ኸረ ማንን እንመን ????

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ኸረ ማንን እንመን ????

Postby moa » Thu Oct 27, 2005 5:51 pm

ወያኔ፤ኢፍቲን፤ሪፖርተር፤ ባንድ በኩል ቅንጅትን ይፈታተኑታል፤ በዘገባዎቻቸውም ውስጥ እነ አቶ ልደቱን ማሞካሸቱን ተያይዘውታል፡ ታክቲክ፤ ወይስ ቅንጅቱን ለመከፋፈል?
እግዚአብሄር ይሰውረን ወዳጅ መስሎ ከሚወጋን ጠላት!!

የዛሬውን የትንሳኤ ራፖርታዤ እባካችሁ አድምጡት?
ማመን እስከሚያቅታችሁ ድረስ እራሳችሁን ትጠራጠሩታላችሁ። ውነት ከሆነ ወያኔ አሰርጎ ያገባቸው የኢፍትን፤ሪፖርተር፤ ቃላቀባዮች ተጋለጡ ማለት ነው።

ኢትዮጵያን ሪቪው በየዋህነት ካልሆነ በዚህ ሴራ እንዳልገባበት እርግጠኛ ነኝ። እኔም የዋህ ካልሆንኩ
እንበራታ !አንዳንዴም ፈተና ለጥራት ነውና!!
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

Re: ኸረ ማንን እንመን ????

Postby ላሊበላ4 » Thu Oct 27, 2005 7:15 pm

ሠላም ሞአ!

ያነሳኸይ ትክክል ነው ወንድም ዓለም::

አሁን የሚመስሉኝኝን የታዘብኳቸውን ነገሮች ልግለጽልህ:: ችግሩ ያለው በኢትዮጵያዊነት ላይ መናናቅ ነው:: ቀጥሎም እኔ ያልሁት ብቻ ሃሣቤ ይፈጸም ነው:: በመጨረሻም ሥልጣንን በብዛት መመኘት ዓይንንም ማስፋት ነው:: የሰውል ልጅ ተፈጥሮ ደግሞ በብዛት ያንን ይመስላል::

አቶ: ልደቱ አያሌው ያኔ የመዐሕድ የወጣቱ ቡድን መሪ በመነበረበት ጊዜ ወጣቱን እንደያዘው ነው ከዚያ ድርጅት የወጣው:: ቀጥሎም ቀኛማቹ ይናገሯቸው የነበሩት አመለካከታቸውን ቀሪው እድምተኛ አልተቀበላቸውም ነበር::

ቀጥሎም የኢደፓ ተመሰረተ ጥሩ አበጀህ የሚባል ከየትኛውም አቅጣጫ ተደረገ:: ከዚያ በሚያስደንቅ አኳኌን የኢደፓ ዋና ጸሐፊ የነበረቺዋን ወ/ት: ከሥራዋ ተባረረች:: አሳዛኝ ነበር::

ቀጥለውም የኢዲዩና የኢደፓ ጥምረት ሆነ ጥሩ:: ከዚያ በመቀጠል ዛሬ "እየተከሰሱ ያሉትን ለመሳብ ውህደት ውህደት በሚል ከወደ ኢደፓ በዛ በመጨረሻም እናጠናዋለን በሚል የወዲህኛዎቹ ተቆጥበው ሳሉ ኢደፓውና መድህኖቺን ያጠቃለለ ሌላ ውሕደቶች ተፈጠሩ::

በመጨረሻም ቀስተዳመናና የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ከሌላ አንድ ድርጅት ጋር ሆነው አጠቃላይ ውህደትን ለመስረት በሚሰሩበት ጊዜ ኢደፓዎች እንዋዋጥ ብለው:: በሊቀመንበራቸው ሳይሆን በዋና ጸሐፊያቸው መሪነት 18 ሰዎችን መርጠው ከዚያም 5 ቱን ለቅንጅቱ ወሳኝ አካል አድርገው መረጡ አቶ ልደቱ ወሳኝ ከሚባሉትንም አንዱ ሆኑ::

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳም ተቀዳሚ ሊቀመንበር ሆነች:: አዎ ይገባታል:: ምክንያቱም ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ሴት ልጅ ወክላ በከፍተኛ ለስልጣን በሚያበቃ ወንበር ላይ መቀመጧ ለቅንጅቱ የተለየ ክብር እንዲሰጠው ሆኗል::

ይህቺ ኢትዮጵያዊት ወ/ት: በመሠረቱ ዳኛ ነበረች አቶ ሰዬ አብርሐንም ሌሎቹንም በሚቀርቡላት ጊዜ ዋስ ጠርተው ወደ ቤትዎ ይሂዱ ያለች ፍጹም ደፋርና በራሷ ማለትም በተማረቺው ህጉ ምን እንደሚል ከነትርጉሙ ያወቀችና ሰባዊ መብትንም ጥሩ አድርጋ የተረዳች:: ከዚያም ቢያንስ የማስትሬት ድግሪ በህግ ሙያዋ ላይ የተቀበለች ናት:: ይህ ቺሎታዋ ህዝቡን በይበልጥ በዚህ አሸናፊ ፓርቲ ቅንጅት ላይ እምነት እንዲፈጥር አድርጎታል:: በውጪም በአገር ቤትም ጭምር::

አቶ: ልደቱ አያሌው ዋና ጸሐፊ ሆነው ፕሬዝዴንቱ የነበሩት የኢደፓ መሥራች ዶክተር አድማሱ ምክትል ሊቀመንበር አልነበሩም:: ዶክተሩ የቱን ያህል ላገራቸው ኢትዮጵያ ለመኖሩዋ ልባቸው የሚያስብ መሆኑን ብገነዘብም ሊቀመንበር እያለ ጸሐፊ ፓርቲውን ወክሎ ከሌሎች ጋራ ምክትል ሊቀመንበር ሆኖ ሊጓዝ ይገባስ ነበረ ወይ?

በዚያው ልክ በስብሰባዎች ህዝባዊ ጥሪዎች ወቅጽ? ለምን ህዝባዊ ሠልፉን የጠራው የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ሆኖ ሣለ የዚህ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ተደርገው በመተባበር እንዲሰሩ ስለተደረጉ:: የቀድሞዎቹን የወያኔ ባለሥልጣናትና ዶክተር ነጋሶ የወያኔውን ፕሬዝዳንት በስብሰባው ላይ መተው ንግግር እንዲያደርጉ አደረጉ::

ያንን ማድረጋቸውን አልቃወምም ህዝብን ለማቀራረብ ነው ይባላል:: በዚያ ላይ በህዝብ ዘንድ ጥሩ ፖፕላር የሚያሰኝ የማይረሳ ስም አገኙ:: እደግልን ያሰኛል:: ጥሩ ከዚያስ ሚሊዮን ኦፍ ማርሽ በአድዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ህዝብ ወጣ ያንን ኃይል እነማን መሩት? ከዚያስ ምርጫው ተካሔደ እነማን አሼነፉ?

በመጨረሻ ደሞ! ማንም ወጣት ሆኖ አይኖርም:: ሰው ስለሆንን እናረጃለን:: ታዲያ እርጅና እኮ ከጥሩ የስራ ልምምድና ተሞክሮ ጋራ አሁን ቅንጅቱን እየመሩት ያሉትን ሽማግሌዎቻቺንን አክብረን መከተል ሲገባ "በመቃብሬ ላይ ለሚነበብ ወረቀት" አይደለም የምሰራው:: መባሉ ይህ ነገር ምንን ያማላክታል? ራሱን የቻለ ዲክታተርዚም አያስመስልም ወይ::

በዚህ ቅንጅት ውስጥ ብዙ በዓለም ደረጃ ቢመረጡ ኑሮ ዓለማቺንን ያለምንም ቺግር ሊመሯት የሚቺሉ ምሁራን ተሰባስበው ባሉበት ሰዓት የልጆች ጨዋታን የመሰለ መጨዋወቱ ለነኛ ታላቅ ምሁራን አይዋጥላቸውም ነው የምለው::

ያዝናሉም ያዝኑብናልም ለዚያም ነው እርምት ይደረግ የምለው:: ኢትዮጵያን ለመጨረሻው የሚመራት እራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር:: አሁን አገሪቱ መንታ መንገድ ላይ ነቺ አቅጣጫዋን ወደ ጥሩነት እንቀይረው ነው:: በዚህ ጊዜ ሌላው ለማፍራረስ የሚሞክረው ሲታሰብ ሲገመት:: አንድ የቶር መሪ ወታደሮቹን ወደ ማለቂ አቅጣጫ አውቆ በመምራት ያሰጨረሳቸውና በኌላም ማርሻል ኮርት የቀረበን ኮሎኔል ወይም ጀነራልን ዓይነት አድርጎ እንድመለከተው አድርጎኛል::

በዚያ ምክንያት አቶ ልደቱ በተዓምር ለአገርዎ ለኢትዮጵያ ጭንቀቷን ተቀብሎና ሰምቶ ያመጣላትን ሽማግሌዎችና ወጣቶች እንዲሁም ሴቶች ልጆቿን አክብረው በማክበርም አብረዋቸው እንዲሰሩ እንጂ
የርሶን ልባዊና ውስጣዊ ኃሣብዎን ለማስፈጸም ብቻ እንደምትበር ቀበሮ አይሁኑ:: በጣም ወሳኝ ወቅት ውስጥ አገራቺን ስለመሆኗም ያወቁት አልመሰለኝም:: እነዚህን የሚተቿቸውን ሽማግሌዎችና ልምዳቸውን ከነቺሎታቸው ለማግኘት መሞከር አለብዎት እንጂ የነሱ ልብ መንፈሳቸው እንዲያዝንብዎት ስለማልፈልግ ይህቺን ግልጽ የሆነቺ ደብዳቤ ለመጻፍ ተነሳሳሁ::

ሽማግሌዎቹ ያስባሉ የኢትዮጵያንም ምንነትና ማንነትታኦንም በሚገባ ያውቃሉ ከሚያስጎመዥ ትምህርታዊና ተፈጥሯዊም ቺሎቶቻቸው ጋርም::
በበኩሌ ደስ እንዲለኝ ነገ አርብ ማንም ሣያሳስብዎት ወደ ጽህፈት ቤትዎ ሄደው የቅንህቱን ሥራ አስኪያጆችና ፕሬዝዴንቱን ጭምር ስብሰባ እንዲሰበሰቡልዎ ሊጠይቋቸው ይገባል ከዚያም ይቅርታ የወጣት አስተሳሰብ ሁሌም ችኮላ ነውና መስሎኝ ብዬ ነበር አሁን ግን የህዝቡም ግፊያ አላስቀምጥ አላስነሳ አለኝ:: ይኸው የተፈለገው ማህተምም በሚል ያድርጉ:: ከዚያ ሰኞ ሥራው አለቀ ማለት ነው:: ስለሚቀጥለው ህዝባዊ ተቃውሞ አብራቺሁ በአንድነትና ለአንድነትም በመቀናጀት መጓዝ ይገባቺኌል እላቺኈለሁ::

ከዚህ በተረፈ ግን ልደቱን ከሚያደንቁት ያገሩ ሰዎች አንዱ ነኝ:: በጣም በታም ለኢትዮጵያ ሲንገበገብላት ሳይ አገሬ ትኖራለች ማንም አያፈርሳትም እሱን የመሳሰሉ ወጣቶች ደርሰውላታልና ያም እውነት ነው:: በዓለም ላይ ካሉት ወጣቶቿ መሐከል ሁሉም የሚያስቡት አንድ አይነት ነው:: በጣም የተቆጩ አገራቸውን ምን እናርግላት ብለው የሚያስቡና የሚከራከሩላት ናቸው:: አበጃቺሁ ዱሮ ፖለቲካና ኮረንቲ ከማለት ተቆጥበው ዛሬ በየ ፓልቶኮቹ በየ ገጾቹና በመጻፍ በድምጽም በመከራከር በፔቴሺኑና በገንዘብ አሰባሰቡ ወጣቱ የሚያደርገው ትብብር በመሠረቱ ከልቤ ደስታ ብቻ ሣይሆን ልለቅሶም ይመጣብኛል:: ይህም ሲያስደስተኝ የወጣቱ ሠራዊት መሪ ደግሞ የመቃብር ወረቅት ሲያነሱ ስለ አሳዘነኝ ነው የወቀስኩት::

ዘወትር አክባሪያችሁ

ላሊበላ4[/b] [b]moa wrote:ወያኔ፤ኢፍቲን፤ሪፖርተር፤ ባንድ በኩል ቅንጅትን ይፈታተኑታል፤ በዘገባዎቻቸውም ውስጥ እነ አቶ ልደቱን ማሞካሸቱን ተያይዘውታል፡ ታክቲክ፤ ወይስ ቅንጅቱን ለመከፋፈል?
እግዚአብሄር ይሰውረን ወዳጅ መስሎ ከሚወጋን ጠላት!!

የዛሬውን የትንሳኤ ራፖርታዤ እባካችሁ አድምጡት?
ማመን እስከሚያቅታችሁ ድረስ እራሳችሁን ትጠራጠሩታላችሁ። ውነት ከሆነ ወያኔ አሰርጎ ያገባቸው የኢፍትን፤ሪፖርተር፤ ቃላቀባዮች ተጋለጡ ማለት ነው።

ኢትዮጵያን ሪቪው በየዋህነት ካልሆነ በዚህ ሴራ እንዳልገባበት እርግጠኛ ነኝ። እኔም የዋህ ካልሆንኩ
እንበራታ !አንዳንዴም ፈተና ለጥራት ነውና!!
ላሊበላ4
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 201
Joined: Fri Dec 24, 2004 8:47 pm
Location: united states

Postby ኪኮ » Fri Oct 28, 2005 12:18 am

ላሊበላ 4 እንደጳፈው/ችው

በበኩሌ ደስ እንዲለኝ ነገ አርብ ማንም ሣያሳስብዎት ወደ ጽህፈት ቤትዎ ሄደው የቅንህቱን ሥራ አስኪያጆችና ፕሬዝዴንቱን ጭምር ስብሰባ እንዲሰበሰቡልዎ ሊጠይቋቸው ይገባል ከዚያም ይቅርታ የወጣት አስተሳሰብ ሁሌም ችኮላ ነውና መስሎኝ ብዬ ነበር አሁን ግን የህዝቡም ግፊያ አላስቀምጥ አላስነሳ አለኝ :: ይኸው የተፈለገው ማህተምም በሚል ያድርጉ :: ከዚያ ሰኞ ሥራው አለቀ ማለት ነው ::


የዋህነት ወይስ ?................
ኪኮ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 62
Joined: Fri Aug 05, 2005 9:33 am
Location: ethiopia

የዋህነት አይደለም ማቀራረብ ነው::

Postby ላሊበላ4 » Fri Oct 28, 2005 1:11 am

ውድ ኪኮ!
ለማቀራረብ ነው:: ምክንያቱም ይህ ሁኔታ ቅንጅቱን ከጉዞው ያሰናክላል:: ይህን ተፈጥሯዊ ባህላቺንን ልንገታው ይገባል ነው__

ምንድነው አሁን ከረሞዳን ጾም በሁዋላ ወደ ከፍተኛ ጥያቄ በታሰበበት ወቅት አሁን በዚያ አካባቢ የሚደረገው ኮመዲ ምን ይመስላል ብለው ራስዎን እንዲጠይቁ አሳስብዎታለሁ::

የኃገራቺን ትግል መካሄድ ያለበት በህዝቡ ፍላጎትና ውሳኔ እንጂ በግለሰቦች ኩርፊያ ያለመሆኑንና ያንንም ለማስገንዘብ ነው:: የህዝቡን ፍላጎት እንዳይነጠቅ ለማለት ነው::

መምከሬ እንጂ የዋህ ወይም የሌላ ጥያቄ ውስጥ አያስገባኝም:: ሰው ያለውን ከሰጠ ንፉግ አይባልም ይባላል:: አዎ የወያኔ ደጋፉዎች ይደሰታሉ:: ያደስታቸው ግን ዘላቂነት የለውም አያገኝም::

አሁንም ሆነ ለወደፊት ህዝባቺን ለግለሰቦች ማንነት ተገዥ መሆን የለበትም ዱሮ ቀረ እሱ በፊውዳል ሥርዓት ጊዜ ጥቂቶች ብቻ ነበሩ ባጠቃላይ አሳቢዎቻቺን ህዝቡ እንደ ምንም እንደማያውቅ ተከትሏቸው ሲጓዝ 3000 ዓመት ኖረ እስከ ቅርብ ጊዜም በሰው በአንድ ሰው ያምን ነበር:: ያንንም ያየነው ነው:: አይደለም ህዝቡ በራሱ ነው ማመን ያለበት::

ስለዚህ ብሄራዊ ግዴታቸውን ሁሉም እየተወጡ ነው:: ያደረጉት ሁሉ ለአገራቸው ጥሩ አደረጉ ይባልላቸዋል ታሪክም ትውልድም ጥሩ ዝና የሰጣቸዋል እንጂ ከዚያ ታልፎ በኔ ይመለክብኝ ወይም ይህን ካልፈጸምኩ ብሎ የሚያኮርፍን ልጅ ኢትዮጵያ አትፈልግም:: በዚያ የተነሳ ሃሣቤን መናገሬ የዋህ ካስባለኝ ብልጥና ሰፊ አስተሳሰብ አለን የሚሉት ደግሞ ወተው በተቻለው ቢያስረዱን?

ቅንጅቱ ግቡን እንዲመታ ኢላማውንም እንዳይስት ከታች እስከ ላይ ከላይ እስከታች ድረስ አብሮ ለመሥራት ያለምንም ተለዋጭ ጥያቄ ሲጓዝ ብቻ ነው ህወኃት ወያኔንና ሻቢያን ሆዳሞችን ከኃዲዎችን ጭምር ማሸነፍ የሚችለው::

አክባሪዎ
ላሊበላ4


ኪኮ wrote:ላሊበላ 4 እንደጳፈው/ችው

በበኩሌ ደስ እንዲለኝ ነገ አርብ ማንም ሣያሳስብዎት ወደ ጽህፈት ቤትዎ ሄደው የቅንህቱን ሥራ አስኪያጆችና ፕሬዝዴንቱን ጭምር ስብሰባ እንዲሰበሰቡልዎ ሊጠይቋቸው ይገባል ከዚያም ይቅርታ የወጣት አስተሳሰብ ሁሌም ችኮላ ነውና መስሎኝ ብዬ ነበር አሁን ግን የህዝቡም ግፊያ አላስቀምጥ አላስነሳ አለኝ :: ይኸው የተፈለገው ማህተምም በሚል ያድርጉ :: ከዚያ ሰኞ ሥራው አለቀ ማለት ነው ::


የዋህነት ወይስ ?................
ላሊበላ4
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 201
Joined: Fri Dec 24, 2004 8:47 pm
Location: united states

ለ ላሊበላ 4

Postby ኪኮ » Fri Oct 28, 2005 4:34 am

አረ ጌታዬ ! ነገሩ ወዲህ ነው......የዋህነት ማለቴኮ እርስዎን ለመተረብ አይደለም.....የመርቆሬዎስ ያለህ!! እንደዛማ አስቤ አልነበረም. ...ምኑን ከምን አገናኙት ባዛኝቱ!....... የተወታተበውን የፖለቲካ ልቃቂት ውል ለማግኘት የሚዳክሩትን... ባንድ ወቅት በዚሁ መድረክ ሳይቀር ያለአቅማቸው ኢትዮጵያዊ ማንዴላ እየተባሉ ሲወደሱ የነበሩትን..የፖለቲካ ሰው.. አቶ ልደቱን ህጳን ልጅ አባብለው እንደሚልኩ አይነት ጎሽ እኔን ደስ እንዲለኝ አርብ በማለዳ ሂድና ይቅርታ ጠይቀህ ማህተሙንም አትም ከዛ ሰኞ ሁሉም ነገር ተረት ይሆናል...ማለትዎ ነውኮ የዋህ ኖት ያስባለኝ........ካጠፋሁ እንግዲህ እንደ ጥንቱ እንደአባቶቼ ልማድ ጥገት ላሜን ልካስ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ

ለነገሩ በዚህ በሸፍጥና በሀሰት በምቀኝነትና በተንኮል በተሞላ አለም ውስጥ የዋህ የሚባል ሰው መገኘቱ ደስ ያሰኛል እንጂ አያስከፋም....በተረፈ ብልጦቹ እስኪ ውጡና ተናገሩ ላሉት ሊቃውንቱ ካሉ ይናገሩ እንጂ እንደኔ አይነቱ ጨዋ መሀይም ከአዋቂዎች ጎራ ምን ይዶለኝና!...እመ አምላክን የውነቴን ነው......እንዲያው ሲፈጥረኝ ነገር አይገባኝም..አብሶ ይህ ቦለቲካውማ...እንዲያው ዝም ነው ጨርሶኮ አይገባኝም....አረግ... አረግ ...አረግ...ብዙ ብልሀት አልፈጠረብኝም.ልበል እናንተዬ!.. ደግሞስ ምን ሊረባኝ..ኤድያ አረ እንኳን ቀረብኝ.....'እጅግም ስለት ይቀዳል አፎት.......እጅግም ብልሀት ያደርሳል ከሞት' ይሉ ነበር እኒያ ደግ ጎረቤቴ ባሻ ቢራቱ.... ጨዋታ እንደሆ አያልቅባቸው መቼም እሳቸው ጋ ያለ እውቀት የትም የለ ብልህ ነበሩ የሰፈሩ ሁላ አድባር! አፈሩ ይቅለላቸውና ዛሬ በህይወት የሉም...........ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ አለማወቄን በዚሁ አራምባና ቆቦ በሚረግጠው የጨዋ (የመሀይም ማለቴ ነው) አነጋገሬ ተረድተው ይቅር እንዲሉኝ እለምንዎታለሁ..

ሊቀ መላኩ ይከተልዎ!
Last edited by ኪኮ on Fri Oct 28, 2005 5:57 am, edited 2 times in total.
ኪኮ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 62
Joined: Fri Aug 05, 2005 9:33 am
Location: ethiopia

Postby ETLOVE » Fri Oct 28, 2005 4:42 am

የሚታመን መች ጠፋ እኔስ ብሆን ቅር ይላችሁ ይሆን :?:
AFRICAN COMMUNICATION PROBLEM
PLEASE LET US LISTEN EACHOTHER.
ETLOVE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Thu Feb 17, 2005 9:19 pm
Location: ethiopia

Re: ለ ላሊበላ 4

Postby ላሊበላ4 » Fri Oct 28, 2005 9:07 am

ዘመዴ!
ይህ ሁሉ የአነጋገር አረቄ ባላስፈለገኝ ነበር:: ጉዳዩ ያገር ነገር ባይሆን ኖሮ ሁላችንም የየግል ህይወት እንዳለን አውቃለሁ::

እኔ ቀጥተኛ ያነጋገር ምሣሌ ብቻ ነው የጻፍኩልዎ:: እርሶ ግን ያልጠቀሱት ተረት የለም:: ምን አስፈለገ ለማለት ብቻ ነው::

አዎ በሰው እምነታቺንን ሁሉ ጥለን አንጓዝ እንደሚል አነጋገርን ነው ያቀረብኩት::እርሶ የየዋህ አጻጻፍዎን እንዲሁም ትርጉሙን አላውቀውም የርሶን አሳብ ያካሄድ መስመር ስለማላውቅ:: ከዚያም የተረትዎ ብዛት መንፈስን ያደክማል:: ያሳይሆን ምክር ለተቃዋሚው ጎራ ተስማምተው እንዲጓዙ በሚል ነው እንጂ እረ ምን አስቸግሮኝ እዚህ ሁሉ የነገር ጥምዝምዝ ውስጥ ሊያስገባኝ የሚቺል ምንም ነገር የለኝምና ይቅርታ ካጠፋሁ መልስ ለመስጠትም ስለማልፈልግ ጭምር

አክባሪዎ

ላሊበላ4
ኪኮ wrote:አረ ጌታዬ ! ነገሩ ወዲህ ነው......የዋህነት ማለቴኮ እርስዎን ለመተረብ አይደለም.....የመርቆሬዎስ ያለህ!! እንደዛማ አስቤ አልነበረም. ...ምኑን ከምን አገናኙት ባዛኝቱ!....... የተወታተበውን የፖለቲካ ልቃቂት ውል ለማግኘት የሚዳክሩትን... ባንድ ወቅት በዚሁ መድረክ ሳይቀር ያለአቅማቸው ኢትዮጵያዊ ማንዴላ እየተባሉ ሲወደሱ የነበሩትን..የፖለቲካ ሰው.. አቶ ልደቱን ህጳን ልጅ አባብለው እንደሚልኩ አይነት ጎሽ እኔን ደስ እንዲለኝ አርብ በማለዳ ሂድና ይቅርታ ጠይቀህ ማህተሙንም አትም ከዛ ሰኞ ሁሉም ነገር ተረት ይሆናል...ማለትዎ ነውኮ የዋህ ኖት ያስባለኝ........ካጠፋሁ እንግዲህ እንደ ጥንቱ እንደአባቶቼ ልማድ ጥገት ላሜን ልካስ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ

ለነገሩ በዚህ በሸፍጥና በሀሰት በምቀኝነትና በተንኮል በተሞላ አለም ውስጥ የዋህ የሚባል ሰው መገኘቱ ደስ ያሰኛል እንጂ አያስከፋም....በተረፈ ብልጦቹ እስኪ ውጡና ተናገሩ ላሉት ሊቃውንቱ ካሉ ይናገሩ እንጂ እንደኔ አይነቱ ጨዋ መሀይም ከአዋቂዎች ጎራ ምን ይዶለኝና!...እመ አምላክን የውነቴን ነው......እንዲያው ሲፈጥረኝ ነገር አይገባኝም..አብሶ ይህ ቦለቲካውማ...እንዲያው ዝም ነው ጨርሶኮ አይገባኝም....አረግ... አረግ ...አረግ...ብዙ ብልሀት አልፈጠረብኝም.ልበል እናንተዬ!.. ደግሞስ ምን ሊረባኝ..ኤድያ አረ እንኳን ቀረብኝ.....'እጅግም ስለት ይቀዳል አፎት.......እጅግም ብልሀት ያደርሳል ከሞት' ይሉ ነበር እኒያ ደግ ጎረቤቴ ባሻ ቢራቱ.... ጨዋታ እንደሆ አያልቅባቸው መቼም እሳቸው ጋ ያለ እውቀት የትም የለ ብልህ ነበሩ የሰፈሩ ሁላ አድባር! አፈሩ ይቅለላቸውና ዛሬ በህይወት የሉም...........ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ አለማወቄን በዚሁ አራምባና ቆቦ በሚረግጠው የጨዋ (የመሀይም ማለቴ ነው) አነጋገሬ ተረድተው ይቅር እንዲሉኝ እለምንዎታለሁ..

ሊቀ መላኩ ይከተልዎ!
ላሊበላ4
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 201
Joined: Fri Dec 24, 2004 8:47 pm
Location: united states

Postby ደምመላሽ » Sun Oct 30, 2005 12:03 am

እውነትም ማንን እንመን? ክርስቶስ ጌታችን ከመሰቀሉ በፊት የየሩሳሌም ህዝብ ሆሳእና እያለ ዘንባባ ይዞ ተቀብሎት ነበር:: ህዝብ ገን ተለዋዋጭ ስለሆነ ዘንባባ ያነጠፉለት አይሁድ በቀናት ልዩነት ይሰቀል ብልው ጮሁበት:: እንግዲህ ሰው በደሎ የማያውቅ ጌታ በህዝብ እንዲህ ከተፈረደበት; እንደኛ አይነቱ ተራ ሰውማ ተሳስቶ ብናገኘው እንዴት እንደምንዘለዝለው አስባችሁ ታውቃላችሁ? የአይሁዶች ንጉስ ከሮማውያን ቀንበር ነጻ ያወጣናል ብለው ሲጠብቁት እሱ ግን የሰላም ሀዋርያ ሆኖ ተገኘ:: ይህ አይሁድን ምን ያህል እንዳናደዳቸው መረዳት አያቅትም:: ኤንግዲህ ህዝብ በተፈጥሮው ክቦ ያወጣውን ስቦ የሚያወርድ መሆኑን ከተረዳን ረጋ ብለን የልደቱን ነገር ማጤን የኖርብናል:: የሰው ፍጹም የለምና ትላንት ብዙዎቻችን ያልከፈልነዉን መሰዋትነት በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በመቀበሉ ብቻ እንኩአን ልንወደውና ይቅር ልንለው የገባል:: ልደቱን ይቅር ማለት ካልቻልን ራሳችንን ይቅር ልንል አይገባም ምክኒያቱም እሱ የከፈለውን ያህል መሰዋትነት ያልከፈልን ብዙ ነን:: የሚሰራ ሰው ይሳሳታል: በሰው ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈርድ ግን ከሁሉ የከፋ ነው::የተሳሳተን ማረም እንጂ ለጠላት አሳልፎ መስጠት ከሀዲነት ነው::
thank yiou for the possibility you gave us to express our views and reveal the enemies of Etiopia.
ደምመላሽ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Mon Oct 10, 2005 1:35 pm
Location: norway

መልእክቶቻችሁን ወደድኩላችሁ

Postby አፈ-ጉባኤ » Sun Oct 30, 2005 2:09 am

እንዴት እሚያረካ ጨዋነት ቁምነገር እምነትና ብስለት የተሞላ የሀሳብ ልውውጥ ነው ጎበዝ እምታካሂዱት?!

በየደረጃው ወዳጆቻችንን እንደ ጥሎ ማለፍ እያንጠባጠብን ጉዟችንን ረጅምና ውስብስብ ከማድረግ እየተቻቻልን እየተወቃቀስን እየተመካከርን እየተወዳደስንና እየተደጋገፍን ልንጓዝ ያሻናል::

ከወጋናዊ ሰላምታ ጋር
አፈ-ጉባኤ
አፈ-ጉባኤ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 302
Joined: Tue Mar 15, 2005 5:20 pm
Location: united states


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests