የትግራይ ምሁራንና አገር አቀፍ አደረጃጀት

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የትግራይ ምሁራንና አገር አቀፍ አደረጃጀት

Postby ወጥመድ » Wed Dec 28, 2005 11:36 am

ሰላም የዋርካ ታዳሚዎች!

ይህንን ርዕስ የመረጥኩበት ምክናዬት ቢኖር ሁላችንም እንደምናውቀው ወያኔ የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ በማለት ከ30 ዐመት በላይ እየተንቀሳቀሰ ቢገኝም ከእለት ወደ እለት ለዚህ ህብረተሰብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዘነ መጥቷል::

መለሰ ዜናዊና ተባባሪዎቹ የህዋሐት አባላት በትግራይ ህዝብ ስም የሚጫወቱት ሚና ልክ ሂትለር በጀርመን አገር ይጫወት እንደነበረው አይነት ፖለቲካ ነው::

ማለትም ሂትለር በዚያን ወቅት ለጀርመኖች
1-የስራ ቦታን ለህዝቡ በሰፊው እንዲደርሰው አደረገ
2-አንዳንድ ፋብሪካዎችን እንዲከፈቱ አደረገ
3-የጀርመን ህዝብ ከአለም ምርጥ ህዝብ እንደሆነ ዘረኝነትን ለፈፈ
4-ጀርመኖች በጦር መሳሪያና በወታደራዊ ትጥቅ እስከ አፍንጫቸው እንዲታጠቁ አደረገ::
5- አውሮፕን አጠቃሎ ለመግዛት የሁለተኛውን አለም ጦርነት በመሪነት አከናወነ:: ወዘተ---

ነገር ግን ይህ ሁሉ ጊዜያዊ አመርቂ መሳይ ነገሮች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሁዋላ ጀርመን እንዳልነበርች ሆና በ4ቱ ሀያላን መንግስት ለሁለት ተከፍላ መከርዋን ስታይ ቆይታ ከ50 አመት በሁዋላ እንደገና ለመዋሀድ በቃች::
ከዚህም ቀውስ ጋር በተያያዘ ጀርመን በብዙ sq.km የሚቆጠር የድሮ የሀገራቸውን ዳንርድንበር ወደ ራሽያ,ወደ ፖላንድ, ወደ ጣሊንና እንዲሁም ወደሌላም አዋሳኝ አገሮች እየተቆራረጠ ለጎረቤት አገሮች ሳትወድ ብግድ እንድታስረክብ ተገደደች:: ልክ አሁን መለስ ዜናዊ በአሰብ ወደብም ሆነ በባድሜ በሄግ ተብዬው ፍ/ቤት እንደሚያደርገው ማለት ነው::

እና ጀርመኖች የነበራቸውን የአገር የግዛት ድንበር እንዲያጡ እና በአለም ህዝብ ዘንድ እስከ አሁንም ድረስ ናዚ ጀርመን እየተባሉ እንዲሰደቡ ዋና የሚናው ተጫዋች የነበረው ሂትለርና ዘርኝነቱ ነበር:: አሁንም በተመሳሳይ የትግራይ ክልል እና የመለስ ፖለቲካ ወደዚህ አስከፊ አቅጣጫ እያመራ ይገኛል::ስለዚህ ይህ አስከፊ የፖለቲካ ቀውስ መልኩን እንዲለውጥ ለማድረግ ከተፈለገ እንደነ

ዶክተር ግደይ አሰፋ
ገብሩ አስራት-------ወዘተ


የመሳሰሉት የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ የሚያንጸባርቁ የትግራይ ምሁራን ተሰባስበው አንድ አገር አቀፍ ማለት የሌሎችንም ብሄር ብሄረሰብ ህዝብ ያጠቃለለ ፓርቲ እንደ ቅንጅት ቢመሰርቱና ቢንቀሳቀሱ የትግራይን ህዝብ ወደ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለማቅረብም ሆነ የአሁኑን የዘር ፖለቲካ አቅጣጫ ተገቢውን ፈር ለማስያዝ በታማኝነት አማራጭ ድልድይ ይሆናሉ ብዬ አምናለሁ::

ወጥመድ
Last edited by ወጥመድ on Wed Dec 28, 2005 9:22 pm, edited 1 time in total.
ወጥመድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Fri Mar 11, 2005 1:52 pm
Location: Semen Walta

Postby ኢትዮጵያዊው1 » Wed Dec 28, 2005 4:09 pm

:lol: :lol: ገብሩ አስራትም ከምሁራን ተቆጠረ ?

ወጥመድ : ጊዜህን አታባክን ; ሁሉም ሆዳም ናቸው:: ገብሩ አስራት ሌላው መለስ ዜናዊ ነው የነበረ:: ለፖለቲካው አዲስ ከሆንህ ጠይቅ:: የጀርመን እና የውትግራይ ፖለቲካም ይለያያል:: ይብዛም ይነስም ; ሂትለር በወታደሮቹ አማካኝነት ለጀርመን የበላይነት ሰርቷል:: በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያን ህዝብ እየገደለ ያለው ግን ; አጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ነው::

ይሄ ትክክል አይደለም ቢል ደስ የሚለኝ ግን ; እራሱ የትግራይ ተወላጅ እንጅ ; መንገደኛ የዋርካ ፖለቲከኛ አይደለም::
ኢትዮጵያዊው1
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Tue Feb 10, 2004 3:27 am

Postby ካር » Wed Dec 28, 2005 4:46 pm

እትዮዽያዊዉ
የእትዮዽያን ህዝብ እየገደለ ያለው የትግራይ ህዝብ ወይስ
አቶ መለስ ከሆዳም የአማራና ኦሮሞ ካድሬዎቹ ጋር??????
የሰዉን ፖለቲካ ስንቃዎም አማራጨ ይዘን መሆን እንዳለበት
የምታቀው ይመስለኛል
የዘር ጥላቻ እያሳየን የነመለስ ደጋፊዎች ወይስ ታቃዋሚዎች
ነን?
የትግራይ ህዝብ አያስፈልገንም ብለህ ታስባለህ???
እንደምትመልስልኝ ተስፋ አደርጋለሁ

ካር ነኝ
ካር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 19
Joined: Sun Dec 18, 2005 6:50 pm
Location: 90735

የኔም ጥያቄ ነው!

Postby የመርካቶው ሰያ » Wed Dec 28, 2005 5:05 pm

ወዳጄ ካር ጥያቄህ ትክክል ነው!
እባካችሁ ይህ የጅምላ ጥዝጠዛ ላገራችን አይበጅም!!
አቁሙ!!! በወያኔ የተላካችሁ የጥፋት ነጋድራሶች አደብ አድርጋችሁ ተቀመጡ! አንዱን ብሔር ካንዱ ለማጣላት የሚደረገው spritual masturbation ተበልቶዋል!
የ ቅንጅት አቁዋም ይህ አይደለም ! ፍትህ ዲሞክራሲ ሰላም
ብልጽግና... ኢትዮዻዊነት ነው በስሙ አትነግዱ
ሌላ አጀንዳ ካላችሁ ራሳችሁን ወክላችሁ ብቅ በሉ!!
እንወቃችሁ: :?:
የመርካቶው ሰያ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 54
Joined: Fri Jan 14, 2005 9:13 am
Location: czech republic

ሌሎችም አሉ!

Postby የመርካቶው ሰያ » Wed Dec 28, 2005 5:10 pm

ትናንት በጀርመን ድምጽ ራዲዮ ቃለምልልስ የሰጡት
ካህሳይ አብረሀ?
የህብረቱ አረጋዊ በረሄ
.........
የመርካቶው ሰያ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 54
Joined: Fri Jan 14, 2005 9:13 am
Location: czech republic

ድንቅ አባባል የመርካቶው ሰያ

Postby ዲጎኔ » Wed Dec 28, 2005 5:34 pm

[quote="የመርካቶው ሰያ"] በወያኔ የተላካችሁ የጥፋት ነጋድራሶች አደብ አድርጋችሁ ተቀመጡ! አንዱን ብሔር ካንዱ ለማጣላት የሚደረገው spritual masturbation ተበልቶዋል!
የ ቅንጅት አቁዋም ይህ አይደለም !

ሰላም ለአንተ ይሁን ወዳጄ ልቤ የመርካቶው ሰያ

ይህ አዲስ ፋሽን ሳይሆን የወያኔ የቆየ ሰራ ነው

1. ወያኔ ባህር ዳርና ጎንደር ላይ ኢዲዩን ከህዝብ ለማጣላት ወፍራም ወፍራም ወያኔዎችን ሰልቫጅ ሱፍ ኮትና ሱሪ አስለብሶ የኢዲዩ ያልሆነ መፈክርን ሲያሰማ ነበር
2. የሰረተኛውን ማህበር ጠንካራ መሪ ዳዊ ኢብራሂምን ለመሸንገልና ተለጣፊ ማደረግ ሲያቅተው ወያኔ የራሱን የሰራተኛ ማህበር በተኮላሸ የትግል ጥያቄ ለማዳፈን ጥሯል
3.የመምህራን ማህበር እውነተኛ መሪ ዶ/ር ታዬን ከውጭ ሲመለሱ ኤርፖርት ላይ ተቀብሎ በእስር አማቅቆ የመምህራንን ትግል የሚያኮላሽ ተለጣፊ ማህበር ሰይሟል
4. ለዛ ቢሷን የቪኦኤ ዘጋቢ ሚሚ ስብህቱን በመግዛት ባሏ ዘሪሁን በሚያዘጋጀው ዋሾ ኢፍትን ጋዜጣ ሀቀኛውን ነጻ ፕሬስ አሰድቧል
5. አሁንም በኢንተርኔት በተለይ Ethioindex ላይ በስፋት ዋርካ ላይ ደግሞ በጥቂቱ የህዝባችንን ጸረወያኔ ተገቢ ትግል ጸረ-ትግሬ አድርጎ መሪዎቻችንን ለመወንጀል ጀሌዎቹን የሚልክብን ያው መርዛሙ ኮብራው ወያኔ ነውና በማስተዋል ነዳፊ መርዛማ የፕሮፓጋንዳ አፉን እንቀጥቅጥ

ዲጎኔ ሞረቴው ከመላዋ ኢትዮጵያ አንድነት ቃልአቀባይ ጽ/ቤት
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Re: የትግራይ ምሁራንና አገር አቀፍ አደረጃት

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed Dec 28, 2005 6:48 pm

[quote="ወጥመድ"]ሰላም የዋርካ ታዳሚዎች!


:

ማለትም ሂትለር በዚያን ወቅት ለጀርመኖች
1-የስራ ቦታን ለህዝቡ በሰፊው እንዲደርሰው አደረገ
2-አንዳንድ ፋብሪካዎችን እንዲከፈቱ አደረገ
3-የጀርመን ህዝብ ከአለም ምርጥ ህዝብ እንደሆነ ዘረኝነትን ለፈፈ
4-ጀርመኖች በጦር መሳሪያና በወታደራዊ ትጥቅ እስከ አፍንጫቸው እንዲታጠቁ አደረገ::
5- አውሮፕን አጠቃሎ ለመግዛት የሁለተኛውን አለም ጦርነት በመሪነት አከናወነ:: ወዘተ---

ሰውዬው ያነሳሀቸው ነጥቦች ዛሬ የወያኔው መንግስት ከሚያደርጋቸው ነገሮ ፍጹም ተጻራሪ ሆነው ስላገኘዋቸው እስቲ ትንሽ ልበል ብዬ ነው

...መላው አውሮፓ የኢኮኖሚ ውድቀት ውስጥ በነበረበት ጊዜ ...አዶልፍ ሂትለር ለመላው የጀርመን ህዝብ ሰፊ የስራ ቦታዎችን እንደሚከፍትና የተዋረደውን የኘርመን ህዝብ ታላቅለቱን እንደሚመልስለት ቃል በገብዋው መጽሀፉ ..."የኔ ትግል "የህዝብን አይንና ጆሮ ..ልብ ስቦ በጀርመን ህዝብ እስከ ቻንስለርነት ደረጃ ደርሷል .....ይሁንም እንጂ አዶልፍ ሂትለር ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ የስልጣን ጥሙ አልደርቅ ብሎ ታላቋን ጀርመንን ብቻ ሳይሆን መላውን አለም ከጫማው ስር ሊያውል ተነሳ .....ለዚህ አላማው በጊዜው ካሉ የጎረቢት ሀገሮች በኢንዱስትሪ ያደገችውን ትንሿን ጎረቢቱን ቼኮዝሎቫኪያን በ1938 ዐ.ም.በሚኒክ በተደረግ የሀያላን አገሮች ስብሰባ ....ቼኮዝሎቫኪያ ለጀርመን እንደምትገባ ተወስኖ የመጀመሪያው የሂትለር የግዛት መስፋፋት መንገድ ከፋች ሆነች ...ዛሬ የቼክ የታሪክ ተመራማሪዎ ይሄን የአያላን ሀገሮችን ጨካኝ ውሳኔ ..."ያለኛ ስለኛ የተወሰነ "ብለው አልፈውታል...
እንዳው ለመጠቆም ያህል ከሁለት አመት በፊት እነዚሁ አያላን ሀገሮች በጄኔቩ ስብሰባቸው 1936 ኢትዮጵያንም ለሞሶሎኒ አሳልፈው ሰተው ነበር ...
ሆነ ቀረ ሂትለር መስከረም 1 1939 ፖላንድን እስከወረረበት ቀን ድረስ ሁሉም ነገር በሀያላን ሀገሮች ዘንድ. ትክክለኛ ነበር ...
ወደኛው የዘመኑ ሂትለር መለሰ ዜናዊና ጀሌዎቹ የተመለስን እንደሆነ በኔ አይን እነዚህ የሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ መዥገሮች ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን የሚያዋርድ እንጂ ኢትዮጵያዊው በኢትዮጵያዊነት እንዲዋረድ እንጂ እንዲኮራ አርድርገዋል የምለው ነገር የለኝም ....እና ይቺን የመንደር ሽፍታ ቡሽም ቢደግፋትም ማለቴ ነው ከሂትለር ጋር ባናወራርዳት ....ሳይሻል አይቀርም ....እላለሁ .....]
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Re: የትግራይ ምሁራንና አገር አቀፍ አደረጃት

Postby ወጥመድ » Wed Dec 28, 2005 9:15 pm

ፓን ሪዚኮ

ወጥመደ wrote:
Code: Select all
ማለትም ሂትለር በዚያን ወቅት ለጀርመኖች
1-የስራ ቦታን ለህዝቡ በሰፊው እንዲደርሰው አደረገ
2-አንዳንድ ፋብሪካዎችን እንዲከፈቱ አደረገ
3-የጀርመን ህዝብ ከአለም ምርጥ ህዝብ እንደሆነ ዘረኝነትን ለፈፈ
4-ጀርመኖች በጦር መሳሪያና በወታደራዊ ትጥቅ እስከ አፍንጫቸው እንዲታጠቁ አደረገ::
5- አውሮፕን አጠቃሎ ለመግዛት የሁለተኛውን አለም ጦርነት በመሪነት አከናወነ:: ወዘተ---


ሰላም ፓን ሪዚኮ

ከላይ ያሉትን ነጥቦች ሂትለር እንደ መቀስቀሻ መሳሪያ አድርጎ የጀርመንን በዘረኝነት ከጎኑ ለማሰለፍ የሞከረበትን ነጥቦች የጠቀስኩበት ምክናየት
ዛሬ መለሰስ ዜናዊ በትግራይ ህዝብና በትግራይ ክልል የሚያደገውን እንቅስቃሴ በማነጻጸር ነው እንጂ አጠቃላዩን ኢትዮጵያ ማለቴ አይደለም:::

ወጥመድ
ወጥመድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Fri Mar 11, 2005 1:52 pm
Location: Semen Walta

ወጥመድ

Postby ገባ-ወጣ » Wed Dec 28, 2005 10:43 pm

ወጥመድ!!

Though I respect your keen concern about Ethiopia, your comment indicates some deficiency on the required understanding to critically evaluate the two unrelated aspects and reach one conclusion. First Tigray and Germany are incomparable, as Tigray is part of Ethiopia and German a well developed industrialist nation. There is also conflict on the personality comparison between Meles Zenawi and Adolph Hitler. Yet I don’t have problem if you critique or even insult Meles. I really do not. My allegiance is with the people. I stand in defense of any oppressed people. As you can read on the forum, some of the fanatic CUD supporters openly ask for killing of Tigreans. And these are the people who would be leaders in the future CUD leaded Ethiopia.
ገባ-ወጣ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 128
Joined: Sat Dec 17, 2005 7:06 pm

Re: ወጥመድ

Postby ወጥመድ » Thu Dec 29, 2005 12:06 am

ገባ-ወጣ wrote:ወጥመድ!!

T As you can read on the forum, some of the fanatic CUD supporters openly ask for killing of Tigreans. And these are the people who would be leaders in the future CUD leaded Ethiopia.


ሰላም የአሁኑ= ገባ -ውጣ
የድሮው= ወዲ ሳባርጉማ

ወዲ በመጀመሪያ ደረጃ እኮ አንተ አማርኛን በደንብ መጻፍ እየቻልክ ከእንግሊዝኛው ጋር ምን አታገለህ? አማራን ስለ ጠላህ አማርኛን ላለመጻፍ ማእቀብ ለማድረግ ፈልገህ ከሆነ ግን መብትህ ነው::

ወደ ዋናው ነገር ስመለስ በጣም የሚገርመው ነገር ቢኖር በአንተም ሆነ በደጋፊዎችህ አስተሳሰብ እንዴት በዋርካ ፎርም ላይ የሚሳተፈውን ሰው ሁሉ የCUD አባል, ደጋፊና በተይ አማራ እያላችሁ ለመስደብ ያስቻላችሁ ምን አይነት መርጃ ይዛችሁ ነው::ደግሞስ some of the fanatic CUD sepporter openly ask for killin of Tigreans. ያልከው ማነው እንዲህ ብሎ የጻፈው?
አንተስ ከምርጫው በፊት አንዱን ወደ ኮንጎ ሌላውን ወደ ማዳጋካር እንመልሳለን ስትል አልነበር እንዴ?

ለማንኛውም ግን መከባበሩ የሚሻል ይመሰለኛል::

ሌላው እንዴት ጀርመንና ትግራይን ታወዳድራለህ ላልከው ኤኔ ያወዳደርኩት የሂትለርን የፖለቲካ አካሄድና የመለስን በትግራይ ክልል ተመሳሳይ ፖለቲካዊ አካሄድ ነው እንጂ
የጀርመን አገርን ከትግራይ ክልል ጋር በማወዳደር አይደለም::

ወጥመድ
ወጥመድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Fri Mar 11, 2005 1:52 pm
Location: Semen Walta

Re: ድንቅ አባባል የመርካቶው ሰያ

Postby CUBBY » Thu Dec 29, 2005 12:14 am

እንደዚህ ያለ ሸጋ አስተሳሰብ በሁላችንም ቢኖር ምን ያህል ዘላቂ አንድነት ይፈጠር ነበር ታንክስ!!
ዲጎኔ wrote:
የመርካቶው ሰያ wrote: በወያኔ የተላካችሁ የጥፋት ነጋድራሶች አደብ አድርጋችሁ ተቀመጡ! አንዱን ብሔር ካንዱ ለማጣላት የሚደረገው spritual masturbation ተበልቶዋል!
የ ቅንጅት አቁዋም ይህ አይደለም !

ሰላም ለአንተ ይሁን ወዳጄ ልቤ የመርካቶው ሰያ

ይህ አዲስ ፋሽን ሳይሆን የወያኔ የቆየ ሰራ ነው

1. ወያኔ ባህር ዳርና ጎንደር ላይ ኢዲዩን ከህዝብ ለማጣላት ወፍራም ወፍራም ወያኔዎችን ሰልቫጅ ሱፍ ኮትና ሱሪ አስለብሶ የኢዲዩ ያልሆነ መፈክርን ሲያሰማ ነበር
2. የሰረተኛውን ማህበር ጠንካራ መሪ ዳዊ ኢብራሂምን ለመሸንገልና ተለጣፊ ማደረግ ሲያቅተው ወያኔ የራሱን የሰራተኛ ማህበር በተኮላሸ የትግል ጥያቄ ለማዳፈን ጥሯል
3.የመምህራን ማህበር እውነተኛ መሪ ዶ/ር ታዬን ከውጭ ሲመለሱ ኤርፖርት ላይ ተቀብሎ በእስር አማቅቆ የመምህራንን ትግል የሚያኮላሽ ተለጣፊ ማህበር ሰይሟል
4. ለዛ ቢሷን የቪኦኤ ዘጋቢ ሚሚ ስብህቱን በመግዛት ባሏ ዘሪሁን በሚያዘጋጀው ዋሾ ኢፍትን ጋዜጣ ሀቀኛውን ነጻ ፕሬስ አሰድቧል
5. አሁንም በኢንተርኔት በተለይ Ethioindex ላይ በስፋት ዋርካ ላይ ደግሞ በጥቂቱ የህዝባችንን ጸረወያኔ ተገቢ ትግል ጸረ-ትግሬ አድርጎ መሪዎቻችንን ለመወንጀል ጀሌዎቹን የሚልክብን ያው መርዛሙ ኮብራው ወያኔ ነውና በማስተዋል ነዳፊ መርዛማ የፕሮፓጋንዳ አፉን እንቀጥቅጥ

ዲጎኔ ሞረቴው ከመላዋ ኢትዮጵያ አንድነት ቃልአቀባይ ጽ/ቤት
CUBBY
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 159
Joined: Wed Oct 15, 2003 3:53 pm

Postby ጢያ2011 » Thu Dec 29, 2005 2:54 am

አሁንስ የቅንጅት ደጋፊዎች ለቀቃችሁ እንደ የምትናገሩትንም የምታውቁ አልመሰልህ አለኝ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
LET'S CONTINUE SUPPORTING ETHIOPIAN DEMOCRACY.
ጢያ2011
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 21
Joined: Mon Dec 26, 2005 11:52 pm

Re: ወጥመድ

Postby ገባ-ወጣ » Thu Dec 29, 2005 3:36 am

ወጥመድ wrote:
ገባ-ወጣ wrote:ወጥመድ!!

T As you can read on the forum, some of the fanatic CUD supporters openly ask for killing of Tigreans. And these are the people who would be leaders in the future CUD leaded Ethiopia.


ሰላም የአሁኑ= ገባ -ውጣ
የድሮው= ወዲ ሳባርጉማ

ወዲ በመጀመሪያ ደረጃ እኮ አንተ አማርኛን በደንብ መጻፍ እየቻልክ ከእንግሊዝኛው ጋር ምን አታገለህ? አማራን ስለ ጠላህ አማርኛን ላለመጻፍ ማእቀብ ለማድረግ ፈልገህ ከሆነ ግን መብትህ ነው::

ወደ ዋናው ነገር ስመለስ በጣም የሚገርመው ነገር ቢኖር በአንተም ሆነ በደጋፊዎችህ አስተሳሰብ እንዴት በዋርካ ፎርም ላይ የሚሳተፈውን ሰው ሁሉ የCUD አባል, ደጋፊና በተይ አማራ እያላችሁ ለመስደብ ያስቻላችሁ ምን አይነት መርጃ ይዛችሁ ነው::ደግሞስ some of the fanatic CUD sepporter openly ask for killin of Tigreans. ያልከው ማነው እንዲህ ብሎ የጻፈው?
አንተስ ከምርጫው በፊት አንዱን ወደ ኮንጎ ሌላውን ወደ ማዳጋካር እንመልሳለን ስትል አልነበር እንዴ?

ለማንኛውም ግን መከባበሩ የሚሻል ይመሰለኛል::

ሌላው እንዴት ጀርመንና ትግራይን ታወዳድራለህ ላልከው ኤኔ ያወዳደርኩት የሂትለርን የፖለቲካ አካሄድና የመለስን በትግራይ ክልል ተመሳሳይ ፖለቲካዊ አካሄድ ነው እንጂ
የጀርመን አገርን ከትግራይ ክልል ጋር በማወዳደር አይደለም::

ወጥመድ


ወጥመድ:

I do not think you got the point. I am tired of writing and I will not try to repeat. But let me explain few points
I am not sebari goma. You are dead wrong on that
I understand Amharic perfectly but have difficulty writing.
I do not hate Amhara, hate is evil.
I have never ever said Oromos should go to Madagascar. In fact I believe the opposite. Oromos are pure Ethiopians. They have been oppressed for centuries, ridiculed by the dominant culture (remember some of the proverbs) and as being the majority of the population, they deserve more political capital. As to the hateful comments (killing tegrians) written in the room, I leave that for your self to read and think. All my writings address specific written message. If you curse ethnic, I will write you back adding some curses. I believe that is well deserved.
ገባ-ወጣ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 128
Joined: Sat Dec 17, 2005 7:06 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests