በቅሎ ገመዷን በጠሰች ; በራሷ አሳጠረች

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በቅሎ ገመዷን በጠሰች ; በራሷ አሳጠረች

Postby ጥልቁ1 » Wed Oct 26, 2005 7:30 pm

የኢዴአፓ-መድህን ወደ ኢዴፓነት እየሄደ ይመስላል።

ሰላም አንባቢያን፡
ሰሞኑን የምንሰማው የቅንጅት የውስጥ ለውስጥ ሽውክቻ ፣ ሌላ ምንም ሳይሆን የቀድሞው ኢዴፓ የአሁኑ ኢዴአፓ-መድህን የፈጠረው ነው። ከጥቂት አመታት በፊት ፣ ኢዴፓ እና መኢአድን አንድ ለማድረግ ሲደረግ የነበረው ከፍተኛ ጥረት ከከሸፈባቸው ጥቂት ምክንያቶች አንደኛው ፣ የስልጣን ክፍፍል ነበር። የትኛውን ስልጣን ብሎ የሚጠይቅ ቢኖር ፣ መልሱ ‘ገና የሚገኘው ስልጣን’ ለማለት ይቻላል። እነሆ ዛሬም ፣ ኢትዮጵያ እጅግ በሚያሳዝን ታሪካዊ ሂደት ላይ ተቀምጣ እና ፣ ህዝቦቿም በአንድነት ዙሪያ ከብበው ፣ የታሪካዊ ጠላታቸው አንግሎ-ጣሊያን ፍልፍል የሆነውን ወያኔን አሽቀንጥረው ለመጣል በሚታገሉበት ፣ በዚህ ወሳኝ ሰአት ፣ ሌላ የውዥንብር ወሬ ይናፈሳል። ይሄውም የቅንጅቱን የአንድነት ውል የሚያጓትት ጥያቄ ፣ በአቶ ልደቱ አያሌው የሚመራው የኢዴፓ-መድህን ቡድን ማስቀመጡ ነው።
በኢዴፓ-መድህን ስለውህደቱ የቀረበው ቅድመ መስፈርት ምንም የማይወጣለት ትክክለኛ ጥያቄ ነው። ይሄው መስፈርትም ፣ “ውህደቱ መፈጸም ያለበት ከላይ በአለን ባለስልጣኖች መካከል ብቻ ሳይሆን ፣ ከወረዳ እና ቀበሌ ጀምሮ ፣ በውጭ አገር ያሉ ደጋፊዎችንም የጨመረ መሆን አለበት” ይላል። ኢዴፓ-መድህን እራሱን ለትችት የሚያቀርበው ግን ፣ ይህ ሁኔታ ካልተስተካከለ ፣ የቅንጅቱን የአንድ ፓርቲነት አለመቀበሉ ላይ ነው። አማራጭ ሃሳብ ብሎም ያቀረበው ፣ “ምንም እንኳ የወያኔው ምርጫ ቦርድ ፣ የፓርቲነት ይዘታችንን እንድናጸድቅ እያሯሯጠን ቢሆንም ፣ እኛ ይህንን ህገ-ወጥ ምርጫ ቦርድ ሰርቴፊኬታችንን አጽድቅልን ማለታችን ፣ ለእራሱ ህጋዊ እውቅና መስጠት ስለሚሆን ፣ ከምርጫው በፊት የነበረንን የውህደት ሰርቴፊኬት አሳድሰን እንቆይ” ይላል።
ቁምነገሩ ያለው ግን ፣ ኢዴፓ-መድህን የሚያቀርባቸው ፣ ምክንያታዊ ጥያቄዎች ላይ ሳይሆን ፣ ‘ጊዜው ለእንዲህ ያለ ቅንጦት ይፈቅዳል’ ወይ የሚለው ነው። በተጨማሪም ፣ እውነት የዚህ ፓርቲ መሪዎችስ የቅንጅቱ አንድ ወጥ ፓርቲነት ያጓጓቸው ይሆን የሚለው እና ስለኢትዮጵያ ህዝብ የስነ-ልቦና ይዘት ያሳስባቸዋል ወይ? የሚለው ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ ፣ ልብ ልንል የሚገባው ፣ ይህ ወቅት የሁሉም ሰው አቅጣጫ መሆን ያለበት ያችን አገር ከገባችበት የፖለቲካ ውጥንቅጥ ማውጣት ነበር። የዚያች አገር ችግር ደሞ ፣ የመፍትሄ ሃሳቦች እና ቅምር-የድል-ሂሳቦች ተጠቃልለው ያሉት በቅንጅቱ ውስጥ ብቻ ነው ማለት ይቻላል። ለዚህም ፣ በቅንጅቱ መሪነት ከኢድ አል አደሃ ፈጥር በኋላ ፣ ህዝቡ የትግል ሂደቱን ሊያከናውን እየተዘጋጀ ይገኛል። ታዲያ በእነደዚህ ያለ ወሳኝ ሰአት ፣ የኢዴፓ-መድህን አዲስ ውዥንብር ፣ ትግሉን ከማዳከም የተለየ ምን አይነት አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል?!

ውህደትን ፣ ያለው የወያኔ ምርጫ ቦርድ እንዲያጸድቅ ማድረግ ፣ ለቦርዱ ህጋዊ እውቅና መስጠት ስለሆነ ፣ ያለንን እናሳድስ የሚለውም ፣ ‘ምታኝ ግን አታሳምመኝ’ አይነት ምክንያት ነው። ውህደቱን የሚያድሰውም ሆነ ውህደቱን የሚያጸድቀው አንድ ነው። ምርጫ ቦርዱም የወያኔ ስራ አስፈጻሚ መሆኑ የሚታወቀው ከምርጫው በኋላ ሳይሆን ፣ በፊት ነው። ውህደቱ በሁሉም አካባቢ ይፈጸም የሚለውም ፣ በዋናነት ፣ ከላይ በአመራር ቦታ ላይ ያሉት በመሰረተ ሃሳቡ ላይ ከተስማሙ እና ውህደቱን ከፈጸሙ በኋላ ፣ ወደታች እና ወደ ጎን ያሉ ስራዎችን ለመፈጸም ምን ያህል ይከብዳል?!

ለማጠቃለልም ፣ በዚህ ሰአት ፣ ኢዴፓ-መድህንም ሆነ ማንም የቅንጅቱ አባል ፓርቲ አፈትልኮ ቢወጣ ፣ ማንም ሳይሆን የሚጎዳው ፣ ያው ያፈነገጠው ፓርቲ ነው። ዛሬ ቅንጅቱ ያለው ስም ትልቅ ነው ፣ የኢትዮጵያ ህዝብም ቅንጅቱ ያቀፋቸውን ፓርቲዎች መጥራት ከአቆመ ሰነባብቷል። በዚህ ወቅት ፣ ማንም እራሱን እንደ የተለየ ዴሞክራት አድርጌ ልውጣ ቢል ፣ ከሚሸምተው ታላቅ የፖለቲካ ጥቅም ይልቅ የሚከፍለው የታሪክ እዳ ይበዛበታል። ብዙ እስራት እና እንግልት የደረሰባቸው የኢዴፓ-መድህን ባለስልጣን አቶ ልደቱ አያሌው ፣ ሰሞኑን ከሰማቸው ግርጌ እየተንጸባረቁ ያሉት የመጥፎ ስሞች መአት ፣ ሌላ ምንም ሳይሆን የኢትይጵያን ህዝብ የትግል አቅጣጫ የሚያመላክቱ ናቸው። ይህ ወቅት ፣ አንድ ግለሰብ ህዝብን የሚያስከትልበት አይደለም። የልቁንስ የህዝቡን የአንድነት መንፈስ ሳይበርዙ ፣ በትግሉ ላይ ማተኮሩ ከራስ ስልጣን የበለጠ ይጠቅማል። የቅንጅቱ ካውንስልም ፣ ለእንደዚህ ያለው ጉዳይ የሚሰጠው ማንኛውም አይነት የተጓተተ ውሳኔ ፣ በህዝቡ ላይ የስነ-ልቦና ተጽኖ ስለሚያሳድር ፣ ኢዴፓ-መድህን የሚያነሳው ጥያቄ እስኪመለስ ድረስ ፣ በአሉት ሶስት ፓርቲዎቹ ፣ ውህደቱን ፈጽሞ ቢንቀሳቀስ ለትግሉ ይጠቅማል። ተጨማሪ ፓርቲዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ ቦታው ሁሌም ክፍት እስከሆነ ፣ ኢዴፓ-መድህንም በማናቸውም ሰአት በውህደቱ ይካተታል።

ቸር ያሰማን
"በቅሎ ገመዷን በጠሰች ; በራሷ አሳጠረች"
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

ሪፖርተርስ በማፈራረሱ ላይ እስክስታ እየወረደም አይደል???

Postby moa » Wed Oct 26, 2005 10:17 pm

በእውነቱ በትላንትናው ማታ ምሽት "ቴሌፎን ኮንፍረንስ" ላይ አቶ ልደቱ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ አድምጬአለሁ። ከዚያም ብዙ ኢትዮጵያውያኖች በሚሳተፉበት ፓል ቶክ ላይ በዚሁ ጉዳይ ላይ ሠፊ ውይይት ተካሂዶበታል ያንንም አድምጬአለሁ እንቅልፌን እስከማጣ ድረስ።

ለኔ እንዳድማጭ መቸም የፖለቲካውን ወጀብ አቅጣጫ ለማወቅ እንደማንኛውም በውጭ ሃገር እንደሚኖር ሰው ብቸገርም ማለትም በሀገር ቤት ያለውን ትኩስ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጌጅ ወዲያውኑ ተመልክቼ መተርጎም ቢያቅተኝም በትላንቱ ምሽት ብዙ ካዘኑት ዜጎች ውስጥ አንዱ ነኝ።

አቶ ልደቱ ስጋታቸውን ከወያኔ ባህርይ አንጻር አንድ ሁለት ብለው ሲያስቀምጡና ቅንጅቱ እንደፓርቲ ባለፈው ከወያኔ ጋር ሲደራደር ያሳያቸውን ስህተቶች በጥሩ ሁኔታ ሲያስቀምጡ፤ የምስረታ ሠርተፊኬትን በማስረከብና ባለማስረከብ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ እንዲሁ ሲያጣቅሱ እንደኔ በሀገር ቤት በቅርብ ለሌለ ሰው እጅግ አሳማኝ ነበር።

በሌላ በኩል ደግሞ የህጋዊ ሰውነትን ሠርተፊኬት የሰጠው ምርጫ ቦርድ እስከሆነ ድረስ ያንንም ኢዴፓ መድህን ምሥክር ወረቀቱን ሲቀበል የምርጫ ቦርድን ቦርድነት አውቆ እነደሆነ እየታወቀ አሁን ምርጫ ቦርድን እውቅና መስጠት የለብንም ብለው አቶ ልደቱ መከራከርያ ነጥብ ማቅረባቸው ጨርሶ ሊገባኝ አልቻለም።
ወደምርጫስ ሲገባ ምርጫ ቦርድን አውቆ አይደለም? ይህን ለምን እነ አቶ ኤልያስ ክፍሌ በዚያን ወቅት አቶ ልደቱን ሊጠይቋዋቸው እንዳልቻሉ አልገባኝም፡

አቶ ልደቱ ትላንት ተሳስተዋል ብዬ እዚህ ላይ የምጠቁመው ነገር ቢኖር ቅንጅቱ ውስጥ ያለውን የሃሳብ መንሸራሸር " በጡረተኞችና በወጣቶች የሚለው አባባል አሳዝኖኛል።ወደ ትግሉ ሲገቡም ሆነ ሲዋሃዱ ከብዙ አዛውንቶች ጋር በመሆኑ ዛሬ የሃሳብ ልዩነት ሲመጣ ያን ዘለፋ ማካሄዳቸው ተገቢ አልመሰለኝም።

ዛሬ "ቅንጅቱ ላይ" የወያኔዎች ርብርቦሽ ፍላጻ በበዛበት ጊዜ እጠቅሳለሁ ! ደቂ አሉላ ላይ የተለጠፈውን የሪፖርተር ርዕሰ አንቀጽ እባካችሁ ሄዳችሁ ጎብኙት አማረ አረጋዊ የጥቂቶች አናሳ አገዛዝ በቅንጅት እንደሚገረሰስ በመረዳቱ ምንያህል በቅንጅቱ ላይና በተለይ ደግሞ በዳያስፖራው ኢትዮጵያዊ ላይ እንደዘመተበት መረዳት ይቻላል።

ቅንጅቱ መንግስትን ለመገርሰስ በሰሜን አሜርካ 75 ሺህ ዶላር አዋጡ እያለ ያስገድዳል በማለት የተልከሰከሰ ዜናውን አይቶ መፍረድ ይቻላል።ድመት ብትመለኩስ እንደሚባለው በነስዬ ክፍፍል ጊዜ ድጋፉን ለነስዬ አድርጎ የሰነባበተው ሪፖርተር አሁን የትግራይ አገዛዝ ከስሩ ለመገርሰስ በደረሰበት ጊዜ በቀጥታ "ወይን ጋዜጣ " በመሆን ለመለስ የሚያበረክተውን ዜና ማንበብ ይቻላል። የሚሚ ስብሃትን "ኢፍቲን ጨምሮ"

ታድያ በዚህ መሃል እነ አቶ ልደቱ ለጠላት በርን ከፍቶ ከመስጠት "ሽማግሌ መርጦ አዛውንቶቹም አጥፍተው ከሆነ ተወቅሰው፤ እነ አቶ ልደቱም በወጣትነት እይታ ተቻኩለው ስህተት እንዳይወድቁ ታርመው መፍትሄ ባስቸኳይ ቢፈለግ ጭራቸውን የሚቆሉ የወያኔ የከሰአት አጋንንቶችን አሳፍሮ መመለስ ይቻላል ብዬ አስባለሁ።እባካችሁ ወገኖች በዚህ ላይ ተወያይተን ነጻ አውጪ ታዳጊዎቻችንን ከስህተት እንመልሳቸው።

ነጋቲ ቡላ!!!
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

Postby ጥልቁ1 » Wed Oct 26, 2005 11:31 pm

ሰላም Moa እንደተጋባባን አምናለሁ:
የአቶ ልደቱን ቃለ-ምልልስም አዳምጫለሁ:: ነገር ግን ; ጠያቂዎች በጥያቄው ዙሪያ ያላቸው ተሳትፎ ውስንነት የነበረው ስለነበረ እና ; እንዳይጠይቁም ሆን ብሎ የሚያፍናቸው የራሳቸው ጉዳይ ተጨመሮ ; ምንም አይነት የሀሳብ ግጭቶች ሳይደረጉ ; እንደ መግለጫ አይነት ቃለ ምልልስ ነበር::

ከምንም በላይ የዘገነነኝ የአቶ ልደቱ ገለጻ ; ትክክለኛ ፍርድ ቤት በሌለበት አገር ; ወያኔ በፍርድ ቤቱ አማካኝነት ድርጅታችንን ያፈርሳል ; መሪዎቻችንም ያስራል የሚለው ነው:: ቅንጅት አሁን በአለበት ሁኔታ ግን ; ልክ ምናባዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርገው በማቅረብ ; ወያኔ አያፈርሰውም ማለታቸውም ሌላው የገረመኝ ነው:: በመጀመሪያ ደረጃ ; አቶ ልደቱም እንደ እነ ዶ/ር መረራ ; የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚኖሩት በወያኔ ፈቃድ አድርገው ማቅረባቸው ; እጅግ አሳዛኝ ነገር ነው:: ሁለተኛም ; ቅንጅት ማለት በህዝቦች ይሁንታ ላይ ያልተመሰረተ እና በመሪዎች እስትንፋስ የሚኖር አድርገው ገምተውታል ማለት ነው:: በተጨማሪም ; አቶ ሀይሉ ሻወልን ለእርሰዎ ጤንነት እኔ አስባለሁ የማለትም ያህል ነው::

በወያኔው ምርጫ ቦርድ የሚጸድቀው ህጋዊነታቸው ; ለቦርዱ ህጋዊ እውቅና ከመስጠት ጋር ምንም አይገናኝም:: ለምን ቢባል ; 299 መቀመጭዎች ይጣሩ ሲባል ; ሌሎችን የምርጫ ቦርዱን ውሳኔዎች ተቀብለው እንደሆነ ሁሉ ; በውህደታቸው እነሱ እስካመኑ ድረስ ; የምርጫ ቦርዱ ማጽደቅ ; ወያኔ ሊፈጽም ላሰበው የደደብ ክስ ምንም ህጋዊ ሽፋን ሊሰጥ አይችልም:: ቅንጅቱኮ ; ይሄ ምርጫ ቦርድ እንደገና ይዋቀር ሲል ; አሰራሩ ይለወጥ ማለት እንጅ ; የፓርቲዎችን እውቅና መስጠት ስልጣን ቦርዱ ይነፈግ ማለት አይደለም::

ብቻ ግን ; የአቶ ልደቱን ገለጻ ; አምኖ ለሚቀበለው የሚጣፍጥ ሲሆን የጥፋት መንፈሱን ለተረዳ ግን አሳሳቢ ነው::

ቸር እንቆይ!!!
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 3 guests