የመስቀል ደመራ ረብሻ ጸረ ኦርቶዶክስ ክርስትና ወይስ ....

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የመስቀል ደመራ ረብሻ ጸረ ኦርቶዶክስ ክርስትና ወይስ ....

Postby ETLOVE » Sun Oct 23, 2005 11:21 am

በእውነት ስለመስቀል ደመራው ረብሻ ለምን ተቃዋሚዎች መግለጫ አላወጡም :?:ሀይማኖቱን ለመጠቀም ፈልገው ነበር ማለት ነው :?: ወይም ረብሻውን ይደግፉታል ማለት ነው ያ ባይሆን ኖሮ ማንም ሰው ለሀይማኖቱ ተቆርቃሪ ነው::
ለራሱ አይማኖት የማይቆረቆር ስለለላው አይማኖት እንደት ግድ ሊለው ይችላል የፖለቲካ ትርፍ ከሌለለው በስተቀር :: ይህንን ልል ያነሳሳኝ የቅንጅት አመራሮች ሰሞኑን ባወጡት መግለጫ ረመዳን በመሆኑ ሰልፍ አናደርግም አሉን::
Last edited by ETLOVE on Sun Oct 23, 2005 8:43 pm, edited 2 times in total.
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

Re: የመስቀል ደመራ ረብሻ ጸረ ሆርቶዶክስ ክርስትና ወይስ ....

Postby ልጁነኝ1 » Sun Oct 23, 2005 12:24 pm

በቀጥታ ከላእላይ አመራሩ ከቤተክርስቲያኗ የመጣ ይመስላል::

አዎ "ቅንጅቱ ያደረገውን " ዕደግፈዋለሁ የስልምናውን ጉባኤ ወገኖቻቺንና ሙስሊም ህብረተሰቡንም ማስታወስ ፍላጎታቸውንም ተቀብሎ ማርካት ይኖርብናል::

ጥያቄዎን ለላዕላይ አቡኑ ያቅርቡ እሳቸው ልክ እንደ አቶ: መለሰ ዜናዊ ሹመት የበለጠ ስላላቸው ይመልስልዎታል::

በተለይ ኢትዮጵያዊነት የሚሰማዎ መንፈስዎ ከተንኮል ይልቅ ቅንነት የሚያስብ ቢሆን ኑሮ በአሁኑ ጊዜ ይህን የመሰለ በታታኝ ወሬ እዚህ ላይ መተው ባልፃፉ ነበር::

የዜግነት ግዴታዎን ለመወጣት በሞከሩም ነበር:: ያንን ባለማድረግዎ ነው ወቅሼ የጻፍኩልዎ:: አዎ የኃይማኖት ጉዳይ በፖለቲካ ውስጥ ባይገባም:: ሃይማኖቶች ተሌሉ ደግሞ አገርና ህዝብ ፖለቲካም የለም:: መሻሻል የለም:: ተደጋግፈው የሚጓዙ ናቸው:: የረሞዳን ፍልሰታ ቀን የሚወጣውን ዜጋ ይመልከቱ እስቲ? ስንት ሚሊዮኖች ናቸው? ያስቡ:: አብረው ሊደሰቱ ይገባል ከወንድሞቻቺን እህቶቻቺኦን ጋር ይህን ልዩነት ይዘው ባሉበት አርፈው ይቀመጡ::

እረሞዳን ብዙ የሚሰራበት ወቅት ነው:: ሰደቃ የሚያደርጉበትና ቺግረኞችንም እየፈለጉ የሚያጠግቡበት የሚያለብሱበትና የሚረዱበት ጊዜ ነው ይህ ጾም በጸሎታቸው ሃያልነት ይዞ የሚመጣው ነገር አለ ለአገር ጠቃሚ የሚሆን::

ከምስጋና ጋር

ልጁነኝ1
ከ(ሰሐሊን)

ETLOVE wrote:በእውነት ስለመስቀል ደመራው ረብሻ ለምን ተቃዋሚዎች መግለጫ አላወጡም :?:ሀይማኖቱን ለመጠቀም ፈልገው ነበር ማለት ነው :?: ወይም ረብሻውን ይደግፉታል ማለት ነው ያ ባይሆን ኖሮ ማንም ሰው ለሀይማኖቱ ተቆርቃሪ ነው::
ለራሱ አይማኖት የማይቆረቆር ስለለላው አይማኖት እንደት ግድ ሊለው ይችላል የፖለቲካ ትርፍ ከሌለለው በስተቀር :: ይህንን ልል ያነሳሳኝ የቅንጅት አመራሮች ሰሞኑን ባወጡት መግለጫ ረመዳን በመሆኑ ሰልፍ አናደርግም አሉን::

yQNJT lxNDnT lÁäK‰s! kFt¾ xm‰éC -Nµ‰Â lS§ú Ãl#TN yTGL _r btkttY XNd¸ÃdRg# xStwq$ÝÝ y±RtEW l!qmNbR x!N©!nR `Yl# šWL X t¼M¼l!qmNbR w¼T BRt$µ ¸dQú xRB :lT bs-#T mGlÅ §Y XNd-qs#T yÑSl!Ñ HBrtsB brmÄN ÛM §Y bmçn# -NkR Ãl yTGL _r ¥DrG xlmÒl#N gL]W kòÑ k_QMT 24 b“§ XNd¸-‰ ”L gBtêLÝÝ xÃYzWM bòÑ wQT yÑSl!ÑN y¦Y¥ñT SR›T b¥ÃdÂQF mNgD l!wsÇ y¸Cl# «lSlS´ Ãl# yTGL SLèCN b¸q_l#T qÂT XÂúW”lN BlêLÝÝquote
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states

Re: የመስቀል ደመራ ረብሻ ጸረ ሆርቶዶክስ ክርስትና ወይስ ....

Postby moa » Sun Oct 23, 2005 5:32 pm

አዛኝ ቅቤ አንጓች!!!
አንተም ከዸደቢት ወጥተህ ሰው ልታጃጅል!!
ይሁዳው ጳጰስህ ያን እለት ምሳቸውን አግኝተዋል!!
በኢትዮጵያችን ታሪክ እንኳንስ ጳጳስ ጎልማሳም ቢሆን ቀድሞ የተከበረ ነበር።ሃገሪቷንም፤ ቤተመቅደሷንም፤ ሃገሪቷንም ያረከሱት ወያኔዎችና አባ ጳውሎስ ከደደቢት ያገዛዙ መንበር ላይ የወጡ እለት ነው።

ወደድክም ጠላህም እስልምናም ሆነ ክርስትና በኢዮጵያችን ታላላቅ ሃይማኖቶች ናቸው። የሁለቱም ሃይማኖት እኩልነት የተከበረ ስለሆነ ልታበላልጥና ጦርነት ለመቀስቀስ አትሯሯጥ።
እንደክርስቲያንነቴ የምነግርህ ቢኖር ታላቁ የእስልምና እምነትም ቢሆን በቀኑ እለት በታላቅ ድምቀት በኢትዮጵያውያን ይከበራል፡ ሞት ለወያኔ ከፋፋዮች!!
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

እምነቱን አላንቋሸሹም!

Postby አፈ-ጉባኤ » Sun Oct 23, 2005 7:35 pm

በጎሳና በጥቅም ችግር የተነሳ ምእመናኑና አስተዳደሩ ተበጣብጠው አንድ የጴንጤ ቤተክርስቲያን ለወራት ተዘግቶ በፖሊስ ይጠበቅ እንደነበር አስታውሳለሁ::

በዘመናችን በየእምነቱ አናት ላይ ቁጢጥ ያሉት ከመንፈሳዊነቱ ይልቅ ወደ አለማዊነቱ ያዘነብላሉ:: ስላባ ጳውሎስማ ምግባር ተዘክዝኮ ያለቀ ጉዳይ ስለሆነ ጊዜ ማጥፋት አያሻም::

ምእመናኖች በአጋዚያን ጥይት ባደባባይ ሲረግፉ ፍታት ያላደረጉ መንግስትን ረጋ በል ብለው ያልገሰጹ ሲኖዶስና አባት መንግስትና ተቃዋሚን ለማግባባትና እርቅ ለመፍጠር ያልሞከሩ ፓትርያርክና ሲኖዶስ በየቱ ሞራላዊ አባትነታቸው ነው ህዝቡን አርፈህ ቁጭ በል አታምጽ እሚሉት?

የህዝቡን ለነጻነትና ለስልጣን መነሳሳት ለማኮላሸት በሰላም ስም አቡኑ ያቀረቡትን ተማጽኖ መቃወም መብትና አግባብ እንጂ እምነቱን ማራከስ አይደለም:: ሲኖዶሱም ድርጊቱን የማውገዝ ሞራላዊ ብቃት የለውም::

በእለቱ የተሰበሰበው አብዛኛው ጠብና ንቀቱ በእምነቱ ጥላ ስር ለጥቅማቸው ካደሩ አባቶች እንጂ ከተዋህዶ አይደለም:: እንዲያውም ለእምነቱና ለነጻነቱ ካለው ቅናት የተነሳ ያደረገውም ሊሆን ይችላል::

ለሁሉም ቤተክርስቲያኒቱ ከመጣው ሁሉ እየተመሳሰለች መኖሯን አቁማ የትናንት ወዲያውን ሞራላዊ የበላይነቷን ልትመልስ ይገባታል:: ህዝቡም ለሌሎች የኢህአዴግ ሹማምንት የነፈገውን ባደባባይ በጸጥታ የመናገር መብት ለአቡኑም እማይነፍግበት ምክንያት የለውም- በልባቸው ኢህአዴግ ናቸውና::

ከወገናዊ ሰላምታ ጋር
አፈ-ጉባኤ
አፈ-ጉባኤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 302
Joined: Tue Mar 15, 2005 5:20 pm
Location: united states

Postby ETLOVE » Sun Oct 23, 2005 8:02 pm

እኔ እንካን አሳበቤ ስለሀይማኖት መሪዎች ለመናገር ፈልገ ሳይሆን ስለ ሀይማኖታችንን ክብር መንሳትና የፖለቲካ መጠቀሚያ መሆን እንደሌለበት አስተያየተን ለመሰንዘር ነው :: ለምን ደርሳችሁ ቱግ እንዳላችሁ ቢገባኝም
አሳቤን በግልጽ ለማስቀመት ሞክሬያለው::

በእውነት የእስልምናን አይማኖት ረብሻ እንዳይፈጠርበት ካሰብን ኦርቶዶክርስ ለምን መበትጥበጥ አስፈለገ :?: ከፖለቲካው ጋር ካያያዝነው ስለምርጫው የኦርቶዶክስ አይማኖት ምንም መግለጫ አልሰጠችም ነገር ግን የእስልምና ሀይማኖት
ጽ/በት መግለጫ ሰጥታል በየት በኩል ነው ኦርቶዶክስን እንደፖለቲካ ወገንተኛ የተደረገውና በአገራችን ታላቅና የውጭ ቱሪስቶች መጥተው ታዳሚ የሚሆኑበትን የኦርቶዶክስ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን በሀል የሆነውን ደመራን ለመበጥበጥ ያስፈለገው :?: ይህ በእውነው ታሪክ ይቅር የማይለውና ተልካሻ ስራ ነው ባይ ነኝ::

ይህ በሀል ከ 14 ሀመት ወዲህ ከሀይማኖታዊ በሀልነቱ ባሻገር የቱሪስት መስህብ ሆኖ የገቢ ምንጫችንም እየሆነ ነውና ቅንጅቶች ሀይማኖቱን ለቀቅ ፖለቲካን ጠበቅ እላለው::

ሀሳቤ ነጻ የትኛውንም ሀይማኖት ያልወገነና : ለሁሉም ሀይማኖቶች ክብር በመስጠት ነው::

ራሱን ያከበረ ሰውንም ያከብራልና ቅድሚያ እስኪ ለማንነታችን ክብር እንስጥ ከየትኛውም ኦርቶዶክሳውያን የሚጠበቅ ይመስለኛል የቅንጅትም ደጋፊ ቢሆን::

ቸር እንሰንብት::
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

Postby የዘመኑ ልሳን » Sun Oct 23, 2005 8:29 pm

እኔ ያልገባኝ የመስቀል ደመራ እና ተቋዋሚዎች የሚያገናኝ ነገር ምኑ እንደሆነ ነው?ህዝብ የሐይማኖቱ መሪ ነጻ ሆነው የማይገባ ነገር ሲፈጸም ህዝብን መከላከል ሲገባቸው በዝምታ በማለፋቸውና እንደውም ቤተ ክርስቲያን ህዝብ ሲጨፈጨፍ ለምን ዝም ብላ ታያለች ያሉትን ደቀ መዝሙራት ማባረራ በአስተዳደሩ ላይ ያሉ ሰዎች ምን ያህል የፖለቲካ ወገንተኝነት እንደያዛቸው ያሳያል::

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ህዝብን በማስተባበር ከጥቃት ትከላከላለች እንጂ እንዲህ ወራዳ ስራ ውስጥ መገኘት የለባትም::ስለሆነም ህዝብ አሁን በአስተዳደር ያሉት ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊና ሐይማኖታዊ ግዴታዎች ባለመወጣቸውና ይባስ ብለው ፖለቲካዊ ወገኝተኝነት ማሳየታችው ድሮም ከመመረጣቸው ጊዜ ጀምሮ በሚሰሩት ጉዳይ አንድም ቀን ደስተኛ ሆኖ የማያውቀው ህዝብ ብሶቱን በመስቀል አደባባይ ለመግለጽ በቅታል::

ይህ የህዝብ ተቋውሞ የፖለቲካ ሰዎች መቀስቀስ የሚያስፈልጋቸው አይመስለኝም: ማንም ከመሬት ተነስቶ ቤተ ክርስቲያን የነፍጠኛ መከማቻ ናት ብሎ ክርስቲያኖችን ሲሳደብ ያለመቋወማ እራሱ በቂ ምክንያት ነው::እነዚህ አሁንያሉ አመራሮች ቤተ ክርስቲያናን እንኳን መከላከል ካልቻሉ ታዲያ ወንበሩ ላይ ቁጭ ያሉት ምን ሊተብቁ ነው::ይሁዳ ብቻ አይደለም የቤተ ክርስቲያናን አስተዳደር በአቀኝነት ለሚያስተዳድሩ ማስረከብ እንዳለባቸው በሰላማዊ ሰልፍና በሌሎችም የተቋውሞ ሁኔታዎች መጠየቅ አለበት እላለሁ::
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

Re: እምነቱን አላንቋሸሹም!

Postby ETLOVE » Sun Oct 23, 2005 8:29 pm

አንተ የምትለው የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ቀድሞ ነጻ ነበረ ነው የምትለኝ :?: እስኪ ንገረኝ አዋቂ ትመስላለህ በየትኛው ዘመነ መንግስት :?:
የቅርቡን ብንመለከት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ጳጳስ የሾሙት ንጉስ ሀይለስላሰ አይደሉ ካወቅከው ማለተ ነው ::የንጉሱ ስም በየቅዳሴው ላይ ሲነገር አልነበር የተኖረው:?: አሁን ያለውን ሁነታ ስንመለከት ጳጳሱ እስካሁን ከነበሩት የሚለያቸው
ብሄራቸው ትግራይ መሆኑና ገለልተኛና አርቆ አስተዋይ : ሚዛናዊ የአይማኖት መሪ መሆናቸው ነው:: ህድሜያቸውን ያርዝምልን::

ነገር ግን :ነገር ግን: ማስተዋል ስላልተሰጠን የኛ ስራ በሆነው ባልሆነው መቃወም ነው::ትልቅ ትንሽ ሳንል መሳደብ ማንቃሸሽ ይህ ሊሆን ነው እንግዲህ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ከዚህ ያድነን :!:

ቸር እንሰንብት::

አፈ-ጉባኤ wrote:በጎሳና በጥቅም ችግር የተነሳ ምእመናኑና አስተዳደሩ ተበጣብጠው አንድ የጴንጤ ቤተክርስቲያን ለወራት ተዘግቶ በፖሊስ ይጠበቅ እንደነበር አስታውሳለሁ::

በዘመናችን በየእምነቱ አናት ላይ ቁጢጥ ያሉት ከመንፈሳዊነቱ ይልቅ ወደ አለማዊነቱ ያዘነብላሉ:: ስላባ ጳውሎስማ ምግባር ተዘክዝኮ ያለቀ ጉዳይ ስለሆነ ጊዜ ማጥፋት አያሻም::

ምእመናኖች በአጋዚያን ጥይት ባደባባይ ሲረግፉ ፍታት ያላደረጉ መንግስትን ረጋ በል ብለው ያልገሰጹ ሲኖዶስና አባት መንግስትና ተቃዋሚን ለማግባባትና እርቅ ለመፍጠር ያልሞከሩ ፓትርያርክና ሲኖዶስ በየቱ ሞራላዊ አባትነታቸው ነው ህዝቡን አርፈህ ቁጭ በል አታምጽ እሚሉት?

የህዝቡን ለነጻነትና ለስልጣን መነሳሳት ለማኮላሸት በሰላም ስም አቡኑ ያቀረቡትን ተማጽኖ መቃወም መብትና አግባብ እንጂ እምነቱን ማራከስ አይደለም:: ሲኖዶሱም ድርጊቱን የማውገዝ ሞራላዊ ብቃት የለውም::

በእለቱ የተሰበሰበው አብዛኛው ጠብና ንቀቱ በእምነቱ ጥላ ስር ለጥቅማቸው ካደሩ አባቶች እንጂ ከተዋህዶ አይደለም:: እንዲያውም ለእምነቱና ለነጻነቱ ካለው ቅናት የተነሳ ያደረገውም ሊሆን ይችላል::

ለሁሉም ቤተክርስቲያኒቱ ከመጣው ሁሉ እየተመሳሰለች መኖሯን አቁማ የትናንት ወዲያውን ሞራላዊ የበላይነቷን ልትመልስ ይገባታል:: ህዝቡም ለሌሎች የኢህአዴግ ሹማምንት የነፈገውን ባደባባይ በጸጥታ የመናገር መብት ለአቡኑም እማይነፍግበት ምክንያት የለውም- በልባቸው ኢህአዴግ ናቸውና::

ከወገናዊ ሰላምታ ጋር
አፈ-ጉባኤ
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

Postby ETLOVE » Mon Oct 24, 2005 12:50 am

ሀይሉ ሻውል ለእስልምና ጠበቃ ሊሆንም ዳዳው ወይ ጉድ አይሰማም የለ አይ ራስን አለማወቅ::
AFRICAN COMMUNICATION PROBLEM
PLEASE LET US LISTEN EACHOTHER.
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

ሌባ

Postby ባና » Mon Oct 24, 2005 1:06 am

--------------------------------------------------------------------------------

የድሀ ኢትዮጲያንን የገጠጠ አጥንት ግጠው በውጭ ባንክ ከ 50 ሚሊየን ዶላር በላይ ያጋበሱት ባልና ሚስት ሌቦች መለስ እና ሚስቱ ክስ ሊቀርባቸው በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ጉዳዩን ያጋለጡት ጋዜጠኞች ጠበቃ አቶ ሼክስፒር አረጋግጠዋል :: የሚቀርበው ክስ በበቂ ማስረጃ የተጠናከረም ነው ::

ቁሻሾቹ በቅርቡ የዘረፉትን ብር 54 ምሊየን ለማድረስ በትንሳኤ ጋዜጠኞች ላይ የ 4.2 ሚ /ን ዶላር ካሳ ይከፈለን ክሥ ክመሰርቱ በሁዋላ ጉዳዩ ወደነሱ መዞሩን ሲያረጋግጡ ክሱን ማንሳታቸው የነቀዞቹ ጠበቃ ከ VOA ጋር ባደረጉት ቃ /ም ትናንት ገልጸዋል ::
ባና
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Fri Apr 01, 2005 7:58 am
Location: united states

Postby ሜሎ » Mon Oct 24, 2005 3:00 am

ETLOVE wrote:ሀይሉ ሻውል ለእስልምና ጠበቃ ሊሆንም ዳዳው ወይ ጉድ አይሰማም የለ አይ ራስን አለማወቅ::


አንድ የማደንቃችሁ ነገር ቢኖር ከመሀይም አንደበታችሁ ለሚወጣው ሀሳብ ያለማፈራችሁ ብቻ ነው:: ጊዜ ያለፈበትና እረኛ እንኳ የማይታለልበትን ከፋፋይ ሀሳብ ይዛችሁ ብቅ ትሉና ሳታፍሩ ለሁሉም መልስ ለመስጠት የቆጥ የባጡን ትቀባጥራላችሁ:: በሌላ በኩል ግን የሚያሳዝኑኝ ለዚህ ለመሀይም አስተያየታችሁ መልስ ለመስጠት ጊዜያቸውን የሚያባክኑ ወገኖቻችን ጉዳይ ነው:: አዙሮ ማየት, አንብቦ መረዳት ከማይችል ወይም ከማይፈልግ ወገን ጋር ዳይሎግ የማድረጉ ጠቀሜታ ምኑ ላይ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም:: ሰውን እንዳያሳስቱ ነው እንዳይባል ዛሬ ማንነታቸው እንኳን ለተማረ ቀርቶ ላልተማረ እረኛ ጭምር ግልጽ ሆኗል:: በምንም መንገድ ማታለል አይቻላቸውም:: ስለዚህ መልስ ባለመስጠት ባዶነታቸውን መግለጽ ይቻላል ነው የምለው


የኢ/ያ ህዝብ ምን ጊዜም ያሸንፋል!!!!!!!!!!!!
ሜሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 252
Joined: Fri Feb 11, 2005 12:31 am

Postby ETLOVE » Mon Oct 24, 2005 3:12 am

ሜሎ እኔም አሳብህን እጋራዋለው:: የሚሰማ ሲኖር አይደል::

ደህና ክረምልኝ::
AFRICAN COMMUNICATION PROBLEM
PLEASE LET US LISTEN EACHOTHER.
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

Re: የመስቀል ደመራ ረብሻ ጸረ ሆርቶዶክስ ክርስትና ወይስ ....

Postby ብሔረ አራዳ » Mon Oct 24, 2005 11:10 am

moa wrote:አዛኝ ቅቤ አንጓች!!!
አንተም ከዸደቢት ወጥተህ ሰው ልታጃጅል!!
ይሁዳው ጳጰስህ ያን እለት ምሳቸውን አግኝተዋል!!
በኢትዮጵያችን ታሪክ እንኳንስ ጳጳስ ጎልማሳም ቢሆን ቀድሞ የተከበረ ነበር።ሃገሪቷንም፤ ቤተመቅደሷንም፤ ሃገሪቷንም ያረከሱት ወያኔዎችና አባ ጳውሎስ ከደደቢት ያገዛዙ መንበር ላይ የወጡ እለት ነው።
ወደድክም ጠላህም እስልምናም ሆነ ክርስትና በኢዮጵያችን ታላላቅ ሃይማኖቶች ናቸው። የሁለቱም ሃይማኖት እኩልነት የተከበረ ስለሆነ ልታበላልጥና ጦርነት ለመቀስቀስ አትሯሯጥ።
እንደክርስቲያንነቴ የምነግርህ ቢኖር ታላቁ የእስልምና እምነትም ቢሆን በቀኑ እለት በታላቅ ድምቀት በኢትዮጵያውያን ይከበራል፡ ሞት ለወያኔ ከፋፋዮች!!

-----------
ወንድሜ ሆይ! ሌላ ምንም አልልህ::
የኢትዮጵያ አምላክ ይ-ባ-ር-ክ-ህ!!
ይኽችኛው (ኢትዮላቭ)ግልገሏ ወያኔ ነች ተልዕኮዋ እንዳበደ ዉሻ እየለካከፈች ሥራ ማስፈታት ነው:: ግድየለም እኛ በአንድ እጃችን እየሠራን በሌላው ምሷን እንሰጣታለን:: መቸም ግልገሎቹ አጥጋቢ መልስ የመስጠት ብቃቱም ሥልጣኑም አይኖራቸውም:: እንዲያው ለመጠየቅ ያህል በዚህ በደመራው የታጋይ ጳውሎስ ቅሌት ላይ አስተያየት የሰጠ የፖሊቲካ ፓርቲ አለ? ከሌለ ዘለህ ለምን ቅንጅት ትከሻ ላይ ትንጠለጠላለህ? ማነህ ኢትዮላቭ ተብየው ጥያቄየ የሚመለክተው በይበልጥ አንተን ነው:: ያንተስ ጳውሎስ ንጹሀን ዜጎች በፋሽሽቱ ፓርቲያቸው የግድያ ቡድን (አግአዚ) በጠራራ ፀሐይ ወገኖቻችን ሲረሸኑ ምነው ድምፅ አላሰሙ? አንተስ ለምን አልጻፍክም? ንገሩኝ ባይ መንገድ ላይ ምን ያደርጋል ነው የሚባለው? ነገሩ ሁሉ አላማረባችሁም:: ወይ አርፎ መቀመጥ አለበለዝያ መስማት የማትፈልጉትን ሐቁን ትሰማላችሁ:: በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጣችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በሙሉ በተለይ ግን ሞዓ እግዚአብሔር ይባርካችሁ::
ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን!
ብሔረ አራዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 39
Joined: Wed May 04, 2005 5:43 am
Location: ethiopia

Postby ሜሎ » Mon Oct 24, 2005 2:35 pm

ETLOVE wrote:ሜሎ እኔም አሳብህን እጋራዋለው:: የሚሰማ ሲኖር አይደል::

ደህና ክረምልኝ::

ኢትዮ ላቭ!! ወዴት ወዴት?


የኔን ሀሳብ መጋራት አትችልም; የበታቸኝነት ስሜት የተጠናወተብህ ወያኔ ነህ:: የኢ/ያ ህዝብ ባንድ ላይ ሆኖ አንፈልጋችሁም ብሏልና እንደአበደች ውሻ ወዲያና ወዲህ ብትቅበዘበዝ የምታተርፈው ምንም ነገር የለም ;;የወያኔና ግብረ አበሮቹ መጥፊያው ወቅት መቃረቡን አበስርልሀለሁ::

ድል ለኢ/ያ ህዝብ!!!!!!!!!!!!!!!!
ሜሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 252
Joined: Fri Feb 11, 2005 12:31 am


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests