ኧረ ምን ይሻላል?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ኧረ ምን ይሻላል?

Postby ብሔረ አራዳ » Fri Oct 21, 2005 6:43 am

ወገኖች ባለፉት ጥቂት ወራቶች ውስጥ በተለይ ሰሞኑን ስለ ሀገራችን የሚሰማው - የሚነበበው ሁሉ ደግ ደጉ አይደለም:: አምባገነኑ የወያኔ ቡድን ሥልጣኑን የሙጥኝ ብሎ ተንፈራጧል:: ሊሰርቅ ገብቶ ባለቤቱ ሲደርስበት ምን አገባህ? ብሎ ግግም ብሎ እንደተከራከረው የሌባ ዐይነ ደረቅ ብጤ ማለት ነው:: ፊታችንን ዘወር ስናደርግ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በየአረቦቹ አገሮች የባርነት የስቃይ ኑሮ በመግፋት ላይ መሆናቸውን እናነባለን እንሰማለን:: ወደ አውሮጳ ብናቀና ኑሮ ለኢትዮጵያውያን ብዙም የተሻለ አይደለም:: መስጊድ እንደ ገባች ዉሻ ከጣልያን እስከ ኖርዌ ኢትዮጵያውያን እየተዋከቡና ግማሹ እስር ቤት እየታጎረ ሌላው እየተሽሎከሎከ ኑሮ ብሎ እየኖረ ነው:: በዚህ ላይ ለፍርፋሪ ያደሩ ሰው መሳይ ውሾች አንድነታችንን እያናጉና የአጉራሻቸውን የወያኔን እድሜ ለማራዘም መርዛቸውን እየረጩብን ነው:: ሕብረት እያሳጡን ነው:: ምን ይሻላል? ይኽ ከላይ የዘረዘርኩት ያነሰ ይመስል የሰሞኑ "የወፍ ጉንፋን" የሚባለውም ካላጣው አገር ወደ እኛይቱ አገር እንዳመራ ይሰማል:: ሌላው ባልተናነሰ ሁኔታ የዘገነነኝና እንቅልፍ የነሳኝ ነገር በእርግጠኝነት የሁላችሁም ሰቆቃ ሊሆን የሚችለው አስከፊ ዜናም/መርዶም አለ:: ኢትዮጵያውያን ከድህነታቸው ብዛት ልጆቻቸውን በሳንቲም በሚቆጠር በመሸጥ ላይ ይገኛሉ ይላል ዜናም ሳይሆን መርዶው:: ኡ!ኡ! የሚያሰኝ ነው:: በድህነት የዓለም የመጨረሻው አገር (መንግሥት አልባ ከሆነችው ሶማልያ በታች!) ሆነናል:: በቃ የዓለም የበታቾች ነን ይሉናል:: ምን ማድረግ አለብን? የዚህ ሁሉ ምንጩ ባይባልም በዋናነት ተጠያቂው ወያኔና ቡችሎቹ ናቸው ስለዚህም ለአንድዬና ለመጨረሻ ጊዜ የሚከፈለው መስዋዕትነት ተከፍሎ መገርሰስ አለበት የሚሉ አሉ:: ይኽ ሁሉ ሰቆቃ ያነሰን ይመስል የጦርነት አታሞ እየደለቁብን ነውና ከመሞታችን እንዲያውም ባታውቁት ነው እንጂ ሞታችኌል ብሎ ዓለም ተባብሮ ሳይቀብረን እንፈራገጥ እላለሁ:: መፍትሄ አላችሁ? ኧረ አንድ በሉ! ኧረ ንቁ! ተቀስቀሱ!!
ወገን አልቀናል እኮ!::
ሀገራችንን አምላክ ይታደጋት!
ብሔረ አራዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 39
Joined: Wed May 04, 2005 5:43 am
Location: ethiopia

Re: ኧረ ምን ይሻላል?

Postby ዱራሰንበት » Fri Oct 21, 2005 5:49 pm

ብሔረ አራዳ wrote:ወገኖች ባለፉት ጥቂት ወራቶች ውስጥ በተለይ ሰሞኑን ስለ ሀገራችን የሚሰማው - የሚነበበው ሁሉ ደግ ደጉ አይደለም:: አምባገነኑ የወያኔ ቡድን ሥልጣኑን የሙጥኝ ብሎ ተንፈራጧል:: ሊሰርቅ ገብቶ ባለቤቱ ሲደርስበት ምን አገባህ? ብሎ ግግም ብሎ እንደተከራከረው የሌባ ዐይነ ደረቅ ብጤ ማለት ነው:: ፊታችንን ዘወር ስናደርግ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በየአረቦቹ አገሮች የባርነት የስቃይ ኑሮ በመግፋት ላይ መሆናቸውን እናነባለን እንሰማለን:: ወደ አውሮጳ ብናቀና ኑሮ ለኢትዮጵያውያን ብዙም የተሻለ አይደለም:: መስጊድ እንደ ገባች ዉሻ ከጣልያን እስከ ኖርዌ ኢትዮጵያውያን እየተዋከቡና ግማሹ እስር ቤት እየታጎረ ሌላው እየተሽሎከሎከ ኑሮ ብሎ እየኖረ ነው:: በዚህ ላይ ለፍርፋሪ ያደሩ ሰው መሳይ ውሾች አንድነታችንን እያናጉና የአጉራሻቸውን የወያኔን እድሜ ለማራዘም መርዛቸውን እየረጩብን ነው:: ሕብረት እያሳጡን ነው:: ምን ይሻላል? ይኽ ከላይ የዘረዘርኩት ያነሰ ይመስል የሰሞኑ "የወፍ ጉንፋን" የሚባለውም ካላጣው አገር ወደ እኛይቱ አገር እንዳመራ ይሰማል:: ሌላው ባልተናነሰ ሁኔታ የዘገነነኝና እንቅልፍ የነሳኝ ነገር በእርግጠኝነት የሁላችሁም ሰቆቃ ሊሆን የሚችለው አስከፊ ዜናም/መርዶም አለ:: ኢትዮጵያውያን ከድህነታቸው ብዛት ልጆቻቸውን በሳንቲም በሚቆጠር በመሸጥ ላይ ይገኛሉ ይላል ዜናም ሳይሆን መርዶው:: ኡ!ኡ! የሚያሰኝ ነው:: በድህነት የዓለም የመጨረሻው አገር (መንግሥት አልባ ከሆነችው ሶማልያ በታች!) ሆነናል:: በቃ የዓለም የበታቾች ነን ይሉናል:: ምን ማድረግ አለብን? የዚህ ሁሉ ምንጩ ባይባልም በዋናነት ተጠያቂው ወያኔና ቡችሎቹ ናቸው ስለዚህም ለአንድዬና ለመጨረሻ ጊዜ የሚከፈለው መስዋዕትነት ተከፍሎ መገርሰስ አለበት የሚሉ አሉ:: ይኽ ሁሉ ሰቆቃ ያነሰን ይመስል የጦርነት አታሞ እየደለቁብን ነውና ከመሞታችን እንዲያውም ባታውቁት ነው እንጂ ሞታችኌል ብሎ ዓለም ተባብሮ ሳይቀብረን እንፈራገጥ እላለሁ:: መፍትሄ አላችሁ? ኧረ አንድ በሉ! ኧረ ንቁ! ተቀስቀሱ!!
ወገን አልቀናል እኮ!::
ሀገራችንን አምላክ ይታደጋት!


ሰላም: ብሔረ አራዳ!

ጥሩ: የመወያያ: ርዕስ: ነው:: ይሁን: እንጂ: መፍትሄ: ሲፈለግ: የችግሮች: ዙሪያ: መከተር: አለበት:: የወያኔዎች: ፓርቲ: የነ-አላሞዲን: ፓርቲ: ነው:: ወያኔን: ለመታገል: ስንነሳ: አላሞዲን: ያዝናል:: አላሞዲን: ደግሞ: ለወያኔ:PR:( የህዝብ: ግንኙነት:) በአውሮፓ: አሜሪካ: ላሉ: ቁልፍ: ሰዎች: ሂሳብ: ዘጊ: ነው:: አገር: ወዳድ: ኢትዮጵያዊ: ደግሞ: ዛሬ: ከአላሞዲን: ጋ: በገንዘብ: አቅም: ለመወዳደር: ይቅርና: ያለውን: ሁሉ: ቢሸጥ: አይችልም::
በዚህ: ላይ: ምን: ብለን: እንጀምር? ካለዚያ:
Code: Select all
አፍንጫን: ሲነርቱት: ዓይን: ያለቅሳል: እየሆነ: ያስቼግራል::
Image
ዱራሰንበት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2995
Joined: Thu Apr 01, 2004 3:29 pm
Location: Dedessa Death Camp, Tach Birr Sheleko


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 8 guests