አይ አዳነች ፍስሃዬ የሥጋ ነገር,,,,

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አይ አዳነች ፍስሃዬ የሥጋ ነገር,,,,

Postby moa » Fri Dec 23, 2005 10:25 pm

ክረስቶስ ለስጋው አደላ እንዲሉ አዳነች ፍስሃዬ በትግሬ ላይ አድማ ተደረገ ብላ ጥያቄ ሳይሆን ሁሉም ትግሬ የቀንጅት ጠላት ነው እንደሚባለው ሁሉ እስዋም ያን መድገምዋ ገለልተኝነትዋን ሳይሆን ለዘርዋ ተቆርቋሪነቷን አሳይቷል።

አቶ ብርሃነ መዋ በዚህ ውይይት ላይ ብቻቸውን ከሶስት ትግሬዎች ጋር እንደሚወያዩ ነው እኔን የገባኝ ። አቶ አብዩ ብርሌ ራሳቸው ታማኝ የወያኔ ተቃዋሚ ነው የሚመስሉት። እኝህ ሰው ራሳቸው ተቃዋሚዎች ለስልጣን ነው የሮጡት ሲሉ ሳዳምጥ አዘንኩ። በህዝብ የተመረጠ ፓርቲ ድሮስ ለምን ለስልጣን አይሮጥም? አዳነች ደንበኛ ወያኔ ትግሬ መሆንዋን አረጋግጣለች። ጭራሽ ጥያቄ ሳይሆን የትግሬነት በሽታዋን ነበር እየተወጣች የነበረው።

በርግጥም ሁሉም ትግሬ የቅንጅተ ጠላት ነው የሚለው አባባል ትክክል እንደሆነ የተረጋገጠው በአዳነች ፍስሃዬ በዚህ ምሽት ተረጋግጧል።

ህዝቡ ጋላቢ ትግሬ ገዳይ እነደሆነ እየገፋች ነበር፤ያሳዝናል አረመኔ ያጋዚ ዘሮቿ ሰው ሲጨርሱ ያልተቸች ሴት ከኪሮስ ጋር አብራ፤ ከአብዩ ታማኝ ተቃዋሚው ጋር አብራ ቅንጅቱን ልትቦጫጭቅ ሞክራለች።
ያሳዝናል እውነትም ክርስቶስ ለሥጋው አዳላ!!
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

Postby ዛግሪ » Fri Dec 23, 2005 11:26 pm

moa
ድሮስ ከቲግሬ ምን ደህና ነገር ይጠበቃል? ወያኔ ሰሞኑን ከወነጀላቸው የVOA ሰዎች አንዷ በመሆኗ እኔን አይመለከትም ከደሙ ንጹህ ነኝ ማለቷ ነው በሷ ቤት:: ወስላታ.- ከህዲ:-ባንዳ ትግሬ!!
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

Postby ሓጎስ » Sat Dec 24, 2005 2:37 am

ዛግሪ እባክህን እያስተዋልክ ተሳደብ :ያንተን ብሄር ሲሰደብ እንደማትወድ ሁሉ ሌላውም ይከፋዋል:: እባክህን የትግራይን ህዝብ ለቀቅ አርገው:: ጠላትህን ለይተህ ምታ:: ኢሃኣዴግ እኮ ከትግራይ ህዝብ ያገኘው 23 ወንበር ብቻ ነው አሸነፍኩ ያለው ግን ከ300 በላይ ነው ስለዚህ ወይም የ አማራ እና የ ኦሮሞ ህዝብ መርጦታል አሊያም ብኣዴን እና ኦሖዴድ አጭበርብረዋል:: ስለዚህ ለምንድነው የትግራይን ህዝብ ጠምደህ የያዝከው::
ልመናየን እንደምሰማኝ ተስፋ አደርጋለሁ
ሓጎስ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Sat Dec 24, 2005 1:53 am

Postby አቡዬ » Sat Dec 24, 2005 8:47 am

ወንድም ዛግሪ እኔም በሀጎስ ሀሳብ እስማማለሁ ወያኔ ኢሀዴግ በትግራይ ህዝብ ስም ቢነግድም የትግራይን ሕዝብ ይወክላል የሚል እምነት የለኝም በወይኔ ተግባራንጀታቸው የቆሰለ ብዙ የትግራይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዳሉ መርሳት የሚገባን አይመስለኝም ከተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍል ውስጥ ለፋሽስቱ ወያኔ ያደሩ ሆዳሞች እንዳሉ ሁሉ በትግራይም ሊኖር ይችላል አይኖርም አልልም በአማራውም በኦሮሞውም .....ወዘተ ስንት ለሆዱ ያደረ ፈርሳም አለ መሰለህ ታዲያ የትግራይን ሕዝብ በአጠቃላይ መፈረጁ ስህተት አይመስልህም????ባለፈው ሳምንት ለምሳሌ
voa አዳምጠህ ከሆነ ሁለት ምሁራን ለኢንተርቪው ቀርበው ነበር ሁለቱም የትግራይ ተወላጆች ቢሆኑም አንዱ ለሆዱ ያደረ ውሽትን መመሪያው ያደረገ ዘረኛ የፋሽስት አቀንቃኝ ሲሆን ሌላኛው ምሁር ግንፍጹም ኢትዮጵያዊና ጸረ ፋሽስት ወያኔ ነበር ታዲያ እንደነዚህ አይነቶች ወንድሞቻችንን ለምን እናስከፋቸው ለምንስ ፋሽስት ወያኔ ባቀደደው ቦይ ውስጥ ገፍትረን እንጨምራቸዋለን በዚህ ዓይነት ባለማወቅም ይሁን በማወቅ ወያኔ እንድንሆን የሚፈልገውን እየሆንለት ነው ስለዚህ ወንድሜ ሆይ አንድን ዘር እየጠቀስን ባንናገር መልካም ነው ትግላችን መሆን ያለበት ከገዢው መደብ ከፋሽስቱ ወያኔ ኢሕአዴግ ጋር እንጂ ከአንድ ዘር ጋር መሆን የለበትም
የወንድምነት ምክር ለማካፈል ስለሆነ በአስተያየቴ ቅር እንደማትሰኝብኝ እተማመናለሁ
በቸር እንሰንብት
አቡዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 240
Joined: Tue Jan 06, 2004 6:17 pm
Location: united states

Postby የዘመኑ ልሳን » Sat Dec 24, 2005 1:13 pm

MOA አዳነች ፍሳአዬ ወያኔ ሰዎኑን በሀገር መክዳት ወንጀል ከከሰሳቸው ሰዎች መካከል አንዳ መሆኑን አትዘንጋ::እኔ ውይይቱን እንደሰማሁት ከሆነ ይህን ያህል የተጋነነ ነገር አላየሁበትም:: ተወያዮች የቅንጅት አመራር Understand በሚያደርገው መልኩ ህዝብ ላይመለከተውና ግለሰቦች ላይ ጥቃት ሊያደርስ ይችላል የሚል ፍራቻ እንዳላቸው ከሀሳባቸው መረዳት ትችላለህ::ይህ ዳግሞ ማንም ሰው ቢሆን ችግሩ ይመለከተኛል ብሎ የሚያስብ ሰው ሊፈራው የሚችለው ሀሳብ ነው:: በተረፈ ሰሞኑን ወያኔ በሀገር መክዳት ወንጀል ከከሰሳቸው ውስጥ ቀላል የማይባሉት የትግራይ ተወላጆች ወገኖቻችን እንዳሉበት አትዘንጋ::ሰሞኑን አንዲት የትግራይ ተወላጅ Girlfriend ስለያዝኩ ነው መሰለይ ትንሽ ሁሉንም በጅምላ ባንከስ የሚል ስሜት ይዞኛል ይህን አስተያየት ስለሰጠሁ እንደማትቀየመኝ ተስፋ አለኝ::
Please በሌላ ቦታ ትግሬ ወደ መቀሌ ምናምን በማለት የከፈትከው ልጅ እርዕሱን Edite አድርገው ይህ ወያኔ የሚፈልገው ነገር ነው:: በትግራይ ተወላጆችን ዘንድ እኔ ከሌለሁ ሌሎች ብሔረሰቦች እንዲህ ያደርጋቸዋል እንዲህ ትሆናላችሁ እያለ ለሚያደርገው ቅስቀሳ ማስረጃ እየሰጠነው እንዳይሆን ፍራቻ አለኝ :;
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

Postby አቡዬ » Sat Dec 24, 2005 1:49 pm

ትክክል የዘመኑ በጣም እስማማለሁ በሀሳብህ ለወያኔ መንገድ አንክፈትለት
በቸር እንሰንብት
አቡዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 240
Joined: Tue Jan 06, 2004 6:17 pm
Location: united states

Postby ወዲ ሰበርጉማ » Sat Dec 24, 2005 2:57 pm

አዳነች ፍሳሐዬ ያሳዘነችኝ ቅንጅት መንግስትን በሚደግፉ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ሎህዝቡ መመሪያ ሰጦዋል በማሎት የቃላት ጨዋታ ሎማድረግ መሞከሯ ነዉ:: የቅንጅት የጥቅምት ወር የሰላማዊ ትግል ጥሪ በአባይ ጋዜጣ እንደተዘገበዉ የሚሎዉ የሚከተሎዉን ነዉ:

"በየአካባቢው ዜጐችን እየጠቆሙ የሚያሳስሩ: እንዲሁም በደህንነት ስራ ከተሰማሩ ሰዎችና ቤተሰባቸው ጋር በሀዘንም ሆነ በደስታ ግንኙነት እንዳይደረግጥሪ ቀርቧል:: የመንግስት ባለሥልጣናት የዴሞክራሲያዊ ሂደት ተባባሪ እንዲሆኑ በስልክ: በኢሜልና በመሳሰሉት መገናኛ ዘዴ ግፊት እንዲደረግባቸው ጠይቋል::"


ጽሁፉ እንደሚገልጸዉ የክፈት ስራን ከሚሰሩት ጋር አትተባበሩ እንጂ የመንግስት ደጋፊን ሁሉ አግልሉ አይልም:: ይህማ ቢሆን ኖሮ ሎምን የመንግስት ባሎስልጣናትን አስመልክቶ በኢሜል ግፊት እንዲደረግባቸዉ ይጠይቃል???

የቅንጅትን ይህንን ሰላማዊ ጥሪና በመጻፍ ቅዱስ ዉስጥ ጳዉሎስ ሎቆሮንጦስ ስዎች የጻፈዉን ጽሁፍ ያነጻጽሩ:

Paul's First Letter to the Corinthians

1st Corinthians : 5:11

"But as it is, I wrote to you not to associate with anyone who is called a brother who is a sexual sinner, or covetous, or an idolater, or a slanderer, or a drunkard, or an extortioner. Don't even eat with such a person."

"ወንድም ነኝ እያሎ ..........ከሚሳደብ ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋር እንዳትተባበሩ....... ከእንደዚህ ዓይነቱ ሰዉ ጋር ምግብ እንኳ አትብሉ::"1st Corinthians : 5:13
"Put away the wicked man from among yourselves."
"ክፉውን ሰዉ ከመካከላችሁ አስወግዱት"

ጳዉሎስ በህይወት ቢኖር ኖሮ ወያኔ የትግራይን ህዝብ ስነልቦና ጎድቷል በሚል "ዘር በማጥፋት ወንጀል" ይከሰዉ ነበር ማሎት ነዉ:: :lol: :lol: :lol:


አዳነች ፍስሐዮ ያልተጻፈን ከማንበብ ብትቆጠብ እንዲሁም ነገሮችን ሎማጣመም ባትሞክር መልካም ነዉ እላሎሁ::

መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ::
ወዲ ሰበርጉማ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 51
Joined: Thu Mar 17, 2005 4:10 pm
Location: united states

Postby ዛግሪ » Sat Dec 24, 2005 4:23 pm

ሐጎስ
ያለምክንያት አይደለም ሁሌ አንድን ብሄር የምኮንነው:- አየህ ከዚህ በፊት ተቃዋሚ የነበሩ ሁሉ አሁን በቁርጥ ቀን ተገልብጠው መልሰው ተቃዋሚዎችን( ራሳቸውን ለመስዋእትነት አሳልፈው የሰጡትን) መኮነንና ማንቋሸሽ ሲጀሚሩ በጣም ነው የተናደድኩት:: ለማንኛውም ሀሳብክን ተቀብያለሁ::
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

ወንድሜ የዘመኑ ልሳን!!

Postby moa » Sat Dec 24, 2005 9:54 pm

wife was mad at me


Two deaf men were in a coffee shop discussing their wives. one signs to the other,boy was my wife mad[/i] at me last night!
she went on and on and would't stop!
The other Buddy says when my wife goes off on me i just dont listen.
How do you do that? says the other.
It's easy! I turn off the light.
"ፍቅር የሌለው ዐይናማ ውጦታልና ጨለማ" ነው ያለው ቴዲ! ይመችህ የዘመኑ ልሳን ከትግራዊቷ ኢትዮጵያዊት ገርልፍሬንድሀ ጋራ!! ለማንኛውም ኦሮማይን መጽሃፍ ደጋግመህ አንብበው።
ከላይ የጻፍኩት ቀልድ አንተን አይመለከትም! እንደው በቀልድ ብጀምረው አንተንም ታዳሚውም ፈገግ ያረገዋል ብዬ ነው።[i]
በመጀመርያ አዳነችን ፍስሃዬን ወያኔ የከሰሣት እስዋ ቀድሞ የኢሃፓ አባል ስለነበረችና የቀድሞው ባለቤትዋ ከነበረው ክፍሉ ታደሰ ጋር ጭምር ነው።
ወያኔ አዳነችን በኢህአፓ አባልነት አሁንም ድረስ ስለሚጠረጥራትና ኤርትራ ብዙ ጊዜ እየሄደች ኢሳይያስን ኢንተርቪው ስለምታደርገው ቅጽል ሰም ጭምር አውጥተውላታል "ድምጸሃፋሽ" እያሉ

እስዋን ያስጠመዳት ያ ነው! አዳነች በትናንትናው ዕለት ኢንተርቪው ላይ እንደጋዜጠኛ እውነትን ፍለጋ ሳይሆን አጠያየቁዋ ቅንጅቱ በአንድ ዘር ላይ እንዳነጣጠረ አድርጋና ህዝቡም መደዴ ክፉና ደጉን እንደማይለይ አድርጋ ነበር ስትኮረኩር የነበረው። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያን ህዘብ እንደመናቅ ይቆጠራል።
ለምን በዘር ላይ የተሳለውን ቅስቀሳ መጀመርያ ወያኔ እንደፈጠረ አልተናገረችም? አስራአምስት አመት ሙሉ ሲያቀነቅነው የነበረው ወያኔ !ቅንጅቱ እኮ የመጣው ባለፉት ስድስት ወራት ነው! ማነው ኢንተር ሃምዌ እያለ የጀመረው ለምን ኪሮስን ይህን አልጠየቀችውም?

አዳነች ካልገባት ግዝቱን እንደገና ታንበው! ከወያኔ ጋር ቡና የሚጣጣ ሁሉ ማለት ትግሬውን፤ሆዳም አማራውን፤ጉራጌውን፤ኦሮሞውን ወዘተርፈ ሁሉ ይመለከታል። ቅንጅትን ትግሬ ሁሉ በጥርጣሬ ያየዋልና አብሬ ልዝመትበት የምትል ከሆነ ተሳስታለች አዳነች ፍስሃዬ!!

አቦ ይቺ የገጠመችህ ትገራዊ እንዴት ያለች ናት እባክሀ? ሁሉም እንደስዋ አፍቃሪ ቢሆን ከትግራይ ምድር ጥላቻ ይጠፋ ነበር።
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

Postby የዘመኑ ልሳን » Mon Dec 26, 2005 12:37 am

moa ጥሩ ባለ ቅኔ ነህሳ ለማንኛውም በቀልድ መልክ ይሁን በቁም ነገር ለማለት የፈለከው ገብቶኛል::እንደ ምክር አድርጌ ተቀብዬዋለሁ::ግን ከላይ የሰጠውትን ሀሳብ በነጻ ህሊና እንጂ Biased ሆኜ እንዳልሆነ እንደተረዳህኝ እገምታለሁ::

ስለ አዳነች ፍሳሃዬ በጣም የሚገርመኝን ጥያቄ ነው የመለስክልኝ::እኔም ብዙ ግዜ ቅንጅትን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ስታጥላላ ስለምሰማት የወያኔ ደጋፊ ትመስለኝ ነበር ለካስ ወያኔ ቂሙን ሁሉ አሁን መወጣት ባይችል እንኳን ማሰማት ስለፈለገ ነው እሳንም የከሰሳት::ለ ኢሳያስን Interview አደረገችው የሚለው ጉጭማውን አስቀንቶት ነበር ማለት ነው::

ኦሮማይን ካነበብኩት በጣም ብዙ አመታት ቢያልፉም ፊያሜታን አረሳትም::መጽሐፍን በቅርብ ካገኘውት ደግሜ ለማንበብ እሞክራለሁ::
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

ዘራፍ!

Postby ገባ-ወጣ » Mon Dec 26, 2005 7:19 am

I use the terms like some and most to express the pervasive hatred used by some CUD members against Ethiopian Tigrees. Seldom have I seen some Amhara compatriots rejecting the orchestrated Tigree bashing new style but most of the time, the majority of the audiences are compliance.

It is quite predictable if these hate mongers start harming the people because of their ethnic linage, their will be fierce revenges here and there and the fire will ablaze many lives. At the end, there will be no gain.

This is not written out of fear but out of strength to remind the wise people that there is nothing to gain out of hateful acts including derogatory terms in this forum. It is important to not that using such belittling terms, insults and racist words is easy and can be used by almost any one if needed. What we have to foresee is the high ground. The art of politics follows strict principles even at trying times. Evil and good are two opposing terms that have completely different outcomes.

ገባ_ወጣ ነኝ
ገባ-ወጣ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 128
Joined: Sat Dec 17, 2005 7:06 pm

Re: ዘራፍ!

Postby ብሔረ አራዳ » Mon Dec 26, 2005 8:46 am

ሰላም ገባ-ወጣ: በመጀመርያ ከስምህ አሰጣጥ ስንነሳ ወላዋይ ነገር ትመስለኛለህ:: የማሌሊቶች በኋላም ያው እንደምታውቀው የወያኔዎች ዋናኛ ስትራቴጂካል መሳርያቸው ሆኖ እስካሁን ያለው ነገር ነው:: እሱም ሲመች ኢትዮጵያን እያሹና እየቦጠቦጦ ውስጧ መኖር:: ገባ ማለት ነው ካልሆነም እንደዚህ ከተነቃባቸውና ተቃውሞው ካየለ ወጣ ለማለት ካለቸው እቅድ አኳያ የተሰጠህ ስም ነው ብዬ ነው የምገምተው:: ከተሳሳትኩም እሰየው:: በእንግሊዝኛ የመጻፍህም አንዱ ትርጉም ለየት ያልኩ ነኝ ለማለት ይሆናል:: እንዳጻጻፍህ ፊደል የቆጠርክ መሆንህ ግልጽ ነው:: ፊደል ከቆጠርክ ደግሞ ወደድክም ጠላህም አማርኛ ተምረሀልና ቢከብደው ነው ማለቱ በእውነት ይከብዳል:: አያጫቃጭቀንም:: እኔን የገረመኝ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም ሆኖ ገና ለገና በትግራይ ሕዝብ ላይ የበቀል እርምጃ ይወሰዳል ብለህ ሰግተሀል:: ለዚህም ነው ፓርቲህ (ወያኔ) የኢትዮጵያን ሕዝብ እርስ በርሱ ከፋፍሎ እርስ በርሱ እያጫረሰ ለረጂም ጊዜ ሊገዛ የዳዳው:: በደኖ- ዋተር - አርባ ጉጉ ወዘተን አሁን ደግሞ የቅንጅት ደጋፊዎች ናቸው እየተባለ በአራቱ የሀገሪቱ ማዕዘናት ሕዝባችን እየተጨፈጨፈ ሕዝብ የመረጣቸው መሪዎች ወህኒ የገቡትን አስታውስ:: ዛሬ የጊዜ ሚዛን ከሻጥር ጋር ተጣምሮ የእናንተ ቢመስልህም አትሳሳቱ ነገ ሌላ ቀን ነው:: ያ የምትፈራው ነገር እንዳይደርስ መፍትሄው እንደ ሰው ከሰው እንደተፈጠረ ማሰብና ማድረግ ነው:: ማንም ሀያል ነኝ ባይ ካላ ሕዝብ ፍላጎት ከተወሰነው በላይ ሲቆይ የሚደርስበትን አስታውሱ!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን በሳልነቱን ታላቅ ሕዝብ መሆኑን በተደጋጋሚ አስመስክሯል:: መሪዎቻችሁ ኢንተርሀማዌ ቅብጥርሶ እያሉ ጸብ ሊጭሩ ሲሞክሩ ሁሉ አዎቆባቸዋል:: ስለዚህም ምንም አስከፊ ነገር አላደረሰም:: ዝም ብለህ ባልተጨበጠ ነገር ፍርሀት ፍርሀት ከሚልህ አሁንም ወንድሜ በድጋሚ ልንገርህ: ሰዎችህን እንደ ሰው አስቡ የምታደርጉትን የምትፈጽሙትን ግፍ ተዉ ካላግባብ ያሰራች ሗቸውን ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የመረጣቸውን ፍቱ በላቸው::
በሏቸው:: "ሗላ ከማዘን ፎቀቅ ብለህ ......" ይባላል::
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጣችሁ ወንድሞች በተለይም moa ስለ አዳነች ማንነት የጻፍከው ከመሰረቷ ማንነቷን እንዳውቅ እረድቶኛልና አመሰግናለሁ::
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይሆናል!!!

----------------------

ገባ-ወጣ wrote:I use the terms like some and most to express the pervasive hatred used by some CUD members against Ethiopian Tigrees. Seldom have I seen some Amhara compatriots rejecting the orchestrated Tigree bashing new style but most of the time, the majority of the audiences are compliance.

It is quite predictable if these hate mongers start harming the people because of their ethnic linage, their will be fierce revenges here and there and the fire will ablaze many lives. At the end, there will be no gain.

This is not written out of fear but out of strength to remind the wise people that there is nothing to gain out of hateful acts including derogatory terms in this forum. It is important to not that using such belittling terms, insults and racist words is easy and can be used by almost any one if needed. What we have to foresee is the high ground. The art of politics follows strict principles even at trying times. Evil and good are two opposing terms that have completely different outcomes.

ገባ_ወጣ ነኝ
ብሔረ አራዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 39
Joined: Wed May 04, 2005 5:43 am
Location: ethiopia

Re: ወንድሜ የዘመኑ ልሳን!!

Postby ወዲ_ፍቃዳ » Mon Dec 26, 2005 12:13 pm

[quote="moa"]
MOኣ 14 አመት ወያኔ አንድም ቢሄር ሲስደብ አልሰማንም
እንድያዉም በብሄራቸው ኢንዲኮሩ አደረገ
የድሮው ኢሀፓ ትናንቱ ቅንጅት ቢሄሮችን መስደብ ጀመረ በተለይ ትግሬ.
ምን መስደብ ብቻ አንዴ ወደ መቃሌ አንደ ወደ ነበሩበት ሽጫካ እንመልሳለን ይላል
ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ ትፈልጋለህ
I love Ethiopia and alll ethiopian
I like to read, wright and chut with my beloved ppl
ወዲ_ፍቃዳ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 72
Joined: Wed Dec 07, 2005 3:23 pm

ወንድም ወዲ ፍቃደ

Postby moa » Mon Dec 26, 2005 1:14 pm

በመጀመርያ ደረጃ ወያኔ የብሄርን እኩልነት ለማምጣት ትግል አላደረገም። የሚገርምህ ታሪክን ወደ ኌላ ሄደህ ብትኮረኩር! መሬት ላራሹን፤የብሄረሰብ እኩልነትን ያቀነቀኑትና የመሩት ዛሬ እናንተ ትምክህተኛ የምትሉት የአማራ ልጆች ናችው። ይህ ውሸት አይደለም አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን ዘመዶችህን ጠይቃቸው።

"ትምክህተኛ" የሚለውንም ሃረግ በቀና ከተረጎምከው አማራው በርግጥ ትምክህተኛ የሆነው በወገኖቹ ላይ ሳይሆን በወራሪ ነጮችና ባንዶች ላይ ነው።ይህ ደግሞ በራሱ ስለሚኮራ ነው። ራሱን በዝቅተኝነት መንፈስ አጥሮ ስላላስቀመጠ ነው ኩሩ የሆነው። ራሱን ሁልጊዜ በዝቅተኝነት መንፈስ ያጠረ ግለሰብ ሁልጊዜ ተንኮል ሲጠነሥሥ ለእድገት መንገድ የማይከፍት ሁልጊዜ ጦርነት ናፋቂ እንደሆነ ነው የሚቀረው።
ተመልከት ቅድመ አያቶችህን! በራሳቸው ኩሩ ወራሪን ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን መክተው የሚመልሱ ጀግኖች የሚወጡባት ምድር ነበረች። አሉላን ክትግሬ መጥቀስ ይቻላል።ለአሉላ ደግሞ የከበረ ቅኔ የተቀኙት አማራው ዮፍታሄ ንጉሴ ነበሩ።አማራው ለወገኖቹ ኢትዮጵያውያን ምንግዜም ክብር የሚሠጥና የሚያከብር በሄር ነው። ትግራይ ላይ እፉኝቶች የበቀሉት ከነመለሰ አያት ጀምሮ የተፈለፈሉት ዜጎች በራሳቸው ላይ ባመጡት የዝቅተንኘት መንፈሰ ደዌ በመሆኑ ችግሩ ቢኖር እንኳ በወንድማማችነት ፈትቶ ምትክ የማይገኝላትን አንዲት እናት ሃገር ከመጠበቅ ይልቅ ያንተ ትውልድ የሆኑት እነመለስ ጭራሽ በወያኔነት አሜርካንን፤ እንግሊዝን፤ ድፍን አውሮፓን ፤ሻብያን፤ ርዳታ በማግኘት የኢትዮጵያ ህዝብም በደርግ ላይ የነበረው ጥላቻ ወቅቱ ስላመቻቸላችሁ
በጎንደር፡መሹለክ እንደማትችሉ ስለምታውቁ የዋሁን ጎንደሬ ቴዎድሮስ የመከላከያ ሃይል ብላችሁ፤ ወሎን ስታልፉ ዋለልልኝ የመከላከያ ሃይል እያላቸሁ፤ ጎጃምንም በላይ ዘለቀ እያላችሁ ሰተት ብላችሀ ገባችሁ። አዲስ አበባን ከተቆጣጠራችሁ በኌላ ደግሞ ትግሬ ጀግና ሌላው ደግሞ ቦቅቧቃ እንደሆነ አሁንም ጉራችሁን ትነፋላችሁ።

ወንደሜ ወዲ ፈቃደ መቀበርያችሁ ደርሷል ሬሳችሁ እንኳ ወደ ምድራችሁ ትግራይ አይደርስም። እስቲ አንድ ነገር ልጠይቅህ ራሳችሁን እንደ ኢትዮጵያዊ ብትቆጥሩ ኖሮ በጦርነት ለገደላችሁት ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ መፎከርያና መሸለያ ሃውልት በስንት ሚልዮን ብር ትግራይ ላይ ታቆሙ ነበር? ያሳዝናል እንደ ሰው መቸ ማሰብ እንደምችሉ አይገባኝም።

በመጀመርያ አሁንም ልንገርህ ቅንጅት መንፈስ ነው ቅንጅት ከትግራይ ህዝብ ውጭ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የመረጠው ስለሆነ 74 ሚልዮን ህዝብ ጨፍጭፋችሁ በጉልበት እንገዛሃለን የምትሉት ከንቱ የከንቱ ህልም እንደሆነ ተረዳ፡ ይልቀስ ያላለፈለትን የትግራይን ህዝብ መብራት ላይ እንኳ ለምኖ እንዳይበላ አታድርጉት!

አንድ በጣም አሳዛኝ አጋጣሚ ላጫውትህ አዲስ አበባ ላይ የዛሬ አራት አመት ገደማ አይቼ የታዘብኩትን! ሥፍራው አሮጌው ፒያሳ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ነው። ባለ አታክልት ቤቱ ሰውዬ ጠውለግ ጠውለግ ያለውን ብርቱካንና ሙዝ ወደ ቆሻሻ መጣያ ኮንቴነር ውስጥ ይጥላል።

እናት ምን ያህል አዛኝ እንደሆነች እኔም አንተም እናውቃለን።ባለጉትዬዎቹ ሁለት ህጻናት ትግሬዎች ከናታቸው እቅፍ ላይ ብርር ብለው ወደ ቆሻሻው ኮንቴነር ላይ ወጥተው የተጣለውን ሙዝ አውጥተው ሊበሉ ሲሉ ባለ አታክልት ቤቱ ተንደርድሮ መጥቶ የኔን አታክልት ወያኔ አይበላውም ብሎ ነጠቃቸው። እንግዲህ አስቡ መለሰና ኩባንያው በበሉትና የኢትዮጵያን ህዝብ በናቁት ደሃ ትግሬ ሁሉ እንደሚሰደብ!

ይሀን ክስተትና ሁኔታ የትግራይ ህዝብ እያወቀ ድንጋይ አቀባይ፤ ቅንጅት ገዳይ፤ መሆኑ አሁንም ይህን ህዝብ አደጋ ውሰጥ ይከተዋል!! ለዚህ ነው አዳነች የያዘችውን ሚድያ ተጠቅማ ያንዣበበውን ደመና ከመግፈፍ ይልቅ ቅንጅት "ትግሬ ገዳይ "እንደሆነ ስትሰብክ የዋለችው።
ግን እንጽናናለን! ዶክተር ሃይሉ አራያን የመሰለ ኩሩ ትግራዊና፤ዶክተር ግደይን የመሰሉም ዜጎች እንዳሉን ስናውቅ!!
moa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Tue May 10, 2005 7:44 pm
Location: ethiopia

Re: ወንድሜ የዘመኑ ልሳን!!

Postby የዘመኑ ልሳን » Mon Dec 26, 2005 7:13 pm

የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ ነው የሚባለው::አስራ አራት አመት ሙሉ ነፍጠኛ እያላችሁ የአማራ ብሔርን እየመረቃችሁት ነበር::ለነገሩ እናንተ ወያኔዎች አማርኛ በአግባቡ ስለማትችሉ ስድብ መሰላችሁ እንጂ ነፍጠኛ ማለት ባለመሳሪያ ያው ጀግና ማለት ነው:: አማርው ደግሞ ከጠቅላላው ኢትዮጵያዊ 1/4 ነው::ይህ ማለት 14 አመት ሙሉ ያለማቋረጥ ከአራቱ ኢትዮጵያዊ አንዱን የተሳደባችሁ እየመሰላችሁ ስትጮሁ ነበር::እንደው በጣም ሁሉም ሰው ያወቀውን ለማለት እንጂ በኢትዮጵያውያን ሱማሌና በአረርጌ ኦሮሞ እንዲሁም በወላይታና አርባ ምንጭ አካባቢ በሚኖሩ ስማአቸውን አሁን የማላስታውሰው ብሔሮ በጋንቤላ ብሔሮችን አንዱን በአንዱ እያጣላችሁ የጎሳ ግጭትን የቀሰቀሳችሁ እናንተ መሆናችሁ ማንም አይረሳውም:: በምስራቅ ሀረርጌ የጨፈጨፋችሁትና ያስጨፈጨፋችሁት ህዝብ ለሌላ ግዜ በይደር የተያዘ አጀንዳ መሆኑን አትርሳ::እናንተ ምን አለ ይህን የጎሳ ፖለቲካችሁን ይዛችሁ ብትጠፉልን::

እኔ ወያኔና የትግራይ ብሔር ህዝቦች በጅምላ ከምንኮንን ወያኔ እና ደጋፊዎችሁን ነጥለን እንናገር አልኩ እንጂ የዚህ ሁሉ ጭፍጨፋ መንስኤና ዋና አቀናባሪ ፈጻሚ ወያኔ ንጹህ ነው አላልኩም::
ወዲ_ፍቃዳ wrote:
moa wrote:MOኣ 14 አመት ወያኔ አንድም ቢሄር ሲስደብ አልሰማንም
እንድያዉም በብሄራቸው ኢንዲኮሩ አደረገ
የድሮው ኢሀፓ ትናንቱ ቅንጅት ቢሄሮችን መስደብ ጀመረ በተለይ ትግሬ.
ምን መስደብ ብቻ አንዴ ወደ መቃሌ አንደ ወደ ነበሩበት ሽጫካ እንመልሳለን ይላል
ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ ትፈልጋለህ
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 9 guests