ወያኔና<~>ጥንቃቄ: የሚያሻው: ሰላማዊ:ትግል!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ወያኔና<~>ጥንቃቄ: የሚያሻው: ሰላማዊ:ትግል!

Postby ዱራሰንበት » Tue Dec 27, 2005 5:52 pm

የሰላማዊ: ትግል: ስልት: በአንድ: ቀን: ለውጥ: ማምጣት: አይደለም:ተልኮው:: የሰላማዊ: ትግል: ዋንኛው: ሥልት: እልህ: ማስጨረስ: ነው:: ከዚህ: አንጻር: ሲገመገም: የኢትዮጵያ: ህዝብ: የመረጠው: ሰላማው: የትግል: ስልት: በእስከዛሬው:እንቅስቃሴ: ከፍተኛ: ድሎችን: እያስመዘገበ: ይገኛል::
ነገር: ግን: ጥንቃቄ: የሚያሻው: ነገር: አለ:: ይኸውም: ችኩልነት: በተወሰኑ: ወገኖች: በኩል: ይታያል::አረመኔው: ወያኔ: ደግሞ: ይህንኑ: የሰላማዊ: ትግል: ስልት: የረብሻና: በደም: የተጥለቀለቀ: የአንድ: ሰሞን: ትግል: ለማድረግና: ይህንኑ: የሰላማዊ: ህዝባዊ: ትግል: ለማምከን: አሉኝ: የሚላቸውን: የማክሸፊያ: ስልቶች: ከሚገባው: በላይ: ሲጠቀማቸው: ይታያል::
በዚህ: ስልቱም: በራሱ: ጆሮ: ጠቢዎችና: የጸጥታ: ኃይሎች: አማካኝነት: በሰላማዊ: ሰዎች: መካከል: በመቀላቀል: የትግራይ: ተወላጅ: ባልሆኑ: የፖሊስ: አባላት: ላይ: ቦምብ: በመወርወር:የእሩምታ: ተኩስ: ልውውጥ: በማድረግና:መኪናዎችን:መደብሮችን:በማቃጠል: ሰላማዊ: ሰልፈኞችና: የተቃዋሚ: ደጋፊዎች:የታጠቁ: ናቸው: ብሎ-: ለመወንጀል: እንዲሁም: የፕሮፓጋንዳ: መርዝ: ለመርጨት: ሲጠቀምበት: ይታያል::
አንዳንድ: የኌህ: ኢትዮጵያውያን: ከችኩልነት: መንፈስ: ተነስተው: የቦምቡንና: የጥይት: እሩምታውን: እንደለውጥ:አፋጣኝነት: መሳሪያ: ይመለከቱታል::
Code: Select all
አሁን: ባለው: የህዝብ: ለበቃኝ:በቃኝ: ነው: የለውጥ: ፍለጋ: ዘዴ: የሰላማዊ: ትግሉ: ሥልት: ለወያኔም: ሆነ:ወያኔን: ለአሰለፉብን: የአንግሎ-አሜሪካ: ነጋድራሶች:የኑኩሊዬር: ቦምብ: ያህል: እያፍረከረካቸው: የሚገኝ: ዓብይ: ዘዴ: ነው::

ቀደም: ብዬ: እንዳልሁት: ወያኔና: የአንግሎ-አሜሪካ: የስለላው: መዋቅር: አማካሪዎች: ግን: ዘገምተኛውን: ህዝባዊ: እሳት: በጥድፈት: እሳት: ለማጥፋት: እየሞከሩ: ይገኛል:: በምሳሌ: ለማስረዳት: ያህል: በአንድ: የደን: ቋጥኝ: የሚጋልበውን: እሳት: በደኑ: መሀል: የተሰሩ: ቤቶችን: እንዳያቃጥል: ሲታሰብ: ሀይለኛው: እሳት: ከመድረሱ: በፊት: ከቤቶቹ: ዙሪያ: እሳት: እሆን: ተብሎ-: ቅጠል: ተይዞ: በአካባቢው: የሚገኘው: የደኑ: አካል: ላይ: በመለኮስ:እንዲቃጠል: ይደረጋል:: ይህም: ከሚመጣው: ከቁጥጥር: ውጪ: ካለው: እሳት: ለመከላከል: ይጠቅማል:ተብሎ: ይታመናል::
እዚህ: ላይ: ነው: ህዝባዊው: ሰላማዊው: የትግል: ስልት: ጥንቃቄን: የሚያሻው:: ቢቻል: በፎቶና: በቪዲዮ: እየቀረጹ:ቦምብ: የሚጥሉ: የወያኔ: የጸጥታ: ኃይሎችን: መለዬት: የሚያስፈልገው::
በሌላ: በኩል: ወያኔ: ይህንኑ: ስልት: ከሚገባው: በላይ: ደጋግሞ: ስለተጠቀመበትና: ህዝቡም: ተንኮሉን: ስለተረዳው:ከጠቀሜታው: ይልቅ: ጉዳቱ: እያመዘነ: እንደሚሄድ: የተረዳ: አይመስልም::
ያም: ሆነ: ይህ: ወያኔን: የመረጠውን: የሽብር: ዘዴ:ለማክሸፍና: ሰላማዊውን: ትግል: ለማጧጧፍ: ጥንቃቄና: የወያኔን: ተንኮል: የመረዳት: ኃላፊነት: ይጠበቅብናል::
Image
ዱራሰንበት
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2995
Joined: Thu Apr 01, 2004 3:29 pm
Location: Dedessa Death Camp, Tach Birr Sheleko

Postby ወጥመድ » Tue Dec 27, 2005 6:32 pm

ትክክል ብለሀል ዱራሰንበት

አሁን በወያኔ ላይ ከአንዳንድ የውጭ አገር መንግስታት ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲለቀቁ ተጽእኖ እየበረከተበት ይገኛል:: ወያኔ ደግሞ ይህንን መልኩን ለማስለወጥ ይፈልጋል::

እራሱ ባፈነዳው ቦንብ ፎቶ እና ቪድዮ አንስቶ ለውጭ አገር ገላጋዮች እንደ መረጃ በማቅረብ እኛ ሰላምን ስንፈልግ ተቃዋሚዎች አሁንም ለነውጥ ይነሳሳሉ በማለት ለውሽት ውንጀላ ለማመቻቸት ነው::

በሌላ በኩል ግን የህዝቡ አመጽ ከተቃዋሚዎች ቁጥጥር ውጭ በመሆኑ የወያኔ ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው::

ህዝብ እኮ ለወያኔ አልገዛም የሚለው ስላልመረጠው ነው:: ባልመረጠው ፓርቲ ደግሞ የመገዛት ግዴታ የለበትም::

ለዚህ ሁሉ ችግር የምርጫ ኮሚሽኑ መሪ ከማል በድሪን ነው::

ወጥመድ
ወጥመድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Fri Mar 11, 2005 1:52 pm
Location: Semen Walta

አልመሰለኝም!

Postby የመርካቶው ሰያ » Tue Dec 27, 2005 10:02 pm

ከማል በድሪ የምርጫውን ውጤት በትክክል ቢገልጽ ኑሮ
ዛሬ ካቶ አደም ጋር ይታሰር ነበር!!
አህያውን ፈርቶ ..... እንዳይሆን..
ላገራችን የዛሬ ችግር ዋናው ተጠያቂ ዳኞቹም አቃቢ ሕጉም
የምርጫ ኮሚሽኑም ወዘተ... አይደለም:: የኢሕአድግ
አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነው!!!ቅቅቅቅቅቅቅ
የመርካቶው ሰያ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 54
Joined: Fri Jan 14, 2005 9:13 am
Location: czech republic


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests