ውረድ እንውረድ ተባባሉና አስደበደቡት .......!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ውረድ እንውረድ ተባባሉና አስደበደቡት .......!

Postby ገዳሙ » Sat Oct 29, 2005 4:29 pm

የትላንቱ ጠባሳ ሳይደርቅ
የጉሮሮው አጥንት ሳይወድቅ

ተርመሰመሰ ደግሞ
ኢትዮጵያዊው ሙህር ተብዬ በራስ መዉደድ ታሞ

ካደ! ረሳ! እንደገና የህዝብን አደራ
እንደ ካቻአምናው ተካካደ ለበሰ የቅጥፈት አዋራ

በጨቅላዎች ደም ታጥቦ
ህሊና አጣ አበደ እርቃኑን ተገልቦ

አላማ አልባ ፈሪ
ሆዳም ለማይጠገብ ፍርፋሪ

ላንዲት ቀን ህይወት ለማኝ --አዳሪ
ሁሌ የራሴ እዉነት አልኝ ባይ እዉነት አልባ ቀባጣሪ

ነገም ደሞ በሰው ሊያሳብብ ጥፋተኛ ሊፈልግ
የህዝብን ድል ትላንት ለደርግ ዛሬም ለኢሀደግ

የገደለው የበደለው እከሌ እኔ ደመ ንጹህ ሊል
ዳግም ጲላጦሳዊ ብልጣብልጥ ከተበዳይ ሊውል


ድል ለኢትዮጵያ !!!
ገዳሙ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Sat Oct 25, 2003 10:04 am
Location: ukraine

Postby ገዳሙ » Sat Oct 29, 2005 5:30 pm

ትግል እንጦጦ ብቻ ከመሰለህ አለማቅ ወንጀል አይደለም አይዞህ በጊዜው ትማራለህ
ወዳጄ ! ጀግናህ መለስ መሆኑ ጀግንነትንና ዱርዬነትን ለይትህ የማታውቅ መሆኑን ያስረዳል አልፈርድብህም እደር ለንጀራህ ሰዉን ሁሉ እንደራስህ ግን አትይ !

ዋናው ጊዜ ያገናኘን ! የት ? ጊዜ ያዉዋል
ያንተው :twisted:
ገዳሙ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Sat Oct 25, 2003 10:04 am
Location: ukraine

የማይነጋ መስልዋት በቋት --- እንዲሉ !!!

Postby ገዳሙ » Sat Oct 29, 2005 7:29 pm

ቲዮድሮስ በዋለበት መለስን መጥቅስ ከማሳፈር በላይ የሚያስደብቅ ነው
ሁሉም ነገር ያልፋል ኢትዮጵያ በዚህ የተካነች ናት
ይብላኝ ለናንተ ቀንና ሌሊትን ለማታዉቁ መንፈሳዊ እዉራን !
ኢህአዴግ ያልፋል !
ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኖራለች !!!
ገዳሙ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Sat Oct 25, 2003 10:04 am
Location: ukraine


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests