አማረች እጅግ ተዋበች ሎንደን በአበሻ አቸበረቀች

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አማረች እጅግ ተዋበች ሎንደን በአበሻ አቸበረቀች

Postby ዲጎኔ » Sun Oct 16, 2005 4:42 am

አማረች እጅግ ተዋበች
ሎንደን በአበሻ አቸበረቀች
የቶኒ ብሌር ቢሮም ሰማች
የወዳጇን ጉድ አወቀች
ነፍሰ-ገዳይ መሆኑን አመነች
በድንቅ የኢትዮጵያ ልጆች
ለወገናቸው ተሟጋቾች
ለንደን ዛሬ ደመቀች
አረንጉአዴ ቢጫ ቀይ ውብ መሰለች
የዛች ቅድስት ሀገርን ሰንደቅ ለበሰች
የቢቢሲ ዘጋቢም እንዲቃና መከረች
ክሪስታል ፓላስ እንዲሁም ብሪክስተን
ኢስት ለንደን ጭምር እስከ ኒውተን
ቾክ ፋርምም ያላችሁ በጸሎትበርትተን
ኒው ሀምፕሻየር ማንቸስተርን ይዘን
አልፎ ከማዶውም ግልሳኮትን ጠርተን
ኦክቶበር በ19 ከአደባባይ ገብተን
የቢቢሲን ቢሮ አላላውስ ብለን
በአለም ሚድያ ትኩረት አሰጥተን
ኮንሰርቫቲቮቹን ከሌበር አጣምረን
የኢትዮጵያን ብሶት እሮሮ አሰምተን
የወያኔን ወንጀል ውሸቱን ገላልጠን
የነሽብሬንም እርማችን አውጥተን
ዋይ ዋይ ብለን ጮህን ደረትን ደቅተን
የተስፋዬን ደምም ከአርሲ አስመጥተን
የቅርቡን የጅማን ኤልያስ ታስቦን
የጋምቤላዎቹን ከምናብ አፍልቀን
ሎንደን በ19 ታሪክ እንሰራለን
እናንተም በስዊዲን በቤልጅየም ያላችሁ
መፈጠሪያ ምድር ወገን ያልረሳችሁ
ከጣልያን ከሆላንድ ከፓሪስ ጠርታችሁ
የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ክፋይ የሆናችሁ
አንዴ ተጠራሩ ይሰማ ድምጻችሁ
በአላማ ጽኑ ዘር አይለያያችሁ
መታገሉ ይብቃ ለብቻ ሆናችሁ
የኖርዌን ገድል በሎንደን ደግማችሁ
የኢትዩኦጵያን እንባ አንዴ አብሳችሁ
ወያኔ ሲጋለጥ ለማየት ያብቃችሁ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests