ይህን ያሉት እሳቸው ባይሆኑ ኖሮ!?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ይህን ያሉት እሳቸው ባይሆኑ ኖሮ!?

Postby ሲምባ-ባ » Mon Oct 17, 2005 12:59 am

ዶ/ር መረራ ጉዲና ወደ ፓርላማ እንዲገቡ የተገደዱበትን ምክንያት ሲዘረዝሩ
1/ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት ስለሆነ
2/ እሳቸውና ፓርቲያቸው ባይገቡ ወያኔ ያዘጋጀው ተለጣፊ እየተንደረደረ በመሆኑ አደጋው ከሌላው የባሰ መሆኑን ገልጸዋል::
የእኔን ትኩረት የሳበውና ርእሱን ያስከፈተኝ ግን
'' 23 የኦሮሞ ልጆች የሞቱበትን የምርጫ ውጤት የትም ልንጥለው ስለማይገባ'' ያሉት ነው:: 23ቱ የኦሮሞ ልጆች የከፈሉት መስዋእትነት በኦብኮ ስም መሆኑ እንጂ ብዙዎች ስለኦሮሞ ህዝብ መሞታቸው እውነት ሆኖ እያለ በተጨምሪም
በሰኔ ወር ውስጥ በአዲስ አበባ ለሰልፍ ወጥተው
የተገደሉት ሰዎች የማን ብሄረሰብ አባላት ይሆኑ? ብዬ እንድጠይቅ አስገደደኝ::መቼም ዘርን እየፈለገ የሚቀጣ ጥይት አልተወረወረም በተለይ ያኔ እናም ዛሬም ያለው የተቃውሞ መንገድ ዘርን/ጎሳን: ቓንቓን መከታ ያደረገ ከሆነ ወያኔን የሚቃወሙት ምን ላይ እንደሆነ መረዳት ስላልቻልኩ ነውና የገባው በጨዋ ደንብ ይመልስልኝ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ:: ይህን ያሉት ዶ/ር መረራ ባይሆኑና ምናልባት ሌላው የተቃዎሚ ፓርቲ መሪ አቶ አረጋዊ በርሄ ቢሆኑስ?
ሲምባ-ባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jul 12, 2005 2:59 pm
Location: ethiopia

Postby ቱሉቦ » Mon Oct 17, 2005 3:01 am

ወንድሜ !
ለኔ እንደገባኝ ከሆነ አባባላቸው እኮ ወያኔ የገደላቸው የኦብኮ አባላት እና ደጋፊዎች ብዛት ለማሳወቅ ያህል እንጂ አንተ እንዳሰብከው በዘር ለመከፋፈል ብቻ ላይሆን ይችላል ::

ፍትህ=ሰላም

ቱሉቦ
ቱሉቦ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 102
Joined: Wed Aug 24, 2005 2:01 am
Location: ethiopia

Postby አገሩ » Mon Oct 17, 2005 5:42 am

ስማኝ ወንድሜ:- ይህንን አይነቱን አመለካከት ለማጥፋት ነው እኮ ትግሉ::
የወያኔ አካል የሆነ ብቻ ነው ይህንን በዘረኝነት መንገድ የሚገልጸው::
አገሩ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Sun Dec 05, 2004 3:57 am
Location: united states

Postby ዞብል2 » Tue Oct 18, 2005 1:24 am

ሲምባ_ባ :P የዶ/ሩ ንግግር አንተ እንዳልከው አይደለም!!.... አንተ ለሆድህ ያደርክ ማፈሪያ "እስስት ደላላ" ነህ :P :P

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1987
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

አደንቃችኍለሁ

Postby ሜሎ » Tue Oct 18, 2005 3:16 am

ከዚህ በላይ ለቀረበው መርዘኛ ጥያቄ ተገቢውን መልስ ለሰጣችሁ ሁሉ አድናቆቴን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ;; አስተያየት/ጥያቄ/ አቅራቢው ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን አፍርሶ በምትኩ ተለጣፊ ኦብኮን ለመመስረት ውንብድናን ስለፈጸመው ወያኔ ብዙ መባል ያለበት ጉዳይ እያለ ዶ/ር መራራ ስለሞቱት የኦሮሞ ልጆች ለምን ተናገሩ ማለቱ ማንነቱንና ያው የተለመደውን የመከፋፈል መርዝ ለመርጨት ብቅ ማለቱን ያስታውቃል;; ጠያቂው ይህን ጊዜ ያለፈበትን ስልት ለመጠቀም ባይሞክር ጥሩ መሆኑን እየጠቆምኩ ባዶነቱን ላረጋገጣችሁለት ሁሉ አድናቅቴን እገልጽላችኍለሁ;;

አንድነት ሀይል ነው!!!
ሜሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 252
Joined: Fri Feb 11, 2005 12:31 am

ምን እያላችሁ ነው?

Postby ሲምባ-ባ » Tue Oct 18, 2005 3:56 am

የሰለጠነ የፖለቲካ አስተሳሰብን ከምንም በላይ የምንሻበት ዘመን ላይ መሆናችንን መልስ ብላችሁ ብቅ ያላችሁ ሰዎች የተረዳችሁ አትመስሉም:: ሰው ከራሱ የተለየ ሀሳብ ሲነሳበት በአግባቡ ከማስረዳት ይልቅ ማውገዝን ይልቁንም ድርብርብ ስም መስጠትን በተለይ ዋርካ ላይ ስራዬ ብላችሁ የያዛችሁ ሰዎች ትገርሙኛላችሁ:: ከእኛ የተለየ ሀሳብ ማራመድ ውጉዝ ነው ካላችሁ '' ተቃውሞን ያሰበ ያሳሰበ'' ይል የነበረው ስርአት ነው የሚገባችሁ:: ይህ ካልሆነ ግን 23 ሰው የሞተበትን ድምጽ ላለመጣል የሚለው ሀሳብ ስሜት አይሰጥም:: ሞትህ የሰማእትነት ክብር ሊሰጠው( ኦሮሞ ሆነህ ከሞትክ) የኦብኮ መታወቂያ ኪስህ መገኘት አለበት ማለት ነው:: ጥያቄዬ ለምን ፓርላማ ገቡ አይደለም መግባታቸውን ከመቃወምም አይደለም ከተሰጡት ምክንያቶች አንዱ ያውም ቀደም ብዬ የጠቀስኩት ስላልገባኝ ብቻ ነው:: ዘረኛ ከፋፋይ ላልከው ግን ኦብኮ ዘርን መሰረት አድርጎ ላለመመስረቱና የዶ/ሩም አባባል ዘረኝነት ያልተንጸባረቀበት ለመሆኑ አንተን በገባህ መንገድ አስረዳኝ እንጂ በደፈናው ለኔ ስም መስጠቱ አንተን አዋቂ አያደርግህምና እንደማመጥ::
በስድብ ለሰለጠንከው ሌላኛው ሰው እኔ ላንተ መልስ የለኝም ምክንያቱም አንተ የሚገባህን አይነት ቁዋንቁዋ ስለማላውቅበት ስላላደግኩበት
ሰላም ሁኑ
ሲምባ-ባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jul 12, 2005 2:59 pm
Location: ethiopia

Postby ዞብል2 » Tue Oct 18, 2005 6:59 pm

ሲምባ_ባ :P ዘመናዊ ፖለቲካ? ስማ ሌላ ሞክር በሳቅ ነው የገደልከኝ :lol: :lol:...ሰደብከኝ ነው ያልከው መጀመሪያ የአንተን ጽሁፍ ከአርእስቱ እስከ መደምደሚያው ያለው ሀሳብ የመወያያ ሳይሆን በግለሰቦች ላይ ተመርኩዞ ብሄሮችን የሚነካ ከፋፋይ ሀሳብ ነው:: ስለሆነም መልሱ በሚገባህ ቁዋንቁዋ ተመልሶልሀል :D

ሲምባ_ባ(ደላላው) :P ሰደብከኝ ነው ያልከው ሌላ ምንም አልልህም አንተን
"የቀበናው ጋንጩር በካልቾ ዝቆህ"
"የአቡዋሬው ቃልቻ በአፍ ጢምህ ይድፋህ" :P :P

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1987
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

ያላዋቂ ነገር

Postby ሲምባ-ባ » Tue Oct 18, 2005 7:57 pm

ላንተ መልስ ለመስጠት ከሞከርኩ የተነሳሁበት ጭብጥ ይጠፋል ዝም ካልኩህ ደግሞ ያሳብድሀል መለፍለፍህን አታቆምም:: በሀሳብም በአስተሳሰብም ባንገናኝ ወንድሜ ነህና ጉዳትህን አልወድም ስለዚህ ትንሽ ልበል::
የምንነጋገረው እኮ ፖለቲካ የሚለው አምድ ላይ ሆነን ነው:: ፖለቲካን የፈጠረው ደግሞ ሁልጊዜም ልዩነት ነው:: ልዩነት በመግባባት በመቻቻል በመፈቃቀድና አንድ አድርጎ ሊያሰባስብ በሚያስማማ ሀሳብ መስማማትን እንጂ አንድ መሆንን አያመጣም::
በአሀዳዊት ኢትዮፕያ በርካታ ብሄረሰቦች የመኖራቸው አንድነት የመፈቃቀዳቸውና የመስማማታቸው ውጤት እንጂ አንድ የማሰባቸው መስማማት አይመስለኝም:: ይህማ ከሆነ እኔና አንተ ያልተግባባንበት የኦሮሞ ብሄራዊ ኮንግረስ ስሙ ይህ ባልሆነ ወይም ጭርሱን ባልተፈጠረ:: ተቃዎሚዋችም'ኮ የመስማማት አንድነትን የመፍጠር ተልእኮ ይዘው እንጂ የተነሱት አንተና ወዳጆችህ እንደምታስቡት ልዩነቶችን ለመጨፍለቅ አይመስለኝም:: አንድ ያለማሰብ ሀጢያት አይደለም::
አሁንም በድጋሚ አነሳለሁ የእናንተኑ ሀሳብ መሰረት አድርጌ:: እሳቸው ምክር ቤት የገቡት በሀገራችን ዲሞክራሲያዊ ስርአት ተፈጥሮ ሁሉም በእኩል የሚታይበት ስርአት ለመገንባት የተከፈለውንና የሚከፈለውን መስዋእትነት 'ሁሉ' መከታ አድርገው ነው ወይስ የ23ቱን?
I think I am wasting my breathe!
ሲምባ-ባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jul 12, 2005 2:59 pm
Location: ethiopia

ጠያቂው ተጠየቅ?

Postby ቱሉቦ » Tue Oct 18, 2005 11:28 pm

ወንድሜ !

በአሁኒቱ ኢትዮጵያ በዘር ከፋፍሎ አገዛዝ ተጠቃሚው ማን ነው ?

ቱሉቦ

ፍትህ = ሰላም
ቱሉቦ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 102
Joined: Wed Aug 24, 2005 2:01 am
Location: ethiopia

Re: ጠያቂው ተጠየቅ?

Postby ሲምባ-ባ » Wed Oct 19, 2005 8:35 pm

ቱሉቦ wrote:ወንድሜ !

በአሁኒቱ ኢትዮጵያ በዘር ከፋፍሎ አገዛዝ ተጠቃሚው ማን ነው ?

ቱሉቦ

ፍትህ = ሰላም

__________________________________________
ቱሉቦ በመጀመሪያ ስነምግባርህን አድንቄ ቀደም ባሉት መልሶቼ ''ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ...'' ስላደርኩህ ይቅርታ እጠይቃለሁ::
ወንድሜ በዘር ከፋፍሎ መግዛት ገዢው መደብም ተጠቃሚ አይመስለኝም ሌላው ቀርቶ:: ምክንያቱም ይህ አሰራር በየትኛውም ጎሳ ዘንድ ተወዳጅነትን አላተረፈለትምና::ይልቁንም በታሪክ ተወቃሽ ሊሆን ዜጎች ተቻችለው ተፈቃቅረው ተከባብረው ባንዲት ኢትዮጵያ ሊኖሩ ከእንግዲህ ሁኔታዎች ምቹ ይሆናሉ ክማለት ካልተቻቻልን እንፈራርሳለን የሚል አንቀጽ በህግ በማስቀመጥ እነሆ ያንጫጫናል:: እንደማይሆን ብናውቀውም እንጠራጠራለን ስለዚህም እኛ የምንለውን ወይም እንዲባል የምንፈልገውን ያልተናገረ ሁሉ ከፋፋይ ይመስለናል:: በመጀመሪያ ደረጃ በጥቂቶች ፍላጎት የምትፈርስ ሀገር የሚከፋፈል ህብረተሰብ የለንም:: ኢትዮጵያዊነት እንዲህ እነሲምባባ-ባ በተናገሩ ቁጥር የሚፈርስ የሚመስለን ካለን ቀድሞውኑ በውስጣችን ያላለቀ/ያልሰካነው peace of puzzel አለ ማለት ነው ::
ያም ሆነ ይህ ጥያቄውን በቅንነት ማየት ከቻልን የሚለው ይህንኑ ነው:: ዶ/ሩ ጎሳን የላካ ቁጥር ከማስቀመጥ ይልቅ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን የሞቱበት ምርጫ ቢሉት ባማረ ለማለት ነበር:: ሌላውን እውነት ግን ለዛሬ አቆየዋለሁ:: ያንተን ሀሳብ ደግሞ እጠብቃለሁ::
ሰላም ሁን
ሲምባ-ባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jul 12, 2005 2:59 pm
Location: ethiopia

Re: ጠያቂው ተጠየቅ?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Oct 19, 2005 10:00 pm

ሲምባ-ባ wrote:
ቱሉቦ wrote:ወንድሜ !

በአሁኒቱ ኢትዮጵያ በዘር ከፋፍሎ አገዛዝ ተጠቃሚው ማን ነው ?

ቱሉቦ

ፍትህ = ሰላም

__________________________________________
ቱሉቦ በመጀመሪያ ስነምግባርህን አድንቄ ቀደም ባሉት መልሶቼ ''ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ...'' ስላደርኩህ ይቅርታ እጠይቃለሁ::
ወንድሜ በዘር ከፋፍሎ መግዛት ገዢው መደብም ተጠቃሚ አይመስለኝም ሌላው ቀርቶ:: ምክንያቱም ይህ አሰራር በየትኛውም ጎሳ ዘንድ ተወዳጅነትን አላተረፈለትምና::ይልቁንም በታሪክ ተወቃሽ ሊሆን ዜጎች ተቻችለው ተፈቃቅረው ተከባብረው ባንዲት ኢትዮጵያ ሊኖሩ ከእንግዲህ ሁኔታዎች ምቹ ይሆናሉ ክማለት ካልተቻቻልን እንፈራርሳለን የሚል አንቀጽ በህግ በማስቀመጥ እነሆ ያንጫጫናል:: እንደማይሆን ብናውቀውም እንጠራጠራለን ስለዚህም እኛ የምንለውን ወይም እንዲባል የምንፈልገውን ያልተናገረ ሁሉ ከፋፋይ ይመስለናል:: በመጀመሪያ ደረጃ በጥቂቶች ፍላጎት የምትፈርስ ሀገር የሚከፋፈል ህብረተሰብ የለንም:: ኢትዮጵያዊነት እንዲህ እነሲምባባ-ባ በተናገሩ ቁጥር የሚፈርስ የሚመስለን ካለን ቀድሞውኑ በውስጣችን ያላለቀ/ያልሰካነው peace of puzzel አለ ማለት ነው ::
ያም ሆነ ይህ ጥያቄውን በቅንነት ማየት ከቻልን የሚለው ይህንኑ ነው:: ዶ/ሩ ጎሳን የላካ ቁጥር ከማስቀመጥ ይልቅ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን የሞቱበት ምርጫ ቢሉት ባማረ ለማለት ነበር:: ሌላውን እውነት ግን ለዛሬ አቆየዋለሁ:: ያንተን ሀሳብ ደግሞ እጠብቃለሁ::
ሰላም ሁን


peace of puzzel or piece of puzzle?
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests