ሳጥናኤል ሲምል : እግዜርን እያለ
ስንቱን የእግዚአብሔር ሰው : ልቡን አማለለ
ኢትዮጵያም ደረሳት : ይኸው ዕጣ ፈንታ
ሰንደቋ ረግጦ : እጇን የሚመታ
ዴሞክራሲም ገብታ : ከመሃላ መዘዝ
ማኅተም ሆና ቀረች : ለጨቋኝ አግዛዝ
ነጻነትም ታየች : ከመሃላ ተራ
የሞት ዕጣ ሰብቃ : ነፍስን ስትጠራ
አልገባ ያለችው : በመሃላ ወጥመድ
እምቢኝ ብቻ ቀረች : ሳትቀለማምድ
በሯን ጥርቅም አድርጋ : ለሃሰት ሳትሰግድ
ያደርጉታል እንጂ : አይምሉም በእምቢኝ
እምቢኝ ልበልና : ያረጉትን : ያርጉኝ