እንደገና እንዋጋ ወይንስ ???

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

እንደገና እንዋጋ ወይንስ ???

Postby አገሩ » Mon Oct 17, 2005 6:46 am

ማሳሰቢያ ለውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ !!
የአቶ መለስን ጭንቀት ለመሸፈን ወይንም አጋጣሚውን ለመጠቀም ሲል የኤርትራው መሪ ኢሳያስ ጦሩን እያመሰ መሆኑን እየሰማን ነው::
ጠላትህን እወቅ!! 70000 ልጅህን ሰውተህ ያገኘኸውን ድል ለቅቀህ ውጣ ያለህ መሪህ ነው ዛሬም የጦር አዛዥ::
የኢትዮጵያ ድንበር ቀይ ባሕር ነው:: ይህንን አለም ጠንቅቆ ያውቀዋል:: መሪህ አልፈልግም ብሎ ነውጅ::
ስለዚህ ልጅህን ለጦርነት ከመማገድህ በፊት እውነተኛውን ለሃገር ተቆርቕሪ የሆነውን መሪህን ምረጥ::
ስለዚህ በመለስ አስተዳደር መሪነት ለጦርነት ብትነሳ ልጅህንም አገርህንም ነው የምታጣ::
ይህንን ሁሉ የሚያደርጉ ጀግንነትህንና ቆራጥነትህን ያወቁና እድገትህንና ብልጽግናህን ክጥንት ጀምሮ የማይፈልጉ የውጭ ጠላቶችሕ ናቸው::
ከአሻንጉሊት መሪ ተላቅቀህ አንበሳውን መሪህን ምረጥ:: ብዙ ብዙ አገር ለመምራት ብቁ የሆኑ ሴት ልጆችም አሉህ::
ብርቅየ የሆኑ እውቀታቸውን ለውጭው አለም እያፈሰሱ ያሉ አገር ገንቢ ልጆችሕን አሰባስብ::

ከሁሉም በፊት ፍላጎታችን ሰላምን ይሁን !!!

አሜን::
አገሩ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Sun Dec 05, 2004 3:57 am
Location: united states

አይጀመር በል እንጂ.....

Postby ሞልጨው » Mon Oct 17, 2005 12:31 pm

ጦርነቱ አይጀመር ብሎ መመኘት ይሻል እንደሆን እንጂ ከተጀመረስ ውስጥ ያለውን ሙግት ለግዜው ገታ አድርጎ ሻብያን እንደያኔው ማባረር ብቻ ሳይሆን መንግሎ መጣል የግድ ይሆናል! አሊያማ እየወደቀ እየተነሳ ያለው ወያኔን መጉዳት መስሎን ሻብያን መሀል አገር እስኪደርስ ዝም ልንል ነው? ነው መለስ ሌላ ያጋዚ ጦር ከ ኤርትራ እንዲመጣለት መፍቀድ? ኢሳያስ አይጀምረው እንጂ ከጀመረውስ ያሁኑ ለ 2 ለቱም የመጭረሻ እንደሚሆን አትጠራጠር!! በሰበቡ መሳሪያውን ማንገትም አንዱ ጥበብ ነው! ከሻቢያ በሗላ መዞር ወዳለበት ታዞረዋለህና! ከበፊቱ ቡዙ ተማርን መስሎኝ!! ጦርነት እንዳይጀመር ግን ከልቤ እሻለሁ: እጸልያለሁም::
selam le sew lijoch hulu
ሞልጨው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Fri Feb 11, 2005 10:36 am
Location: finland

Re: አይጀመር በል እንጂ.....

Postby አገሩ » Tue Oct 18, 2005 4:24 am

ሞልጨው wrote: በሰበቡ መሳሪያውን ማንገትም አንዱ ጥበብ ነው! ከሻቢያ በሗላ መዞር ወዳለበት ታዞረዋለህና! ::


በጣም ጥሩ ብለሀለ:: ብቻ መለስ ያንን ፈርቶ ሰራዊቱን በዚያው ካላስቀረው::
አገሩ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Sun Dec 05, 2004 3:57 am
Location: united states

Postby አባዊርቱ » Tue Oct 18, 2005 5:19 am

ጎበዝ, አንድ አባባል አስታወሰኝ!

'' በግርግር ፍየል እናቱን ሰረረ..''' ይባላል...ይቅርታ ሰለጸያፍ አባባሉ....እንግዲህ ፍየሉ ማን እንደሆነ ከታወቀ ውሎ አድሯል..ግን ተሰራሪው ዳግም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳይደለ ሻቢያም ሆነ ወያኔ ያውቁት ይመስለኛል....70000 የሞተው የመሀል አገሩ ልጅ ነው.....ወያኔ ለሻቢያ መገበሪያ አርጎ የሰጠብን....እንግዲህ ያርጉትና ጉዱ ይለያል....ምናልባት የአገር መለያችን ድንበሩ ትግራይ ላይ ይሆን ይሆናል...የትግራይ ልጆች እሺ ብለው ለነዚህ አገር ገዳዮች ከተገዙ....ሞኝ አንሁን: ሻቢያና ወያኔ ተጣልተውም አያውቁም...አንድ አይደሉም ወይ?? ይቺ የጦርነት እስክስታ ማዘናጊያ ትባላለች...ዳግም ጭዳ የሚሆን የወገን ልጅ ግን ከቶ ሊኖር አይችልም!!
በነገራችን ላይ ሰሞኑን የማነበው የዛሬ 10 አመት ገደማ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ የተባሉት የጻፉትን The pillage of Ethiopia የሚለውን ነው...ያኔ እንዲየው ላይ ላዩን ነበር ያየሁት እንደገና አጣጥሜ ሳነበው ሰውየው እውነትም ሊቅ ናቸው...አንዳንዶቻችን ነፈዞች ነገሩ ከ 10 አመት በሁዋላ ነው አይናችን የሚገለጥልን ያለው...እነዚህ ጉዶች እኮ ከቀበሩን ሰነባብተዋል...ወይ አገሬ እንዲህ ሞተሽ አትቀሪያትም!

ኤታማዦሩ!
ነገሩ መላልሶ, መላልሶ ቅጥል እያረገው ያለው!
ነገም ተስፋ ነው ብቻ!
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

Postby maki » Tue Oct 18, 2005 5:40 am

እንኩዋን ባድማ ቀይ ባህርም ሄዶ የለ እንዴ? አሁን ቀይ ባህር ላይ ከሻቢያና ከወያኔ ጋር ሲዋጉ የሞቱትን የሚያስባቸው አለ??? የገሬ ሰው ምን ቦጣው እንደገና ለባድማ የሚሞተው??????

ወያኔ እንዳመጣው ወያኔ ይጨርሰው!
maki
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Sun May 02, 2004 1:12 am


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 6 guests

cron