የቆጡን ላውርድ ብላ የብብትዋን ጣለች::

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby ስደት1 » Mon Jan 23, 2006 2:41 pm

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ደርጂቶች

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጂቶች ከዛላቂ ጥቅም ይልቅ በጊዚያዊ ጥቅም የሚንቀሳቀሱ ናቸው ለማለት የሚቻልበት አገር ነው ያለነው:: እንደተፈለገውን ባይሆንም አንዳደቹ በሂደት ራሳቸውን እያስተካከሉ የሚሄዱ እንዳሉ ሁሉ ሌለቹ ደግሞ እንደ ተቸከለ እንጨት ራሳቸው ይትም አይንቀሳቀሱም ሌለውንም እያሰናከሉ ይገኛሉ::

አብዛኛወቹ አገር ከመግንባት ይልቅ አንዱን አንዱን እንዴት አድርጊ ልጣለው እያሉ ማኖቆ ሲያበጁ ኑረዋል አሁንም ይገኛሉ:: ለስሙ ለአገር ሀብት እና አንድነት ተቆርቃሪ መስለው ቢቀርቡም በትግባር ግን ሁሉም ሙሾ ናቸው::

አንዱን አንዱን ለመጣል በሚያደርገው ንትርክ በማሕበረሰቡ ሂወት ምን ያህል ተፅኖ ያመጣል የሚለዉን ቢቀር እካ በራሳቸው ሂደት እና በሌለቹ የፖለቲካ ታሪክ ሊማሩ ያላቻሉ ናቸው::

ድርጂርቶቹ ራስ በራሳቸው በሚፈጥሩት የሩጫ ውድድር አገርን ትልቅ ቦታ ሊያደርሱ የሚቹሉ ብዙ ሰዎች በየበረሀው ወደቀው እና በስደት ዓለም ሂወታቸው እየመሩ ይገኛሉ::

ከኃይለስላሴ መውደቅ ያለዉን እስቲ ነካካ ለማለት እንሞኩር::
አብዛኛወቹ የፖለቲካ ድርጂቶች የተመሰረቱት እና እንቅስቃሴ የሚያደርጉት የነበረው በሰሜኑ ኢትዮጵያ በተለይ በትግራይ ነበር::

ሕዋሓት እና ኢዱ በትግራይ ዋና መንቀሳቀሻ ቦታቸው ነበር:: ቦታው ለሁሉም ይበቃ ነበር:: የጋራ ጠላት የሆነዉን ከማጥቃት የሕዝብ ጥቅም ከማንገብ ይልቅ እርስ በርሳቸው ንትርክ ገብተው አብረው መስራት ስላልቻሉ ግና ሁሉትም ድርጂቶች እልህ አስጨራሽ ጦርነት አድረገዋል:: አብዛኛወቹ የሕዋሐት ሙሁራን የተሰዉት በዚያ ጦርነት ነው::

ኢሕአፓ እና ሕዋሓትም ቢሆኑም ያደረጉት የሀው ተመሳሳይ ነው:: ይባስ ብሎ ኢሕአፓ ቤዙን አሲንባ እኒዲያጣ ምክንያት ሁኖታል::

እነ ኢሕአፓ ሚኤሶ እና ሌለቹ ድርጂቶች ባደረጉት የተሳሳተ አካየደ ብዙ ወጣቶች በደርግ ቀይ ሽብር እንዲረሸኑ ተደርገዋል:: አብዛኛው ወደ ስደት ዓለም ያመራው በዚያ ሰዓት ነበር::

በዚያ ሰዓት በየክልሉ የቢሄር ቢሄረሰቦች ስም በማንገብ የፖለቲካ ድርጂቶች የሚፈሉበት ወቅት ነበር:: ሕዋሓት አንሳሱ ለትግራይ ቢሆንም የኛ መብት ከተጠበቀልን የሌላዉን ቢሄር ቢሄረሰብ መብት ከተጠበቀ ሁላችንም ጭቁኖች ከሆነ አብረን ትልቅ ኢትዮጵያ የማንገነባበት ምክንያት የለም በሚል ትግራይን ለመገንጠል የነበረዉን ዓላማ እርግፍ አድርጎ ራሱን ዓብነት ልሁን ብሎ ብ1975 ወሰነ::

የሕዋሓት አካየዱ ከጊዜ ጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በሜሄዱ ሌሎቹ እየከሰሙ ሲሄዱ ሕዋሐት ግና እየተጠናከረ በሜሄድ ከቀነ ቀነም በጠላቱ ድል እያደረገ ሲገስገስ ቆይተዋል:: በሂደትም ከመሰሉ የፖለቲካ ድሪጅቶች ውሕደት ለመፍጠር ቻለ:: ከኢሕአፓ ራሱን ነጥሉ በኢሕድን ስም ሲታገለ ከነበረው ድርጂት ጋር ውህደት ፈጥሮ ጣምራ ክንድ በመፍጠር ጠላት የተሻለን ሲያንኮታኩቱ ቆዩ:: ራስ በራስ ማዳካም የትም እንደማያደርስ ሁለቱም ድርጂቶች በመገንዘባቸው ደርግ ለመጣል ለነበረው ትግል ትልቅ ስራ ሰርተዋል:: ከሁሉም በለይ ግን እነዚህ ድርጂቶች ውህደት በመፍጠራቸው በሰመኑ አርሶ አደር ትልቅ መቀራረብ ፈጥረዋል::

ኢሕአድግ ከሁለት ድርጂት ወደ አራት ሕብረት ድርጂት ተሻግሮ ክንዱን አጠናክሮ ደርግን ወደ ግባአተ ወድር ይዞ እየሄደ ባለ ወቅት በዘመቻ ቴድሮስ ጊዚያዊ ጥቅምን ፍለጋ ድርግና ኢሕአፓ ውስጣዊ ስምምነት አርገው ኢሕአድግን ከጀርባው ወጥተው የጀርባ አጥንቱን ሊመቱ መኮሩ::

ኢሕአፓ ከሁሉም በላይ ትልቅ ስተት የፈፀመው እዛ ወቅት ነበር:: ለራሱ መቹ ሁኔታ ሳይተክል ለስልጣን ሺሚያ ሲል ደርግን አግዞ ኢሕአድግን ለማደከም በመፈተኑ ኢሕአድግ በአንፃሩ ኢሕአፓ እስካልነካኝ ምን አደረገኝ የጋራ ጠላታችን የሆነዉን ማጥቃት ይሻላል:: ልዩነታችን በክብ ጠረጴዛ እንፈታወለን ሲል የነበረ እስክ አሁንዋ ሰዓት ኢሕአፓ በኢሕአድግ የጦርነት አዋጅ ስላወጀበት ኢሕአፓ አሁን ላለዉ ሁኔታ ደረሰዋል::

ኢሕአፓ ሌላው ትልቅ ነገር ያጣው ኢሕአድግን ለማጥቃት ብሎ በከፈተው ጦሩነት ትልልቅ መሪዎቹ አጥተዋል:: አብዛኛወቹ ትልልቅ መሪወቹ ከስዳን ገብተው በዛ አካባቢ ስለነበሩ ኢሕአድግ በአንዱ ደርግን አይየተዋጋ በሌላው ከኢሕአፓ ጦር እየተፋለመ የኢሕአፓ መሪዎች ያሉበት ቦታ ገብቶ እንደ በግ ከዛ ጭካ እየጎተተ አውጥቶ እስከአሁን እዚህ ገቡ አይባሉም:: መሪወቹ ጥቂት የሚባሉ አደለሙ:: ከሳላስ እስከ ሀምሳ ትልልቅ መስራች ከሚባሉት ሰዎች ናቸው:: አሁን አለን የሚሉት የነሱ ተሚሪዎች ናቸው::

ኢሕአፓ ይህችን የፖለቲካ ቁማር ምንነቱ ስለምታጋልጠው በምድረክ ብዙ አይጨሁባትም:: በጣም ጢቂት ጊዜ በሬድዮው ስማቸው ጠርተዋል:: ኢሕአድግም ይችንን ተንኮል ስለሚይውቅ የሀው 16 ዓመት ምንም ሳይተነፍስ ፀጥ ብሎዋል:: ሰዎቹ የት እንዳሉ ፈጣሪ እና የተወሰኑ የኢሕአድግ ባለስልጣኖች ብቻ ናቸው የሚያውቁ::

ኢሕአፓ እኔ ታላቃቹ ነኝ አክብሩኝ; ያልካቹ ስሙ እያለ በቁሙ ያረጀ እና የተቀበረ ድርጂት ነው::
ስደት1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 459
Joined: Sun Jul 18, 2004 9:51 pm

Postby ወጥመድ » Mon Jan 23, 2006 3:48 pm

ስደት!!

አሁንስ ጃጀህ::

የዚህ ሰሞን ዘፈናችሁ ደግሞ አላፊ አግዳሚውን ኢሕአፓ ነው ሆኗል::
ታዲያ ምን ይጠበስ?

ባይገባህ ነው እንጂ ኢሕአፓ ዎች እኮ ወንድሞቻችን ነበሩ:: አሁንም ናቸው::

በኢትዮጵያ ታሪክ ወስጥ እንደ ወያኔ ድርጅት ሀገር ቆርሶ ከመስጠት በላይ ምን የሚያሳፍር ነገር አለ?

የኢሕአፓ ትልቁ ስህተት የነበረው ትግሬዎችን አምኖ ትግራይ ውስጥ መግባቱ ነበር::

አሲንባ ላይ ላፈሰሳችሁት ደምና ላጠፋችሁት ሕይወት የደስታ መግለጫ ኃውልት መቀሌ ላይ አቆማችሁ::

አሁን ግን ጫወታው መልኩን የቀየረ ይመስለኛል::

ወጥመድ
ወጥመድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Fri Mar 11, 2005 1:52 pm
Location: Semen Walta

Postby አቡኑ » Mon Jan 23, 2006 4:20 pm

አይ ሰደት ጥሩ የፖለቲካ ተኝታኝ ነህ ግን ምንም የማታወቅ ልክ እንደ ፓሮት የሰማህዉንና የተነገረህን ብቻ ደግማህ ታወራለ :roll:
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጂቶች ከዛላቂ ጥቅም ይልቅ በጊዚያዊ ጥቅም የሚንቀሳቀሱ ናቸው ለማለት የሚቻልበት አገር ነው ያለነው :: እንደተፈለገውን ባይሆንም አንዳደቹ በሂደት ራሳቸውን እያስተካከሉ የሚሄዱ እንዳሉ ሁሉ ሌለቹ ደግሞ እንደ ተቸከለ እንጨት ራሳቸው ይትም አይንቀሳቀሱም ሌለውንም እያሰናከሉ ይገኛሉ ::

አብዛኛወቹ አገር ከመግንባት ይልቅ አንዱን አንዱን እንዴት አድርጊ ልጣለው እያሉ ማኖቆ ሲያበጁ ኑረዋል አሁንም ይገኛሉ :: ለስሙ ለአገር ሀብት እና አንድነት ተቆርቃሪ መስለው ቢቀርቡም በትግባር ግን ሁሉም ሙሾ ናቸው ::

አንዱን አንዱን ለመጣል በሚያደርገው ንትርክ በማሕበረሰቡ ሂወት ምን ያህል ተፅኖ ያመጣል የሚለዉን ቢቀር እካ በራሳቸው ሂደት እና በሌለቹ የፖለቲካ ታሪክ ሊማሩ ያላቻሉ ናቸው ::
እንግዲህ እዚህ ላይ የምንመለከተዉ የናንተን ማንነት ይሆናል በዚህ ሽኩቻ ዉስጥ ከፍ ያለዉን ሚና የተጫወተዉ ህውሀት እንጂ ሊሎቹ እንዳልሆኑ ታሪክ ይመሰክራል እዉነት እኮ አይሞትም

በሁለተኛ ደርጃ ደሞ


እነማን? ቅንጀቶች? እንግዲህ ለመረዳት ከፈለግህ ይሂ አመለካከት ያዉ የወያኒ እንጂ የማንም አይደለም ሆኖም አያዉቅ ህዝበ እርቅ ይደረግ ተስማምተን እንስራ ባሉ እኮ ነዉ ስብስባችሁ ውህኒ የጣላችሀቸዉ ልጆቻቸዉንና ሚስቶቻቸዉን ባልሰለጠነ አዉሪ በጠራራ ጸሀይ የደፋችሁት በደማቸዉ እጃችሁን የታጠባችሁት ስራ ፈት ቦዘኒ ሞተ ብላችሁ የተዛበታችሁት ተለጣፊ ደርጅቶችን ፈጥራችሁ እኮ ነዉ ዛሪም በህይወት አለን ለማለት የምትሞክሩት ታድያ አንድነት በዚህ ይመጣል?

ኢሕአፓ እና ሕዋሓትም ቢሆኑም ያደረጉት የሀው ተመሳሳይ ነው :: ይባስ ብሎ ኢሕአፓ ቤዙን አሲንባ እኒዲያጣ ምክንያት ሁኖታል ::

እነ ኢሕአፓ ሚኤሶ እና ሌለቹ ድርጂቶች ባደረጉት የተሳሳተ አካየደ ብዙ ወጣቶች በደርግ ቀይ ሽብር እንዲረሸኑ ተደርገዋል :: አብዛኛው ወደ ስደት ዓለም ያመራው በዚያ ሰዓት ነበር ::

ደሞ ሰለ ትግራይ ማኒፊስቶ ለትነግረን አትሞክር እዚህ ህጻን የለም ሁሉም ቢያንስ ማንበብ መጻፍ ይችላል

በዚያ ሰዓት በየክልሉ የቢሄር ቢሄረሰቦች ስም በማንገብ የፖለቲካ ድርጂቶች የሚፈሉበት ወቅት ነበር :: ሕዋሓት አንሳሱ ለትግራይ ቢሆንም የኛ መብት ከተጠበቀልን የሌላዉን ቢሄር ቢሄረሰብ መብት ከተጠበቀ ሁላችንም ጭቁኖች ከሆነ አብረን ትልቅ ኢትዮጵያ የማንገነባበት ምክንያት የለም በሚል ትግራይን ለመገንጠል የነበረዉን ዓላማ እርግፍ አድርጎ ራሱን ዓብነት ልሁን ብሎ ብ 1975 ወሰነ :: What does the TPLF 1976 manifesto state in its principles for its fight for the greater tigray?

The manifesto of the TPLF on 'Republic of Greater Tigray'
The new map of Tigray is based on the 1976 TPLF (*) manifesto, which defined who a Tigrayan is, the land that the TPLF considers of Tigray, and the final destination of the TPLF. The following comprises some important contents of the manifesto.
· A Tigrayan is defined as anybody that speaks the language of Tigrinya including those who live outside Tigray, the Kunamas, the Sahos, the Afar and the Taltal, the Agew, and the Welkait.
· The geographic boundaries of Tigray extend to the borders of the Sudan including the lands of Humera and Welkait from the region of Begemidir in Ethiopia, the land defined by Alewuha which extends down to the regions of Wollo and including Alamata, Ashengie, and Kobo, and finally the lands of Eritrean Kunama which includes Badme, the Saho (close to the conflicting area of Zala Ambessa) and Afar lands including Assab.
· The final goal of the TPLF is to secede from Ethiopia as an independent 'Republic of Greater Tigray' by liberating the lands and peoples of Tigray

የትኛዉ ነዉ ኢሀዲግ የቅጥረኛዉ ስብስብ ስም ለማዉጣትማ ቀላል ነዉ ትልቁና ትንሹ ወያኒ ብትለዉ አይቀልህም ለመሆኑ የት ቦታ ነዉ አንድ ኢርተአዊ ያማራ ፓርቲ ሀላፊ የሚሆነዉ እንደነ በረከት
እነ ተራ ወታደር አባዱላም ዱላ ራስ ---- ምርኮኛ ነዉ ወንድሞቹን ከጀርባ በጥይት የሚመታ የዉስጥ አርበኛ ታዲያ የትኞቹ እነ ታምራት ለምንም ያልታደለ ከንቱ ሊባ እህ እነማን?
ኢሕአድግ ከሁለት ድርጂት ወደ አራት ሕብረት ድርጂት ተሻግሮ ክንዱን አጠናክሮ ደርግን ወደ ግባአተ ወድር ይዞ እየሄደ ባለ ወቅት በዘመቻ ቴድሮስ ጊዚያዊ ጥቅምን ፍለጋ ድርግና ኢሕአፓ ውስጣዊ ስምምነት አርገው ኢሕአድግን ከጀርባው ወጥተው የጀርባ አጥንቱን ሊመቱ መኮሩ ::

ሰለዚህ ሰለ አስተያየትህ እነመሰግናለን ግን ተነቃቅተናል
አቡኑ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 907
Joined: Tue Oct 11, 2005 7:42 pm
Location: Mars

Postby ስደት1 » Thu Jan 26, 2006 12:20 am

ኢሕአድግ ሁሉንም ዘመቻዎች ኣጠቃሎ በስተመጨረሻ በዘመቻ "ዋለልኝ" አዲስ አበባ እና አካባቢዋ በቀለበት አስገብቶ ሊገባ ሲሰናዳ ነብሳቸው ይማራቸው የሁለተኛው ክፍለጦር ለበርካታ ዓመታት ሲመራ የነበሩ ኮነሬል በስተመጨረሻው ፕሬዝዳንቱ የሆኑት "ልዩነታችን በክብ ጠረጴዛ እንድንፈታው ጤሬ አቀርባለሁኝ" አሉ:: "ጂብ ከሄደ ውሻ ጮሆ" ሆነ ነገሩ እንጂ::

የሆነ ሁኖ ማንም ከጠበቀው በላይ አዲስ አበባ በሰላም በኢሕአድግ ቁጥጥር ስር ሆነች::
ኢሕአድግ ሁሉንም ተጋፍጬ ብቻየ ደርግን ስለደመሰስኩ ብቻየ ስልጣን ሊያዝ አላለም:: ኢሕአፓም ሳይቀር የጦርነት አዋጅ ሰርዞ ሊገባ ይችላል እስከሚባል ተለምኖ ነበር:: ኢሕአድግ ይህንን ስራ በመስራቱ በታራኪ ትልቅ ስፍራ የሚያስይዘው ስራ ሰርተዋል::

በዚያ ሰዓት የአዲስ አበባ ሕዝብ እና ሌላው ክልል ኢሕአድግ በመግባቱ በተለያየ መልኩ ደስታው ገልፀዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በውጪ ያለው ሕዝብ በሦወስት ተከፋፍሎ ነበር:: :lol: :lol: ደስታኛ; 8) 8) ተመልካች (ሁኔታው የሚያጣራ) :evil: :evil: ይህ አካል ለምን ገባ ብሎ አካኪ ዘራፍ ያለው ነው::

ሁሉም የራሳቸው ጎጂም ጠቃሚም ሊኖራቸው ይችላል:: ከሁሉም የተሳሳተው አሁንም ከሁደት ሊማር ያልቻለው ከመጀመሪያው የተቃወሞው ክፍል ነው:: አንድ ጊዜ ስለጠላሁት ሌላጊዜም ላየው አልፈልግም ብሎ ልቡን በጠላትነት የመረዘ አካል ነው::

አንድ ነገር ግን አለ ሁሌ የከንቱ እሪ ጭሆት ነው የሚያሰሙ:: እስከአሁን ምንም ፋይዳ አልባ ራስ ወዳድ የሆኑ በሰዎች ደም እና ኣጥንት ተሸጋግሮው ስልጣን የሚያፈነፍኑ ናቸው::

ውደ ላይ ልመለስ እና በሽግግር መንግስቱ የነበሩ ድሪጅቶች እንደተፈለገው ሊቀጥሉ አለመቻላቸው ነበር:: ዋናው በኢትዮጵያ ለውጥ ሊያመጣ እና ኢሕአድግን በተጠንካራነቱን ይወዳደረዋል የተባለው ኦነግ ራሱ ማኖቆ ማበጀቱ ነበር:: ደርግ ለመጣል ትልቅ ቦታ ከነበራቸው ድርጂቶች በበለጠ 12 ወንበር የተሰጠው ድርጂት ነበር::

ኦነግ በብዙ አካባቢዎች በተለይ በበደኖ በፈፀመዎ አሰቃቂ የጅምላ ጪፍጨፋ መጀመሪያ አላደረኩም ቢልም ኃላ ያመነበት ዋናው ከጨዋታ መይዳው ያባረረው ነበር:: ኢሕአድግ ለሁለተኛ ጊዜ ታሪክ የሰራበት ሰዓት በዚህ ነበር:: ይሆዉም የኦነግ ባለስልጣኖች ያንን የመሰለ መንጀል ፈፅመው ሳይበቃ ከሃያ (20) ሺ በላይ የታጠቀ ወታደር በመንግስት ጦርነት እንዲዘምት አውጆው ባለስልጣኖቹ በቦሌ እንዲወጡ ነበር ያረገው::

ያን ጊዜ ኢሕአድግ አሳማኝ ማስረጃ ስላለው ሊያስራቸው በቻለ ነበር:: ሆኖም ግን ኦነግ ከስተቱ ይመለሳል በሚል እና በርካታ ጠንካራ ድርጂቶች በአንድ አገር መኖር ለዲሞክራሲ ማበብ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው በሚል ነበር:: ቀጥታም ይሁን ተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ አሁን ላለቸው ሁኔታ ኦነግ ተጠያቂ ነው:: እሱ ቢኖር ንሮ እስስቶች ሊፈጠሩ ባልቻሉ ነበር:: ኢሕአድግም አያቀላፋም ነበር::
ስደት1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 459
Joined: Sun Jul 18, 2004 9:51 pm

Postby አቡኑ » Thu Jan 26, 2006 9:36 pm

አረ ለመሆኑ የት ነዉ ይህን ሁሉ የተማርከዉ ቀላማጅ ወያኒ ስማ አይደለም ሊሎቹን ድርጀቶች( ፓርቲዎች ) ወያኒ እኮ ያራሱን አብሮ አደጎች የበላ የወንጀለኛ ጥርቅም ነዉ ይሂን ጊዚ ሲደርስ ሀቁ ይወጣል ደሞ ልንገርህ አይደለም መለስና ግሩፑ ለማንም የማይተኙ መሆናቸዉንም ይግባህ

አዲስ አበባ ስለመግባቱ ጉዳይ ማንም በደስታ የተቀበላችሁ የለም እንደ ተናካሽ አዉሪ ነገሩ ሁሉ ግራ ገብቷችሁ ስትንገላወዱ እንደነበርም አስታወስ
አቡኑ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 907
Joined: Tue Oct 11, 2005 7:42 pm
Location: Mars

Postby ስደት1 » Sun Feb 05, 2006 5:52 pm

የጊዜው ተቃዋሚ ደጅቶች ነን ባዮች::

የኢትዮጵይ ሕዝብ ለበርካታ ዓመታት የገነበው ዲሞክራሲ ሂደት ሊቀለብሱት የሚጣጣሩት መነሻቸው ሲታይ ለስልጣን ፍላጎታቸው ሊያሰኩ እንጂ ለሕዝብ እንዳልሆነ ግልፅ ነው::

1997 የነበረው ቅንጂት ነኝ ባዩ የአመራር ሰዎች እነማናቸው ብለን ውስጥን ብናይ የአንዱ ሰው ብቻ ብንይ ራሱ ስንት ጉድ አለ::

ፕረፌሰር መስፍን ወለደየስ በራሳቸው የማይተማመኑ ራሳቸው ለሌላ የሸጡ ማንነታቸው የማይተወቁ ወፍ ዘራሽ ናቸው ለማለት ይቻላል::

አንድ ግዜ ስለ ፕረፌሰሩ ወይን ጋዜጣ የሚከተለዉን ለሕዝብ አስነብበዋል:-
http://eprdforgans.org/woyin/Woyin_PDF/ ... yin663.pdfፕረፌሰሩ በደርግ ጊዜ የኃላ አዚሪት በመሆን ሕዝብ ያስጨረሱ ወንጀላኛ ናቸው:: 60 ሚንስተረቹ የማስገደል እና ሌላው መጨፍጨፍ የሳቸው እጅ እንዳለበት ኮ/ሌ መንግስቱ ኃይለማራም ምስክርነታቸው ሰጥጠዋል:: በደርግ ጊዜ ስልጣን ላይ ለመውጣት ያላደረጉት ሙኮራ አልነበረም:: በስተመጨራሻ ደርግ ጥሎልኝ ይህዳል በሚል ተስፋ በሄሕዝባዊ ሾንጎ ማዚያ 1983 "የአደራ መንግስት ይቃቃም" ብለው ፍላጎታቸው በዳጋህድ አውጥቶው ነበር:: ደርግ ግን ኃሳባቸው ችላ በማለት የሞት ሽረት ቢያደርግም በስተመጨረሻው የሁሉም ኃሳብ ለጊዜው ቢሆንም አፈር ለብሶ ነበር:: ዛሬ ስማቸው እና ልብሳቸው ቀይረው መጥተዋል::

ፕረፈሰሩ ሕዝብን እንዳላልጨረሱ እና እንዳላስጨፈጨፉ ሁሉ ሰብኣዊ መብት የሚባል ድርጂት አቃቃሙ:: የሕዝብ አለኝታ ነኝ ብለው ቀረቡ:: መንግስቱ ኃይለማራም መስራቹ እና መሪው ሲሰሙ ይህም ሰብኣው መብት አውቆ አቃቆመ ብለው ተገርመዋል:: ምክንያቱም የመንግስቱ የኃላ አዛዥ ስለነበሩ:: ይተዋወቃሉ እና::

የሆነ ሆኖ ፕረፈሰሩ የፈለጉት ነገር ለህዝቡ ሌላ ሰው ሁኖው ለምቅረብ እንጂ ሌላ ዓላማ አልነበቸውም:: ይህም ጊዜው ደርሰዋል ባሉት ሰብኣዊ መብቱን ትተው ወደ ድረው ፖለቲካቸው ገቡ:: የቅንጅት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ዋና አሽከርካሪዎች ከሆኑ ሰዎች አንዱ ሊሆኑ ቻሉ:: የለመደች ጦጣ እንደሚባለው ፕረፈሰሩ በደርግ የለመዱትን ውንጅል አሁንም በሕዝቡ ላይ አዘነቡት:: ሰው አድጎ ካለፈው ስተቱ እንደመማር ይልቅ እኝህ ሰው በእድሚያቸው እና በሙያቸው እንቱ እንዳይባሉ ራሳቸውን እንደጨርቅ ያቀለሉ ያዋቂ አላዋቂ የሆኑ ሰው ናቸው::

ቅንጅት የሚባለው ድርጂቶች እንዲህ ያሉ ሰዎች ናቸው የሚመሩት ያሉት:: ድርጂቶቹ አንባገነንታቸው በሌላ ማሳረፍ ብቻ ሳይሆን በራሳቸው ጭምርም ነው:: አሁን ቅንጅት በውጭ የሞት ሽረት እይተፈራገጥ ቢገኝም በአገር ውስጥ ግን በድንም አፈር ብልቶት ወደ ተረት ተረት ተቀይረዋል:: ለዚህም ማስረጃው ቅንጂት የሚባል ሕጋዊ ድርጂ በኢትዮጵያ ውስጥ የለም:: የነበርቱም ራስ በራሳቸው ተከፋፍለው አንዱን አንዱን እያጠፋው ይገኛል:: አራት የተባሉ ሕጋዊ ሕብረት የላቸውም:: በሂደትም አንዱ ራሱን ከአንባገነኖች ጋር አብሬ ልሰራ አልችልም ብሎ ራሱን አገለዋል:: የቀርቱም በገኙት መንገድ እየተንከራፉ, እየዋዠቁ, ገደል እየገቡ እረ ምን ያልሆኑት አለ:: እነዚህም የኔ ወጎኖች ናቸው ብሎ የሚያስጠይቅ ነው:: የሚያሳፈሩ ወገኖች::

በውጪ ያሉ አሁን ምን እንደሚውጣቸው እንጃ:: አሁን ቅንጂት በመባል ለምርችጫ ከተወዳደረው ከጋኘው 109 ወንበር ከ85 በላይ በፓርላማ ገብተው ይገኛሉ:: የቀሩት በሰሩቱ ወንጅል ወህኒ ቤት የሚገኙት ናቸው::

ቅንጅት እንደ ቅንጅት ግን ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታውች ካልተማሉልኝ ፓርላማ ሆነ አዲስ አበባን አልቀበልም ብሎ አሻፈረኝ ብሎ ነበር:: አሁን ግን ተጨባጭ ያለው ሁኔታ ሌላ ነው:: ይህ ማለት ቅንጅት እንደከሰመ ራሱን እዉን ያደረገ ድርጂት ነው::
አሁን በየቦታው እሪ በከንቱ ማለት ጥቅሙ ምንድ ነው :?: :?: ውኃ ከፈሰሰ አይታፈስም ይላሉ አቦቶቻችን::

ቅንጅት ራሱን ከሕዝብ ጋር አዋሕዶ በሪሞል ኮንትሮል ከመቆጣጠርት ነፃ ቢያደርግ ንሮ ዛሬ በኢትዮጵያ ሌላ ገፀታ በነበረው:: በውስጡም ያከተታቸው ሰዎች ራሳቸውን ንፁህ አድርገው ሌላ ዓላማ አንግበው ቢመጡ ንረው ለኢትይጵያ እድግት መፋጠን ትልቅ ድርሻ ይኖራቸው ነበር::

አሁን ባትሪ የሌለው እና ለቆጣጠረው የማይችል ሮሞት ኮንትረል ተይዞ በየ ፓርላመንቱ እና ውጪ ጉዳይ ምኒስተር መጮሁ የትም አያደርስም:: ይህንንም እያየነው ነው:: መንግስት በ12 ወራት ይሰራል ያለው በ6 ወር እያገባደደው ይገኛል::

በሞቀ ቦታ ተሁኖ ራሳቸውን እያማረጡ እየበሉ ልጆቻቸውን በሰላም አያስተማሩ ሌላው እንዳያልፈለት ከሩቅ ሁነው ንፁሕ ውኃ የሚበክሉት ውኃው ሌሎቹን እንዳሰመጠ ሁሉ ቀሪዎቹም እንደሚያሰምጥቸው ካለፉት ታሪካችን እይተናል::

ኢትይጵያ በኢኮነሚዋ ከምንግዜም በላይ በተሻለ ሁኔታ ትገኛለች:: ይህ ግርግር ባይኖር የበለጠ ይሰራ እንደነበር ግን ግልፅ ነው::
ስደት1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 459
Joined: Sun Jul 18, 2004 9:51 pm

Postby ስደት1 » Thu Feb 09, 2006 9:35 pm

የአማራ አንድነት የሚል ድህረ ገፅ ስለ አሁኑ ተቃዋሚዎች ለንባብ ያበቃው::


እነገብሩ አሥራት ከመጀመሪያው ጀምሮ ከፍተኛ የወያኔ አመራር አባል ሆነው ሠርተዋል። አሁንም ከመለስ ጋር ተጣልተው ከሥልጣን ይባረሩ እንጅ ያው እንደጥንቱ ወያኔ ናቸው። ወያኔ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በወሰዳቸው ውሳኔዎች በሙሉ ተካፍለዋል። የወያኔ ውሳኔዎች በሙሉ በጋራ የተወሰኑ እንጅ የመለስ ዜናዊ ብቻ አይደሉም።
ነጋሶ ጊዳዳን በተመለከተ ቀደም ካለው ታሪኩ ሥንነሳ ይህን ግለሰብ የምናውቀው ሻዕቢያ እንዳደረገው ሁሉ የተማሪውን እንቅስቃሴ ተጠግቶ የኦሮሞ ሕዝብ እንዲገነጠል ለማድረግ ሲታገል እንጅ በኢትዮጵያ አንድነት አይደለም። ከተማሪው እንቅስቃሴ ጀምሮ ሲያወሩ ያወራል እንጅ ሥለኦሮሞም ቢሆን ታሪኩን በሚገባ እንደማያውቅ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ኦሮሞ የኢትዮጵያን ምድር ከመረገጡ ቀደም ብሎ አሁን ኦሮሞ የሚኖርበት መሬት ላይ የትኞቹ ጎሣዎች ይኖሩ እንደነበር፣ ኦሮሞ ከየት እንደመጣ፣ መቼ እንደመጣ፣ እንዴት እንደመጣ፣ እንዴት እሥከራያና አዘቦ እንደሄደ፣ አንፊሎ የሚባለውን ጎሣ እንኳን እንዴት ኦሮሞ እንደዋጠው፣ ጋፋቶችን ምን እንዳደረገ ማጣፊያ የለውም። ከጭፍን ጥላቻና ቅናት በሥተቀር ታሪክን በአግባቡ ያልተገነዘበና ያልተረዳ ከመሆኑ የተነሣ "ይች አማራ አንገቷን ቀና ማድረግ ጀመረች" ብሎ ከመፎከርም አልፎ " ምኒልክ ጡት ቆርጧል" ያለ ነው።አሁን ኦሮሞ የሚኖርበት መሬት ኦሮሞ ኢትዮጵያን ከመረገጡ በፊት የአማራው፣ የአንፊሎው፣ የጋፋቱ፣ የህዲያው፣ የከምባታው ወዘተ.. መሆኑ ተዘንግቶ "በኋላ የመጣ አይን አወጣ" እንደሚባለው ኦሮሚያ የሰፋሪዎች (አማራ) ቅኝ ግዛት እንደሆነችና ሰፋሪዎች መሬቱንና ሥልጣኑን ለኦሮሞ ማስረከብ አለባቸው እያለ ሲሰብክ የኖረና የኢትዮጵያን አንድነት ሲንዱ ከነበሩት ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ ከሆኑት "የጥቁር ነጮች" አንዱ ነው።


ይቀጥላል
Last edited by ስደት1 on Thu Feb 09, 2006 9:56 pm, edited 2 times in total.
ስደት1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 459
Joined: Sun Jul 18, 2004 9:51 pm

Postby ስደት1 » Thu Feb 09, 2006 9:36 pm

የአማራ አንድነት የሚል ድህረ ገፅ ስለ አሁኑ ተቃዋሚዎች ለንባብ ያበቃው::


በአንድ ወቅት አንድ አፍሪቃዊ ጋዜጠኛ "ኢትዮጵያዊያን ማሰብ አቁመዋል" ሲል ያሥነበበን ትውሥ አለን። ከባድ አነጋገር ነው። የማገናዘብ ችሎታ ላለው ሠው የጋዜጠኛውን አባባል የሚያጠናክሩ ብዙ ማሥረጃዎችን ማግኘት እንደሚቺል አንጠራጠርም። ማሰብ አላቆምንም ብለን መሟገት ባንችልም ማሰብ ማቆማችንን የሚያሳዩና የሚያመላክቱ ብዙ ምልክቶች ተከስተዋል። የሚታረስ መሬት እያለን በርሃብ መርገፋችንና ከአርባ ዓመት በላይ በለማኝነት መኖራችን ራሱን የቻለ አንድ አብይ ማሥረጃ ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያ በተደረው ሰላማዊ ሰልፍ የተከሰተው ቲያትርም ካለፉት ሥህተቶች መማር አቅቶን ከውድቀት ላይ ውድቀት ተደራርቦ የባሰ ረግረግ ውስጥ መዘፈቃችንን ነው። ይህም የጤንነት ምልክት አይደለም። ማስብ ማቆማችንን ከሚያሳዩት ምልክቶች አንዱ ነው። ዓለም ከአለፈው ታሪክ እየተማረ ወደፊት ሲገሠግስ እኛ የኋሊት የምንሄደው እሥከመቼ ይሆን? የተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ። አንድነቶች ተመሰረቱ ሲባል ብዙ ጊዜ ሰማን። ምን እንደሰሩ ሳናውቅ እንደብርጭቆ እርስ በርሳቸው ተጋጭተው በመሰባበር ከሰሙ። ብዙ ቢወራላቸውም የምናውቀው የውሃ ሽታ ሆነው መቅረታቸውን ነው። የተቃዋሚዎች አንድነት መፍጠር አገራችን ያለባትን ግዙፍ ችግር ለመፍታት የሚደረግ ግብግብ መሆኑ ቀርቶ ትርጉም የሌለው የአገር ማፍረሽያ ፋሺን መሆን ከጀመረ ውሎ አድሯል። የኢትዮጵያን ሕዝብ የሃሰት ተስፋ እየሰጡ በስሜቱ፣ በብሶቱና በህሊናው መጫወት ባህል ሆነ። ምስኪኑ ሕዝባችንም ያስተማራቸው ልጆቹ እንደሱ ቀናዎች፣ ባለወኔ አገር ወዳዶች ሥለመሠሉትና በዚህም ሣቢያ የተስፋ ጭላጭል ያየ እየመሰለው አምኖ የተከተለበትና የደገፈበት ወቅት ነበር። የተያዘው ግን በእርሱ ላይ ማሾፍና መነገድ መሆኑ ቢገባውም ለመቀበል አዳግቶት ኖሯል። ሙያችን ዓላማን ተከትሎ መታገል ሳይሆን ሆ! ብሎ መዝመም ብቻ ሆነ። የተቃዋሚዎች ድርጅት ተፈጠረ፣ የአንድነት ፓርቲ ተመሰረተ፣ ወዘተ.. ሲባል ሆ ብለን እንወጣለን። ወሬው ይደራል። መንፈቅ ሳይሞላው ሁሉም ፈራርሷል። ሁሉም ተረስቷል። እንዴት እንጓዝ ዓላማችንስ ምንድን ነው አይባልም። በባዶ ሜዳና በሆያ ሆዬ ከችግር ላይ ችግር እየጨመሩ ችግር እንደሚቃለል ሲነግሩን በጥሞና እናዳምጣለን። አፍ ያላቸውና በማደናገር የተካኑ ሲያዘናጉን ዘመናት አለፉ። ድህነታችንና ችግራችን ብሎም መዋረዳችን ግን እየባሰና እየከፋ መጣ።

አሁንም በቅርብ የቅንጅቶች ቅንጅት ተብሎ ሰልፍ ተጠራ። መልዕክቱን በሚገባ ያልተረዳው ሕዝባችን ጥሪውን በመቀበል የሰልፉ ተካፋይ ሆኗል። በዚህ ሰልፍ ላይ የአዘጋጅ ኮሚቴ ተብየው በወያኔ ውስጥ ከመለስ ጋር ሆነው ኤርትራን ያሥገነጠሉትን እነገብሩን በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ሥር ተቃዋሚውን የሚያዘናጋና የሚያለዝብ ንግግር እንዲያሠሙ አቅርቧቸዋል። እነገብሩ በመለስ ከሥልጣን የተባረሩበት ዋናው ምክንያት መለስ ለኤርትራና ለትግሬ አንድነት እቆማለሁ ሲል እነርሱ ለኤርትራ ሳይሆን ለትግሬ የበላይነት ብቻ እንቆማለን በማለታቸው መሆኑን ማንኛውም አገር ወዳድ ሊያጤነው ይገባል። በዚህ የንግግር መድረክ ላይ አሸናፊው የእነገብሩ ቡድን ነው። አሁንም እንደጥንቱ የእነገብሩ አመጣጥ የኢትዮጵያ አንድነት ተቆርቋሪ ነኝ የሚለውን ተቃዋሚ ኃይል " ዱሮም አጅበህ ሥልጣን ላይ እንዳወጣኸን ሁሉ ዛሬም በእኛ አመራር እንደልማድህ አጅበህ ሥልጣን ላይ አውጣን" ለማለት ነበር። ይህም ግቡን መቶላቸዋል። በተቃዋሚው ጎራ ውስጥ ነን የሚሉትም እንደ እነልደቱ አያሌው ዓይነቱም በራዲዮ ቃለ ምልልሳቸው የእነገብሩን ንግግር ከመጠን በላይ አጋነው በማቅረብና በማድነቅ ይባስ ብለው ሕዝቡን ውዥንብር ውስጥ ሲከቱት ተደምጠዋል።


ይቀጥላል
ስደት1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 459
Joined: Sun Jul 18, 2004 9:51 pm

Postby ስደት1 » Thu Feb 09, 2006 9:41 pm

የአማራ አንድነት የሚል ድህረ ገፅ ስለ አሁኑ ተቃዋሚዎች ለንባብ ያበቃው :: የቀጠለ


የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረት ተብዬው ከተከፋፈለ በኋላ ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ የሚባል ሕብረት መፈጠሩ ይታወቃል። ይህ ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ የሚባል ሕብረት የብሄር ካህናትን ይዞ ባለመደራጀቱ ከኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረት ለየት ያደርገዋል። ለኢትዮጵያም አንድነት ቆሜያለሁ በማለቱ ሕዝቡ መደናገሩ አልቀረም። ስለሆነም በጠራው ስልፍ በርካታ ዜጎች ተገኝተዋል። ከአጀማመሩ የሰልፉ አዘጋጅ ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ እንደሆነ ይታወቃል። ሆኖም የሰልፉ ዕለት ሲቃረብ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረትም እንዳለበት በድንገት ለሕዝቡ መገለፁ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረት ሲያወግዛቸው ከነበሩት ድርጅቶች ጋር በተባባሪነት የተሰለፈበት ምክንያቱ ግልፅ ነው። ከእሥከዛሬው ተመክሯችን እንደምናውቀው ለኢትዮጵያ አንድነት አስቦ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት የደረሰበትን ሽንፈት፣ ውርደት፣ ኪሳራና የሕዝብ አመኔታ ማጣት ለማለዘብ፣ በማስመስል ለማደነጋገርና የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲን የበላይነት ለማርገብ ነበር።
ስደት1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 459
Joined: Sun Jul 18, 2004 9:51 pm

Postby ስደት1 » Thu Feb 09, 2006 10:21 pm

በአንዳንድ ቦታዎች የሚያለቅሱ ያሉ ሰዎች ለምን ሰልፍ እንደሚወጡ ሀቁ ሲገልፅ
የአማራ አንድነት የሚል ድህረ ገፅ ለንባብ ያበቃው::

ብዙዎቻችን ለምንና እንዴት እንደተሰደድን እናውቀዋለን። ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልገንም። ለህይወታችን በሚያሰጋ የፖለቲካ ተግባር ሳንካፈል የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ አግኝቶ በፈረንጅ አገር ለመኖር በፖለቲካ ንቁ ተሳት በማድረጋችን ለፍርድ የምንፈለግ መሆናችን ለማስረዳት ያልዳሰስነው ፖለቲካ፣ ያልዋሸነው ውሸት ካለመኖሩም ሌላ የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ምን ያህል አሰቃቂ እንደሆነ ፈቃድ ለሚሰጡን ባለስልጣናት መዘላበዳችን የማይካድ ነው። ፈቃድ ለማግኘት ፖለቲካን እንደምክንያት ማቅረብ አማራጭ የሌለው ነው::
ስደት1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 459
Joined: Sun Jul 18, 2004 9:51 pm

Postby ስደት1 » Sat Feb 11, 2006 4:18 pm

"ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም" አሉ አባቶች

በብረፌስር በየነ ጴጥሮስ ስለሚመሩት እና ተሳቢዎች::

ሕብረት ብውስጡ ብዙ ድርጂቶች ተሰበሳበው የመሰረቱ ድርጂት ነው:: የሕብረቱ አካያድ ስንያው ግን ከውጪ ትልቅ ስም ያለው ውስጡ ግን ባዶ የሆነ ቆፎ ነው:: እነዚህ ድርጂቶች ሕብረት ሲፈጥሩ አንደ ሕፃኖች ለሳምንት የሚያስኪይዳቸው እንጂ ለዜላቄታ ሊያስኪይዳቸው የሚችል አጃነዳ ቀድመው ያልቀሱ ያልቻሉ ናቸው::

እንሱ ይድርስ ይድረስ ባሉት ሕብረት ፈጥረው ዋናው ነገር ለግንቦት 7 ምርጫ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ እንጂ ከምርጫው በኃላ ብንሸነፍ እንዲት እንቀጥላለን ብለው ለስከንድም አላሰቡም::

ሕብረትም ሆኑ ቅንጅቶች በለስ ቀንታቸው በትረ ስልጣኑ ከያዙ ጥሩ ካልሆነ ግን ከተሸነፍን እንዴት ለኢትይጵያ የበኩላችን አስተዋፅኦ እንዳረግላን የሚለውን ግን ሊያስቡት አልፈለጉም:: እንደሚሸነፉ ግን ልባቸው ሙሉ በሙሉ ያውቃ ነበር::

ምርጫ በተደገረበተ ቀን ውደ ማታ የምርጫው ውጤት አንቀበለም ሙሉ ለሙሉ ተጭበርብረዋል ብለው ለቢቢሲ መግለጫ ሰጡ:: በነጋታው ጥዋትም አቃማቸውን ደገሙት:: ከሰዓት በኃላ ግን ምርጫ ቦርድ አዳስ አበባ ተቃዋሚዎች አሸናፋቹዋኃህል ሲላቸው ወድያው አቃማቸው ለውጡ:: ይህንን የሚያሳይን ነገር ከሁነታው ጋር የሚገላበጡ መሆናቸው ነው::

የሚጣራውም ተጣርቶ ዳግመ ምርጫ የሚደረግበትም ተደርጎ ሁሉ ከተጠናቀቀ በኃላ ፓርላማ እንግባ ወስይ አንግባ በሚለው ራሳቸውን ወደ ፈና ጣሉ::

ሕብረት በተስማሙት መስረት ዋና ቢሮው አገር ቤት ሁኖ ማናው መሪዎቹም እዚያው እንዲሆኑ ተውስኖ ስለነበር እነ ዶ/ር ሚራራ እና ፕረፌሰር በየነ የመራጣቸዉን የሕዝቡን ድምፅ ሊያከብሩ ፓርላማ ሊገቡ ሲወኑ ከኔ ከሞትኩ ስርዶ ኣይብቀል እንዳለቸ እንስሳዋ ውጪ ያሉት ተንሳፋፊዎች ድርጂቶች የሚከተለዉን ወሰኑ:-

«ዶ/ር በየነና ዶ/ር መረራ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል» የሕብረቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር በየነ ጴጥሮስና ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው የሕብረቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ይህን የወሰነው ባለፈው ሰኞ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሲሆን በምትካቸውም የሕብረቱ ም/ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ግርማ ሹምዬና ዋና ፀሐፊው አቶ ደረጀ ከበደ አጠቃላይ ምርጫ እስኪደረግ ፓርቲውን እንዲመሩ ተመርጠዋል።

ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ይህን የወሰነው ባለፈው ሰኞ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሲሆን በምትካቸውም የህብረቱ ም/ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ግርማ ሹምዬና ዋና ፀሀፊው አቶ ደረጀ ከበደ አጠቃላይ ምርጫ እስኪደረግ ፓርቲውን እንዲመሩ ተመርጠዋል።

ጉዳዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው ዶ/ር መረራ ጉዲና «ውሳኔው የተወሰደው ኮንግረሱም ሆነ የደቡብ ህብረት ባልተካፈለበት ነው» በማለት ውሳኔው ውጤት አልባ መሆኑን ጠቅሰው «እንዲያውም ይህ አካሄድ ማንንም የማይጠቅምና ለኢህአዴግ መንገድ የሚከፍት ነው» ብለዋል። የሥራ አስፈፃሚውን ተግባር «ባዶ ጫጫታ» ያሉት ዶ/ር መረራ «ፓርላማ መግባታችን እንዳስከፋቸው ብናውቅም የወከልነው በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ የሚፈልገውን ነገርና የተነሳንለትን አላማ ከዳር ለማድረስ ከመቶ ሺህ በላይ አባሎቻችን በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም ታሳቢ አድርገን ነው» ብለዋል። የአመለካከት ልዩነቶች ሲፈጠሩ ሁልጊዜ የተሻለውን አማራጭ መውሰድ ስለሚገባ የኮሚቴውን አባላት ብዙ ጊዜ ልንመክራቸው ሞክረናል ብለዋል። እነዚህ ወገኖች በተደጋጋሚ የሚያነሱት ህብረቱን በገንዘብ ሲረዱ መቆየታቸውን ቢሆንም እኛ ግን የንፁሃን ህይወት የጠፋበትን ትግልና የፈሰሰውን ደም በገንዘብ አንለውጠውም ህብረቱም ይቀጥላል በማለት ገልፀዋል።


ልዩነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ሂዶ ፕረፈሴር በየነ ጴጥሮስና ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና በሕብረት ስም ከሌላ ቦታ የሚወጡ መግለጫውቹ ድርጂቱን እንደማይወክል ባዶ ጫጫታ" በማለት አውግዞታል::

በስተመጨረሻ ሕብረት እንደ ሕብረት እንደማይቀጥል ጋሕድ ሆኖ አዲስ ድርጂት እንዲፈጠረ ሆነ::
አዲስ ህብረት የሚከተለው ይመስላል:-
http://www.ethiopianreporter.com/module ... e&sid=3047

በተለይ በውጪ የሚንጫጩ ያሉት የስራ ባልደርባቸው የነበሩት ዶ/ር ሚረራ ጉዲና የሚከተለዉን ብለዋል:: «ፓርላማ መግባታችን እንዳስከፋቸው ብናውቅም የወከልነው በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ የሚፈልገውን ነገርና የተነሳንለትን አላማ ከዳር ለማድረስ ከመቶ ሺህ በላይ አባሎቻችን በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም ታሳቢ አድርገን ነው»"
ስደት1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 459
Joined: Sun Jul 18, 2004 9:51 pm

Postby ዞብል2 » Sat Feb 11, 2006 5:31 pm

ወዲ_ስደት :P ወያኔ/ኢህአድግ የደም መጣጮችና የነፍሰ በላዎች ጥርቅም ነው :oops: :evil: :oops: :twisted:

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2285
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ስደት1 » Sat Feb 11, 2006 7:58 pm

ዞብል2 wrote:ወዲ_ስደት :P ወያኔ/ኢህአድግ የደም መጣጮችና የነፍሰ በላዎች ጥርቅም ነው :oops: :evil: :oops: :twisted:

ዞብል ከፒያሳ


የፈለከው የማለት ሙሉ መብት አለህ:: ተጨባጭ ሀቁ እንግዲህ ይህ ነው:: በኃይል አልግትህ
ተቃዋሞዎች ነን ባዮች በሚያደርጉት ራስ በራስ ማነቆ ማበጀት በኢሕአድግ ሊያስታክኩ ይመኩራሉ:: ዶ/ር መረራ ያሉትን ደጋግመህ ብታነበው ነገሩን ጥርት ይልልህ ነበር::
ስደት1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 459
Joined: Sun Jul 18, 2004 9:51 pm

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests