ሰበር ዜና:-አራቱም ፓርቲዎች የውህደቱን ማህተም መቱ::

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሰበር ዜና:-አራቱም ፓርቲዎች የውህደቱን ማህተም መቱ::

Postby የዘመኑ ልሳን » Fri Oct 28, 2005 6:48 am

ቅንጅትን የማዋአዱ ስራ እንቅፋት ሆኖ የነበረው የአቶ ልደቱ ቡድን ማኅተም አንመታም የሚል ሰንካላ ምክንያት የኢዴፓ-መድን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተሰብስቦ ስለሁኔታው ማኅተብ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመታ ሲዎስን ማኅተሙን በጸሐፊነታቸው ይዘውት የሚገኙት አቶ ልደቱ ማኅተሙን አልሰጥም የሚል እንቅፋት ለመሆን ቢሞክሩም የኢዴፓ-መድን ስራ አስፈጻሚ አባላት በመተዳደሪያቸው ደንብ መሰረት አዲስ ማኅተም ወዲያውኑ አሰርተው የውኅደቱ ሰነድ ላይ መተዋል::ስለዚህና ስለሌሎችም ጉዳዮች አርብ ከሰዐት በኃላ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይታወቃል::

በተያያዘ ዜና ወያኔ ለፓርላማ የተመረጡ አንዳንድ አባላትን በገንዘብ እየገዛ ፓርላማ ለማስገባት በመራራጥ ላይ እንደሆነ እንዲሁ ታውቋል::
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

የዘመኑ ልሳን ሁለቱን ዶክመንቶች እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል

Postby ማድረግ » Fri Oct 28, 2005 7:37 am

http://aigaforum.com/cud/cudsergogeb.htmhttp://aigaforum.com/cud/cudsergogeb.htm


እርስዎ ታዲያ ከየትኛው ቅንጅት ነዎት? በመኢአድ ከሚመራው (ሐይሉ ሻውል ሀላፊነቱ ያልተወሰነ የግል ኩባንያ እያሉ ደጋፊ ነበሮች ከሚጠሩት) ወይንስ በኢዴፓ ከሚመራው?
ማድረግ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Fri Jun 10, 2005 7:15 pm
Location: ethiopia

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Oct 28, 2005 9:09 am

ሁለቱም እኮ አንድ ዶኩመንት ነው ማድረግ!
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1034
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby አቡዬ » Fri Oct 28, 2005 9:43 am

የሁለቱ ዶክመንቶች ልዩነት አልገባኝም አቶ ማድረግ ሊያስረዱን ይችላሉ?
በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ቅንጅት እንጂ ሁለት ቅንጅት የለም ኢዴአፓ-መድህን የአቶ ልደቱን ግግም ያለ አቋም ስላልፈለጉ ነው አዲስ ማሕተም አሰርተው የልደቱን ድርቅ ባይነት ያኮላሹት ይህ የሚያሳየው አቶ ልደቱ ከእንግዲህ በኢዴአፓ-መድሕን ውስጥ ወሳኝነት እንደሌለው ነው
በደስታ አሰፍስፎ የነበረው ወያኔ አንጀቱ ሲኮማተር ይታየኛል ይጠሉት የነበረው ውሕደት ዕውን ስለሆነባቸው የሰላም ዕንቅልፍ እንዳይተኙ አደረጋቸው አቶ ልደቱም እንግዲህ ስህተቱን አምኖ ይቅርታ በመጠየቅ ወደ ትግሉ እንደገና መመለስ ወይም በፋሽስቱ ወያኔ ጉያ መሸሸግ ያለው ምርጫ ይኸው ነው
በጣም የሚያሳዝን ነው በእርግጥ ይህን ያህል ታግሎ ታግሎ በመጨረሻው ላይ እንዲህ አይነት ነገር በመፈጠሩ
ለማንኛውም ትግሉ ከግብ ሳይደርስ የሚቆም አይደለም
ሕዝባዊ ትግል ምንጊዜም በአሸናፊነት ይወጣል
አቡዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 240
Joined: Tue Jan 06, 2004 6:17 pm
Location: united states

Postby ወጥመድ » Fri Oct 28, 2005 10:13 am

ጎበዝ እንዳትወናበዱ እኔ እንደሚመስለኝ ሁለቱም ጽሁፎች ሕዝብን ለማወናበድ የተቀነባበሩ ሆነው የወያኔ የውሸት ማሕተብ ያረፈበት ነው ::

ይልቅስ ቅንጅት አይጋ የሚባለውን ድሕረ ገጽ መክሰስ አለበት::ከህግ ውጭ የድርጅቱን ማሕተብ አስመስሎ ቀርጾ የተዛባ ዜና በማሰራጨቱ በወንጀል ድርጊቱ በሕግ ፊት ሊጠየቅ ይገባል::

ወጥመድ
ወጥመድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Fri Mar 11, 2005 1:52 pm
Location: Semen Walta

Postby አጋም » Fri Oct 28, 2005 11:19 am

አጋም
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Wed Sep 29, 2004 5:35 pm
Location: united states

Re: የዘመኑ ልሳን ሁለቱን ዶክመንቶች እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል

Postby ወዲ ሰበርጉማ » Fri Oct 28, 2005 12:05 pm

ሁሎቱም ጽሁፎች በ አይጋ/ወያኔ የተዘጋጁ ናቸዉ:: በመጀመሪያ በአንድ አይነት ማህተም ሁሎት ተቃራኒ ጽሁፎች ሊወጡ አይችሉም:: በተሎይ አንዱ ስሎ ኢዴፓ-መድህን እያወራ የቅንጅትን ማህተም ሊያደርግ አይቻሎዉም:: ከዚህ በተሎዬ መልኩ ግን ጽሁፎቹ የተቋጩበት አረፍተ-ነገር, ቀንና ማህተሙ ያረፈበት ቦታ 100% አንድ አይነት ነዉ:: ማህተሙ ሁሎቱም ጽሁፎች ላይ "ቲን" እንዴት ሊረግጥ ቻሎ?? ይህ በምንም መልኩ ሊሆን አይችልም:: አይጋ/ወያኔ ሁሎቱንም ጽሁፎች በመጻፍ በ copy & paste ሁሎቱም ጽሁፎች ላይ ማህተም ያረፈበት ሎማስመሰል ያደረገዉ ስራ ነዉ:: ሎማታሎል ሲያስቡ ምናሎ ብልጥ እንክዋ ሎመሆን ቢሞክሩ!! ማፈሪያዎች ናቸዉ::
ማድረግ wrote:http://aigaforum.com/cud/cudsergogeb.htmhttp://aigaforum.com/cud/cudsergogeb.htm


እርስዎ ታዲያ ከየትኛው ቅንጅት ነዎት? በመኢአድ ከሚመራው (ሐይሉ ሻውል ሀላፊነቱ ያልተወሰነ የግል ኩባንያ እያሉ ደጋፊ ነበሮች ከሚጠሩት) ወይንስ በኢዴፓ ከሚመራው?
ወዲ ሰበርጉማ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Thu Mar 17, 2005 4:10 pm
Location: united states

Re: የዘመኑ ልሳን ሁለቱን ዶክመንቶች እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል

Postby የዘመኑ ልሳን » Fri Oct 28, 2005 4:03 pm

ማድረግ wrote:http://aigaforum.com/cud/cudsergogeb.htmhttp://aigaforum.com/cud/cudsergogeb.htm


እርስዎ ታዲያ ከየትኛው ቅንጅት ነዎት? በመኢአድ ከሚመራው (ሐይሉ ሻውል ሀላፊነቱ ያልተወሰነ የግል ኩባንያ እያሉ ደጋፊ ነበሮች ከሚጠሩት) ወይንስ በኢዴፓ ከሚመራው?


ወያኔዎች ያሰቡት የመከፋፈል ሴራ ሲከሽፍባቸው ጊዜ የሌለ ታሪክ ፈጥረው ማውራት ጀመሩ::ይህ የወያኔዎች ምኞት ሲያምራቸው ይቀራል እንጂ በቅንጅት አይፈጠጥርም::ለመከፋፈል የሞት ሽረት ትግል አርገው ነበር ግን አልተሳካላቸውም::ማፈሪያዎች
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

Postby የዘመኑ ልሳን » Fri Oct 28, 2005 5:02 pm

UEDP-Medhin its stamp of approval on the CUD merger, putting an end to the regrettable and time consuming controversy that arose over this matter

... ER, Oct 28, 2005

http://ethiopianreview.homestead.com/
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

ታሪክ ራሱን ሲደግም!

Postby ማካሮቭ » Fri Oct 28, 2005 5:56 pm

http://aigaforum.com/cud/cudsergogeb.htm

የደርግ ፕሮፓጋንዳ ፎቶኮፒ ይመስላል:: ሰሞኑን ሕብረቱ አንቱ የተባሉትን በሳል ሁለቱን ምሑራኖች ካለምንም መሰረት በአጭር መግለጫ ሲያባርር ጎራዴው የተባለው የዋርካ ደንበኛ ታሪክ ራሱን ደገመ:: ብሎ ማለቱ ምንም ሐሰት የለለው እውነት ነው::

በፖለቲካ ትግል የሚያኮርፍ ወገን የራሱ የሆነ አሳማኝ ምክንያት ይኖረዋል:: ምክንያቶቹንንና የውስጥ ልዩነቶችን በመነጋገር ማጥበብ ብሎም በመተራረም ማስወገድ ሲቻል በችኮላ ስም ማጥፋትና እንዲህ ዐይነቱን አስፈሪ መግለጫ ማውጣት ራሱ የዴሞክራሲን አሰራር ያልተከተለና የትላንቱን ጨፍጫፊውን ደርግ የሚያስታውስ አምባገነንነት ነው:: ፖለቲካ የብዙሀኑ ፍላጎት ማንጸባረቂያ እስከሆነ ድረስ ትዕግሥትን መቻቻልን ይጠይቃል:: በትግል ጉዞም አብሮ መቸገርን መከራን መቀበልን መሰደድን ይጠይቃል:: ፍጹም መግባባት ካልተቻለም ጊዜ ተወስዶ የሚከፈለው መስዋዕትነት ተከፍሎ በትዕግሥት የውስጥ ድርድር በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል አለበት:: <መቁረጥንና ማስወገድ> ግን የሀሳብ ልዩነቶችን መሆን ይገባዋል እንጂ አሳቢውን መሆን አይገባውም:: ባጠቃላይ የአፍሪካ ፖለቲካ የተወራረሰ ተመሳሳይ ችግር ሥር የሰደደበት ይመስላል:: ለውጥ የማይታይበት ሁሌም መወነጃጀል: መገዳደል: አለመተማመን: መጠራጠርን እንዳዘለ ይጓዛል::
Wisdom is better than weapons of war: but one sinner destroyeth much good.
ማካሮቭ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 337
Joined: Tue Dec 07, 2004 7:20 am
Location: united states

ውዲ ስበርጎም

Postby አፈር » Fri Oct 28, 2005 6:11 pm

ብዚህ ስም የምትጽፉ ሰወች ብዙናቹህ ወይስ ያው የድሮው ወዲ ነው እንደዚህ የሚጽፈው:: ከሆነ የሚገርም ነው. ጥሩ ነው ለማለት ነው::
አፈር
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Thu Jun 02, 2005 10:51 am
Location: ethiopia

Postby ዞብል2 » Fri Oct 28, 2005 6:19 pm

ወዲ_ማካሮቭ :P መጀመሪያ ማወቅ ያለብህ ጽሁፉ "የቅንጅት" አይደለም....የፈለገው ያለመግባባት በማሀከላቸው ቢኖር እንደዚህ አይነት ለህዝብ የሚያሳዝን "ለወያኔ" ደስ የሚያሰኝ ስነስራት የጎደለው አዋጅ የመሰለ ጽሁፍ አያወጡም :!:

ወዲ_ማካሮቭ :P ጽሁፉ የወያኔ ፕሮፓጋንዲስቶች የጻፉት ለመሆኑ <መጠነ ሠፊ> የሚለውን ቃል ብቻ አይቶ ማውቅ ያቻላል :oops: ምነው አንተ ትእዛዝ የደረሰህ ዘግይቶ ነው መሰለኝ :wink: አሁንም አፍሪካ ምናምን እያልክ አታላዝንብን የሆንክ ማፈሪያ ወያኔ :P :oops:

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1997
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ማካሮቭ » Fri Oct 28, 2005 7:27 pm

ዞብል2 wrote:ወዲ_ማካሮቭ


በቅድሚያ ስለሰጠሄኝ ስም ትርጉሙን ባላውቀውም አመሰግንሀለሁ::

:P መጀመሪያ ማወቅ ያለብህ ጽሁፉ "የቅንጅት" አይደለም....የፈለገው ያለመግባባት በማሀከላቸው ቢኖር እንደዚህ አይነት ለህዝብ የሚያሳዝን "ለወያኔ" ደስ የሚያሰኝ ስነስራት የጎደለው አዋጅ የመሰለ ጽሁፍ አያወጡም :!:


ወዳጄ ዞብል2 የፒያሳው እንዴት ሰነበትክ?? :wink:
እንዳልከው የቅንጅት ማህተም ያረፈበት መግለጫ በርግጥም የወያኔ ስራ ከሆነ ማስረጃ ብታቀርብ ከወንበሬ ብድግ ብዬ አክብሮቴንና አድናቆቴን እቸርህ ነበር:: አስታውስ አይጋ ዌብ ሳይት በዐለም ዐቀፍ ኢንተርኔት ሳይበር ህግ ውል ፈርሞ ሪጅስተርድ የሆነ ባለፈቃድ የመገናኛ መረብ መሆኑን አትዘንጋ:: በድርጅት ስም <<ይህን የመሰለ>> የተጭበረበረ መግለጫ ወጥቷል ተብሎ በዐለም የመገናኛ ሳይበር እንደሚያሳግደውና አደገኛ ወንጀል እንደሆነ AYGA ያልተገነዘበው ይመስልሀል ???


የሆንክ ማፈሪያ ወያኔ :P :oops:
ዞብል ከፒያሳ


ስለተለመደው ስድብህ በድጋሚ እያመሰገንኩህ የምሰናበትህ የማከብርህ ወንድምህ ነኝ::
ማካሮቭ ፐትሪሎቫ
ብሄረ አብሲኒያ ዘ ደቡብ
Wisdom is better than weapons of war: but one sinner destroyeth much good.
ማካሮቭ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 337
Joined: Tue Dec 07, 2004 7:20 am
Location: united states

Postby ሳም2 » Fri Oct 28, 2005 10:15 pm

ማፈሪያ ወያኔካለዚ: ስድብ :ሌላ: አታቅም: ስውን: ለማስረዳት: ካልቻልክ :አንባቢ: ሁን : መቼ:ነው:እንደአዋቂ የምትጽፈው:እስኪ:የጽሁፍን:መዝጊያ:ተመልስህ:እየው
በል :ደህና :ሁን::
test
ሳም2
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 5
Joined: Sat Aug 13, 2005 3:09 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests