ዋርካ ከማን ጋር ነው?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ዋርካ ከማን ጋር ነው?

Postby ARERU » Sat Oct 22, 2005 4:45 pm

ሰላም ከይቅርታ ጋር ዋርካ ከማን ጋር ነው መልስ እፈልጋለሁ ምክኒያቱም አንዳንድ ሰውች ትንሽ ሲነጋገሩ አስፈንጥረው ይጥላሉ ዛሬ ግን ይሄው ከሁለት ስአት በላይ አቶ ኮኮብ1010 የሚባል ሰው በግድ ወያኔ ለዘላለም ይኑር በሉ እያለ ሲበጠብጠን ብዙወቹ እየተማረሩ ሲወጡ አንዳንዶቻችንም ያው እንዳለን ስቃይ እንቀበላለን ታዲያ ለምንድን ነው ኪክ ያልተደረገው እባካችሁ እንደዚህ አይነት ሰውች እሚወገዱበትን ወይንም ደግሞ እሚታረሙብተን ካለበለዚያ ለህዝብ እያላችሁ ሽልማት በሽልማት ስትሆኑ ህዝቡ ግን እየተበጠበጠ ነውና እምታደርጉትን አድርጉ ::
ታላቅ ይቅርታ በሽቆኝ ስለሳፍኩት አስፈላጊ ያልሆኑ ቃላቶች ተተቅመ ይሆናልና::
ቻው::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

ዋርካ ከማን ጋር ነው

Postby ብሉ በርድ » Sat Oct 22, 2005 5:01 pm

ሰላም ዋርካዎች ወይም የዋርካ ተተቃሚዎች መቼም ምን እንደምል በጣም ግራ ይገባኛል በመጀመሪያ ዋርካ ያለው በማን ስር ነው ነው የመንግስት ነው? እንዴት አይነት ነገር እንደሆነ ግራ የሚያጋባ ነው ይሄንን መስመር ተጠቅመንኮ ቁም ነገር ወይም አንዳንድ ህገራዊ ወይም ግለሰባዊ ቁም ነገሮችን ልንነጋገርባቸው እንጂ አሁን እየሆነ እንዳለው ያንድ ፖለቲካ ፓርቲ መጠቀሚያ መሆን የለበትም ምን እየተሰራ እንደሆነ እራሳችሁን ፈትሹ ለማንናውም እኔ ጨረስኩኝ አመሰግናለሁ::
ብሉ በርድ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Fri Aug 05, 2005 12:14 am
Location: ethiopia

Postby ENGEDA1967 » Sat Oct 22, 2005 5:02 pm

በጣም ያሳዝናል . በእረፍት ሳአታችን እንዳንነጋገር ሲያደርገን ዋርካ ዝም ማለትዋ የሚደንቅ ናእ ይህን ነገር መቆጣጠርያ የሌላቸው ይሆን ? ለሁሉም አንድ በሉት ይሄን ሰው
ENGEDA1967
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Fri Aug 27, 2004 11:09 pm
Location: united states

ጥሩ ጥያቄ ነው!

Postby Monica**** » Sat Oct 22, 2005 5:07 pm

እኔም ይሄ ኮከቡን ያጥፋውና ከከብ 1010 ከሚባል የታሪክ አተላ ጋር ለስአቶች ሌሎች ስዎች እንዳይወያዩበት ወያኔ ለዘላለም ይኑር በሉ እያለ ቻት ሩሙን በደደብ ጽሁፉ ሞልቶታል!
ዋርካዎች ታድያ ይሄንን አላየንም ነው የምትሉት ወይስ መብቱን እናንተ ናችሁ የስጣችሁት?????
ማንኛውም ግለስብ የመረጠውን የፖለቲካ ፓርቲ መደገፍ መብት አለው ......ሆኖም አላግባብ የማንፈልገውን ነገር አድርጉ ማለት ስለማይችል ዋርካዎች አንድ ነገር አድርጉ.....ካልሆነም እሱ ትክክል ነው የምትሉ ከሆነ አሳውቁንና ቁርጣችንን እንወቅ :?
ወያኔ አገራችንን እንደቁንጫ ደሟን የሚመጠው አንሶ እዚህ ዋርካ ቻት ላይ እየመጡማ አይደነፉንብንም :evil: :evil: :evil:
እነዚህን ትንኞች የማጥፋት መብት የተስጣችሁ የዋርካ ባለቤቶች ናችሁና በአስቸክዋይ ይታስብበት ስል በትህትና እጠይቃለሁ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ሞት ለወያኔ
ሞኒካ ነኝ ከኢትዮጵያውያኖች መንደር
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

እውነትም ዋርካ የማን ነው,

Postby The Aviater » Sat Oct 22, 2005 8:10 pm

ለዋርካ Admin, moderater or who ever is responsible monitoring this forum, ከላይ ብዙ ተሳታፊዎች እንደገለጱት ማንኛችንም የትኛውንም ፓርቲ ደግፈን ሀሳብ የመስጠት መብት አለን, ግን ከዛ አልፎ ልክ እንደኢህአድግ የግል መድረክ እንድህ በሉ ወያኔን ደግፉ እሱን እሚያወድስ ሀሳብ ስጡ ማለት እሚቻል አይመስለኝም, ህገወጥም ነው, ዋርካ እንደገባኝ የነጳ መድረክ ከሁሉም ነጳ የሆነ ከሆነ እንደነዚህ አይነት ስዎችን ባለው መንገድ ማስወገዱ ግዴታው ይመስለኛል, ከአሁን በፊት በተለያዪ ምክንያት ስዎች ሲወገዱ እንደነበር የታወቀ ነው ታዲያ አሁን ምን ተፈጠረ, ወይስ ነገሩ እንደ SOWRDFISH ፊልም, ማን, ለምን ,ለማን እንደሚሰራ
አልታወቀም, በጣም ግራ የገባ ነገር ነው, ብቻ ከከብ 1010 የተባለው Bozo, እራሱ Admin እንዳይሆን, just a taught, ለማንኛውም, መልሱን ብታሳውቁን ይበጃል,


WE STAND UNITED!!!
ድል ለኢትዪፕያ ህዝብ
The Aviater
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 70
Joined: Sat Feb 19, 2005 1:40 am
Location: united states

ለ Cyber Ethiopia ምስጋና

Postby Monica**** » Sun Oct 23, 2005 12:20 am

ለዋርካ (Cyber Ethiopia moderators)!!!!
ከላይ በጻፍናቸው ነጥቦች ላይ ዋርካን ያለማቁዋረጥ ለበጠበጠን ግለስብ ከዛም ስሙን ቀይሮ ን*** ብሎ ለገባው በሽተኛ ስውዬ ላይ ፈጣን ርምጃ በመውስዳችሁ በዋርካ ታዳሚዎች ስም ምስጋናዬ የላቀ ነው::

አክባሪያችሁ
ሞኒካ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

ትንሽ አስቡ

Postby አዲስዋ » Tue Oct 25, 2005 1:36 am

እዚህ ጉዳይ ላይ እነዚህን አሪፍ የ ሳይበር ኢትዮጵያን ልጆች አትውቀሱ, ትርጉሙ ካልገባችሁ ይሄ ነፃ መድረክ ነው: ዶማ ራስ አትሁኑ::

ስለ ዋርካ ማወቅ ከፈለጋችሁ አብራሩልን ብሎ መጠየቅ? እኔ እስከማውቀው ግን:ዋርካ ከ ሆኑ አመታት በፊት በኖርዋይ የሚቀመጡ ጀመሩት ቡሀላ ግን ተሻሽሎ በሳይበር ኢ. ስር ሆነ::ይሄን ሁሉ ልፍለፋ እየተከታተሉ ማስቆም የሚቻል አይመስለኝም ሰዎቹ ሌላም ስራ ያላቸው መሰለኝ::

እውነተኛው ወንድማችሁ
አዲስዋ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 22
Joined: Thu Oct 20, 2005 12:27 am
Location: sweden

አዲስ ሰው

Postby ARERU » Tue Oct 25, 2005 7:45 pm

ለምን እንደጽፍነው የገባህ ስላልመሰለኝ አባባልህን ስህተት ነው አልለውም ግን ይሄን ነገር የጽፍነው እነሱን ለመውቀስ ሳይሆን ከነሱ ጋር ስለሆንን ነው ታድያ ምን ሆነ መሰለህ ባለፈው ቅዳሜ እለት አንድ በጣም የሚበጠብጥ ኮከብ1010 የሚባል ሰው ስለነበር ቀኑን ሙሉ ቻት ሩም ውስት ሰውን ሲበጠብጥ ስለዋለና ሊያባሩት ባለመሞከራቸው እኝ አንደ ፖሊስ ሆነን ነው ጥፋተኛ አለና አባሩት ያለው እንጅ ለላ አይደለም ዋርካወች ብይኖሩ ኖሮ እኛ ምን ይውጠን ነበር ደግሞ እልሀለሁ እና የገባህ መሰለኝ አሁን::
አመሰግናለሁ
አረሩ::
thank you
ARERU
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:18 pm
Location: ethiopia

ዋርካዎች

Postby እንታደስ » Tue Oct 25, 2005 11:38 pm

ዋርካ የኢትዮጵያኖች ለኢትዮጵያኖች የተዘጋጀ ነጻ መድረክ ነው: የዋርካ መነሻን መጠለያ በስዊዘር ላንድ በ ጄነቫ ከተማ ሲሆን እስከምናውቀው ድርስ
የዋርካ ወጣት ባለሙያ ከፓለቲካና ከጎሰኝነት የጠራ ነው::
እንግዲህ ወያኔ የማይገባበት ቦታ የለምና ይህንን ባለሙያ መጠቀሚያ ሊያደርጉት ይከጅሉ ይሆናል ሆኖም እስካሁን የተለያዮ ድርጅቶች ከለወትሯቸው በዋርካ ባለሙያዎች ዙሪያ ሲያንጃብቡ ይታያሉ: ሌላውን በሂደት እናያለን:.
እንታደስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1043
Joined: Mon Jan 24, 2005 5:46 pm
Location: Europe

Re: ዋርካዎች

Postby ልጁነኝ1 » Wed Oct 26, 2005 11:08 am

እውነትም እንታደስ!
ከብዙ ምሥጋና ጋር ነው ሰላምታዬን የማቀርብልህ::

ያሰፈርካቸው እጥር ምጥን ያለቺዋ ኃሣብህ በሁሉም በኩሏ የምታስረዳ ነቺ::

አዎ ከወያኔው እስከ ተቃውሞው ጎራ ያሉት አንዣበውባታል:: መቸስ እንደ ባሕል ሁኖብን አንድን ቅን ሰራተኛ ስናገኝ በተለያዩ ነገሮች ካስቸገርናቸው በኌላ ከጨዋታው ለማስወጣት ወይም ለማግለል የማይሞከር ነገር የለም::

ታዲያም ሳይበር በሳይበር ላይ ከመሄድ እርምጃዋን ማንም ሊቀንስ አይቺልም:: ፓርላሜንቱን ህወኃት ሻቢያዊያን እንደተቆጣጠሩት ሁሉ ሣይበር ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ኃሣቡን የሚገልጽባት ሸንጎው ያውም ህዝብ በነጻነቱ ኃሣቡን የሚገልጽባት ሁና ትቀጥላለቺ ይህን ምኞቷም መላው ኢትዮጵያዊና ጥቁር ነጭ ሣትል ሁሉም የዓለምን ህዝብም ታገለግላለቺ::
'
አዎን እንዳልከው የፖለተካ ፓርቲዎች መሣሪ ለነሱ ስሜት ብቻ መገልገያ ለማድረግ ማሰብብ አይኖርባቸውም:: ሁሉም ግን ኃሣባቸውን በወርካ ላይ ማንጸባረቅ ይቺላሉ እሱም ሰላም ያዘለ ሌሎቹን ሌላውንና የግለሰብ ነጻነትንም ጭምር የጠበቀ መሆን ይገባዋል::

ወያኔ ህወኃትና ሻቢያም ቢሆን ወይም ሌሎቹ ሣይበርን መጠቀም ያለባቸው ህዝብን ለማገልገል እንጂ ሥልጣናቸውን ለማሳዬትና ለመሞላቀቅና ለማስፈራራት ሳይሆን ሰላምና ፍቅር እንዲሁም አንድነትና ልማት ብልጽግና በተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲቀጥል የሚያድስና የሚገነባ ኃሣብ እንጂ በሰው ብቻ እመኑ በሚል የጠመንጃ ተኩስ ዓይነት ጋጋታና ማስፈራራት መሣደብ ሊያቆሙ ይገባል::

"ሕዝብ የማወቅ መብት አለው" ያንን መመሪያ በማድረግ ነጻ ተሆኖ ወደ ዓለም እንደተመጣ ሁሉ ነጻ ሁኖ ተናግሮ" አብሮ መኖርን የምታንጸባርቅ ነቺ:: ያንንም እምነት ሁሉ ተቀብሎ ይኸን ዕድል ሊጠቀምበት ይቺላል::

ይህ አዲስ አመት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት መርካት እንዲሁም ከድህነት ማጥ ውስጥ እንዴት መወጣት እንደሚቻልና ሁሉም ወደ ኃገሩ (የቴዲ አፍሮን) ዘፈን እየዘፈነ ለግንባታ ለመሥራ ወደ አገራሩ እንዲገባ ሣይበር የምታደርገው የውይይት መድረኳ ሲበዛ ጠቃሚያቺን ነውና አንዳንድ ወገኖች የወያኔ ሻቢያ መጠቀሚያ መሳሪ ከመሆን ሊቆጠቡ ይገባል::

ታደሰ እውነትም መታደስ ነው ያልኩበት በዚያ ባነሳኌቸው ምክንያት ነው::

*ቀይ ባህር ዳር ድንበራቺን ነው*
ደብረ ቢዘንም የኢትዮጵያ አንጡራ ኃብቷ ነው::
የአድዋው ስምምነት ደብረ ቢዘንን አንስቶ ይገልጻል:: ህወኃት ወያኔ ግን ቢዘንን እስከዛሬ አላነሳም:: ምናልባት ለቀሩት ተገዥ ህዝቦች አያገባቸውም በኛ ብለው ይሆን እንደአሁን ቀደሙ?

አክባሪህ

ልጁነኝ1
ከ(ሰሐሊን)እንታደስ wrote:ዋርካ የኢትዮጵያኖች ለኢትዮጵያኖች የተዘጋጀ ነጻ መድረክ ነው: የዋርካ መነሻን መጠለያ በስዊዘር ላንድ በ ጄነቫ ከተማ ሲሆን እስከምናውቀው ድርስ
የዋርካ ወጣት ባለሙያ ከፓለቲካና ከጎሰኝነት የጠራ ነው::
እንግዲህ ወያኔ የማይገባበት ቦታ የለምና ይህንን ባለሙያ መጠቀሚያ ሊያደርጉት ይከጅሉ ይሆናል ሆኖም እስካሁን የተለያዮ ድርጅቶች ከለወትሯቸው በዋርካ ባለሙያዎች ዙሪያ ሲያንጃብቡ ይታያሉ: ሌላውን በሂደት እናያለን:.
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states

Re: ዋርካዎች

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Oct 26, 2005 9:15 pm

ልጁነኝ1 wrote:[color=blue]

መቸስ እንደ ባሕል ሁኖብን አንድን ቅን ሰራተኛ ስናገኝ በተለያዩ ነገሮች ካስቸገርናቸው በኌላ ከጨዋታው ለማስወጣት ወይም ለማግለል የማይሞከር ነገር የለም:: ያንንም እምነት ሁሉ ተቀብሎ ይኸን ዕድል ሊጠቀምበት ይቺላል:
[/quote]

ትክክለኛ አባባል ነው::
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1034
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 7 guests