የገና እንዲሁም የአውሮጳ አዲስ ዓመት ጥያቄዎቼ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የገና እንዲሁም የአውሮጳ አዲስ ዓመት ጥያቄዎቼ!

Postby ወርቅሰው1 » Sat Dec 24, 2005 2:17 pm

የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል እጅግ አድርጎ ያስደንቀኛል:: ህዝቡ ከፍተኛ መስዋይት እየከፈለ ይገኛል:: በዚያው ልክ ግን አሁንም ከወያኔ በኌላ እንኳን ቢሆን ይህ ነው የማይባል ከፍተኛ መስዋይትነትና ሕዝባዊ ክንድን አስተባብሮም ትግሎች እንዳሉበት ማወቅ ይኖርበታል::

1ኛ: አሁን አገራቺንን ምንቅርቅሯን እያወጣት ያለው የወያኔ ህወኃት መንግሥት የሚባለውን ለማባረር በሚደረግ የተሰባጠረ ትግሎች ውስጥ ከምንሰማቸው ለሞቱ እንኳን ተለያይተን እንሙት የሚሉ የአንዳንድ ጽንፈኛ ኃይሎችን እነሱ እንኳን ባይሆኑ ደጋፊዎቻቸው የሚያወሩትን ሲሰሙ ልብን ያቆስላል::

2ኛ: ነገሮቻችንን በጥሞና ተወያይቶ መፍትሄውን ከማምጣት ይልቅ ከመቶ አመት በፊት እንዲህ ተፈጽሞብናልና አሁን እናንተ የምትሉዋትን ኢትዮጵያን ሳይሆን እኛ የምንፈልጋትን ኢትዮጵያን ለማምጣት ነው ውጣ ውረድ የያዝነው ይላሉ:: አዎ ህወኃትም ለ15 ዓመት ሲመራ ለኢትዮጵያ ያመጣላት ቢኖር ጦርነትን:: ግድያዎችንና አገናዎችን ማጥፋትንና ዘረኝነትን አንቀጽ 39ኝን ነው:: እነዚያም እንግዲህ ይህንን ሥራውን የሚደግፉ ይመስላሉ:: ህወኃትን ባይወዱት እንኳን ኃሣቡ ጥሩነው ብለው ይቀበላሉ:: ስለነማን እንደምናገር የምትገነዘቡት ይመስለኛል::

3ኛው: የሚያስገርመኝ:: ኢትዮጵያን ለ3000 ዓመታት አንቀጥቅጠው የገዟት የንጉሣውያን ስብስቦቺና ሟ አንበሳዎችን እንዲሁም ደጃዝማችና ራሶች ያቀፏቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ወዴት ደረሱ ድምጻቸውስ ወዴት ጠፋ:: በተለይ በአሁኑ ግዜ የዘውዱ ምክር ቤት የሚባለው ቡድን ምን እየሰራ ነው? ምንዓነጽ ንቅናቄዎች በኢትዮጵያ መበደል የተነሣ ያሳዬው የቀደመ የቅስቀሳ ዘዴዎች አሉት ወይ አድርጎስ ነበር ወይ?

በተቃዋሚዎቹ የስብሰባ ውይይቶችስ ጊዚያቶች ተገኝነተው ነበረ ወይ በኤኮኖሚስ ድጋፋቸውን አሳይተዋል ወይ? ይህንና ሌሎቹንም በተለይ በኢንግላንድ በስፔንና በሆላንድ በቤልጂየም በዓለም አቀፍ የዙፋን ስብሰባዎች ወቅቶች የአገራቸውን ህዝብና ጥያቄውን መደብደቡና ሞቱን መታሰሩን ጭምር በማንሳት ለቢጤዎቻቸው አስረድተዋችው ነበር ወይ?

እንግዲህ አሁን ኢትዮጵያ ያለቺበት መንታ መንገድን ቢያንስም ቢያድግም ሁኔታዋን ለማስለወጥና ቀጥታ መንገድዋን አስተካክላ እንድትይዝ ከፍተኛ ትጋት ይጠበቅባቸው ነበር:: ኢትዮጵያ ሣትኖር የቀ.ኃ.ሥ ታሪክም ሆነ ምን የለም:: ቅድሚያ ለኢትዮጵያ የሚባለውም ለዚያ ነው ለዚያም ሲባል እነኝህ ሰዎች ምን አስተዋኦ አድርገዋል::

4ኛ: ቢቻል ወያኔ ያሰራቸውን ንጹሐን ዜጎች ከነመሪዎቻቸው ጭምር ሊለቅ ይገባዋል:: ያን ሳያደርግ ቀርቶ በየአቅጣጫው ያውም ያለ ዓዘኔታ ለሚደርስበት ከፍተኛ ህዝባዊ ትንንቅ ሊወጣው እንደማይቺል ሊያውቅ ይገባዋል:: ይህን ህዝብ ንቆ እንደፈለግሁ በአጋዚ ኃይሌ እየገደልኩ በጉልበቴ እቆያለሁ ብሎ የሚያስብ ተሆነ መጥፎ መንገድ መጓዙ ነው ማለት ይመስለኛል:: በፈለገው ዓይነት ታግሎ ሕዝብ አሸናፊ ይሆናል::

በዚያን ጊዜ ግን እሳካሁን እየተዝናና ህዝቡንና አገሩን አፍኖ ለመግዛት የሚፈልገው መለሰ ዜናዊና የሱ የቤተሰብ ስብስብ መንግሥቱ ከፍተኛ ድንጋይ ከፊቱ እያለ በዚያም ላይ ነድቶ እንደሚገለበጥ ደንባራ ሾፌርን ይመስላል:: ያን አውቆ ህዝብንና በድምጹ የመረጣቸውን መሪዎቹን ከማሰቃዬት እንዲቆጠብ ይጠየቃል::

ለማንኛውም ለወያኔ ህወኃት መምከር አይቻልም:: እነሱ የሚያምኑበት ኢትዮጵያን አንኮታኩቶ እነሱ በሰላም የሚኖሩ የሚመስላቸው አንዳንድ አክራሪ ወያኔዎች ታሉ ተሳስተዋል:: መሳሳታቸውንም ህዝቡ በነቂስ ከቤቱ ወጥቶ ነግሯቸዋል:: የሚሰማ ጆሮ የሚያስተውል መንፈስ ባለመታደላቸው እጃቸው በኢትዮጵያ ህዝብ ደም ተነክሮ ዓለም ሣይቀር እያወገዛቸው መሆኑን በመዘንጋታቸው ዛሬ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ከ180 ሺህ - 350 ሺህ የወጣት ትውልድ እስር ቤትና እንደናዚ ሥርዓትም በየ ጦር ካምፖች ውስጥ በማሸግ በኮሌራና በወባ እንዲሁም በአንድ ምላጭ ከ10 በላይ እንዲላጪ እያደረጉ ህዝብን በግፍ እየጨረሱ ለመሆናቸው ዓለም የተገነዘበው ጉዳይ ነው:: በየትም አገር ጥፋት ቢሰራ ህግ እስካለ ድረስ ህግ ይፋረዳዋል እንጂ:: ከኛ ሌላ መረጣቺሁ ተብለው እነኝህን የሚያህል አገር ተረካቢ ትውልድ አስሮ ማሰቃየቱና የመንፈስ ቀው ማድረሱ እራሱን የቻለ ወያኔ መለስ የሚጠየቅበት የሚገረፍበትም ጉድይ ነው::

ይቀጥላል::

አክባሪያችሁ

ወርቅሰው1
ከ(ሰሐሊን)
ወርቅሰው1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4075
Joined: Wed Nov 05, 2003 9:49 pm
Location: Sehalin

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests