ለሳይበር ኢትዮጵያ አስተዳደር

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ለሳይበር ኢትዮጵያ አስተዳደር

Postby ያሙ » Mon Oct 24, 2005 3:17 am

ለዋርካ (ሳይበር ኢትዮጵያ ዌብ ሳይት)ባለቤቶች

በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታዮ አቀርባለሁ።በመቀጠልም ከአንድ አመት በላይ

የተጠቀምኩበት ዋርካ ፖለቲካና ዋርካ ቻት ሩም ለምንና በምን ምክንያት

እንደታገድኩኝ በናንተ በኩል አጥጋቢ መልስ እንድትሰጡኝ የቅሬታ

ደብዳቤዮን ለመፃፍ ተገድጃለሁ።እንደሚታወቀው በወቅቱ የአገራችን ፖለቲካዊ ትኩሳት ሁላችንም ከያለንበት

የተሰማንን ስንፅፍና ስንከራከር፡መላው የዋርካ ተሳታፊ እንደየግል እምነቱ

የፈለገውን የፖለቲካ ድርጅት በመደገፍ ባንፃሩ ደግሞ ለማይደግፈውን

የፀና ተቃውሞውን እያቀረበ ሁላችንም የተቻለንን እውቀት ለመግብየት

መቻላችን ሃቅ ነው።እኔም የተቃዋሚ ቡድኖች በመቃወምና ገዢው ፓርቲ በመደገፍ የራሴን

አመለካከትና አስተሳሰብ ስፅፍና ስከራከር ቆይቻለሁ።በሌላ በኩል ደግሞ

እኔ ወያኔን በመደገፌ ጠንካራ ውግዘትና ስድብ ስቀበል አንድም ቀን

ለሰደቡኝ ሁሉ በስድብ ላለመመለስ ብዙ ጥረት አድርጌያለሁ።አመለካከቴን

በገለፅኩበት ሁሉ የዋርካ ተሳታፊ አብዛኛው ማለት ይቻላል የስድብ ናዳ

ሲዘረግፍልኝ የዋርካ አስተዳዳሪዎች ሳትመለከቱት አትቀሩም።እንግዲህ ሳይበር ኢትዮጵያ(ዋርካ ፎረምን) ለአገልግሎት ስታቀርቡ የናንተ

ፖለቲካዊ እምነት ምንም ይሁን ምን ወደ ጎን በመተው እንደሆነ አልጠራጠርም።

እንዲህ አይነት “ፈረም” ሲከፈት የሁሉንም አመለካከት ያላንዳች ተፅእኖ

ማስተናገድ እንዳለባችሁም የምትስቱት አይመስለኝም።ታድያ ይሄ መሆኑ እየታወቀ የኔ በዋርካ የመሳተፍ እገዳ መጣላችሁ እኔን ከማስደንገጡ

አልፎ በጣም አስዝኖኛል።ወያኔ መደገፌን ይሄን ያህል የሚያስጠላና ከተሳትፎ

የሚያሳግድ ከሆነ በዋርካ ባልሳተፍም በአንባቢነት ለመቀጠል እሞክራለሁ።የሚገርመው ደግሞ የዋርካ “ፀሃፊ” ሁላ የሚፅፈውን አጉራ ዘለልና በወያኔ ሰበብ

ሌላው ብሄር የሚኮነንበትና የሚሰደብበት ሁኔታ እየተስተዋለ በናንተ በኩል አንድም

ጊዜ ማስጠንቀቅያና እገዳ አለመስጠታችሁ ነው።ወይስ ሳይበር ኢትዮጵያ “የቅንጅት”

እና “የሕብረት” ደጋፊዎች መፈንችጫ ነው?በመጨረሻም ለማለት የምፈልገው አንድም ቀን ዋርካ ያልጎበኘሁበት ቀን

እንደሌለና ዋርካ ማለት ለኔ በጣም አስፈላጊ ነገር መሆኑ ተረድታችሁ ያጠፋሁት ካለ

እርምት እንድወስድበት ጥቆማችሁ እንድሰጡኝና እንደ ቀድሞ የመሳተፍ መብቴን

እንድትጠብቁል በትህና ሳሳስባችሁ አሁን ከከፍተኛ ሃዘኔታ ጋር ነው።ለጥያቄዮ

አጥጋቢ ምላሽ እንደምትሰጡኝ እተማመናለሁ።አመሰግናለሁ

*በዋርካ ፎረም “አለክስ” በሚባለው የተጠቃሚ ስም የተመዘገብኩ ነኝ
እባካችሁ፡እንደማመጥ..."ሃሳብን በሃሳብ መግደል ይቻላል፡ሃሳቡን የተሸከመው ሰው መግደል ግን አይቻልም"
ያሙ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Mon Oct 24, 2005 3:03 am
Location: united states

Postby ETLOVE » Mon Oct 24, 2005 3:33 am

መጻፍህ ለነገሩ ትኩረት መስጠትህንና አስተዋይ መሆንህን ያመለክታል ነገር ግን ይህን ያህል ባንተ ላይ የሚያመጣው ለውጥ ሊኖር ስለማይችል አትጨነቅ:: ወንድም: በርካታ መድረኮች ስላሉ ጎራ በልና ተስተናገድ ኢትዮጵያውያን ዋርካ ላይ ብቻ ናቸው ያለህ ማን ነው :?:
የሰረዙህ ዋርካዎች ዋርካ ሊሆኑም ላይሆኑ ይችላሉና ነቃ በል.......

ቸር እንሰንብት::
Meles Zenawi my hero.
AFRICAN COMMUNICATION PROBLEM
PLEASE LET US LISTEN EACHOTHER.
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

አመሰግናለሁ

Postby ያሙ » Mon Oct 24, 2005 3:52 am

ETLOVE wrote:መጻፍህ ለነገሩ ትኩረት መስጠትህንና አስተዋይ መሆንህን ያመለክታል ነገር ግን ይህን ያህል ባንተ ላይ የሚያመጣው ለውጥ ሊኖር ስለማይችል አትጨነቅ:: ወንድም: በርካታ መድረኮች ስላሉ ጎራ በልና ተስተናገድ ኢትዮጵያውያን ዋርካ ላይ ብቻ ናቸው ያለህ ማን ነው :?:
የሰረዙህ ዋርካዎች ዋርካ ሊሆኑም ላይሆኑ ይችላሉና ነቃ በል.......

ቸር እንሰንብት::
Meles Zenawi my hero.በመጀመሪያ ላመሰግንህ እወዳለሁ::በእውነቱ ነው የምልህ በዋርካ (ሳይበር ኢትዮጵያ) አስተዳዳሪዎች እርምጃ በጣም ነው የተናደድኩት::እንዴው ሲያስቡት የወያኔ ደጋፊ መሆኔ እያወቁ "ቅንጅትና" "ሕብረት" ልደግፍና በነሱ ምትክ ላቅራራላቸው ጠብቀው ይሆን?እንዴት ይሆናል?ወይም ከጅምሩ ዌብ ሳይቱ ለ"ቅንጅትና" "ሕብረት" ደጋፊዎች ብቻ የተከፈተ ነው ብለው ቢያሳወቁንና እኛም በነሱ ዌብ ሳይት ባልተሳተፍን:ከዛ ውጭ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች ብለው ካሉ ጥሩም ይሁን መጥፎ አመለካከት የማስተናገድ ግዴታ አለባቸው::

ወያኔን በተለያየ አመለካከት እንደሚነቅፉትና እንደሚሰድቡት እኔም የወያኔ ደጋፊ እንደመሆኔ መጠን ወያኔን ብደግፍና የተሰማኝን አመለካከት ባንጸባርቅ ምኑ ላይ ነው ሃጢያቱ?

ለማንኛውም ሳይበሮች ይህን ጉዳይ በጥልቀት ተገንዝበው አንድ መፍትሄ የሰጡኝ ዘንድ አሁንም በድጋሜ እጠይቃቸዋለሁ::ስለሆነም ድሮ ስጠቀምበት የነበረውን የተጠቃሚነት ስሜ ከእገዳ ነጻ እንደሚያደርጉልኝ ተስፋ አለኝ::

አመሰግናለሁ
እባካችሁ፡እንደማመጥ..."ሃሳብን በሃሳብ መግደል ይቻላል፡ሃሳቡን የተሸከመው ሰው መግደል ግን አይቻልም"
ያሙ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 6
Joined: Mon Oct 24, 2005 3:03 am
Location: united states

Postby ETLOVE » Mon Oct 24, 2005 4:55 am

ወንድሜ አለክስ ከመለሱልህ እሰየው ካልሆነም ብዙም አትጠብቅ አሁን በምትጽፍበት ቀጥል::
የምትጽፈውን እንደሚያጠፉት ተገንዝበሀል :?:
ሳይበሮች ብቻ ሳይሆኑ ስልጣን የተሰጣቸው በጅሮንዶች አሉ ስራቸው እነሱን የሚቃወም ጽሁፍ ማጥፋት(መሰረዝ) ነው::

ነገሩ የኦርቶዶክስና ፕሮተስታንት ሀይማኖተኞችን አስታወሰኝ አሁንም በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች ይስተዋላል:: ሀይማኖቱን የቀየረ እሳት አይጭርም ከዕድር ይባረራል ከማህበራዊ ኑሮው ይገለላል::
አሁን ደግሞ በባህር ማዶው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይህ ነገር እየተስተዋለ ነው::

በባህር ማዶ የሚገኙ የቅንጅት ደጋፊ ግለሰቦች
በተለያዩ ዌብ ሳይቶች ላይ ተጽህኖ እያደረጉ ነው
ማንኛውንም ቅንጅቱን በተደጋጋሚ የሚጻረሩ ጽሁፎች ሲወጡ ለዌብ ሳይቱ ባለበት ባስቸካይ ይደውሉለታል ጽሁፎቹንም እንዲሰርዛቸው በተደጋጋሚም እንደዚህ ሀይነት ጽሁፍ የሚጽፉትን ከአባልነት ያሰርዛሉ ያን ካላደረገ በአድማ ከማህበራዊ ኑሮ ያስወጡታል
ስለዚህ እነ በባለበቶቹ ላይ አልፈርድም መኖር አለባቸውና:: ኢትዮጵያውያን በነጻነት ሀሳባቸውን መግለጽ አልቻሉም:: ሀሳባችንን በነጻነት መግለጽ አለብን ያካልሆነ ደግሞ ለዘላለም ደንቆሮ ነው የምንሆነው::

ትንሽ የተረዳህኝ መሰለኝ ደህ ና ሁን::

ቸር እንሰንብት::
AFRICAN COMMUNICATION PROBLEM
PLEASE LET US LISTEN EACHOTHER.
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

Postby እንድሪያስ » Mon Oct 24, 2005 2:51 pm

ቅንጅት ማለት በኢትዮጵያን የተዋቀረ ....ለፍትህ ለሰላምና ለዴሞክራሲ የሚታገል ህዝባዊ ፓርቲ ነው ::
ቅንጅት ማለት ኢትዮጵያዊያን በጠበመንጃ የተነጠቁትን መሰረታዊ መብት ህጋዊ በሆነ መልኩ ታግሎ ለማስመለስ ቆርጦ የተነሳ የህዝብ ጠበቃና ልሳን ነው ::
ሳይበር ደግሞ የኢትዮጵያዊያን መናኸሪያ(home) እንደመሆኗ መጠን ቅንጅትም ብዙ ደጋፊዎች እንደሚኖሩት የታወቀ ነው ::
እውነት እልሀለሁ "ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች" የሚለው ስንኝ ወያኔንና የወያኔ ደጋፊዎችን የማይመለከትና የማያካትት መሆኑ አግባብነት አለው እላለሁ ::
በበኩሌ አምንበታለሁ ::
ምክንያቱም ኢትዮጵያዊያንን እያፈነና እየገደለ ለራሱ "ከራሱ" ብቻ መከላከያውን እያጠናከረና በዝርፊያ ሀብት እያካበተ የሚኖር ጎጠኛ የፖለቲካ ድርጅት ነውና ::
ኢትዮጵያ ያለውን ሁሉ በአማራ ትምክህተኛነት በመፈረጅ የጥላቻና የማራራቅ ፖሊሲ የሚያራምድ:-
ሻቢያ የጠላውን (ኢትዮጵያዊነት) ጠልቶ ይህንንም ጥላቻ ትናንት በገሀድ ዛሬ ደግሞ በስውር አጀንዳ የሚያንቀሳቅስ የህዝብና የአገር ጠላት ነውና ::
ስለሆነም እንደአንተ አይነቱን የህዝብ ጠላት ከዚህ ማባረሩ ፍትሀዊ ብቻ ሳይሆን የዜግነት ግዳጅንም እንደመወጣት እቆጥረዋለሁ::
ያሙ wrote:......ወይም ከጅምሩ ዌብ ሳይቱ ለ "ቅንጅትና "ሕብረት" ደጋፊዎች ብቻ የተከፈተ ነው ብለው ቢያስውቁንና እኛም በእነሱ ዊብ ሳይት ባልተሳተፍን: ከዛ ውጭ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች ብለው ካሉ ጥሩም ይሁን መጥፎ አመለካከት የማስተናገድ ግዴታ አለባቸው ::
ኢትላቭ የሚሉህ ....ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ገደብ ሀሳባችን እየገለጽን ነው ::
የትኛው የወያኔ ዊብ ሳይት ላይ ነው ወያኔን በመተቸት መጻፍ የሚቻለው ? ይሄ ይታሰባል ?
ለምን አይጋ ፎረም ገብተህ አትደናቆርም ?
ETLOVE wrote:


Code: Select all
  ኢትዮጵያውያን በነጻነት ሀሳባቸውን መግለጽ አልቻሉም:: ሀሳባችንን በነጻነት መግለጽ አለብን ያካልሆነ ደግሞ ለዘላለም ደንቆሮ ነው የምንሆነው::


ትንሽ የተረዳህኝ መሰለኝ ደህ ና ሁን::

ቸር እንሰንብት::
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1784
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

Postby ወዲ ሰበርጉማ » Mon Oct 24, 2005 3:07 pm

እንድሪያስ wrote:እውነት እልሀለሁ "ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች" የሚለው ስንኝ ወያኔንና የወያኔ ደጋፊዎችን የማይመለከትና የማያካትት መሆኑ አግባብነት አለው እላለሁ ::
ወዲ ሰበርጉማ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Thu Mar 17, 2005 4:10 pm
Location: united states

አንድርያስ!

Postby ላሊበላ4 » Mon Oct 24, 2005 3:19 pm

ሠላምታዬ የቀደመ ይሁንልህ:: ወንድሜ ያነሳኃቸውን መልክቶቺህ ሁሉ በዕውነት ላይ ያነጻጸሩ ናቸው::

ወያኔን በመደገፌ የዋርካ ላይ ጸሐፊዎች ሁሉ ይሰድቡኝ ነበር ይላል:: በተጨማሪ ህዝብን ለህዝብ የሚያለያዩ መልክቶቻቸውን ስለተቃወምኩ በሚል ይደሰኩራል ሰውዬው::

ይልቅስ ቆሜለታለሁ ለሚለው ለወያኔ ሕወኃት ምክሩን በአቀረበላቸው ነበር:: ምክንያቱም ሕዝባዊ መዓበል ይዟቸው ከመጉረፉ በፊት::

ማንም ሊወዳደረው የማይቺል የማይቻለውም ነው:: የህዝብ ቁጣ ያንን የተገነዘበው አይመስለኝም:: እንዲያውም ለፈጠራቸው ሻቢያ ያሰጋዋል:: ምክንያቱም የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ቀይ ባህር 680 የባህር ማይሎች ናቸው እዚያ ነው ድንበራቺን:: ይህን ባለመገንዘብ ህወኃቶች ወያኔዎች ድንጋዮቹ ቢባሉ አያንስባቸውም:: ያገራቺንን በደሃ አቅሟ በህዝብ ግብር ያሰራቺውንና እስካሁንም እዳው ተከፍሎ ያላለቀውን የአሰብ ነዳጅ ማጣሪያና ቢያንስ ወደ 11 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በብድርና እንዲሁም ከካዝናዋ አውጥታ ያስፋፋቺውን ወደቧንና ከተማውን ጭምር ከአፋር ህዝብ ጋር አብሮ የሰጠው ወራዊውን ወያኔን የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጠላት ደግፎ "እዚህ ከኢትዮጵያ አንበሶች" ግሩፕ ወይም ዋርካ ፖለቲካ ውስጥ መጥቶ ታልጻፍኩ በሚል ለሳይበር አስተዳዳሪዎቾና ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ማቅረቡ ያስደንቃል::

ህወኃቶች እነ ቴዎድሮስ ሐጎስ:: እነ የማነ ጃማይካ:: እነ መለሰ ዜናዊ (አለማሽ) እነ ስብኃት ነጋ እነ ነዋይ መንግስት አብ::እነ በረከት ሲሚኦን ሌሎቹም ጭምር የሚያራምዱብን የተጠናበዘ ዘረኛና ፈንጋይ ሥርዓትን ደግፎ ከመሐላቺን ገብቶ ሲረብሸን ከርሟል:: ከንግዲህ ይበቃኃል መባሉ በመሠረቱ ዋርካ ለምን እንደቆመቺ ያመለክታል:: ከዚያ አልፎ ሊወቅሳት አይገባም::

የህዝቡን ድምጽ በጠመንጃ ቀምተዋል:: የቀራቸው ቢኖር ይህቺን ሣይበር ኢትዮጵያን ለመቀማት የሚያደርጉት ጥረት አይሳካላቸውም:: በተለይ ከሰሞኑ ደግሞ የሲቪል ኮሌጅ ምሩቆች የወያኔ አዳዲስ ካድሬዎች መተዋል:: እነ ኢትዮ ላቭ አይነቷም የዚያው ድምር ነች::

ስለዚህ ያሳየኃቸውን ትምህርታዊነት የሚሰጥና አንጎላቸውንም ወደ ማመዛዘን የሚመራ(የሚጋብዝ) መልክቶቺህን አደንቃለሁ::

*ቀይ ባህር ዳር ድንበራችን ነው*

*ደብረ ቢዘን (አቡነፊሊፖስ) የኢትዮጵያ አንጡራ ኃብቷም ነው*

ዘወትር አክባሪህ
ላሊበላ4
ላሊበላ4
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 201
Joined: Fri Dec 24, 2004 8:47 pm
Location: united states

Re: አመሰግናለሁ

Postby ሜሎ » Mon Oct 24, 2005 3:55 pm

ያሙ wrote:
ETLOVE wrote:መጻፍህ ለነገሩ
ትኩረት መስጠትህንና አስተዋይ መሆንህን ያመለክታል ነገር ግን ይህን ያህል ባንተ ላይ የሚያመጣው ለውጥ ሊኖር ስለማይችል አትጨነቅ:: ወንድም: በርካታ መድረኮች ስላሉ ጎራ በልና ተስተናገድ ኢትዮጵያውያን ዋርካ ላይ ብቻ ናቸው ያለህ ማን ነው :?:
የሰረዙህ ዋርካዎች ዋርካ ሊሆኑም ላይሆኑ ይችላሉና ነቃ በል.......

ቸር እንሰንብት::
ለያሙ!

ስማ ወንድማለም! እንደአባባልህ ሁሉም የውርካ ፎረም ተሳታፊዎች ሀሳብህን የማይወዱት ከሆነ ሌላ ሰው ከሚያባርርህ ይልቅ እራስህ ለምን ለቀህ አልወጣህም ነበር? ይህ ፎረም የውይይት ፎረም መሆኑን ከተረዳህና የምታቀርበውም ሀሳብ የሚያወያይ መሆኑን አምኖ ለመወያየት የሚፈልግህ ከሌለ ያንተ እዚህ መዳከር ምን ፋይዳ አለው ትላለህ:; አንተ እራስህ እንደገለጽከው ያንተ ሀሳብ/የወያኔ ሀሳብ/ የተጠላውና የተወገዘው በዋርካ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢ/ዊያኖች ዘንድ ነው;; ወንድሜ! ስላሳዘንከኝ አንድ ነገር ልምከርህ:-
አንተ/ወያኔ/ የተቸገራችሁት ሀሳባችሁን የምታሰራጩበት መድረክ / ሚዲያ በማጣት ሳይሆን ሀሳባችሁን የሚያዳምጥ ወገን ማግኘት ያለመቻላችሁ ነው ስለዚህ እንደ እርጎ ዝምብ በየቦታው እየገባችሁ ቫይረሳችሁን ለማሰራጨት ባትደክሙ መልካም ነው እላለሁ;; ቆማጣን ቆማጣ ነህ ካላሉት ገብቶ ከመፈትፈት ወደ ኍላ እንደማይል ሁሉ የአንተና የመሰሎችህም ሀሳብ የማይፈለግ መሆኑ ካልተነገራችሁ እየገባችሁ መሞጫጨራችሁ ስለማይቀር የተደረገብህ እቀባ ትክክለኛ ውሳኔ ነው እላለሁ: ሌሎች ጥቂት ግብረ አበሮችህ ማለትም እንደ ኢትዮ ላቭ ም አይቀርላቸውም::

በሁሉም ዘርፍ ድል ለኢ/ያ ህዝብ!!!

Meles Zenawi my hero.በመጀመሪያ ላመሰግንህ እወዳለሁ::በእውነቱ ነው የምልህ በዋርካ (ሳይበር ኢትዮጵያ) አስተዳዳሪዎች እርምጃ በጣም ነው የተናደድኩት::እንዴው ሲያስቡት የወያኔ ደጋፊ መሆኔ እያወቁ "ቅንጅትና" "ሕብረት" ልደግፍና በነሱ ምትክ ላቅራራላቸው ጠብቀው ይሆን?እንዴት ይሆናል?ወይም ከጅምሩ ዌብ ሳይቱ ለ"ቅንጅትና" "ሕብረት" ደጋፊዎች ብቻ የተከፈተ ነው ብለው ቢያሳወቁንና እኛም በነሱ ዌብ ሳይት ባልተሳተፍን:ከዛ ውጭ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች ብለው ካሉ ጥሩም ይሁን መጥፎ አመለካከት የማስተናገድ ግዴታ አለባቸው::

ወያኔን በተለያየ አመለካከት እንደሚነቅፉትና እንደሚሰድቡት እኔም የወያኔ ደጋፊ እንደመሆኔ መጠን ወያኔን ብደግፍና የተሰማኝን አመለካከት ባንጸባርቅ ምኑ ላይ ነው ሃጢያቱ?

ለማንኛውም ሳይበሮች ይህን ጉዳይ በጥልቀት ተገንዝበው አንድ መፍትሄ የሰጡኝ ዘንድ አሁንም በድጋሜ እጠይቃቸዋለሁ::ስለሆነም ድሮ ስጠቀምበት የነበረውን የተጠቃሚነት ስሜ ከእገዳ ነጻ እንደሚያደርጉልኝ ተስፋ አለኝ::

አመሰግናለሁ
ሜሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 252
Joined: Fri Feb 11, 2005 12:31 am

Postby 2005_00 » Mon Oct 24, 2005 4:55 pm

የሳይበር ኢትዮጽያ መልስ ምን ይሆን??
2005_00
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Fri May 20, 2005 12:13 am
Location: ethiopia

Postby ሜሎ » Mon Oct 24, 2005 5:15 pm

2005_00 wrote:የሳይበር ኢትዮጽያ መልስ ምን ይሆን??

ለ 2005_00 !

የሳይበር ኢትዮጵያ መልስማ "" ሀሳብህ አብዛኛውን የዋርካ ፎረም ተሳታፊ የሚያበሳጭና ስነስርአት የጎደለበት በመሆኑ የተወሰደብህ ውሳኔ ትክክለኛ ነው"" የሚል ነው የሚሆነው:: ገባህ? :lol: :lol: :lol:

ድል ለኢ/ያ ሰፊ ህዝብ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ሜሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 252
Joined: Fri Feb 11, 2005 12:31 am

Postby ዞብል2 » Mon Oct 24, 2005 5:33 pm

ወዲ_አለክስ :P ደብዳቤ መጻፍ ያለብህ ለወያኔዎች ነው ታክቲካችን ተበላ ሌላ ዘዴ እንፍጠር በላቸው....እኛ ወያኔዎች ገና "እርጥብ ነን" 14አመት ሙሉ ዝም ብለን ስንጃጃል ነው የኖርነው....
እኛ ወያኔዎች "አዱ" ስንገባ "ዳዴ" ይሉ የነበሩ ህጻናት "ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት" ምን መሆኑን ተረድተው ከውጭም ከውስጥም እያዋከቡን ነው እንዲያውም የጫካና የዱር ስነልቡና እና ህግ ለሰው ልጅ አስተድዳደር የሚያስገኘው ለውጥ የለም እያሉ ነው ብለህ እቅጩን ንገራቸው :wink:

ወዲ_አለክስ :P "ጥሬው እስኪበስል የበሰለው አብሮ ማረር የለበትም" የሆንክ ማፈሪያ ወያኔ :oops:

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1987
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ዞብል2 » Mon Oct 24, 2005 5:40 pm

ዞብል2 wrote:ወዲ_አለክስ :P ደብዳቤ መጻፍ ያለብህ ለወያኔዎች ነው ታክቲካችን ተበላ ሌላ ዘዴ እንፍጠር በላቸው....እኛ ወያኔዎች ገና "እርጥብ ነን" 14አመት ሙሉ ዝም ብለን ስንጃጃል ነው የኖርነው....
እኛ ወያኔዎች "አዱ" ስንገባ "ዳዴ" ይሉ የነበሩ ህጻናት "ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት" ምን መሆኑን ተረድተው ከውጭም ከውስጥም እያዋከቡን ነው እንዲያውም የጫካና የዱር ስነልቡናና ህግ ለሰው ልጅ አስተድዳደር የሚያስገኘው ለውጥ የለም እያሉ ነው ብለህ እቅጩን ንገራቸው :wink:

ወዲ_አለክስ :P "ጥሬው እስኪበስል የበሰለው አብሮ ማረር የለበትም" የሆንክ ማፈሪያ ወያኔ :oops:

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1987
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ባየልኝ » Mon Oct 24, 2005 5:45 pm

አየህ አቶ ያሙ የሀሳብ መለያየትና መከራከር ያለ የነበረና የሚኖር መሆኑ ከድሮ ጀምሮ የሚያታወቅ ነገር ነው ::ይህም ማለት ተቃዋሚና ደጋፊ የሀገርን የፖለቲካ አቅጣጫ ;የኤኮኖሚ የድገት ፕላንን ወይም ሌሎችን ጉዳዮች በተመለከተ የሀሳብ መለያየት የሚያስፈልግ ጉዳይ ነው ይሁን እንጂ ለዚህ ክርክር መኖር ትንሹ መስፈሪያ እንዚህ ተከራካሪ ወገኖች ቢያንስ በሚከራከሩበት ጉዳይ ላይ ሁለቱም የሚያገባቸው ወይም የሚያከራክራቸው ጉዳይ ሁለቱንም የሚያሳስብ መሆን አለበት ::
እንግዲህ በሀገራችን ውስጥ ሥልጣንን በጠመንጃ
ነጥቆ ለዘመናት ተከብሮ የኖረውን የሀገር ድንበር በፈለገው መንገድ የፈረካከሰ ;የህዝቡን አንድነት በፈለገው መንገድ የበጠበጠ ከ14 ዓመት ጨካኝ አገዛዝ በኌላ ከ15 ሚሊየን ህዝብ በላይ በችጋር የሚያስገርፍ ;ሚሊየን ህዝብ በኤች አይቪና በቲቢ የሚያስጭርስ ;በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት በአረቡ ሀገር እንድዕቃ እንዲሸጡ ያደረገ መንግሥት ;የሀገራችንን ድንበር (ባድሜን) ለማስለቀቅ ከ 100 ሺህ በላይ ዜጎች የረገፉበትን የደም ምድር ለጌታው (ሻእቢያ ) ለመሥጠት ከተስማማ በኌላ ማን ሄዳችሁ ተዋጉ አላችሁ ብሎ የጠየቀን መንግስት ; በኤርትራ ለኢትዮጵያ የባህር በር መከበር ሲዋደቁ በምርኮኝነት በሻእቢያ ተይዘው የቀሩትን ኢትዮጵያውያን ባርያ ሆነው እስከ እድሜልካቸው እዲቀሩ ያደረጋቸውን መንግሥት; ዋናው ደግሞ ኤርትራን አስገንጥሎ እንኴን ደስ አላችሁ ለማለት የመጀመሪያው የሆነውን መንግሥት ;አሁን ደግሞ ለምን በደጃችሁ ቆማችሁ ብሎ በጠራራ ጸሀይ ብህእገራችን ህዝብ ንብረት በተገዛ መሳሪያ ጭፍጭፎ የእሬሣ ነዶ የከመረን መንግሥት ደጋፊ ነኝ ስለሆነም የኢትዮጵያውያንን አንጀት እንዳላሳርር መድረክ ተከለከልኩ ብለህ ስትጽፍ እንዲታዘንልህ አስበህ ኖሯል ???ይህንን መንግሥት የምትደግፍ ከሆነ ለምን እንደአለቃህ ሄደህ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ህዝቡን አጸድብም ማንም አይከለክልህም እንዲያውም ሹመት ቢጤም አታጣም ::
ባየልኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 136
Joined: Fri Dec 19, 2003 2:23 pm

Postby ወንዴ_85 » Mon Oct 24, 2005 9:16 pm

ቀደም ሲልም ሌሎች የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ሳይበሮች ያዳላሉ ብለው ኮምፕሌይን አርገው ነበር:: ነገሩ እውነት ከሆነ ይደብራል:;
ወንዴ_85
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 360
Joined: Sat Dec 25, 2004 2:20 am
Location: DownTown

Postby ETLOVE » Tue Oct 25, 2005 1:47 am

እነ አቶ ቅንጅቶች

እንግዲህ ንገረኝ ካላችሁ ልንገራችሁ
ኢህአዴግ ማለት የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ወጣት አዳኝ ነው::
ኢሕአዴግ የመላው ኢትዮጵያውያን ብሂር ብሂረሰቦች አለኝታ ነው::
ኢህአዴግ የሴቶች የገበረዎች አለኝታ ነው::
መላው ብሂር ብሂረሰቦች በኢትዮጵያነት ስም ለዘመናት ተንቀው ተንቃሸው ኖረዋል ያ ዘመን ለመላው ኢትዮጵያውያን ብሂር ብሂረሰቦች የጨለማው ዘመን ነው: በፍጹም በምንም ምክንያት በኢትዮጵያዊነት ስም ላይመለስ ተመትቶዋል::

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በፍላጎት(በፈቃደኝነት) ላይ ተመስርተው አብረው ሊኖሩባት የምትችል ሀገር እንድትሆን ኢህአዴግና የኢህአዴግ ፖሊሲ ዋናው መንገድ ነው::

ቅንጅቶች ወደዳችሁም ጠላችሁ ኢህአዴግ ቀጣዩን 5 ሀመት ይመራል::

መቸም ቢሆን የዘመናት የኢትዮጵያ ብሂር ብሂረሰቦች ጠላቶች በምንም ምክንያት ኢትዮጵያን ሊያስተዳድሩም ሆነ ሊመሩ አይችሉም::

ዋርካችሁ ምን እንደሆነ ከናንተ በበለጠ እናውቃለንና መጨፈር መብታችሁ ከሱ ለላ የምትፈይዱት ስለ ሌለ ከፈለጋችሁ ቦታውን እንለቅላችዋለን::

የዌብሳይት ጀግኖች መሆናችሁ ሁሉም ያውቃልና
ለኛ አትንገሩን::

ለሰላም ለልማትና ደሞክራሲ ኢህአዴግ :!:
AFRICAN COMMUNICATION PROBLEM
PLEASE LET US LISTEN EACHOTHER.
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests