ኣማራና ትግሬ:- ኣማርኛና ትግርኛ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby thtna » Thu Dec 29, 2005 3:07 pm

ሰላም ነህ ወይ ወንድሜ ወዲ ፍቃዲ?

ይቅርታህን ተቀብያለሁ:: የጨዋ ኢትዮጵያዊ ሥነምግባር ነው::

እምዬ ሚኒልክ ተሳስተዋል ያልካቸውን ነገር በሙሉ ብናያቸው ....በዛን ጊዜ የግድ መደረግ ነበረባቸው ከዛ የተሻለ ምርጫ አልነበረም:: በተለይ የውጫሌ ውል ላይ ብንነጋገር አንተም እንዳልከው....ጣሊያን አፍርሶታል:; ታዲያ ስህተቱ ያለው ..መፈረሙ ላይ ሳይሆን ...አፍራሹ ወይም ጉልበተኛው የጣሊያን መንግሥት ላይ ነው:: በነገርህ ላይ ወንድሜ...በዛን ጊዜ ከዛ የበለጠ መፍትሄ አልነበረም....እኔና አንተ ተሳስተዋል እያልን የምናወራው በዛሬው ዘመን ነው:: ያኔ ብንኖር ኖሮ ግን ...የሳቸው ሀሳብ ደጋፊ እንሆን ነበር ብየ አስባለሁ:: /አኔ አሁንም እደግፋቸዋለሁ/ :)

እንደኔ እንደኔ....እምዬ ምኒልክና አጴ ቴዎድሮስ ያለዘመናቸው ...የተፈጠሩ ሰዎች ነበሩ ብየ አስባለሁ:: ብዙ ቁምነገር ሰርተዋል እኮ:: እስኪ መጥፎ የምትለውን ትተህ ደግ ደጉን አስብ:: /ሰዎች ናቸውና መቸም 100/100 አንጠብቅባቸውም::/ ደሞ አሁን አንተ ሰሩ የምትሉትን ስህተት የሰሩት /ስህተት ከሆነ/ ሀገር ለመጉዳት ሳይሆን መፍትሄ ለማምጣት ወይም ከአቅም በላይ ሆኖባቸው ነው::

ይሄን ስጵፍ አስተዋይዋን, ለሚኒልክ ሚስትና የቀኝ እጅ የነበሩትን እቴጌ ጣይቱን አስታወስኩ:: ይሄውልህ እንግዲህ ወንድሜ ወዲ ..ንጉሱና ንግስቲቱ /እምየ ሚንልክና እቴጌ ጣይቱ/ ተባብረው ነው በዛን ጊዜ የነበረችውን ሀገራችንን ያስተዳደሩት::

ሰላም ሁን::
thtna
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 46
Joined: Thu Sep 18, 2003 5:43 pm

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: ምሰጢር and 3 guests