ያደረጉትን ያድርጉኝ!!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ያደረጉትን ያድርጉኝ!!!

Postby ጉማ » Mon Oct 17, 2005 10:50 pm

ሳጥናኤል ሲምል : እግዜርን እያለ
ስንቱን የእግዚአብሔር ሰው : ልቡን አማለለ
ኢትዮጵያም ደረሳት : ይኸው ዕጣ ፈንታ
ሰንደቋን ረግጦ : እጇን የሚመታ
ዴሞክራሲም ገብታ : ከመሃላ መዘዝ
ማኅተም ሆና ቀረች : ለጨቋኝ አገዛዝ
ነጻነትም ታየች : ከመሃላ ተራ
የሞት ዕጣ ሰብቃ : ነፍስን ስትጠራ
አልገባ ያለችው : ከመሃላ ወጥመድ
እምቢኝ ብቻ ቀረች : ሳትቀለማምድ
በሯን ጥርቅም አድርጋ : ለሃሰት ሳትሰግድ
ያደርጉታል እንጂ : አይምሉም በእምቢኝ
እምቢኝ ልበልና : ያረጉትን : ያርጉኝ
Tesfa Z Guma
ጉማ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Wed Oct 12, 2005 4:59 am
Location: united states

Postby ጥልቁ1 » Tue Oct 18, 2005 7:05 am

አሁን ምን ይገርማል ሰይጣን ቢል በእግዚያብሄር
እንደሆነ ሲያውቀው እሱም የአምላክ ፍጡር?

እንዴውም ደስ ይላል የሰይጣን መሀላ
ይሄው አስተማረን ስለከይሲው ሁላ::

ጣሊያን እጅ ነስቶ ከአድዋ ማማ
መለስ የአድዋው ልጅ ቢረግጥ ያንን አርማ;
ጣሊያንን ሊማርክ እሱም በግልብጡ
ማንነት መካዱ ታሪክ መሸምጠጡ ;
አይሁድ አዳኝውን ጌታን እንደወጋ
ይሄም ትምህርት ነው የተፈጥሮ ጸጋ::

የእምቢታውን ነገር እኔም እስማማለሁ
ዳሩ ማን ሊሰማኝ ዋርካ ውስጥ እምቢ ባልሁ?
የእምቢተኛ ልጆች መቶ ተዋሱና
መጠጡን አብዝተው ሲሉ ሽና ሽና
ሽ 'አድርገው ከፈሉት ለራዲዮ ፋና::

እምቢ እንጃ ማለትም ፋሽኑ ተበልቶ
ሰርቶ መበያውን ቅን እጅቱን ሰጥቶ
ሲሞት የሚቀብር በህብረት መስርቶ
ዘንጋዳ የዘራው በቆሎ ኮትኩቶ
ለውጥ እንዳላማረው ቀረ ጤፉን በልቶ::

ሚስትን ላያሸኙ ለሌባ ወስላታ
ሰይፍን ለሞረደ እጅን ለሰላምታ
በራስ ላይ ማሳቅ ነው የማታ የማታ::

ለወያኔ ቢጤ ለቀሊለ ታሪክ
ትግስት ለሚመስለው ለመብት መፍረክረክ
በቃህ እንጃ እንጅ በአደባብባይ በሰርክ ;
እንዴው ቢናገሩ የሰላምን ቋንቋ
ቁፋሮ ማገዝ ነው መቀበሪያ አረንቋ::


ቸር እንቆይ!
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests