ሪፖርተር ....ህምምምም

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሪፖርተር ....ህምምምም

Postby ማይ ኔም » Mon Oct 17, 2005 8:29 pm

selam all,
I recommend you to read the following link, about how Reporter news paper is supporting Dictatorship in our country.


http://www.ethiopianreporter.com/module ... le&sid=106
ማይ ኔም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 164
Joined: Thu Mar 17, 2005 6:16 pm
Location: united states

Postby ጥልቁ1 » Mon Oct 17, 2005 10:39 pm

ማይ ኔም : ለጥቆማህ እያመሰገንሁ ፣ ስለሃተታው የምለውን ልበል፡

በእውነቱ ፣ የጽሁፉ አቅራቢ ፣ እጅግ እውነትን የሚሻ ፣ ጥሩን ከመጥፎ አገናዛቢ እና መተቸት ብቻ ሳይሆን ማድንቅም የሚችል ሚዛናዊ ሰው መሆኑን ጽሁፉ ይናገራል። የዚህ ጸሃፊ አንድ ችግር መስሎ የታየኝ ፣ ሪፖርተርን በስጋ ለባሽ ፍጡራን የሚተዳደር እና ትክክለኛ የጋዜጣው /መጽሄቱ ምንጭ ማን እንደሆነ አለማገናዘቡ ነው። ለማብራራትም ያህል…

ለምሳሌ ፣ ጸሃፊው ሪፖርተር ጋዜጣን የሚያደንቅባቸው ሁሉ ነጥቦች ፣ ከጋዜጣው የሚያገኛቸው መረጃወች እጅግ ጥሩ እና ፋይዳ አዘል መሆናቸውን ገልጻል። ይህንን እንዲል የሚያደርገው ደሞ ፣ በሪፖርተር ላይ የሚነበብን አይነት መረጃ ፣ ሌሎች ምስኪን የፕሬስ ውጤቶች ላይ አለመነበባቸው ነው። አንድ ነገር ልብ ማለት ያለብን ግን ፣ ሪፖርተር ያንን መረጃ እንዲያገኝ ያደረገው ፣ የተለየ የሙያ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ኖረውት ሳይሆን ፣ የጋዜጣው ባለቤት ለወያኔ ፖለቲከኞች ያለው ታሪካዊ ቅርበት ነው። ይህንን የሚጠራጠር ካለ ወደ ታች ወረድ ብሎ የምጽፈውን ማንበቡ አይጠቅመውምና ከዚህ ላይ ይሰናበተኝ።

ከላይ ያስቀመጥሁት … ‘የጋዜጣው ባለቤት ለወያኔ ፖለቲከኞች ያለው ታሪካዊ ቅርበት ነው’ አረፍተነገር ፣ የጋዜጣውን ታሪካዊ አመጣጥ እና አካሄድ ይገልጸዋል። ስለዚህ ፣ ስጋ ለባሽ የሆነውን የጋዜጣ ባለቤት ፣ የፍጹም የጋዜጠኛን እስትንፋስ የምንጠብቅበት ከሆነ ፣ ለአዘጋጁም ይከብደዋል ፣ አንባቢያንም እራሳችንን ማገናዘብ ከብዶናል ማለት ነው። ለምሳሌ ፣ የአስተያየቱ አቅራቢ ፣ ያስቀመጠው ሃተታ ሁሉ እውነት ቢሆንም ፤ የሪፖርተርን ወያኔያዊነት ከማንጸባረቁ ጀርባ ፣ ጸሃፊውም የወያኔን ባዶነት እና እራሱም ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የቆመ ኢትዮጵያዊ ነው ማለት ይቻላል። እንደዚያ ባይሆን ኖሮ ፣ ምን ሊሰራ ይህንን ያህል በጽሁፍ ይደክማል ?!

ሪፖርተር ለሚያቀርበው መረጃ ሊመሰገን ይገባዋል ፣ ምክንያቱም መረጃወቹ ስለሚጠቅሙ። በዚህ አጋጣሚ ፣ እኔም እንደሪፕርተር ጋዜጣ የማነበው የለኝም።
ነገር ግን ፣ መረጃውን የሚያቀርበው ለመሸጥ እንጅ ለነፍስ እንዳልሆነ እና ፣ የሚያቀርበው መረጃም ፣ የወያኔን እድሜ በማያሳጥር መልኩ እንዲሆን ታቅዶ የሚቀርብ መሆኑም ሊታወቅ ይገባዋል። ለምሳሌ ፣ የአሜሪካኖች ተንኮል ሁሉ ፣ በዜና መቅረብ የሚጀምረው ፣ ተንኮላቸውን ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ እንደሆነ ሁሉ ፣ እስኪ ሪፖርተር ቀድሞ ያመላከተው እና ወያኔን ሊጎዳ የሚችል መረጃ እንደ ምሳሌ ይቀመጥ ?! የሚገኝ አይመስለኝም።

ሪፖርተርን ልብ ብለን አይተን ከሆነ ፣ ወያኔን የሚያናጋ ንቅናቄ በተፈጠረ ሰአት ፣ ጥንቃቄውም ያን ያህል የጎላ ይሆናል። በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፣ በአገራቸው ጉዳይ ላይ ምንም አያገባቸውም የሚል ድምዳሜ ላይ የደረሰበት ርእሰ -አንቀጽ ፣ ፍጹም ሃቅን ያላገናዘበ እና የርእሰ -አንቀጽ መስፈርትንም የማያሟለ ነው።
አንድ ርእሰ -አንቀጽ መጠንቀቅ ካለበት አንዱ ፣ ሁሉን ነገር በጥቅል ከማየት መታቀብ ነው። በህውሃት ክፍፍል ጊዜም ፣ ጥሩ የሚጣፍጡ ጽሁፎች ያስነብበን እና የሚያበረከቱት አስተዋጽኦ ግን ከታሪክነት ያለፉ አይደሉም።

ሌላው አንድ የታዘብሁት የወያኔወች ስራ ፣ ጥሩ መስለው የሚታዩ ነግሮች ሁሉ በእነሱ ውስጥ እንዲያልፍ መሞከራቸው ነው። ራዲዮ ፋና የሚያደርገውን ባዶ ፕሮፖጋንዳ የሚሸፍንባቸው ፣ ሌሎች አስደሳች የሬዲዮ ፕሮፕግራሞች ማካተቱ። ትላንት ፣ የአዲስ አበባን ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያዊያን ዲኖች ሲያገለግሉት ታይቶ የማይታወቀው የውይይት መድረኮች ፣ ዛሬ ወያኔው ኢንድሪያስ እሸቴ ሲመጣ ፣ ዩኒቨርሲቲውን የዲሞክራሲ መድረክ ያለው ለማስመሰል መሞከር ፤ እና ሌሎችም።

ሃሳቤን የማጠቃልለውም ፣ የሚቀርቡ የጋዜጣ ርእሰ -አንቀጾች ፣ እኛነታችንን ወደ ተሳሳእተ መንገድ እንዳይመሩን የሚረዳን ፣ የሚጻፉት እራሱ ኑሯቸው ጋዜጣ ሸጠው ለመኖር በሚዳክሩ ግለሰቦች መሆኑን ማሰብ ነው። ‘ለህሊናው የሚኖር ምድርን ይልቀቅልን’ የሚለውን ልብ ይሏል። ምክንያቱም ምድር ፣ ለህሊና የሚኖርባት አይደለችምና።
ቸር እንቆይ !
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

Postby ዘርዐይ ደረስ » Mon Oct 17, 2005 11:30 pm

ጥልቁ1 wrote:
ሃሳቤን የማጠቃልለውም ፣ የሚቀርቡ የጋዜጣ ርእሰ -አንቀጾች ፣ እኛነታችንን ወደ ተሳሳእተ መንገድ እንዳይመሩን የሚረዳን ፣ የሚጻፉት እራሱ ኑሯቸው ጋዜጣ ሸጠው ለመኖር በሚዳክሩ ግለሰቦች መሆኑን ማሰብ ነው። ‘ለህሊናው የሚኖር ምድርን ይልቀቅልን’ የሚለውን ልብ ይሏል። ምክንያቱም ምድር ፣ ለህሊና የሚኖርባት አይደለችምና።
ቸር እንቆይ !


ሰላም ጥልቁ:-
ያቀረብከውን ትንተና ከላይ ኮት ካደረግኩት በቀር እኔም እጋራለሁ::
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1090
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ማይ ኔም » Tue Oct 18, 2005 12:25 pm

ሰላም ወገኖች

ጥልቁ ሰለ ጥልቅ አስተያያተህ አመሰግናለሁ,
ማይ ኔም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 164
Joined: Thu Mar 17, 2005 6:16 pm
Location: united states


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests