ከሰላማዊ ትግሉ ጎን ጡንቻም ያስፈልጋል

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ከሰላማዊ ትግሉ ጎን ጡንቻም ያስፈልጋል

Postby ጥራኝ ደኑ » Tue Oct 18, 2005 5:54 am

እነ ዶክተር መራራና ዶክተር በየነ ጰጥሮስ ወከባውን መቃቃም ስላቃታቸው የመረጣቸውን ህዝብ ሳይሆን የመለስን ተዕዛዝ ተቀብለው ቅንጅትን ብቻውን በመተው ፓርላማ ገቡ አብዛኞቹ የቅንጅት አባላትና ደጋፊዎች አሁንም እንደታሰሩ ናቸው:በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ደማቸው የፈሰሰ ህይወታቸው በኢህአድግ ጥይት ያለፉትስ የደምና የህወት ዋጋ ሳንስከፍል ልንቀር?ወጣቱ ትውልድ የመለስን መንግስት አሽቀንጥሮ ለመጣል ዝግጁ ነው:
ችግሩ የሚያስተባብረው ድርጅት አለመኖሩና አንዳንድ ምሁራኖች ብዙ መስዋዕትነት ያስከፍላል ብለው መገመታቸው ነው:ዳሩ ግን ከበርሀ የመጡት ወንበደዎች አብዛኞቹ 50 አመት ያለፋቸውና ወደ 60 የተጠጉ ናቸው የአገሪቱን ሀብትና ንብረት ተከፋፍለው ባለካፓኒ እና ባለትልቅ ንብረት በመሆናቸው ዳግመኞ መዋጋት አይፈልጉም ቢያስቡም
አይችሉም ምቾት ለምደዋል ወፍረዋል እውነት እውነት ልንገራችሁ የመለስ ጉልበቱ ባዶ ጉራና ምላሱ ብቻ ነው: በ 14 አመት ውስጥ የሰበሰባቸው ምልምል ወታደሮች የመለስን ከሀዲነትከተረዱ ቆይተዋል ወያነ እኮ ጾረና ላይ ታይታል ነባሩን ሰራዊት የድረሱልን ጥሪ ያቀረበው የኢርትራን ኅይል ብቻውን መዋጋት ባለመቻሉ ነው: በትጥቅ ትግሉ በ አነስተኞ የሰው ኅይል በአፋጣኝ የመለስን መንግስት
ማፈራራስ ይቻላል ወገኖቸ ወያነ በፈቃዱ መቸውንም ጊዘ ስልጣን አያስረክብም አጉል ወገኖቻችንን በሰላማዊ ትግል ስም አናስገድል
እስቲ ስለ ትጥቅ ትግል ችሎታ ያላችሁ አድሚን በመሆን ፓልቶክ ከፍታችሁ እንወያይበት ህዝቡ የሚመራው ድርጅት ካልፈጠርንለት ገንዘብ ካላሰባሰብንለት ትግሉን እንደት መጀመር ይችላል የማደራጀቱና ገንዘብ የማሰባሰቡ ሀላፊነት የወደቀው በ እኞ ላይ ነው
ጥራኝ ደኑ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 25
Joined: Tue Oct 18, 2005 4:51 am
Location: ethiopia

Postby ሞልጨው » Tue Oct 18, 2005 6:10 am

እርግጠኛ ነኝ የ አረጋኽኝ ወራሽን ""ተነስ ታጠቅ ዝመት ተደፍሯል እና ያገር ነጻነት............."" የምትለዋን ዜማ እየሰማህ ነው ይቺን ፖስትህን ወደዋርካ ያሰናበትካት አይደል?

ዶክተር ብርሀኑ አሁን በቅርብ ሲውዲን የመጣ ግዜ እንዳንተ አይነት ሰዎች ምን ብለው ጠየቁት መሰለህ? አንተ በጣም ለዘብተኛ እየሆንክ ትግሉን እያዳከምከው ነው! ለምን ትግሉን ታበርደዋለህ? ትግሉን ማፋፋም ነው የምንሻው.......... ቀጠሉ እስኪበቃቸው አዳመጣቸው እና ምን እንዳላቸው ታውቃለህ?

እንግዴያውስ ትግሉ አሁን ከተያያዝነው በላይ እንዲፋፋም ከፈለጋችሁ ወይም እናንተ በፈለጋችሁት መንገድ እንዲቀጥል ከሆነ የምትሹት እዚህ ምን ትሰራላችሁ? ነገ ዛሬ ሳትሉ ሱዳን, ኬንያና, ሱማሌ ድንበር ላይ ለምን አንገናኝም? የትጥቅ ትግል ከሆነ አማራጩ ተነሱ ነበር መልሱ::

ላንተ ሌላ መልስ ያስፈልግ ይሆን? ባህር ማዶ በሰላም ቁጭ ብሎ የደሀን ደም ለማስፈሰስ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት የተበላበት እቁብ ነውና አንተም ሱዳን ድንበር እንገናኝ!!
selam le sew lijoch hulu
ሞልጨው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Fri Feb 11, 2005 10:36 am
Location: finland

Postby ጉማ » Tue Oct 18, 2005 7:50 am

ጥራኝ ደኑ:
ያቀረብከውን የመፍትሔ ሀሳብ እንደ ሀሳብነቱ የማንወያይበት ምክንያት ያለ አይመስለኝም:: እኔን እንደሚገባኝ ለችግራችን የመፍትሔ ሀሳብ ማለት : ለበሽታችን መድሐኒት እንደማለት ነው:: አገር ቤት ላለ በሽተኛ ፈውስ የሚሆን መድሐኒት : አሜሪካን ያለ ዶ/ር አዘዘው ጀርመን ያለ ሐኪም አዘዘው ፈውስነቱ ያው ነው:: ባይሆን መድሐኒቱ አገር ውስጥ ከሌለ ካለበት ቦታ ማስመጣቱ ይሻላል::
ሞልጨው ብትረዳ ደስ የሚለኝ : ዶ/ር ብርሀኑ ስዊዲን ሄደው ኢትዮጵያውያንን ሲያነጋግሩ : ካንተ እንደተረዳሁት በዚህ ትግል ውስጥ እርሳቸው ውጪ በሚኖረው ሕብረተሰብ ላይ የሞራል የበላይነት እንዳላቸው የሚያምኑ ይመስለኛል::
በአገር ጉዳይ የሞራል ዘበኝነት ያተረፈልን ነገር ቢኖር አምባገነንነት እና ትምክህተኛነትን ብቻ ነው::
የትጥቅ ትግል ያዋጣል ወይስ አያዋጣም ለሚለው ጥያቄ : መልሱ ማነው ጠያቂው ሊሆን አይችልም::
በዶ/ር ብርሀኑ መልስ ሱዳን እና ኬንያ ድንበር መጠቀሳቸው አሳፋሪ ነው:: እንኳንም የዶ/ር ብርሀኑ አስተማሪ አላደረገኝ:: በዓለም ላይ እንደ ዶ/ር ብርሀኑ በተደጋጋሚ የሚሳሳት ሰው ያለ አይመስለኝም:: ስለ መስዋዕትነትና ደም መፋሰስ ከሆነ የሚያወሩት እርሳቸው በሚመሩትም 'ሰላማዊ ትግል' : መሀል ከተማው ጭምር ደም እየተንዠቀዠቀ ነው:: ምናልባትም እስካሁን የተከፈለው መስዋዕትነት እኮ በተደራጀ መልኩ ቢሆን ኑሮ ለድል ያበቃን እንደንበር አስበነው እናቃለን?
እንደ እኔ እንደኔ እነ ዶ/ር ብርሀኑ ትግሉ ገና ተጀመረ እያሉን ነውና : እስከ ዛሬ የተከፈለው መስዋዕትነት ላልተጀመረ ትግል ነው ማለት ነው:: እንደዚያ ከሆነ ቢያንስ ወደፊት ስለሚከፈለው መስዋዕትነት በምን መልኩ : ብለን መነጋገር አግባብነቱ አያጠያይቅም::
ወንድሜ ሞልጨው በነገርህ ላይ ወያኔን በትጥቅ ለመፋለም ሱዳን ድንበር መሄድ ለምን አስፈለገ? ዛሬ እኮ ወያኔ እንደ ዱሮው ሱዳን ድንበር ላይ አይደለም አራት ኪሎ እንጂ!!!
ብቻ ዋናው በልብ ምሸፈቱ ላይ ነው:: ጦር ይዞ ከሸፈተ ሠራዊት ለቡ የሸፈተ ሕዝብ አሸናፊ ነው!! የሚለውን ብሂል ልብ እንበል::
በደማችን ድል ለሕዝባችን!!!
Tesfa Z Guma
ጉማ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Wed Oct 12, 2005 4:59 am
Location: united states

ለ ወንድሜ ጉማ

Postby ሞልጨው » Tue Oct 18, 2005 10:23 am

ምላሽህን በጥሞና አነበብኩት ግን በሀሳብ ትንሽ የተራራቅን መሰለኝ! እኔ የዶክተሩን ምላሽ ለምሳሌ ተጠቀምኩበት እንጂ ትክክል ናቸው ወይም አይደሉም የሚል ድምዳሜ ላይ አልደረስኩም! ወደ ዋናው ሀሳብ ግን ስንገባ የትጥቅ ትግል አስፈላጊ ነው ካልን ማነው ጀማሪ ተኳሽ? ማነው ጀማሪ ታጣቂ? ማነው ግንባሩን ቀድሞ የሚሰጥ? ይህ ነው የኔ ጥያቄ! አንተ እንዳልከው ልክ እንደመድሀኒቱ ጦርነቱንም አሜሪካና ጀርመን ሆኖ ማዘዝ ይቻላል የሚል ሀሳብ ግን አይደልም ዛሬ 20ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ሆነን ቀርቶ ከ 100 አመት በፊት ተወልጄም ቢሆን እንኳን የማምንበት ሀሳብ አይደልም በጭራሽምም! እንግዴህ ጥሌ እዚህ ጋር ነው ለዛ ደሀ እና ምንም ጠብ ለማይልለት ህዝብ ጦርነት አማራጭ ነው ብለን ሆ ብሎ እንዲነሳ ጠርተን እኛ ሰላማዊ ኑሮዋችንን መኖርን ነው? እስኪ በጦርነት ያውም ደሀ ሞቶ ለውጥ መጣ እንበል ምን ይሆን ደሀ የሚጠብቀው ተስፋ? ሌላ ሞት ካልሆነ ምንም እንደማይሆን ልባችን እኮ ያውቀዋል! እናም ያለ ደም መፋሰስ እና የከፋ እልቂት የሚደረጉ ሙከራዎች ሁሉ እንዲቀጭጩ ለምን ይፈለገል? እንዴትስ እኛ በድሎት እየኖርን ደሀን ለእልቂት እናመቻቻለን?

አሁንም ማንኛውም ሰላማዊ ትግልን እደግፋለሁ! ግንባራቸውን ላይሰጡ ተነስ ታጠቅ ዝመት የሚሉትንም አጥብቄ እቃወማለሁ! እስከመጨረሻው! የትጥቅ ትግል አማራጭ ነው የሚሉን ቀድመው ምላጭ ይሳቡና ያሳዩን ባይ ነኝ!!
selam le sew lijoch hulu
ሞልጨው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 117
Joined: Fri Feb 11, 2005 10:36 am
Location: finland

Re: ከሰላማዊ ትግሉ ጎን ጡንቻም ያስፈልጋል

Postby የዘመኑ ልሳን » Tue Oct 18, 2005 5:50 pm

ጥራኝ ደኑ wrote:እነ ዶክተር መራራና ዶክተር በየነ ጰጥሮስ ወከባውን መቃቃም ስላቃታቸው የመረጣቸውን ህዝብ ሳይሆን የመለስን ተዕዛዝ ተቀብለው ቅንጅትን ብቻውን በመተው ፓርላማ ገቡ አብዛኞቹ የቅንጅት አባላትና ደጋፊዎች አሁንም እንደታሰሩ ናቸው:በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ደማቸው የፈሰሰ ህይወታቸው በኢህአድግ ጥይት ያለፉትስ የደምና የህወት ዋጋ ሳንስከፍል ልንቀር?ወጣቱ ትውልድ የመለስን መንግስት አሽቀንጥሮ ለመጣል ዝግጁ ነው:
ችግሩ የሚያስተባብረው ድርጅት አለመኖሩና አንዳንድ ምሁራኖች ብዙ መስዋዕትነት ያስከፍላል ብለው መገመታቸው ነው:ዳሩ ግን ከበርሀ የመጡት ወንበደዎች አብዛኞቹ 50 አመት ያለፋቸውና ወደ 60 የተጠጉ ናቸው የአገሪቱን ሀብትና ንብረት ተከፋፍለው ባለካፓኒ እና ባለትልቅ ንብረት በመሆናቸው ዳግመኞ መዋጋት አይፈልጉም ቢያስቡም
አይችሉም ምቾት ለምደዋል ወፍረዋል እውነት እውነት ልንገራችሁ የመለስ ጉልበቱ ባዶ ጉራና ምላሱ ብቻ ነው: በ 14 አመት ውስጥ የሰበሰባቸው ምልምል ወታደሮች የመለስን ከሀዲነትከተረዱ ቆይተዋል ወያነ እኮ ጾረና ላይ ታይታል ነባሩን ሰራዊት የድረሱልን ጥሪ ያቀረበው የኢርትራን ኅይል ብቻውን መዋጋት ባለመቻሉ ነው: በትጥቅ ትግሉ በ አነስተኞ የሰው ኅይል በአፋጣኝ የመለስን መንግስት
ማፈራራስ ይቻላል ወገኖቸ ወያነ በፈቃዱ መቸውንም ጊዘ ስልጣን አያስረክብም አጉል ወገኖቻችንን በሰላማዊ ትግል ስም አናስገድል
እስቲ ስለ ትጥቅ ትግል ችሎታ ያላችሁ አድሚን በመሆን ፓልቶክ ከፍታችሁ እንወያይበት ህዝቡ የሚመራው ድርጅት ካልፈጠርንለት ገንዘብ ካላሰባሰብንለት ትግሉን እንደት መጀመር ይችላል የማደራጀቱና ገንዘብ የማሰባሰቡ ሀላፊነት የወደቀው በ እኞ ላይ ነው


እኔም በዚህ ሀሳብ መቶ በመቶ እስማማለሁ::
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

ተዋግቶ መሞት ወይስ በአደባባይ መረሽን

Postby ጥራኝ ደኑ » Tue Oct 18, 2005 6:51 pm

የሚገባህ ከሆነ በቀላሉ ላስረዳህ:ኢትዮጵያውያን
3 ጠላቶች አላቸው 1) የወያነ/ኢህአድግ አማባገነን መንግስት 2)የኢድስ በሽታ 3) ድህነት ናቸው:
ሶስቱም በመተባባር ወገናችንን ለሞት እየዳረጉት ነው:በኢህአድግ አመራር ድህነት አይጠፋም ለኢድስ በሽታም ፈውስ አይገኝም: አልፎ ተርፎ ወገን በአድባባይ በኢህድግ ጥይት እየተረሽነ ነው
በእስር የሚንገላቱት በጣም ብዙዎች ናችው:የታሪክ አተላ ወያነን ተሸክሞ መኖር የኢትዮጵያዊ ባህሪ አይደለም: ኢትዮጵያዊ ለክብሩና ለመብቱ የመዋደቅ ታሪኩ ከጥንት ያለ ነው:በስላም ትግል ዉጠት ካልተገኘ መለስና ግብር አበሮቹ የህዝብን ክንድ ሊቀምሱ ይገባል ጦርነት እንዳይነሳ በ እጅጉ የሚፈራው ወያነ ብቻ ነው ምክናያቱም ምንም የጎደለበት የለም በአድስ አበባ ብቻ 300,000 የጎዳና ተዳዳሪዎች አሉ በየመኪና ማቆሚያ ላይ የሚለምነው ወጣት አንተን መሰል የወያነ/ ኢሀድግ አጋሰስ እየተናነቀ ቢሞት የክብር ሞት ነው በአደባባይ የተገደሉትንስ 42 ሰዎች ረሳሀቸው የዉሻ ወይም የአህያ ደም መሰለህ የጀግኖቹ የ አንበሶቹ ኢትዮጵያዉያን ደም እኮ ነው: አውሮፓ በመኖር የደላኝ እንዳይመስልህ ደግሞስ አውሮፓ የሚኖር አይዋጋም ያለህ ማነው. የአማሪካና የእንግሊዝ ወታደሮችን በተለቪዢን ተመልከት ዋናው ቁም ነገር እኞ ጀግናና ተዋጊ አላጣንም ያጣነው አደራጅና የገንዘብ እርዳታ ነው: ይህን በሚመለከት እርዳታ ብንሰጥ እንደተዋጋን ይቆጠራል
ጥራኝ ደኑ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 25
Joined: Tue Oct 18, 2005 4:51 am
Location: ethiopia

Postby አንጅባ » Wed Oct 19, 2005 3:58 pm

ጥራኝ ደኑ በሀሳብህ አስማማለሁ በኔ በበኩሌ የምለው ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ከህጻን እስከ አዋቂ ሳይማር ፖለቲከኛ ሁኗል ማለት እችላለሁ ይበቃል ካሁን በሁዋላ መነጋገር ወይም ስለፖለቲካ በየ ሰፈሩ እና በየ ሚዲያው ማውራት ሳይሆን የተግባር ሰው መሆን ነው ያቃተን ዝም ብሎ ወያኔ ወያኔ ብንል ትርጉም የለውም ወያኔም እኮ ከዚህ ቦታ ሲደርስ እኛ ባን ፈልጋቸው እንሱ የሚፈልጎአቸው ስንት ሰወቻቸውን አጥተው ነው ከዚህ የዳረሱ ታድያ እነ አቶ መለስ ባልተማረ አንደበታቸው ይህን ቦታ ዝምብለው እንዴት ይለቃሉ ለማንኛውም ሱዳን ሆነ ኬንያአንውራ ወጥተን እንየው ድልለኢትዮጵያ ህዝብ አሜን
አንጅባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 22
Joined: Sun Sep 18, 2005 8:03 pm
Location: ethiopia

Postby አንጅባ » Thu Oct 20, 2005 10:29 am

ወልቂጡማ 1ኛ ደረጃ ለማን እንደሆን አይታወቅም ከዚህ የሚሳተፉሁሉ መልስ አላቸው ስለዚህ ለማን ስትፅፍ ግለፅ አድርገው ሊላው ፈሪለምትለው ደግሞ አንተከየትኛው በርሀ ሁነህ ነው የምታቅራራው ?
አንጅባ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 22
Joined: Sun Sep 18, 2005 8:03 pm
Location: ethiopia

ኣቦ ስንት ፉፈኛ ነው የሞላው በዚህ መድረክ ከለፍልፍክ አይበቃህም ::

Postby አዲስዋ » Tue Oct 25, 2005 2:17 am

:twisted: :twisted: :twisted: :twisted:
አዲስዋ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 22
Joined: Thu Oct 20, 2005 12:27 am
Location: sweden


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 8 guests