አቶ ደበበ እሸቱ : ቅንጅት የ299 ወንበሮቹን ጉዳይ ትቶታል ሲሉ : ቅንጅትን አጋላጡ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አቶ ደበበ እሸቱ : ቅንጅት የ299 ወንበሮቹን ጉዳይ ትቶታል ሲሉ : ቅንጅትን አጋላጡ

Postby ጉማ » Sun Oct 23, 2005 3:41 am

አርቲስት ደበበ እሸቱ ዋሽንግተን ዲሲ በሚሰራጭ መብት በተሰኘ ራዲዮ በ10/20/2005 ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቅንጅት የተሰረቀውን የህዝብ ድምጽ የማስመለስ ትግል ሊገፋበት እንዳልቻለ ጠቅሰው ለዚህ የሰጡትም ምክንያት : ኢሕአደግ ይሄ ጉዳይ ሲነሳ ያንገሸግሽኛል ስላለ የ299ኙን ድምጾች ጉዳይ ትተነዋል ነበር ያሉት::
እግዚኦ ቅንጅት!!
የሰማዕታቱ አምላክ ይቅር ይበላችሁ
Tesfa Z Guma
ጉማ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Wed Oct 12, 2005 4:59 am
Location: united states

Postby ጥልቁ1 » Sun Oct 23, 2005 4:30 am

እጅግ አሳፋሪ እና የሚያቅለሸልሽ ስራ ነው:: ወያኔን የሚያስደስት ነገር ብቻ የሚሰሩ ከሆነ ; ምኑን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሆኑ ታዲያ :?: :!:
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

Postby ጉማ » Sun Oct 23, 2005 5:13 am

አሁን በደረሰኝ መረጃ ደግሞ (በቴፕ የተቀዳ) ዋናው ተደራዳሪ ዶ/ር ያቆብ ህ/ማርያም ቃል በቃል 'በረከት ስሞዖን የ299ኙን ወንበሮች ጉዳይ ጨርሶ እንዳታነሱ ብሎ ስላስጠነቀቀን ትተነዋል::' ሲሉ እቅጩን ተናግረዋል::
ይህ ስም ማጥፋት ወይም ሐሜት አይደለም መረጃውን የሚፈልግ አቶ ኤልያስ ክፍሌን (ኢትዮ ሪቪኢው) ማግኘት ይቻላል::
ቅንጅት የህዝብን ድምጽ ማስከበር ከሚለው መፈክር : የህዝብንመብት ማስከበር ወደሚል መፈክር መሸጋገሩን ልብ ብላችኌል?
የትኛውን መብት
Tesfa Z Guma
ጉማ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Wed Oct 12, 2005 4:59 am
Location: united states

Postby ጥልቁ1 » Sun Oct 23, 2005 7:24 am

ሰላም ጉማ:
ያኔ ፓርላማ እንደማይገቡ ባስታወቁበት እለትኮ ; ምንም እንኳ መስፈርቶች ውስጥ ; የ299 መቀመጫዎች ጉዳይ ባይኖርም ; የህዝብ ድምጽ ሊከበርበት የሚችለውን መዋቅር በመጀመሪያ አስተካክለው እንደሚመለሱበት ነበር የተናገሩት:: ምንአልባት ; ይሄ አሁን የያዙት አቋም ; የህዝቡን ልቦና እንዴት መስለብ ይቻላል የሚል ቀመር ያቀፈ ; የፈሪዎች ስሌት ሳይሆን አይቀርም::

አንድ ነገር ግን ግራ የገባኝ ; እንዴት አንድ ነፍስ ያለው ብቸኛ ሰው ጠፋ?! ትክክል እየተሰራ እንዳልሆነ የሚያጋልጥ እንዴት አንድ ሰው ይጠፋል?!

አንድ ቁልጭ ብሎ የሚወጣ ሀይል ይኖራል ብየ አስባለሁ:: ያኔ ቅንጅት ....
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

Postby የዘመኑ ልሳን » Sun Oct 23, 2005 7:26 am

ጉማ ሀሳብህ ባልከፋ::አሁንም እኮ የህዝብን ድምጽ ለማስከበር የበኩላቸውን ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው::አሁን ወቅቱ የህዝብን ትግል ከኛ የሚጠበቀውን በማድረግ የታሪክ አደራችንን መወጫ ጊዜ እንጂ በሆነ ባልሆነው እየተነታረክን ጊዜያችንን በከንቱ የምናጠፋበት ወቅት አይደለም::ይህ እማ ወያኔ የሚመኘውና ሌት ተገን የሚደክምበት ሁኔታ ነው::ስለሆነም በአንድነት ወደፊት ለሚቀጥለው ሰላማዊ ትግል እራሳችንን ማዘጋጀት አለብን::

ስላልከው 299 የምርጫ ክልሎች ጉዳይ ወያኔ በነዚህ ጉዳዮቹ ላይ አልወያይም ካለ ለሰላምማዊ ውይይት ህድል ለመስጠት ቅንጅት ጥያቄውን ማንሳቱ ብዙም የሚያስነቅፈው አይደለም::ዋናው የህዝብን ሰላማዊ መብት ማስከበር ላይ ነው ቁምነገሩ::ሌላውም ጊዜውን ጠብቆ የማይረጋገጥበት ምክንያት የለም::እስቲ እንታገስ::
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

Postby ሊቃውንት » Sun Oct 23, 2005 9:03 am

ሰላም ለሁላችሁ:-

ምን ያህል ታማኝነት ያለው መረጃ እንደሁነ ለማወቅ ባይቻልም ይህችን ቁንፅል ነጥብ በማሳት ለዲሞክራሲ መስፈን በሚጥሩ የህዝብ ኃይሎች ላይ የወቀሳ ውርጅብኝ ማድረጉ አሰፈላጊ መስሎ አልታየኝም:;

በርግጥ የዚህ ሁሉ መነሻው የምርጫው መጭበርበር መሆኑ ቢታወቅም ተፈላጊው አውሬው ወያኔ በዚህ ጉዳይ ላይ አትምጡብኝ ስላለ ብቻ በአንድ ኃሳብ ላይ ግትር አቋም በመያዝ እንደወያኔዎቹ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ አስፈላጊ አልመሰለኝም

የቅንጅቶች አረማመድ የሚያሳየው ድልን አስፈላጊ መሆነ መልኩ (ሰላማዊ) ለመቀዳጀት የሚያደርጉትን አሰራር በግለሰባዊ አመለካከት ብቻ ተነስተን ወቀሳ ባንሰነዝር ከሚቀጥለው ፀፀት ለመዳን ይቻላል::

ስለዚህ በነዚያ 299 ወንበሮች ጉዳይ የነበረውን ጥያቄ ማንሳቱ የወያኔን ሥልጣን ያራዝማል የሚል አመለካከት የለኝም::

አንድን የፖለቲካ ድርጅት ለፖለቲካ ኪሳራ ከሚዳርጉን አበይት ነጥቦች አንዱ ከአመራር አባላት ወጪ የሚሰጥ አስተያየት መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል::

ለሁሉም ከዘለፋ በፊት ጉዳዪን በጥሞና መከታተሉ ተገቢ ይመስለኛል:;
The truth is out there.
ሊቃውንት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 10, 2004 9:21 am
Location: Far_east

አዎ ሊቀሊቃውንት

Postby ልጁነኝ1 » Sun Oct 23, 2005 12:40 pm

በባህላችን ይሁን በምናስበው!
አንድን ነገር ስናመሰግን እንከርምና ወደኌላ ደግሞ ስናበሻቅጥ እንስተዋላለን::

አሁንም እንደዚያ እንዳይደገም እፈራለሁ:: እንዴት ቢባል ያንን ያለፈውን የሞተውን መንግሥት ከምናድምበት ይልቅ ከፍተኛ ትብብር ልክ እንደ ሶማሌ ወረራ ጊዜ ከሚሊሺያ ድራፍት እስከ ጦር ሜዳው ከገንዘብ እስከ ቤንዚን አቅርቦት ድረስ ቢጣር ነበር ዛሬ ወንበዴዎች አይጫወቱብንም ነበር:: የሽፍታ መንግሥት:: ስለ ኢትዮጵያዊነት ግድ የሌለው ሥራ ፈት የነበረ ዱርዬ ባልተዝናናብን አገራቺንንም ባልገነጣጠለ ነበር::

ያንን ልናስብ ይገባል:: አሁንም ህወኃት ወያኔን እስከዚህ ሄደን ልንቃወም የሚያበቃ የራሳቺን የሆነ ኃይሎቻኢንን ማጠናከር ይኖርብናል እንጂ ደርሶ 10 ዓመት ተቓቁመው የተደራጁ በማስመሰል ልንተቻቸው ሳይሆን በሃሣብ በገንዘብና በሞራል ልንተባበራቸው ሲገባ አሁን ይህን የመሰለ ወሬ ይዞ ብቅ ማለቱን አልደግፈውም::

አንድን በጦር ቀጠና ውስጥ ያለን ሠራዊት ስለ ፍቅርና ስለ ግል ኑሮው ልጠይቅህ ብትለው ሊመልስህ አይችልም ምክንያቱም ዛሬን መኖሩን አያውቀውምና ረጅም ዕይታዎችም ስለማይታዩት::

ቅንጅቱም በምን ላይ እንደሆኑ ልናስብ ይገባል:: የሚደርስባቸውንም ዕለት ተለት ሁኔታዎንም አስበን ሊሰማን ይገባል:: የሚሰራን ደግሞ አይዞህ ከጎናቺሁ ነን ማለት ይኖርብናል:: ምክሩን በግልጽ ባልሆነ መንገድ እነሱጋ ሆምፔጅ ሄዳቺሁ ኢሜይል ልታደርጉት ቢቻል ሁሉም አልጋ ባልጋ ይሠሩታል ማለት ነው:: ዕርምት አይኑር አላልኩም ለወያኔ ህወኃት ሻቢያና ጸላኢ ኢትዮጵያዊያንን እንዳያስደስት ብበሚል ስለፈራሁ ነው::

*ቀይ ባህር ዳር ድንበራቺን ነው*

አመሰግናለሁ

ልጁነኝ1
ከ(ሰሐሊን)

ሊቃውንት wrote:ሰላም ለሁላችሁ:-

ምን ያህል ታማኝነት ያለው መረጃ እንደሁነ ለማወቅ ባይቻልም ይህችን ቁንፅል ነጥብ በማሳት ለዲሞክራሲ መስፈን በሚጥሩ የህዝብ ኃይሎች ላይ የወቀሳ ውርጅብኝ ማድረጉ አሰፈላጊ መስሎ አልታየኝም:;

በርግጥ የዚህ ሁሉ መነሻው የምርጫው መጭበርበር መሆኑ ቢታወቅም ተፈላጊው አውሬው ወያኔ በዚህ ጉዳይ ላይ አትምጡብኝ ስላለ ብቻ በአንድ ኃሳብ ላይ ግትር አቋም በመያዝ እንደወያኔዎቹ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ አስፈላጊ አልመሰለኝም

የቅንጅቶች አረማመድ የሚያሳየው ድልን አስፈላጊ መሆነ መልኩ (ሰላማዊ) ለመቀዳጀት የሚያደርጉትን አሰራር በግለሰባዊ አመለካከት ብቻ ተነስተን ወቀሳ ባንሰነዝር ከሚቀጥለው ፀፀት ለመዳን ይቻላል::

ስለዚህ በነዚያ 299 ወንበሮች ጉዳይ የነበረውን ጥያቄ ማንሳቱ የወያኔን ሥልጣን ያራዝማል የሚል አመለካከት የለኝም::

አንድን የፖለቲካ ድርጅት ለፖለቲካ ኪሳራ ከሚዳርጉን አበይት ነጥቦች አንዱ ከአመራር አባላት ወጪ የሚሰጥ አስተያየት መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል::

ለሁሉም ከዘለፋ በፊት ጉዳዪን በጥሞና መከታተሉ ተገቢ ይመስለኛል:;
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states

ለሊቃውንትና ልጁ ነኝ1

Postby አፈ-ጉባኤ » Sun Oct 23, 2005 7:43 pm

መልእክቶቻችሁ ማለፊያዎች ናቸው::
አፈ-ጉባኤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 302
Joined: Tue Mar 15, 2005 5:20 pm
Location: united states


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests