቃወመው ወይም ረግጠው ሲወጡ የሚያስደስታችሁ ከሆነ ; በሉ እንዳሰኛችሁ::


ሰላም!

ተቃዋሚዎች ፓርላማ ረግጠው መውጣታቸው ሥራቸውን በሚገባ መስራታቸውን ያስረዳኛል:: ተቃውሞ የሚገለጥበት አንዱ የሰለጠነ መንገድ ይህ ሲሆን በዚህም እንዲቀጥሉ ምኞቴ ነው! በኤሽያ በጃፓን ጭምር ፓርላማ ውስጥ ሲደባደቡ ማየት አዲስ ነገር አይደለም::

ጧት ተመልሰው ፓርላማ ይገኛሉ ያልከው ትክክል ነው! ይህም ማለት እንደገና ፓርላማውን ረግጠው አይወጡም ማለት አይደለም:: ሥራቸው ነው! መንግሥት እስከሚያስቆማቸው ድረስ!

አክባሪህ!
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Oct 12, 2005 9:54 am

ሰላም ጥልቁ:-
በዚህ ጽሑፍ ላይ እራስህን እየተቃረንክ እንደሆነ ነው የተረዳሁት::ባንድ በኩል የነርሱ ነገር የበቃኝ ፓርላማውን ከረገጡ በሗላ ነው ትላለህ::ሆኖም ግን አልተውካቸውም::በሌላ በኩል ደግሞ ቅንጅት የራሱን ተመራጮች መቆጣጠር ሲችል...ያልከው ምን ለማለት ፈልገህ እንደሆነ አልገባኝም::እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት 13 የሚሆኑ የቅንጅት አባላት የተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደተገኙ ነው የማውቀው::
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1034
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ጥልቁ1 » Wed Oct 12, 2005 7:16 pm

ሰላም
አንዳንዴ...
እንኳንስ በጽሁፍ ; በአካልም እየተወያየሁ የማልግባባቸው ሰዎች አሉ:: ከላይ ልትከራከሩኝ የሞከራችሁትም ; ወይም እናንተ አለያም እኔ ወይም ደሞ ሁላችንም ; የሆነ የጎደለን ነገር ያለ ይመስለኛል::

እንደማንግባባም አውቃለሁ:: ምክንያታችሁም ይገባኛል:: እኔ ግን ; በዚህ ሰአት ; ኢትዮጵያዊያን ከተከበቡበት የታሪክ ነቀርሳ ወያኔዎች በሚገላገሉበት ዙሪያ የሚወያዩት ወንድሞች እና እህቶች ናቸው የናፈቁኝ::

ቸር እንቆይ!

ቸር እንቆይ!
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

ህመምህ ህመሜ ነው!!!!

Postby ቢሌ » Wed Oct 12, 2005 8:31 pm

ውድ ጥልቁ 1, በውነቱ ማስረዳት ነገር ለሚገባው ነው ማስረዳት:: በነኝህ 2 ዶክተሮች ድኖ የነበረው ጨግዋራዬ ተቀስቅሷል:: እንዳልከው የምርጫውን ውጤት የተቀበለ ብቻ ነው የ ወያኔ ትያትር ቤት የሚገባው:: እንዳውም ምርጫው ትክክለኛ ነበር የቀንደኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች የምርጫውን ውጤት ተቀብለው በፓርላማው ተሳትፈዋል እና የደስታ መግለጫ ለወያኔ መሪ ተብየው ለመላክ እየተጣደፉ ያሉ መንግስታት እንዳሉ አውቃለሁ:: ማንም ከትግሉ ቢያፈነግጥ የተረገጠው ህዝባችን ግን ለነጻነቱ ቆርጥዋል!!!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ሞት ለወያኔና ለግብረአበሮቹ
ቢሌ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 586
Joined: Wed Aug 18, 2004 7:29 am
Location: united states

Postby አንጅባ » Wed Oct 12, 2005 9:05 pm

በኒ በኩል እንኳን ይህን የምለው ቢኖር ከወደቁ በሗላ መፈራገጥ ጀርባን መላጥ ነው በመጀመርያ ደረጃ ትላንት የፈሰሰውን ደም እረስተውት ፓርላማገቡ 1ኛ ወያኒ አላቸነፈም እያሉ ፓርላማ መግባት ወያኒ ማቸነፉን ማፅደቅ ነው ካሁን በኋላ በነሱ ያለኝ ተስፋ በኒ በኩል ተምዋጥዋል ረገጡ አልረገጡ ትርጉም የለውም:: ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ አሚን ;:
አንጅባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 22
Joined: Sun Sep 18, 2005 8:03 pm
Location: ethiopia

Postby ወጥመድ » Wed Oct 12, 2005 9:19 pm

ዘርዐይ ደረስ wrote:
እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት 13 የሚሆኑ የቅንጅት አባላት የተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደተገኙ ነው የማውቀው::


ሰላም ዘርዓይደረስ

ይህንን ዜና ገና አሁን ካንተ ማንበቤ ነው::

መረጃ አለኝ ካልከን ዘንድ የግለሰቦቹንም ስም ዝርዝር ታውቃለህ ማለት ነውና, መረራንና በየነን ብቻ ከምንኮንን ከቅንጅትም የገቡ ካሉ ግልጽ ብታደርግልን ውይይቱንም ሰፋ ያደርገዋል ብዬ አምናለሁ::

አመሰግናለሁ

ወጥመድ
ወጥመድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Fri Mar 11, 2005 1:52 pm
Location: Semen Walta

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: ምሰጢር and 2 guests