በዋርካ ውስጥ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያኖች !!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በዋርካ ውስጥ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያኖች !!

Postby Fesame » Thu Oct 20, 2005 1:20 pm

ይህን ለመጻፍ የተገደድኩበት ዋናው ምክንያት በአንድ ወገን ብቻ እየታየ እና እኛ ያልነው ካልሆነ በሰማይ ቤት አይሰራ እየተባለ የሚጮህበት መድረክ እየሆነ በመምጣቱን በጣም ሰላሳሰበኝ ብቻ ነው::

ዋርካ ከህዝብ ጋራ መገናኛ ጥሩ መንገድ ሊሆንን ይችል ነበር በደንብ ከተጠቀምንበት :---------

ዋርካ ላይ የምንገባው ብዙዎቻችን እንደተገነዘብኩት ከሆነ መራቃችንን ዋጥ ያደረግን ሰዎች መሆናችን በቀላሉ በምትጽፉት መልክት መረዳት እችላለሁ ግን የማይገባኝ ነገር ቢኖር :-

1) ለምን ጥላቻን በዚህ መደርክ ላይ እንዲስፋፋ እና እንዲወራ ብቻ ይደርጋል ??

2) ያለው መንግስት በህዝብ የተመረጠ አይደለም ሁላችንም እንስማማለን የኢትዮጵያ ህዝብም በቃኝ ብሏል ! ግን ለምን በአግባቡ ጨዋነት በተላበስ መንገድ አንቃወምም ? መልክት አናስተላልፍም !?

3) ለምን የመፍትሂ ሀሳቦችን አናቀርብም ሁል ግዜ ከተመሳሳይ ጭቅጭቅና ንትርክ ትውልድን ከማይጠቅም ወሬና አሉባልታ !!

4) ትምህርታዊ የሆኑ ጹሁፎችና ለመሳተፍ የሚማርኩ መጣጥፎች ቢቀርቡ ለውይይት የሚጋብዙትን ማለቴ ነው!! እንዲሆኑ አንሞክርም ከእኔ ጀምሮ !?

ይህን ለማለት ያስገደደኝ የእኔ ትውልድ የሆናችሁት በጠቅላላ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሳንጠቅማት እርስ በራሳችን ተጫርስን ፍሬ አልባ ሁነንና በሰው ሀገር ተሰድን እየኖርን አሁንም እኛው በምንፈጥረው ፍጥጫዎች እና የፓለቲካ ቀውሶች ህዝባችን እንዳንጎዳው እስጋለሁኝ !!

ለማንኛውም በዋርካ ውስጥ በአንዳድ ነጥቦችን እያነሱና ጨዋነት በተላበስ መንገድ ለማወያየት የሚሞክሩትን ወንድሞቼን ሳላመስግን አላልፍም ::


ምስጋና ለእነዚህ ወንድሞቼ ይድረስ ብያለሁኝ !!

ዱርንስብት, ጥልቁ1, ዋቆ, ወርቅስው, ልጅነኝ

ሁላችንም ሰለሀገራችን የምንመኘውን የምንቃወመውን መናገር መብታችን እየሆነ ሳለ ግን በአግባቡ ማስተላለፍ ካልቻልን ግን የድክመታችን ምልክት መሆኑን እንዳንዘነጋው እወዳለሁኝ !!!


መልካሙን ሁላ ለኢትዮጱያ ህዝብ እመኛለሁ !!
Fesame
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Fri Sep 03, 2004 11:15 pm
Location: united states

Postby ናይክ » Thu Oct 20, 2005 4:34 pm

ሰላምታን በማስቀደም አጭር መልስ ለመመለስ እወዳለሁ::
ከአስተያየትህ በሳልነትህን ብሎም አስተዋይነትህን መረዳት ብችልም አንድ ያላስተዋልከው ነገር እንዳለ በቀላሉ መረዳት ችያለሁ ይህም.............

1ኛ ታጋሹ የኢትዬጵያ ህዝብ ወያኔ ለርስ በርስ
ጦርነት ሊማግደው ሲያመቻቸው ባርቆ አስተዋይ
ነቱ ትግስትን መምረጡን....

2ኛ እኛ ኢትዬጵያውያኖች የአመጽም ሆነ የረብሻ ባህል ኖሮንም ሊኖረንም አይችልም......

3ኛ አንተዛሬ ልትመክረን ያቀረብከውን ህሳብ ቀድሞ ለ 17 አመታት አሁን ለ14 አመታት ስናንጸባርቀው መኖራችንን.......

4ኛ 17 + 14=ለ 31 አመታት ማለትም ከእሩብ ምእተአመት በላይ ህዝቡ ያሳየው ትእግስት....

እነዚህ እና ሌሎቹ ተደምረው ዛሬ ኡኡ በቃን መረረን ብለን ብንጮህ ጥፋታችን ምኑላይ ነው?????

ነው ወይንስ እንደነ መለስ(ለገሰ ዜናዊ) እየተጃጃላችሁ ኑሩ ነው ያንተ አስተያየት እና ምክር::

ነብሰገዳዬቹ የነመለስ(ለገሰ ዜናዊ) ቡድን 14 አመታት ሙሉ የህዝቡን ጥያቄ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ከመመለስ ይልቅ አገሪቱዋን በደም ጎርፍ ሲያጥለቀልቁዋት ዛሬም የደም ጥማታቸው አልረካም::

ሰላም ላንተ ይሁን!!!!!
Senef Gebere Be sene yemotal !!!!
ናይክ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Sep 23, 2004 6:11 pm
Location: united states

ተጩሆም የትም አልተደረሰ ሳይጮህም የተግኘ ነገር የለም

Postby አዲስዋ » Tue Oct 25, 2005 2:45 am

ወያኔ እግዚአብህእር ያመጣብን ቅጣት ነው አርፈህ ተቀጣ:በ ጦርነት አይውርድ በሰላም አይወርድ አላማቸው እስከሚያረጁ ድረስ ነው:አርጅተውስ በሰላም ይለቃሉ? ሰዉ እንዳይዋጋ የ ፉፋ ዲሞክራሲ አስተማረው:እግዚአብሄር የሚበጀውን ይስጠን ውይም ልቦናቸውን ይመልስለን ብሎ መፀለዩ ይሻላል መሰለኝ ብቻ እንደዚህ አይነቱ አባባል እዚህ የፖለቲካ ፎሩም ላይ ተቀባይነት እንደለለው አውቃለሁ ግን እውነት የመሰለኝን ሀሳቤን ማግለፄ ደግሞ ያዝናናኛል.
እውንወተኛው ወንድንማችሁ
አዲስዋ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 22
Joined: Thu Oct 20, 2005 12:27 am
Location: sweden

Postby ETLOVE » Tue Oct 25, 2005 2:57 am

ጎበዝ ያንተ ማመን ይሻላል:: ቅቅቅቅቅቅ
AFRICAN COMMUNICATION PROBLEM
PLEASE LET US LISTEN EACHOTHER.
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

ጥሩ ነው

Postby ፕላን » Tue Oct 25, 2005 4:14 pm

ምን ዋጋ አለው ሁሉም ያወራል እንጅ ደፋር የለም መለስ እራሱ ፈሪ ነው አፍ ብቻ ነው ከሱ የበለጠ ፈሪ ስለሆንን
ፕላን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Sun Oct 23, 2005 10:38 am
Location: switzerland

መፍራትም አንድ አዋቂንት ነው

Postby አዲስዋ » Tue Oct 25, 2005 9:36 pm

ትድያ ዝም ብለህ ብትሮጥ ያደናቀፈህ ጊዜ ዋጋ የለህም የ ኢትዮጵያ ህዝብ በ ታሪክ ውስጥ ፈርቶ አያውቅም: ተንደርድሮ ሮጦ ላለመውደቅ ነው አንድ ቀን ታያለህ:: ብቻ እንተባበር እና እርስበርሳችን አንነቋቕር::ትግሬውን ወያኔ:ኦሮሞውን ኦነግ:አማራውን ቅንጅት እያልን የዘመኑ ሰው አንሁን:: በተለይ የሚያሳዝነው እኛ እዚህ አውሮፓ የምንቀመጠው ነን:ውጭ ስንቀመጥ ከተለያየ የውጭ ዜጎች ጋር ተስማምተን እንኖራለን ግን ወደ አገራችን ሰው ስንመለስ ደንበኛ ጠባብ እንሆናል:: ምን አይነት በሽታ ይሆን የያዘን.
እውነትን ተናግሮ የመሸበት ማደር!!
:
አዲስዋ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 22
Joined: Thu Oct 20, 2005 12:27 am
Location: sweden


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests