ከቅንጅት ም/ፕት አቶ ልደቱ አያሌው ጋር የተደረግ ቃለ ምልልስ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ከቅንጅት ም/ፕት አቶ ልደቱ አያሌው ጋር የተደረግ ቃለ ምልልስ

Postby መታፈሪያ » Wed Oct 26, 2005 10:40 pm

Image

EMF (October 26, 2005) – "ፖለቲካችን ውዥንብርና አሉባልታ የበዛበት ስለሆነ ጋዜጣዊ መግለጫ ላለመስጠት ወስኜ ነበር። አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግን ለህዝቡ ተገቢ መግለጫ መስጠቱ ጠቃሚ ነው።" አቶ ልደቱ

ዳዊት- አቶ ልደቱ ረዘም ላለ ጊዜ ምንም አይነት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደማይሰጡ ገልፀው ነበር። ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነው በመገኘትዎ እጅግ በጣም እናመሰግናለን። በዚሁ ወደ መጀመሪያው ጥያቄ ላምራ። እስካሁን ጋዜጣዊ መግለጫ አለመስጠት ለምን አስፈለገ? አሁንስ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ወቅቱ ነው ብለው ያምናሉ ወይ?


Lidetu Ayalew


አቶ ልደቱ አያሌው- እኔም ስለተሰጠኝ እድል በጣም ነው የማመሰግነው። እንዳልከው ጋዜጣዊ መግለጫ ላለመስጠት ወስኜ ነበር። ምክንያቱም ፖለቲካችን ውዥንብርና አሉባልታ የበዛበት ስለሆነ፤ በዚህ ላይ አላስፈላጊ እሰጥ አገባ ውስጥ መግባቱ ያለውን ችግር እያሰፋ፤ ምናልባትም ህዝቡ ከሚፈልገው አቅጣጫ ላለመውጣት ጉዳዮቹ በኔ ቢቀሩ ይሻላል በሚል፤ መግለጫ ላለመስጠት ወስኜ ነው የቆየሁት። ነገር ግን የአሉባልታው መጠንና ይዘት እየሰፋ በመሄዱ፤ ዝርዝር ወደሆኑ ጉዳዮች ውስጥ የመግባት ፍላጎት ባይኖረኝም፤ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግን ለህዝቡ ተገቢ መግለጫ መስጠቱ ጠቃሚ ነው በሚል ነው ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት የጀመርኩት። እና አሁንም ቢሆን ህዝቡ እንዲያውቀው የምፈልገው የኔን ዝም ማለት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመቁጠር አሉባልታውን ስለቀጠሉበት፤ በዚህ ምክንያት ነው ለመስጠት የተገደድኩት፤ አሁንም የምሰጠው። ይህንን መግለጫ የምሰጠው በፓርቲው ውስጥ ባለኝ ሃላፊነት ሳይሆን በግሌ ይሆናል። በተቻለ መጠን ወደ ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ መቀጠል እንችላለን።

ዳዊት- ከዚሁ በማያያዝ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ላይ በወጡ ጋዜጦች ላይ ስምዎን የሚያጎድፉ ነገሮች መውጣታቸውን ለማወቅ ችለናል። ከዚያ በፊትም ቢሆን ልዩ ልዩ ወሬዎች ወጥተዋል። እስካሁን ድረስ በሰዎች ዘንድ የሚወራው ግን “ልደቱ ከኢህአዴግ ሰዎች ጋር ግንኙነት አለው” የሚለው በሰፊው ሲሰማ ቆይቷል። ይህን አስመልክቶ ለተነሱት ወሬዎች ምን ምላሽ ይሰጡናል?

አቶ ልደቱ አያሌው- ነገሮችን ለሚከታተል ሰው… በኔ ላይ አሉባልታ መወራት የጀመረው ዛሬ አይደለም። ምናልባትም የፖለቲካ ትግሉ ውስጥ ከገባሁበት ከዛሬ 13 እና 14 አመታት ጀምሮ እስካሁን ድረስ፤ በተለይም ላለፉት 7 እና 8 አመታት አንዳንድ ጋዜጦች አስበውና አቅደው በኔ ላይ የተቀነባበረ ዘመቻ ሲያደርጉ ቆይተዋል። እና ባለፉት የትግል አመታት ያልተባልኩት ነገር የለኝም። ከተራ አሉባልታ ጀምሮ “ልደቱ የኢህ አዴግ ቅጥረኛ ነው” ተብያለሁ። ከዚህ በላይ ልባል የምችለው ነገር ስለሌለ ይሄ አያስጨንቀኝም። ነገር ግን የሚገርመኝ ነገር ሁልጊዜ በኔ ላይ አሉባልታ እየተወራ፤ አሉባልታው ውሸት መሆኑ እየተረጋገጠ፤ እንደገና ሌላ አሉባልታ ሲነገር ደግሞ ህዝቡ አዲስ እየሆነበት እና እየተደናገጠ ማየቴ በጣም ያሳዝነኛል። ምክንያቱም ፖለቲካውን አሁን የሚመራው የጋዜጣ ውዥንብርና አሉባልታ እየሆነ ነው። በዚህ ብዙ መስራት በምንችልበት ወሳኝ ወቅት ጊዜያችንን በአሉባልታ ማጥፋታችን በጣም ነው የሚያሳዝነኝ።

እንዲህ ያለው አሉባልታ ለትግሉ መጥፎ ቢሆንም፤ በግሌ እንደልደቱነቴ… ያገራችን ሰው ሲተርት “ጠላት አታሳጣኝ” ይላል። ጠላት ያጠናክርሃል፤ ውስጥህንም እንድትመረምር ያደርግሃል። ለቆምክለት አላማ በጽናት እንድትቆም ያደርግሃል። በኔም ላይ የሆነው ይሄ ነው። እኔ መጥፋት ካለብኝ በአሉባልታ ሳይሆን፤ በራሴ ስራና ተግባር ነው የምጠፋው። ከዚያ ውጪ የኢትዮጵያ በአምባገነኖች አገዛዝ እየማቀቀ ነው ያለው። ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ አሉባልታን አይደለም የሚፈልገው። የሚያሳዝነው በተቃዋሚ ጎራ ውስጥ ያሉ ሰዎች በዋናነት አሉባልታ በማሰራጨት እኔን ለማጥፋት መሞከራቸው ነው የሚያሳዝነኝ።

ከስብሃት ነጋ፣ ከአላሙዲን ጋር ተገናኘ የሚለው ነገር ተራ ፈጠራ ነው። ለኢትዮጵያ ህዝብ አስባብያለሁ።የሚያሳዝን ነው። ግን በጣም የማዝነው እንዲህ ብለው የሚያወሩ ሰዎች ለምን አላማ እንደምታገል ይረዳሉ። …የምንታገለው እኮ ሰዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው በጠላትነት መተያየት አቁመው በጋራ የሃገራችንን ጉዳይ ጤናማ በሆነ መልኩ የመነጋገር ባህል እንዲያዳብሩ ነው። እንደዚያ አይነት ባህል ለማምጣት ነው ኢትዮጵያ ውስጥ የምንታገለው። ነገር ግን ይሄ የተባለው ሁሉ ያልሆነ ነው።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት “ልደቱ ፓርላማ ሊገባ ነው። ካልገባን ብሎ ቅንጅቱን ለማሳመን ጥረት እያደረገ ነው” ተብሎ ትልቅ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ተከፍቶብኝ ነበር። ፓርላማ ተከፍቶ በቴሌቪዥን ሲተላለፍ፤ እውነት መስሎት ህዝቡ ከቴሌቪዥን ስክሪን ውስጥ እኔን ነበር የሚፈልገው። ያ ግን ሃሰት መሆኑ ሳይውል ሳያድር ተረጋገጠ። ያ አሉባልታ ሳያበቃ ነው ደግሞ አሁን አዲስ አሉባልታ የተጀመረው። ለቅንጅቱ እዚህ መድረስ ከማንኛውም ሰው ባልተናነሰ ሰርተናል። ሆኖም በጣም አዝናለሁ። ባዝንም እንደ አንድ በትግሉ ሂደት ልናልፈው የሚገባ ችግር አድርጌ ነው የማየው። ይህን ካላለፍን የትም መድረስ እንደማይቻልና በትግሉ ውስጥ የግድ ተፈትነን ልናልፍ እንደሚገባ ሂደት አድርጌ ነው የማየው።

ኤልያስ - በኢዴአፓ መድህን በኩል ቅንጅት ውስጥ ጥያቄ እየቀረቡ ናቸው። ይህ ደግሞ የሃሳብ አለመስማማትን እየፈጠሩ ናቸው። አቶ ሙሼ ሰሙ እንዳስረዱን ከሆነ ይሄ በአንድ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ውስጥ ያለ እና ሊለመድ የሚገባው ነገር ነው። እና ቅንጅት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ስለሆነ እንዲህ ያለ ነገር መጠበቅ አለብን የሚል ነው። እኔ መጠየቅ የምፈልገው ይህ የሃሳብ አለመግባባት ወደ መፍትሄ እየደረሰ ነው ወይ?

አቶ ልደቱ አያሌው- በቅድሚያ መታወቅ ያለበት ተፈጠረ የተባለው ችግር ማህተም የማድረግና ያለማድረግ አይደለም። ችግራችንን ለመፍታት በውይይት ላይ ነው የምንገኘው። ሂደቱ ገና አላለቀም። ሂደቱ ባላለቀበት ሁኔታ ዝርዝሩን ለህዝብ ማውጣት አስፈላጊ ነው ብለን አናምንም። ነገር ግን ይህ ሁኔታ በዴሞክራሲያዊ ውይይት እንዲፈታ የማይፈልጉ ሰዎች ቀደም ብለው ያደርጉ እንደነበረው ችግሩ ከልክ እንዳለፈና አቅጣጫውን እንደሳተ አድርገው በጋዜጣ ሆን ተብሎ እንዲወጣና ቅንጅቱ ችግር ውስጥ እንዲገባ እያደረጉ ነው። በዚህ በጣም ነው የምናዝነው። እኛ ይህንን ጉዳይ ቀድመን አላወጣንም። ሊጠፋ የሚፈለገው ግን የኛ ስም ነው። ሆኖም የተፈጠረውን ሁኔታ ጠቅለል ባለ መልኩ ህብረተሰቡ ቢያውቀው ተገቢ ይመስለናል።

1ኛ- ቀደም ብዬ እንዳልኩት ጉዳዩ ማህተም የማድረግና ያለማድረግ ሳይሆን፤ ከህልውናችን ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። ከህልውናችን አንጻር ስል፤ አንድም ከኢዴአፓ_መድህን አንጻር፤ ይህ እንደቀላል ችግር ሊታይ ይችላል። ሁለተኛ እና ዋነኛው ግን ከቅንጅቱ ህልውና አንጻር። እኛ በዚህ ዙሪያ አንድ አቋም እንድንይዝ ያስገደደን ከምንም ነገር በላይ የቅንጅቱ ህልውና ጉዳይ ነው። ይህንን ጉዳይ ከፓርቲ ወይም ከግለሰቦች የስልጣን ፍላጎት ጋር አያይዞ ማየት ትልቅ ስህተት ነው። ይሄ መታወቅ አለበት። ችግራችን ምንድነው? ኢህአዴግ በሚያዘጋጅልን ወጥመድ ውስጥ እየዘለልን የምንገባ መሆኑ ነው። ኢህአዴግ እንድናነብ የሚፈልገውን ነገር ነው የምናነበው። እራሳችን ከኢህአዴግ ቀድመን ትግሉን መምራት አልቻልንም። በጣም ፕሮአክቲቭ የሆነ እርምጃ ውስጥ ነው ያለነው። ስለዚህ አሁን የተፈጠረውም ነገር ማህተም የማድረግና ያለማድረግ ነገር ሳይሆን፤ ቅንጅቱን እንደ ቅንጅት በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ በሚቆጣጠረው ምርጫ ቦርድ ማስመዝገብ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? ነው ጥያቄው። እኛ “አይደለም” ብለን ነው የምናምነው።

…በፓርቲያችን ጠቅላላ ጉባዔ አድርገን የተሰጠው ውሳኔ “የውህደቱን መፈጸም እንፈልገዋለን፡ በአስቸኳይ። ነገር ግን ውህደቱ ተፈጠረ የሚባለው በወረቀት ላይ ብቻ ሳይሆን፤ ስምምነቱን ለመፍጠር በተስማማንበት መሰረት ከላይኛው መዋቅር እስከታች ድረስ ያለው መዋቅር፤ በእኩልነት ሙሉ ለሙሉ ተዋቅሮ ሲያልቅ ነው ‘ውህደቱ ተፈፀመ’ የሚባለው። ይህንን ባስቸኳይ ካደረጋችሁ በኋላ የውህደቱ ስራ ሙሉ ለሙሉ ከተጠናቀቀ በኋላ ህጋዊ ሰርተፊኬታችሁን መልሱ።” የሚል ውሳኔ ነው የሰጠው። …ስለዚህ በዚህ ደረጃ ላይ ሆነን፤ አሁን በስራ አስፈጻሚ ደረጃ እንኳን የተቀናጀ የስራ አመራር ድልድል ባላደረግንበት ሁኔታ አራቱ አባል ድርጅቶች “ሰርተፊኬታቸውን ለምርጫ ቦርድ ይመልሱ” ተገቢ አይደለም። ዋስትና አይኖርም፤ ለቅንጅቱም ህይወት ጤናማ አይሆንም። ይህንን እንደቀላል ነገር ልንቆጥረው እንችላለን። ምክንያቱም ከኢዴአፓ_መድህን ህልውና ጋር የተያያዘ ስለሆነ። ትልቁና መሰረታዊ ችግራችን ግን፤ “በአሁኑ ወቅት ቅንጅቱ ለምርጫ ቦርድ ማመልከቻ ማስገባት የለበትም” ብለን የምናምነው ለቅንጅቱ ካለን ፍቅርና ህልውና አንጻር ነው። ዛሬ “ቅንጅቱ ህጋዊ ህልውና የለውም፤ ለምርጫ ቦርድ ጥያቄውን አስገብቶ ህጋዊነት መጠየቅ አለበት” እያለ ግፊት የሚያደርገው ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ ነው። ይህን የሚያደርጉበት ሁለት ምክንያት አላቸው።

እኛ ባለን መረጃ መሰረት አንደኛው ምክንያታቸው፤ አራቱም ፓርቲዎች ህጋዊ ሰርተፊኬታችንን አስረክበን አዲስ ህጋዊ ሰርተፊኬት ብንጠይቅ፤ የሁላችንንም ሰርተፊኬት ከተቀበሉ በኋላ፤ አንድ ግልጽ የሆነ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ግምትና መረጃ አለን። የሚያቀርቡት ጥያቄ ምንድነው “ምርጫ ቦርድን እንደ አንድ ህጋዊ አካል አናውቀውም፤ ነፃ አይደለም’፤ ብላችሁ መግለጫ ሰጥታችኋል። ይሄ እናንተ የማታውቁት ምርጫ ቦርድ እናንተንም ሊያውቅ አይችልም። ስለዚህ መጀመሪያ በቅንጅቱ ስም አዲስ ሰርተፊኬት እንድንሰጣችሁ፤ የምርጫ ቦርድን ህጋዊነትና ነፃ መሆን መቀበል አለባችሁ” የሚል ቅድመ-ሁኔታ ህግ አስቀምጧል የሚል ስጋት አለን።

ይህን ቅድመ ሁኔታ ካስቀመጡ፤ ቅንጅቱ የምርጫ ቦርድን ነፃነትና ህጋዊነት አውቃለሁ ብሎ ከነሱ ሰርተፊኬት ተቀብለን መሄድ ትልቅ የፖለቲካ ክፍተት ፈጥረን እንቀጥል፤ ለህልውናችን ብለን ይህንን ሰርተፊኬት ተቀብለን እንቀጥል ብንል፤ “የአመጽ ቅስቀሳ እያደረጋሁ ነው። በአመፅ ኢህአዴግን እንጥላለን እያላችሁ ነው። ፕሬዘዳንታችሁ ከዚህ በኋላ ስራችን ኢህአዴግን ማስወገድ ነው ብለዋል። ስለዚህ ለህገ-መንግስቱ ተገዢነታችሁን እንድታረጋግጡና ለፓርላመንታዊ አሰራር ያላችሁን ኮሚትመንት ፓርላማ ውስጥ በመግባት መጀመሪያ እንድታረጋግጡልን እንፈልጋለን” ብለው ቅድመ ሁኔታ ሊያስቀምጡ ይችላሉ። ይሄ ከሆነ በቅንጅቱ ህልውና ላይ ትልቅ አደጋ ይፈጠራል።

ይህንን መመለስ የማንችለውን ጥያቄ መልሰንላቸው በሁለተኛ ደረጃ- ሰርተፊኬታችንን ብንረከብ እንኳን ሌላ ቀጥሎ የሚመጣ አደጋ አለ። ኢህአዴግ የድጅታችንን መሪ አቶ ኃይሉ ሻወልን ፍርድ ቤት ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገ ነው። ሰሞኑን በሚወጡ ሚዲያዎች መረጃ መሰረት አቶ ኃይሉ ሻወልና ቅንጅቱ ተከሰዋል። ሆንም ይህንን ክስ ለፍርድ ቤት ለማቅረብ ቴክኒካል ችግር ገጥሟቸዋል። ምክንያቱም አሁን ቅንጅቱ እንደቅንጅት የራሱ የሆነ ሰርተፊኬት የለውም። በስሩ ያሉት አራት ፓርቲዎች ደግሞ ህጋዊ ሰርተፊኬታቸውን ለምርጫ ቦርድ አልመለሱም። በዚህ ሁኔታ ክስ ቢመሰርትና በዚያ ክስ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጥትቶ አሁን ያለው ቅንጅት ቢታገድ ወይም እንዲጠፋ ቢደረግ ከላይ ያለው የቅንጅቱ አመራር ብቻ ነው የሚጠፋው። አራቱ ፓርቲዎች ገና ህጋዊ ህልውናቸውን እንደያዙ ስለሆነ፤ እነሱን የማፍረስ ህጋዊ መሰረት ያገኛል።

በአሁኑ ሰአት ደግሞ በአራቱም ፓርቲዎች ላይ በአንድ ጊዜ ክስ ከሚመሰርትባቸው፤ ያላቸውን ሰርተፊኬት መልሰው አንድ ሆነው ብቻቸውን ሲቀሩ፤ በቅንጅቱ ላይ ክስ መስርቶ ፓርቲው እንዲፈርስ ቢደረግ ቴቃዋሚ የሚባል ፓርቲ አይኖርም። መዋቅሩ ከላይ እስከታች ይፈርሳል። እንዲህ ያለ አደጋ ከፊታችን ላይ አለ። ኢህአዴግ የራሱን ወጥመድ ዘርግቶ ቅንጅቱ በዚህ መንገድ እንዲሄድ እያደረገ ነው።

በዚህ ላይ ተነጋግረን “ከዚህ ወጥመድ እንዴት ነው መውጣት የምንችለው?” ብለን መነጋገር ሲገባን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት የሚጠብቀውን የቅንጅት ፓርቲ አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ውሳኔ ነው እየተሰጠ ያለው።
ህዝቡ ለሰላማዊ ትግሉ ጥሪ እንድናደርግለት እየጠበቀን ነው ያለው። ያንን ህዝባዊ ጥሪ ከማድረጋችን በፊት ለምርጫ ቦርድ በእጃችን ያለውን ህጋዊ ሰርተፊኬት ከሰጠን ግን…l(ይቀጥላል)
መታፈሪያ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Thu Aug 28, 2003 11:53 pm
Location: ethiopia

Postby ወጥመድ » Thu Oct 27, 2005 8:39 am

አቶ ልደቱ ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር በተዘዋዋሪ በኩል ወያኔን በሀሳብ እየረዱት ነው:: ማለትም ወያኔ ቅንጅትን ለመጠየቅ ያልተዘጋጀበትን ነጥቦች ሁሉ እንዳይዘነጉት ቅስቀሳ የሚያደርጉ ይመስላልና ቢጠነቀቁ የሚሻል መስለኝ::


ወጥመድ
Last edited by ወጥመድ on Thu Oct 27, 2005 2:02 pm, edited 1 time in total.
ወጥመድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Fri Mar 11, 2005 1:52 pm
Location: Semen Walta

Postby ጥልቁ1 » Thu Oct 27, 2005 9:43 am

ወጥመድ ; በጥም ጥሩ ታዝበሀል:: ያም ብቻ ሳይሆን ; ወያኔ እንደ እግዚአብሄር እንዲታይ ነው እየሰበከ ያለው>>> www.zinqekin.com
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

ጥታቄ ለ አቶ ልደቱ

Postby በዙ » Thu Oct 27, 2005 12:25 pm

እኔም በውጥመድ ሃሳብ 110% እስማማለሁ ከዛ በሗላ ደግሞ ታልገባኝ ነገር ቢኖር ለልደቱ የደረሰው ያደጋ መረጃ ለምን ለሌሎቹ ሳይደርስ ቀረ?የሰርተፊኩ ጉዳይ ደግሞ አራቱ ድርጅቶች የተቀበሉት ከቦርዱ አይደለ እንዴ?ታድያ ቅንጅቱ ቢውስድ ምኑ ላይ ነው ልዩነቱ? ለማፍረስ ለማፍረስ አንደም ዩሁን አራት ለውጥያለው አይመስለኝም: ነገርግን ከደረጅቶቹ ውስት በመሪነት ደረጃ ለወያኔ ይሚያደላ ካለ ወያኔ ድርጅቶቹን ማፍረስ ሲጀምር አቛዋም በመቀየር ወደ ወያኔ ጉያ ለመድባት ካልታሰበ በስተቀር::

ፈቅሩን ይስጠን
በዙ
በዙ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Wed Feb 02, 2005 11:59 am
Location: united states

ተቃዋሚዎች ሀይላቸውን ዘነጉት!

Postby አፈ-ጉባኤ » Thu Oct 27, 2005 4:22 pm

እኔም ወጥመድ ባለው ፍጹም እስማማለሁ::

1. ቅንጅቱ ሀይላቸውን (ህዝቡንና ህብረታቸውን) ባጭር ጊዜ የዘነጉት ይመስላል::

2. ኳሷ በጠመንጃ አፈሙዝና በህዝብ መካከል ያለች መሆኗ ተዘንግቶ በኢህአዴግ እጅ ውስጥ ብቻ ያለች አስመሰሉት ይባስ ወደዚያ እየገቡ ናቸው:: የኢህአዴግን ስራ በተሻለ እየሰሩለት ነው::

3. ነገሮችን ለህዝብ ግልጽ ማድረጉ ባይከፋም በውይይት ላይ ያሉ ነጥቦችን ለባላንጣቸው እንዲዘጋጅበት ማሳሰቡ በጎ አይደለም:: በዚያ ላይ የቅንጅቱን ችግር ላገር አሳውቆ ትግሉን ማቀዝቀዝ አሳዛኝ ድርጊት ነው::

4. ይልቅ በሬ ወለደ ፍራቻቸውን መናቆራቸውን ትተው ተስማምተውና ተቻችለው ትግሉን ይምሩ:: ሰላማዊ አመጹን ያስተባብሩ:: አልረፈደም! ኢህአዴግ ቀንደኛ መሪዎቹን ቢያስር ረብሻ አልባ አመጹን ሊያስተባብሩ እሚችሉ ከታች ሌሎችን ያዘጋጁ:: ለራሳቸውም ለወከላቸውም ህዝብ ሳይሆኑ አጉል እንዳይቀሩ ይጠንቀቁ!
አፈ-ጉባኤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 302
Joined: Tue Mar 15, 2005 5:20 pm
Location: united states

Postby ሊቃውንት » Sat Oct 29, 2005 3:23 pm

ጎበዝ ልደቱ አያሌው ከአመራር አባልነቱ ታገደ መባሉ የትግል ሥልት ነው ቢባል ማን ሊያምን የሚችል አለ:;

በእኔ ግምት ይህንን የትግል ሥልት እውነት ብሎ ሊያምን የሚችል ወያኔ ብቻ ነው:;
The truth is out there.
ሊቃውንት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 10, 2004 9:21 am
Location: Far_east


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests