የኢትዮጲያና:የኤርትራ:ሕዝብ:ጠላቶች:አይደሉም!! ሁለቱም:የመሪ:ተበዳይ:ናቸው!!!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የኢትዮጲያና:የኤርትራ:ሕዝብ:ጠላቶች:አይደሉም!! ሁለቱም:የመሪ:ተበዳይ:ናቸው!!!!

Postby SAY-NO-TO-HATRED » Sat Oct 22, 2005 10:09 am

ውድ:ወገኖቼ:በያላችሁበት:ሰላምታዬ:ይድረሳችሁ!!

መለስ:የወያኔ:መንግስት:ሀይል:እንደተዳከመ:በማወቅ:
በመጨረሻው:ሰአት:ላይ:ብዙ:የፍርሀት:ዳንስና:ጨዋታዋችን:
እየተጫወተ:ይገኛል::


አንዳንዱን:በጥቂቱ:ለመጥቀስ:

1)ተቃዋሚዎችን:በያሉበት:ማሰር:መግደል:ማስፈራራት:ቢሯቸውን:
መዝጋት::ያልተገነዘበው: ግን: የእውነትን:የአምላክና:የሕዝብን:ሀይል:ነው!!!

2)የአዲስ:አበባ:ዩኒቨርሲቲ:እንዳይከፈት:በወቅቱ:
ማዘግየት:: አዋ:በእውነት:በእውቀትና:በብሶት:የተሞላ:ህዝብ: (ተማሪ)ያስፈራል!!!!

3)ከኤርትራ:ጋር:ሌላ:ጦርነት?? ይገርማል!! ""ሁሌም:ሁሌን:ሰው:ማታላል:አይቻልም""
መለስና:ዘመዱ:ወይም:ጉዋደኛው:ኢሳያስ:ስልጣናቸውን:
ለማራዘም: አንዴ:ጦርነት:እርስ:በእርሳቸው:ላይ:በመቅሰቀስ:አንዴ:ደግሞ:
አንዱ:አገር:አንዱ:ላይ:እዳ:አለበት:እያሉ:የተገኘውን:ትልቅ:ገንዘብ:ከአበዳሪ:አገራት:
ተካፍሎ:የግል:ካዝና:ውስጥ:ለማስገባት:የማይዶልቱት:ተንኮልና:
ሀጢያት:የለም::

ሆኖም:ግን:ከሁሉም:ጊዜ:በላይ:ለኢትዮጲይና:ለኤርትራ:
ሕዝብ:ግልጽ:የሆነው:ችግር:የፈጠሩት:እነዚህ:ሁለት:መሪዎች:
እንጅ:ሕዝቡ:እርስ:በእርሱ:ወንድማማች:እንደሆነ:ነው::
ሁለቱም:አገሮች:የተበደሉት:መሪ:አምላኩና:ሕዝቡን:የሚወድና:
የሚያከብር:እንጅ:ህዝቡ:እርስ:በእርስ:ጠላት:እንዳልሆነ:
ተገንዝቦታል:: ሕዝቡ:ዲሞክራሲ:ሰብአዊ:መብትና:አምላኩን:የሚፈራ:መሪ:
ካለው:ምንም:እንዳማይፈልግ:ነው::ከኤርትራ:ጋር:አብሮ:
የመኖር:ወይም:ደግሞ:እንደ:ጎረቤትም:አብሮ:የመኖር:ሁኔታ:
የዲሞክራሲ:መብቱ:ከተከበረለት:በሁዋላ:በምርጫ:የሚወስነው:
ነገር:ሊሆን;ይችላል!!

ዋናው:ቁም:ነገር:ግን:በምንም:አይነት:የኢትዮጲያ:ህዝብ:ከእንዲህ:
የጦርነት:victim ሊሆን: አይገባውም:: ከእንግዲህ:ወያኔ:አስገድዶ:የኢትዮጲይን:ሕዝብ:ለጦርነት:
ቢገፋፋ:ከኢትዮጲያ:ሕዝብ:በኩል:የሚሰነዘረው:የጦርነት:
ትግል:ራስን:ለመከላከልና: ለወያኔ: exit door ለማሳየት:የሚጠቀመው:የስልት:መንገድ:ብቻ:ይሆናል!!

አንዴ:ሰው:ይታለላል::ሰው:ነውና!! እንደዛም:ሆኖ:ከ100,000 በላይ: ድሀ:የኢትዮጲያ:ህዝብ:አልቁዋል::ድሀ:የኤርትራ:ወንድሞቻችንና:
እህቶቻችንም:በዚሁ:አላስፈላጊ:ጦርነት:ህይወታቸው:አልፏል::
ነገር:ግን:ብልህ:ከስህትቱ:ይማራል!!
የኢትዮጲያ:ሕዝብ:ታጋሽ:ጨዋና:አስተዋይ:እንጅ:ነገሮች:የማይገቡት:
እንደተገፋ:የሚሄድ:አይደለም!!ያያል:በማስተዋል:ይታገሳል:በቃ:ካለ:
ግን:በቃ:ነው!!!ነጭ:ጋቢ:ለብሶ:የማእድ:ቤት:ቢላዋች:እንደ:መሳሪያ:
ይዞ:በሶ:ለምግቡ:እየበላ:የጣሊያንን:ታንክ:360 degree እንዲመለስ:ያበቃ: ሕዝብ!!!!! ነው!!!!!
አቶ:መለስ:የአድዋን:ጦርነት:ታሪክ:ያንብቡ:በአክብሮት:
እጠይቃለሁ!! ትእግስት:ፍርሀት:አይደለም!!

የጦርነት:ዘመን:አከተመ!! ለሁለት:መሪዎች:ስልጣን:ለማራዘም:የሚደረግ:ጦርነት:
ህዝብን:ሊያታልል:አይችልም!!! እናንተ:ሁለታችሁ:ብቻ:
ሳትሆኑ: chess game master ያደረጋችሁት:ታዛቢውችም:ጨዋታውን:በሚገባ:የሚያነቡ:
እንዳሉ:እስቲ:አሁን:እንኩዋን:ይግባችሁ!!
የኢትዮጲያ:ህዝብን:እጅግ:ናቃችሁት:በዝምታው:በትእግስቱና:
በጨዋነቱ:::በዛ!!!!!ልክ:አለው:ሁሉም:ነገር!!!


የተለየው:የኢትዮጲያ:አምላክ:ሕዝባችንና:ሀገራችንን:ይጠብቅልን!!!

ኢትዮጲያን:ማጥፋት:ማለት:የአምላክን:ቃል:ማጥፋት:
ከአምላክም:ጋር:መጣላት:ነው!!!


አክባሪያችሁ:

እምቢ:ለጥላቻ:

ነኝ
WE ARE NOW AMBASSADORS FOR OUR BELOVED COUNTRY AND ONE DAY WE WILL BE CITIZENS IN ETHIOPIA, ONCE AGAIN!!
SAY-NO-TO-HATRED
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1354
Joined: Sat Mar 12, 2005 8:29 pm
Location: united states

Postby መራር » Sun Oct 23, 2005 9:12 am

ምነው ወንድሜ የዘፈንካት ዘፈን ትንሽ ትንሽ አስመራ አስመራ ትሸታለች::

ያንተ ዘፈን ዜማው ኤርትራዎች ያለፈው የሰላሳ አመት ጥጋባቸው ውጤቱ በረህብ እና በርዛት እየተቀጡ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የሚዘፍኑት ዘፈን አይነት ነው::

በሁለቱ አገሮች አንድነት ተጠቃሚው የኢትዬ. ህዝብ ይመስል ወንድሞቻችን እያልን እሹሩሩ ስንላቸው ጥሬ አራቸውን ሲያሩብን ከርመው ዛሬ የጥጋባቸውን ማብረጃ ድህነት እና እከክ የሚልሱት የሚቀምሱት እስኪያጡ ድረስ በየተራ በዳዴ እያስኬዱዋቸው ነው::

ብሎም ወደ ኢትዬ. ጠፍተው ለመግባት በ አሁኑ ሰአት ከ6 እስከ 12 ሺህ የነሱን የጦጣ ፍራንክ ይከፍላሉ::

ስለዚህ አሁን ካለብን የጊዜ ማነስ የተነሳ ቅድሚያ የምንሰጠው ለልማት እና ለህዝባችን ህልውና እንጂ ስለቀድሞ ቅኝ ግዛቶቻችን አለመሆኑን ልትረዳ ይገባህል::

ሰላም ላገራችን!!!!!
lk
መራር
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Tue Sep 28, 2004 9:26 pm
Location: united states

ምን:ማለት:ይሆን:አስመራ:አስመራ:መሽተት:ማለት???

Postby SAY-NO-TO-HATRED » Mon Oct 24, 2005 12:28 am

ውድ:መራር:ሰላምታዬ:ይድረስዎ::

መለስ:ኢሳያስና:አንዳንድ:ጥቂት:ሆዳሞችና:ዘረኞች:ባጠፉት:
ጥፋትና:በሚሸርቡት:ተንኮል:ለምን:ይሆን:የድሀው:ሕዝብ:
ሁሉ:አንድ:ላይ:የሚወነጀለው?

ዳቦ:ማግኘት:ነጻነት:ማግኘት:የሰብአዊ:መብት:ማግኘት:
የሚፈልገው:ድሀ:ሕዝብ:በምን:እዳው:በምን:ጥፋቱ:አንድ:ላይ:
ከእነ:መለስ:ኢሳያስና:ከሆዳም:ጅቦች:በሆድ:ብቻ:እንጅ:
ህሊናቸው:ከከዳቸው:ህዝብና:በዘር:ቆጠራ:ከሰከሩ:ዘረኛ:
ከንቱዎች:ጋር:አብረው:ይወነጀላሉ??

መለስ:ኢሳያስና:አንዳንድ:ሆዳሞችና:ዘረኞች:ላጠፉት:ጥፋት:
እነሱ:ራሳቸው:ብቻ:ናቸው: responsible መሆን:የሚገባቸው:እንጅ:የሀገሩን:ሁሉ:ህዝብ:አንድ:ላይ:
እንደወንጀለኛ:እንደከጅና:እንደዘረኛ:ማየት: እጅግ:ስህተት:አደገኛና:ትንሽነት:ይመስለኛል:: መለስ:ዜናዊም:ከዚህ:የተለየ:ስራ:አይደለም:እየሰራ:ያለው:የአንድን:
ዘር:ህዝብ:እንዳለ:አብሮ:ሲጨፈጭፍ:ይገኛል:: ይህ:ደካማነትና:ዘረኛነት:ነው::

ስለ:ኤርትራና:ኢትዮጲያ:እንደገና:አብሮ:የመሆን:ያለመሆን:
ሁኔታ:የሚወሰነው:በሁለቱም:ሀገር:ህዝቦች:ምርጫ:ነው::
ያንን:ደግሞ:ለማድረግ:በመጀመሪያ:እውነተኛ:ዲሞክራሲ:
በሀገሮቹ:ውስጥ:ያስፈልጋል::እውነተኛው:አይነት:ዲሞክራሲ:
እንጅ:የመለስና:የኢሳያስ:አይነት:በዘር:ቆጠራ:ላይ:ያለ:
አይነት:ዲሞክራሲ:አይደለም::
ሕዝቡ:አብሮ:እንኑር:ወይንም:አንኑር:የሚለውን:በጨዋነት:
መምረጥ:ይችላል::እንጅ:ከእንግዲህ:በሁዋላ:የመለስንና:
የኢሳያስን:ውስጣዊ:ፍላጎት:ማለትም:ስልጣናቸውን:ለማራዘም:
ተብሎ:የሚኖር:ምንም:አይነት:ጦርነት:ሊኖርም:አይችልም::
ማንም:ዳግመኛ:አይጃጃልም::ሰው:አንዴ:ብቻ:ይታለላል::
ሰው:ነውና::ያ:አንዴ:የጠፋ:ጥፋት:በ100,000በላይ:ምስኪን:
ድሀ:ህዝብ:ከሁለቱም:ሀገሮች:ህይወት:አልፏል::አላስፈላጊ!!

ውድ:መራር:አስመራ:አስመራ:መሽተት:ማለት:ምን:ማለት:ነው??
ሰው:እኮ:ግለሰብ:ነው:: ይህማ:ባይሆን:ኖሮ:ፍርድ:ቤት:ባላስፈለገና:አንድ:ግለሰብ:
ጥፋት:ባጠፋ:ቁጥር:እሱ:ያለበትን:አካባቢ:ያሉ:ስዋች:ሁሉ:
እንደወንጀለኛ:ተቆጥረው:ሁሉም:ለፍርድ:ይቀርቡ:ይሆን:
ነበር:: ለማንኛውም:አባባሉ:አይገባኝም::

ጥፋተኞቹ:መለስ:ኢሳያስና:አንዳንድ:ሆዳሞችና:አንዳንድ:
ዘረኞች:ናቸው:: ሌላው:ምስኪን:ህዝብ:ግን:አምላክን:የሚፈራ:መሪ:ያጣ:ህዝብ:
ብቻ:ነው::


አክባሪ:እህትዎ:

እምቢ:ለጥላቻ:

ነኝ
WE ARE NOW AMBASSADORS FOR OUR BELOVED COUNTRY AND ONE DAY WE WILL BE CITIZENS IN ETHIOPIA, ONCE AGAIN!!
SAY-NO-TO-HATRED
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1354
Joined: Sat Mar 12, 2005 8:29 pm
Location: united states


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests

cron