ሸዋ ባላመጠ.................

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሸዋ ባላመጠ.................

Postby ነቅንቄ » Tue Jan 24, 2006 12:18 am

ሰላም

ወያኔን ባለ በሌለ ሀይል ተጠቅሞ እንደማስወገድ የሰሞኑ የፖለቲከኞች አይነተኛ መሳርያ ይህ character assasinationየሚሉት ሲሆን ኢላማቸዉም በግንባር የተሰለፈዉን ሁሉ አንድባንድ በመደዳ ማጋደም ሆኖዋል.

በልደቱ አያሌው ላይ እየተካሄደ ያለው ቅስቀሳ እና ስም ማጥፋት ሁሉ ከዚህ ቀደም የተካሄዱትን ዘመቻዎች ሁሉ ከማስታወሱ በላይ ማነህ ባለሳምንት...... ብለን እንድንጠይቅ እየተገደድን ነው.

ልደቱ ጸረ-ወያኔ ትግሉ ያፈራው አንድ ወጣት ነው. ያዉም እጂግ ከፍተኛ ፖለቲካዊ --ኢኮኖሚያዊን ማህበራዊ ችግሮች ከተቆለሉበት የወሎ ክፍለሀገር የወጣ በመሆኑ ሀላፊነቱም ሆነ የተጣለበት አደራ ከፍተኛ መሆኑ አያጠያይቅም. የወጣበትን ህብረተሰብ እና ወግ እንዲሁም ልማድ ጠንቅቆ የሚያዉቀው ልደቱ ለምን የወቅቱ ኢላማ ሆነ ብሎ መጠየቅ እና ትንሽ ምርምር ያስፈልግ እንደሆን እንጂ ዛሬ በስም ማጥፋት ላይ የተሰማሩት ዝናናታሪክ እንዲሁም ማንነት ለህዝባችን እንግዳ አይደሉም.

ላለፉት አስራስንት አመታት በጸረ-ወያኔው ተጋድሎ የግንባር ስጋ አድርገው ሲጠቀሙበት ከቆዩ በሁዋላ ዛሬ እንደአሮጌ ቁና ሊወረዉሩት ፈልገው ይሆንን???

መንገድ የዘጋባቸው ወይም በመሰላሉ ላይ የመዉጣት እና የመዉረድ አባዜ ያላቸው ሊጠልፉት ፈልገው ይሆንን??

ለነገሩ ይህን ያህል የሚያሻፍድ እና የሚያቁዋምጥ ስልጣን ተገኝቶ ይሆንን???

በግንቦት ሰባት የተነጠቅነዉን ድምጽ መልስን የምንጭብጥበት ቀን እና ሰአት ተዳርሶ ይሆን???

የስልጣን ኮርቻዋ አምራና ደምቃ እያየናት ተጎምዥተን ይሆንን???

ለነገሩ ልደቱ ቢያንስ ቢያንስ በወሎ ህፍለሀገር ነዋሪዎች ላይ ያሳደረዉን ስሜት እና አለኝታነት ምንም አይነት ምድራዊ ሀይል አይነጥቀዉም.
ዛሬ የሸዋ የፖለቲካ መኩዋንንት እና መሳፍንት ልጆች እና የልጅ ልጆች ይህን "" ወሎየ"" ቀንድ ሊያስበቅሉት ብሎም ከፖለቲካው መድረክ ሊያገሉት የሚፍጨረጨሩት((አይሳካላቸዉም እንጂ..) ወያኔ ያበቃለት ስለመሰላቸው እና መራራው ትግል በድል አድራጊነት የተጠናቀቀ ስለለምሰላቸው ነው. ለዚህ ድል መብቃት ደግሞ እነልደቱን የመሳሰሉ ደፋሮች አቅማቸው በፈቀደ እና በመሰላቸው መንገድ ያበረከቱት አስተዋጾ ከእንግዲህ አላስፈላጊ ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅም ስላልሆነ በዘዴ እና በጊዜ ገለል ማድረጋቸው ነው.
ለዚህ ነው ሸዋ ባላመጠ ባመቱ ይዉጣል ያልኩት.

በቅንጂት ዙርያ ያለው የሸዋ ምሁር እና ስብስብ እንዲህ አይነቱን ተልካሻ አስተሳሰብ ማጥራት እና ሁሉን አቀፍ ትግል ለማድረግ ካልቻሉ"" መንገዱን ጨርቅ ያድርግላች ሁ........'' የሚባሉበት ጊዜ ሩቅ አይደለም.

ስለዚህ መጨው ትግል በአድዋ ምሁር እና በሸዋ ምሁር መካከል እንጂ በፍጹም መላ ሀገሪቱን እንደማይመለከት መግለጽ ያስፈልጋል. ሁለቱም ፈላጊና ተፈላላጊ አጥፊ እና ተጠፋፊ ስለሆኑ በራሳቸው ጊዜ አንድ መላ ይፈልጉ ካልሆነም እኛ ጪቁን ህዝቦች በፍጥነት አንድ መላ እንፈልግላቸዋለን.

በልደቱ ላይ እየተካሄደ ያለው ቅስቀሳ ያስታወሰኝ የሰገሌ ጦርነት ነው. የዚህ ጦርነት መንስ ኤ ሪጅናዊ ጥላቻና ንቀት እንዲሁም ከእኛ ወዲያ ላሳር የሚል ተእቢት እንደነበረ እናስታዉሳለን. የስልጣን ሽኩቻ.አገሪቱ ፈረሰች..ተበታተነች....... አንዱ ወገን አሳቢ እና ተቆርቁዋሪ ሌላው የክልል ሰው ደግሞ መሀይም እና ሀላፊነት የማይሰማው.

ዛሬም እያየን የምንመሰክረው ነገር ትናንሽ ተሰግሌ ጦርነትን ሲሆን ይህም ገና እጃችን ባልገባ ድል ተመጻድቀው እና ተኮፍሰው ነው.

ወያኔ ይህን የሪጅኖች አለመመጣጠን እና ልዩነት ለማጥበብ የተነሳ ሀይል መሆኑን ሲያበስር እጂግ አድርጎ የሚያቅለሸልሻቸው የሸዋ ልጆችን ሲሆን እኛን ግን እንዳልከፋን ሊታወቅ ይገባል. እንዲያዉም ከወያኔ የተሻለ ህብረብሄራዊ ሀይል መጥቶ ይህን መበላለጥ ማጥፋት ካልሻልን የሸዋ ምሁራን በእኛ ላይ የሚያሳዩት ትተቢት ማለቂያ ያለው አይመስለኝም.

የሸዋ ቢሮክራት እና ምሁር በየክፍለሀገሩ ጉቦ ,ሙስናን,ዝርፊያን የስራ መንዛዛትን አስፋፍቶ ብሩንም ጪኖ ወደቤቱ የሚመለስ ሆዳም እንጂ ለተመደበበት ክፍለሀገር ልማት እድገት አንዲትም ቀን አስቦ እና ተጨንቆ አያዉቅም.. ስለዚህ በነዚህ ሆዳሞች ልደቱ ቢሰደብ ክብደት አይኖረዉም.

በመላው አለም የምትገኙ የወሎ ክፍለሀገር ተወላጆች ይህን አዲስ የሸዋ ምሁራን የሻገተ የስም ማጥፋት ሴራ እንድታጋልጡት እጠይቃለሁ.

ነቅንቄ
ይቀጥላል
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Postby የዘመኑ ልሳን » Tue Jan 24, 2006 12:29 am

ወያኔዎች ምንም ስማችሁን ብትለዋውጡ በጭንቅላታችሁ ላይ የተተከውን ህዝብን በዘርና በጎማ የመከፋፈል ካንሰር በቀላሉ እናንተን ለመለየት ያስችለናል:: ዛሬ ደግሞ የወሎ የሸዋ ማለት ጀመራችሁ? ይህ የበሰበሰ የወያኔ የዘር ፖለቲካ ከህእገራችን ተነቅሎ ሊጠፋ ጥቂት ስለቀረው ከአሁን በኃላ ምንም ብትለፈልፉ እንደመዝናኛ እንጠቀምበታለን እንጂ እንደ ቁምነገር አናየውም:: ልደቱ የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ድምጽ ከሀዲ ብሎታል:: ከአሁን በኃላ ምንም ብትለፈልፉ የባንዳ ልጆች ባንዳን ቢደግፉ አይስደንቀንምና ግዜያጩን በከንቱ አታጥፉ::
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA

ተጋዳላይ ነቅንቄ የጎሳ ልክፍትህ አሁን ደግሞ አገረሸብህ

Postby ዲጎኔ » Tue Jan 24, 2006 12:33 am

ተጋዳላይ ነቅንቄ

አሁን ደግሞ የተጠናወተህ የጎሳ ልክፍትህ አምሀራ ኦሮሞ ቀርቶ ሸዋ ወሎ በማለት ያስገዝፍህ ጀመር? ጻ መንፈሰ ርኩስ ወከመ ጎሳዊ ልቀቅ!ልቀቅ!

የኢዴፓ-መድህን አባላት የትግል አጋሮቻቸው ያለፍትህ ቃሊቲ ተጠፍንገው ስልጣን ከወያኔ ጋር ለመጋራት የቁዋመጡት በመሪው በዶ/ር አድማሱ ገበየሁ አመራር ከቅንጅት የተለየ ኢዴፓ መድህን እንደማይኖር መሪዎች ታስረው ከግፈኛው አሳሪ ጋር ለመጣመር ወደወያኔው ምክር ቤት አንገባም ብለው በሰጡት መመሪያ ስለቀረ ሌላ መከፋፈያ ካለህ ወደ ደደቢት ብቅ በልና ሞክር!

የቅንጅትን መንፈስ አታውቅም እንዴ? በስመ አንድነት በቁርጥ ቀን ልጆች በአንዲት ኢትዮጵያ መንፈስ እንጂ የአንተ ጎሰኛ ቅኝት ላሊበላ ወሎ እምድብር ሸዋ ወይም መተማ ጎንደር ወዘተ ግንቦት 7/1997 ተቀብሯል!!!

ዲጎኔ ሞረቴው የጁ ወሎ ጣይቱ ብጡል አንድነት አደባባይ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ነቅንቄ » Tue Jan 24, 2006 1:19 am

ወያኔን በምስል ወይም በአካል እንጂ ትክክለኛ ምንነታቸዉን ከዘፍጥረት ጀምሮ የምታዉቃቸው አይመስለኝም.
የዘመኑ ልሳን wrote:ወያኔዎች ምንም ስማችሁን ብትለዋውጡ በጭንቅላታችሁ ላይ የተተከውን ህዝብን በዘርና በጎማ የመከፋፈል ካንሰር በቀላሉ እናንተን ለመለየት ያስችለናል::


የሸዋ ፈሊጥ እኮ የተበላ እቁብ ከሆን አመታት ብቻ ሳይሆን ዘመናት ተቆጥረዋል.ከእኛ ያልሆነ ጠላት ነው የሚል አስተሳብ እና ዘዉዳዊ አመለካከት አገሪቱን እዚህ ደረጃ ያደረሰ ካንሰር ስለሆነ በትንሽ በትንሹ እያቃለልንው የመጣን ሲሆን ቀሪዉን የመጠራረግ ተግባር ከወያኔ ዉድቀት በሁዋላ የሚቀጥል ሀላፊነት ነው.
የደርግ ካድሬ ትመስለኛለህ. ምክንያቱም የተቃወማች ሁ ሁሉ አናርኪስት, ሻእብያ, ኢዲዩ, ወንበዴ ወዘተ እየትባለ ስንቱን ንጹህ ጨፈጨፋች ሁ. እኔንም ወያኔ ብለህ ብትለቀልቀኝ አይደንቀኝም.


ዛሬ ደግሞ የወሎ የሸዋ ማለት ጀመራችሁ? ይህ የበሰበሰ የወያኔ የዘር ፖለቲካ ከህእገራችን ተነቅሎ ሊጠፋ ጥቂት ስለቀረው ከአሁን በኃላ ምንም ብትለፈልፉ እንደመዝናኛ እንጠቀምበታለን እንጂ እንደ ቁምነገር አናየውም::


የበሰበሰዉስ የሸዋ ህውላቀር አስተሳሰብ. ከእኛ ወዲያ ላሳር...የሚል ፊውዳላዊ የበከተ አስተሳሰብ. ዛሬም በልጆቻቸው አእምሮ ዉስጥ ሰርጾ አንዲት ድንጋይ በተወረወረች ቁጥር ዙፋኑ ከነ ብሩ አይናቸው ላይ ድቅን የሚልባቸው. ለነገሩ ድንጋይ ያስወረዉራሉ እንጂ እነሱ ንክቺ አያደርጉዋትም. እንድነልደቱ የመሳሰሉትን እንደሸኮራ እየመጠጡ መጣል እንጂ የወንድነት ሙያ የላቸዉም.


ልደቱ የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ድምጽ ከሀዲ ብሎታል:: ከአሁን በኃላ ምንም ብትለፈልፉ የባንዳ ልጆች ባንዳን ቢደግፉ አይስደንቀንምና ግዜያጩን በከንቱ አታጥፉ::


ህልም እና ቅዠት እንደሆነብህ ይኖራል እንጂ ልደቱን ሚያዉቅ ያዉቀዋል.እጂግ ብዙ ልደቱዎች እንዳሉን አትጠራጠር. ለባንድነቱ ደግሞ ሸዋን የሚስተካከል የለም እና መሳቂያ ባትሆን. ታሪክ አንብብ. :idea: :twisted:

ነቅንቄ
ከላስታ
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Postby ራስ ንጉስ » Tue Jan 24, 2006 1:50 am

ነቅንቄ!ስም ብሎ ዝም ነው

መነቃነቅ አይደለም ተንገጫግጫችሗል አንድ ሀሙስ ነው የቀራችሁ ያን አይቀሬውን ግባተ መሬታችሁን ለማስታስታወስ ይመስላል ስም አወጣጥህ?

ወገኖች:- ቤተሰቤ ውስጥ እንደማንኛውም ድሀ ኢትዮጵያዊ እናትና አባቴ ስምንት ጤናማ ልጆች አፍርተዋል አራቱ ወንዶች ነን አንዱ ወንድማችን ኑግ የመሰለ ጥቁቁቁርርር! ነው ታድያ እናታችን አባቴን ነው የሚመስለው ትላለች ይሁን እንጅ "ሻንቅላ" እያለች ነው ስትጠራው እኛ ወንድሞቹና እህቶቹ ግን ስንጣላው ሻንቅላው የሚለው መጠርያው ወደ ቁራነት ይወርዳል "ቁራው! እንለዋለን ያናደድን መስሎን እሱ ምን ገዶት ይስቃል ዋና መጠያ ሰሙ ተረስቷል! ሁላችንም ታድያ ያንድናት ያንድአባት ልጆች ነን:

እነዚህ ዝቃጭ አጋዚዎች በዚህ በያዙት ሁኔታ ወንድማችንን "አንተንኮ እነዚህ ትምክህተኛ ጠያይሞች ቤተሰቦችህ ሻንቅላ ቁራ ይሉህ ነበር" ስለዚህ አንቀጽ 39ኝን በመጠቀም ለምን ከቤተሰቦህ አትገነጠልም? የሚሉበትን ቀን እኔ በበኩሌ እየጠበኩ ነው

ሰወንሰሶቹ እነ ነቅንቄ ሁሉ አልቆባቸው እንደገደል ማሚቶ መድገም መደጋገም ብቻ ሆነዋል

ጣእረ ሞት ውጭ ግቢ ውጨ ነፍስ እንዲህ ያረጋል
Etiopia Tikdem!
ራስ ንጉስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 376
Joined: Mon Dec 08, 2003 8:10 pm
Location: Jupiter

Postby ዞብል2 » Tue Jan 24, 2006 2:44 am

ውዲ_ቅንቅን :P አሁንም "አልባኒያ"ነው የምትኖረው :wink: ማፈሪያ ወያኔ :oops:

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2296
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Postby ሳተርን » Tue Jan 24, 2006 4:46 pm

ነቅንቂ

ከወያነ አለቃህ ጋር በመሆን አዲስ የትግል ስልት የነደፋች ሁ ይመስላል;; አማራውን ከኦሮሞ ሞከራች ሁ አልተሳካም, ጉራጊውን ከአማራውም ተሞከረ አልሳካ አለ,, ትግራዩን ህዝብ ካማራው ሞከራች ሁ,, እሱም ከሽፈ; አሁን እስቲ አማራውን ርስ በርሱ እንሞክረው ይመስላል የተያያዛች ሁት;; ያም የተበላ እቁብ ነው;;
አይ የኝአ ምሁር ቂቅቂቅቂቅቅ;;; በሽዋ ምሁርና በትግራይ ምሁር መካከል ያለ ችግር,, ድንቂም አልቀረብህም;; የትግራይ ምሁሩ ማለት አንተ ወይም መለስ ወይም ያ የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትር የነበረው ደንቆሮ ????,, ማንን ለማለት ነው የፈገለግኽው;; ባታውቀው ነው እንጂ የትግራይ ህዝብና ምሁር ኮ ከቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መወገኑን ማን በነገረህ! አይ መንፈራገጥ.. ደርሶ ለመላላጥ;; ወየው እናንተን አያርገኝ የዚያ የቁርጥ ቀን ,,

ድል ለህዝባችን
ሳተርን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 397
Joined: Wed Dec 28, 2005 6:12 pm

እውር አሞራው ነቅንቄ

Postby ቢሌ » Tue Jan 24, 2006 5:24 pm

አይ ዎያኔ እንደው እውር አሞራ ሁሉ ተሰብስቦ የኢትዮጵያን አንድነት ለመነቅነቅ መርገፍገፍ:: አርማጌዶው ደርሷል አልታይ ስላላችሁ የኢትዮጵያ አምላክ ብዙ ደም ሳታፈሱ ነቅሎ ነቅንቆ ይጣላችሁ!!!!!!

ሊነጋ ሲል ይጨልማል

ኢትዮጵያ በአንድነትዋ ጸንታ ለዘላለም ትኖራለች!!!!!

ቢሌ
ቢሌ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 586
Joined: Wed Aug 18, 2004 7:29 am
Location: united states

Postby ነቅንቄ » Tue Jan 24, 2006 9:00 pm

ራስ ንጉስ ሆይ//ቅቅቅ

አዲሱ ንጉስ ሆይ-----ጀንበር አዘቅዝቃ አዲስ ንጋት በጉጉት እየጠበቅን ስለሆነ ወይ ስምህን ቀይር አለበለዝያም ወይ የሻገተ አመለካከትህን ቀይር.

ራስ ነገስታት በዘመናቸው ይጠቅማል ያሉትን ሰርተው አልፈዋል. አንተ ግን ሁሌ የነገስታትን ዘመን ስትናፍቅ ጊዜው እየቀደመህ ነው. ህዝቡም ጪምር ጥለዉህ ወደሀያአንደኛው ክፍለዘመን ተሸጋግረዋል. ችግሩ ግን ሌሎች ህዝቦች በስላም ሲሸጋገሩ እኛ ግን ገና እያከክን ስለሆነ የተሻለ የፖለቲካ እና ማህበረኢኮኖሚያዊ ስራትን ለማምጣት ደፋቀና ማለት ጀምረናል.

ራስ ንጉስ wrote:ነቅንቄ!ስም ብሎ ዝም ነው

መነቃነቅ አይደለም ተንገጫግጫችሗል አንድ ሀሙስ ነው የቀራችሁ ያን አይቀሬውን ግባተ መሬታችሁን ለማስታስታወስ ይመስላል ስም አወጣጥህ?


ወያኔ አንድ ሀሙስ የቀረው አይመስለኝም. በዚህ አያያዛች ሁ እና አካሄዳች ሁ ምናልባትም አንድ ተጨማሪ ምእተአመት ስልጣንዋን ይዞ ሳይገዛን የሚቀር አይመስለኝም. ለዚህ ሁኔታዉን እና መደላድሉን የምታመቻቹለት እናንተው ስለሆናችሁ በርቱ ቀጥሉ እንላለን. መንገዱን ጨርቅ ያድርግላ ችሁ.

በጣልያን ወረራ ወቅት አጼ ሀይለስላሴ ለአለማቀፍ ትግል ወደለንደን ሲሄዱ ጂቡቲ ላይ እግራቸው መርከቡን ሳይረገጥ የሸዋ መኩዋንንት ግን ወደባንዳነት የተለወጠው በብርሀን ፍጥነት እንደነበረ ጣልያኖች በወርቅ ቀለም ጽፈዉላች ሁዋል. እናንተም የነሱ የልጅ ልጆች ሀገሪቱን ለወያኔ እና ለሻእቢያ አሳልፋችሁ የሰጣችሁት አንሶ ዛሬ ድምጽቸዉን ከፍ አድርገው ለሀገሪቱ የሚጮሁትን ድባቅ ለመምታት የምታደርጉትን መፍጨርጨር በእንጭጩ መቅጨት ይቻላል. እናሳያች ሁዋለንም.


ወገኖች:- ቤተሰቤ ውስጥ እንደማንኛውም ድሀ ኢትዮጵያዊ እናትና አባቴ ስምንት ጤናማ ልጆች አፍርተዋል አራቱ ወንዶች ነን አንዱ ወንድማችን ኑግ የመሰለ ጥቁቁቁርርር! ነው ታድያ እናታችን አባቴን ነው የሚመስለው ትላለች ይሁን እንጅ "ሻንቅላ" እያለች ነው ስትጠራው እኛ ወንድሞቹና እህቶቹ ግን ስንጣላው ሻንቅላው የሚለው መጠርያው ወደ ቁራነት ይወርዳል "ቁራው! እንለዋለን ያናደድን መስሎን እሱ ምን ገዶት ይስቃል ዋና መጠያ ሰሙ ተረስቷል! ሁላችንም ታድያ ያንድናት ያንድአባት ልጆች ነን:ችግሩ የቀለም አይደለም ንጉስ ሆይ////

በ1965 አንድ ከወደሸዋ ለወሎ ክፍለሀገር እንደራሴ ተመድበው የመጡ ደጃዝማች የወይዘሮ ስህን ተማሪዎች አድመው አንማርም ብለዋልና አንድ መላ ፍጠሩ ቢልዋቸው "" ይህ የደሀ ልጅ ሁሉ ልኩን ነው የማሳየው "" ብለው በትእቢት ተወጥረው በተለምዶ ፒያሳ ከሚባለው ቦታ ግንቦት 10 ቀ ይሰበስቡዋቸዋል.

ተማሪዎች ዛሬም ድረስ መፍትሄ ያላገኙ የክፍለሀገሩን መሰረታዊ ችግሮች በመፈክር እና በንባብ እንዲሁም በንግግር ይገልጻሉ. ሰዉየው ግን ቦርጫቸዉን እያሻሹ "" ወሎ ድሮዉንም ቅሉን አንጠልጥሎ መሰደድ ልማዱ ነው. ..የምታወሩትን ችግር አናዉቀዉም. እናንተንም አይመለከትም'' የሚል ተእቢት የተሞላበት የንቀት መልስ ይሰጣሉ. ከተማሪው መሀል አንዲት ድንጋይ ተወርዉራ የእንደራሴዉን ግንባር በርቅሳ ደም በደም ታደርጋለች. ከሸዋ ያመጡት ቦዲ ጋርዳቸው በጥቂት ደቂቃወች ዉስጥ ከአስር በላይ ተማሪዎችን እንደቅጠል ያረግፍ እና ደሴ ብቻ ሳይሆን ክፍለሀገራችን በዋይታ ትጥለቀለቃለች. ከዚያ በሁዋላ ከገዢው መደብ ጋር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተቆራርጠናል. ዛሬም እናንተ ልጆቻቸው ሀገሪቱ ፈረሰች--ተናጠች--ወደቀች የምትሉት የአባቶቻች ሁ አሮጌ ዜማ እንጂ በሀገሩ ባይተዋር የሆነዉን ንጹህ ኢትዮጵያዊ የማይመለከት መሆኑን ላረጋግጥልህ እወዳለሁ.

እነዚህ ዝቃጭ አጋዚዎች በዚህ በያዙት ሁኔታ ወንድማችንን "አንተንኮ እነዚህ ትምክህተኛ ጠያይሞች ቤተሰቦችህ ሻንቅላ ቁራ ይሉህ ነበር" ስለዚህ አንቀጽ 39ኝን በመጠቀም ለምን ከቤተሰቦህ አትገነጠልም? የሚሉበትን ቀን እኔ በበኩሌ እየጠበኩ ነው


ይህ ራሱ የእናንተ ባህርይ አንድ መግለጫ ነው.

እኛ ስለ ህዝቦች መሰረታዊ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግሮች ስናወራ እናንተ ስለቀለም መጥቆር እና መቅላት ትቀባዥራላች ሁ.

እኛ የሀገሪቱን ህልዉና የሚፈታተኑ አብይ ቀዉሶች ስንሙዋገት እናንተ ደግሞ አንቀጽ 39ን ቀለሙ ጠቆረ ጠይም ሆነ ትሉናላች ሁ.

ከላይ ያነሳሁት የእንደራሴው ምሳሌ ለዚህ ማስረጃየ ነው. ችግሩን አታውቁትም. ለማወቅም አትፈልጉም. መፍትሄ የምምጣት ችሎታዉም ሆነ ብቃቱ የላችሁም. ስለዚህ በአንድነት ስምሁሉንም ጨፍልቃችሁ ልትገዙት እና ልትነዱት ትመኛላች ሁ. እንደአባቶቻችሁ አንዴ በህብረብሄራዊነት ስም ሌላ ጊዜ ጂራት እና ቀንድ በሌለው ""ኢትዮጵያዊነት"" ስም ልትገዙት ትመኛላች ሁ. ኢትዮጵያን አታውቁዋትም. የምይሳካላች ሁም በዚህ ምክንያት ነው.

ዛሬም ልደቱ ላይ የምታሳዩት ተእቢት እና ንቀት ወያኔ በፕሮፓጋንዳው ስለእናንተ ከሚለው በተጨማሪ ሌላ ትኩስ ማረጋገጫ ስለሆነ እኔም ያን ያህል መድከም ያለብኝ አይመስለኝም.


አዲስ አበባ ላይ ተኮፍሳች ሁ ክልሎች እና ክፍለሀገራት ለአንተና ለዘመዶችህ ገባር ከሚሆኑ አንቀጽ 39 በስራ ላይ በአስቸኩዋይ እንዲዉል አሁን አሁን እያመንኩበት መጥቻለሁ. ያን ጊዜ የት ትደርሱ ይሆን.


ነቅንቃቸው
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Re: ተጋዳላይ ነቅንቄ የጎሳ ልክፍትህ አሁን ደግሞ አገረሸብህ

Postby ነቅንቄ » Wed Jan 25, 2006 12:23 am

ዲጎኒ

የተጠናወተህ የዘር ልክፍት አልከኝ?????
አጻሳት. ዘረኝነትን ፍጹም ከሚያወግዙት አንዱ ከመሆኔ በላይ በተግባርም ማንነቴን ያረጋገጥኩ መሆኔን ስገልጽልህ በኩራት ነው. ሆኖም ግን የዘረኘት ምንጩ በሀገራችን ለምን እንደሆነ የሸዋ ምሁራን ሊያጠኑትም ሆን ሊያውቁት ስለማይከጂሉ ጠባብነት እና ዘረኝነት ሁልጊዜም ኢትዮፕያን የሚንጥ አስቸጋሪ ጉዳይ ሆኖ ይኖራል. ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እንደሚባለው ያንተ ዘመዶች አራትኪሎ ቁሽህ ብለው የብሄረሰብ ቅራኔ ሲያጭሩ ለመኖራቸው ብሎም ያ የለኮሱት እሳት ሀገሪቱን ከድጡ ወደማጡ እየመራት እንደሆነ እያየን ነው. ህዝቦች በገዛ ሀገራቸው ባይተዋር እና ተመልካች መሆናቸዉን አትዘንጋ. ዛሬም የሚያጥድፋችሁ ያንኑ እሳት ይበልጥ ለማቀጣጠል እና ሀገሪቱን ለመበተን እንጂ የቸዋ ልጆች ስልጣን ቢቆናጠጡ ችግሮቻችንን እንደማይፈቱልን አስቀድሞ እናዉቀዋለን.

ዲጎኔ wrote:ተጋዳላይ ነቅንቄ.......የቅንጅትን መንፈስ አታውቅም እንዴ?


ቅንጂት መንፈስ የሆነው በሸዋ ልጆች አንጎል ዉስጥ እንጂ እኛን እንደማይመለከት ጠንቅቀህ መረዳት አለብህ.
ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ. ህልማች ሁ እና ህልማችን ፍጹም ተቃራኒ መሆኑ ስለልደቱ የለፈለፋችሁትን ስለሰማን ከነመንፈሳች ሁ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላች ሁ//////

በስመ አንድነት በቁርጥ ቀን ልጆች በአንዲት ኢትዮጵያ መንፈስ እንጂ የአንተ ጎሰኛ ቅኝት ላሊበላ ወሎ እምድብር ሸዋ ወይም መተማ ጎንደር ወዘተ ግንቦት 7/1997 ተቀብሯል!!!


በስመአንድነት ተጠፍረን የምንገዛበት ጊዜ ማክተሙን አላወቅህም እንዴ???ጌታው/// የምትመሩት በስልጣን መንፈስ /አባዜ ስለሆነ የህዝቡን የልብ ትርታ የሚያዳምጡ መሪዎችን ቀንደኛ ጠላት የምታደርጉት ለዚህ ነው.
ዲጎኔ ሞረቴው የጁ ወሎ ጣይቱ ብጡል አንድነት አደባባይ


አስመሳይ ነህ. የጁን የት ታውቀዋለህ. ድጋፍ ለማሰባሰብ ከሆነ አይሳካልህም.አትድከም.

ነቅንቄ
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Postby ነቅንቄ » Wed Jan 25, 2006 3:38 am

ሳተርን

በጣም የዋህ እና ስለምትጽፈዉም ጉዳይ በቂ ግንዛቤ ያለህ አይመስለኝም. ለሀገርህ የበኩልህን ድርሻ ማበርከት ፈልገህ ከሆነ ከፋፋይ እና በታኝ የሸዋ ተንኮልን በአለህ አቅም ልማጋለጥ እና ለማስወገድ ጥረት አድርግ.

በዚያ ቀውጢ በሆነ የቀይ ሽብር ዘመን በራሱ ልጆች አስከሬን ላይ የጨፈረ እና ዳንኪራ የረገጠ ማን እንደሆነ ታውቃለህ???አንድ ስንኝ ልጠቁምህ እና ትደርስበታለህ.

""አቤት ደስ ማለቱ---የአናርኪስት ደም ሲፈስ ማየቱ.."" ያለው ማነው. የትስ ነው የተገጠመው. ይህስ ""ወገን"" ለልደቱ ይራራል ብለህ ታስባለህ?? በሌሎችም ላይ ያየነው ዘግናኝ ድርጊት ሁሉ የሚመነጨው ከዚሁ የሸዋ ልጆች አካባቢ ስለሆነ ዛሬ በድል አጥቢያ አርበኝነት ሳይቀድሙን እንቅደማቸው በሚል ተንኮል ያንኑ ፊውዳላዊ ሴራ በመጎንጎን ላይ ናቸው. ህልማቸው አይሳካላቸዉም. ስልጣንዋንም አያገኙዋትም. ምን እየተፈጠረ እንደሆን ታዉቃለህ በአሁኑ ሰአት??? ዳግመኛ ምርጫ ቢጠራ ያሰከራቸው የስልጣን ስካር ይበርድላቸው ነበር.

""ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ፍጥጥ.."" የተባለዉን ያስታዉሰናል ዛሬ የሚሰራው ስራ ሁሉ.

ሳተርን wrote:ነቅንቂ

ከወያነ አለቃህ ጋር በመሆን አዲስ የትግል ስልት የነደፋች ሁ ይመስላል;; አማራውን ከኦሮሞ ሞከራች ሁ አልተሳካም, ጉራጊውን ከአማራውም ተሞከረ አልሳካ አለ,, ትግራዩን ህዝብ ካማራው ሞከራች ሁ,, እሱም ከሽፈ; አሁን እስቲ አማራውን ርስ በርሱ እንሞክረው ይመስላል የተያያዛች ሁት;; ያም የተበላ እቁብ ነው;;


ስማኝ ጃል/// የሸዋ ልጆች ወያኔን ያወቁት በጂማ በር ከች ሲልባቸው ነው. ከዚያ በፊት ስንት እና ስንት አመት አታውቁትም. እንድነጋበት ጂብ የሚያሩዋሩጣች ሁም ለዚህ ነው. ጀግናው ወሎየ ግን ወያኔን አርበድብዶዋል. በየፈፋው--በየማሳው--በየጋራው. በየሸለቆው. ዛሬ ሳይሆን ጥንት እንተዋወቃለን. አዞ እና ክብሪትን የመሳሰሉ ሽምቅ ተዋጊዎቻችን ወያኔን በእንጪጩ ለመቅጨት ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍለዋል. በታሪክም የተመዘገበ ነው. የሸዋ ባለስልጣኖች እና ምሁራን ግን በለመዱት ሴራ እና ተንኮል እነዚህን የክፍለሀገሩን ታጋዮች እንዲበታተኑ አድርገው ለወያኔ /ሻእቢያ በር ከፍተዉላቸዋል. ይህም ከፍተኛ በደል በልባችን ዉስጥ ለዘላለም ሀዘን ሆኖ ይቆያል.


አይ የኝአ ምሁር ቂቅቂቅቂቅቅ;;; በሽዋ ምሁርና በትግራይ ምሁር መካከል ያለ ችግር,, ድንቂም አልቀረብህም;; የትግራይ ምሁሩ ማለት አንተ ወይም መለስ ወይም ያ የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትር የነበረው ደንቆሮ ????,, ማንን ለማለት ነው የፈገለግኽው;;


አዎ ///አሁንም ለክፍለሀገራት ህዝቦች በደል መባባስ እና እነዚሁም ህዝቦች የአመጽን መነገድ እንዲከተሉ የገፋፉዋቸው እና ለሀገራችንም እዚህ መድረስ ተጠያቂው የሸዋ መኩዋንንት እና ዛRእም ራሳቸዉን እጩ ያደረጉ ልጆቻቸው ተንኮል እና ሴራ ነው. ይህ እምነቴ ወያኔ ካደረገኝ የህወሀትን ሊቀመንበርነት ብትሰይመኝ አይኔን አላሽም.

[quote] ባታውቀው ነው እንጂ የትግራይ ህዝብና ምሁር ኮ ከቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መወገኑን ማን በነገረህ! አይ መንፈራገጥ.. ደርሶ ለመላላጥ;; ወየው እናንተን አያርገኝ የዚያ የቁርጥ ቀን ,,

የትግራይ ህዝብ ከተቀረው ወገኑ ጋር ወግኖዋል ያልካት እንደቀልድ ያመለጠች ህ እንጂ አስበህባት አይመስለኝም. ምክንያቱም ገና ዘንቦ ተባርቆ ነው ይህ ወዳጂነት እና ፍቅር የሚመለሰው እንጂ እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አይደለም.
በፍጥነት ሁለቱም ወንድማማች ህዝቦች ቢስማሙ ደስታዉን አልችለዉም. አሁን በቅንጂት አካባቢ ያሉት በሚሰሩት ተንኮል ይህ የሚፈጸም አይመስለኝም. እንኩዋን ትግራይ ሌላዉም በቁዋፍ ነው ያለው. ሀገራችን ገና ገና ረዢም የሽግግር ዘመን ዉስጥ ማለፍ ያለባት ይመስለኛል. አሁን የተያዘው አባዜ ሁሉንም በተናጠል መምታት እና ማጋደም ስለሆነ የሸአው ልጆች እስኪነቁ መጠበቅ አስፈላጊ አይመስለኝም.የለኮሱት እስኪፈጃቸው ላንጠብቅም እንችላለን. ለሁሉም ጊዜ አለው ይባል የለ.

ነቅንቄ
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

የቅንጅት መንፈስ ወሎ እንደሰፈነ የደሴው ተጋድሎ ብቻ ይበቃል

Postby ዲጎኔ » Wed Jan 25, 2006 3:57 am

ወዳጄ ልቤ ነቅንቄ

በአሉታዊ መልኩ ወሎ ሸዋ እያልክ የጋመውን የኢትዮጵያ የነጻነት ትግል ስታበላሽ ሌላ ግምት አጥቼልህ ልክፍት መሆኑን ለማጣራት እንጂ ልፈርድብህ አልነበረም:: ወገን ሲለከፍ ወደ ጠበል አሊያም ወደ ጸሎት ቤት ወይም ወደነ ሀጂ መሀመድ ሳኒ መስጂድ መውሰድም የወሎ ልማድ ነው::

አሁንም አረመኔው ወያኔ የኢትዮጵያዊያዊያን የጋራ ደመኛ ጠላት ህዝባችንን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲጨፈጭፍ የትግሉን መንፈስ ሸዋ ወሎ ጎጃም ጎንደር እያለ የሚለያይን ሁሉ ያለ አድልኦ እንደምፋለም አረጋግጥልሀለሁ::በተረፈ የተቀናጀው የአንድነት መንፈስ ወሎ የለም ብትለኝ ደሴ የቅንጅት ጀግና አባላትን ቆራጥ ፍልሚያ መጥቀሱ ይበቃል::

የውጫሌ ውል ስውር ሸር ገላጭ የአድዋ ጀግና ጣይቱ ብጡልን ቀየ የጁን ለማወቄና ከወሎው ቅድመ አያቴ ለመወለዴ ጊዜና ቀኑ ሲገጥም ሁሉም ወደብርሀን ሲወጣ በነፋሪስ የልጅ ልጆች እማኝነት ቆቦ ወረኢመኑ ወልድያ ወይም ገራዶ ላይ በላሌ ጉማ እንጉርጉሮ ይፈተሻል::

አቶ ልደቱ የትግል ተሳትፎና መከራውን ከሸዋ ሮቢት ጀምሮ የማደንቅለት ቢሆንም አሁን ጸረ-ወያኔ ብሄራዊ ትግሉን የሚፈታተን አቁዋሙን እንዲያስተካከል ከመገሰጽ ወደሁዋላ የማልል ሲሆን የቅንጅቱ አባል ኢዴፓ-መድህን በቅርቡ ለሰጠው የቅንጅት አባል ድርጅቶች ውህደት ውሳኔ ተገዥ እንደሚሆንም ሙሉ ተስፋ አለኝ::

ዲጎኔ ሞረቴው መቅደላ ወሎ ከተዋበች አሊ የአንድነት ግንባር
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ወጥመድ » Wed Jan 25, 2006 7:56 am

ነቅንቄ!!
ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ

አሁንም በድሮ በሬ እያረስክ ነው??
ወሎ ጎጃም ጎንደር ሸዋ እያሉ ማላዘን ያኔ----ያኔ--- ቀረ እኮ :: ዛሬ ነገሩ ሁሉ እናንተ እንዳሰባችሁት ሳይሆን ቀርቶ የተገላቢጦሽ ሆኖ በግንባር ቀደምትነት ወያኔን የሚያርበደብደው የባህሕር ዳር, የደብረማርቆስ, የደሴ, የኮምቦቻ የባቲ--- የጎንደር ህዝብ---ወዘተ ሆነና እርፍ አለ:: እንግዲህ ነቅንቄ ነኝ አዝብጤ ነኝ ብትል በስም የሚለወጥ ምንም ነገር የለም::

ይልቅስ ከወሎ ክ/ሀገር ወደ ክልል 1 (ትግራይ) የተዘረፈውን ለም ለም መሬት በሰላም መልሱ::

ቅ :lol: ቅ :lol: ቅ
አላርፍ ያለች ጣት----

ወጥመድ
ወጥመድ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Fri Mar 11, 2005 1:52 pm
Location: Semen Walta

Postby ሳተርን » Wed Jan 25, 2006 4:11 pm

ነቀንቂ

ላንተ መልስ መስጥእቱ ተገቢ አይመስለኝ;; የደንቆሮ ለቅሶ ሆነብኝ
አንድ ልነግርህ የምፈልገው ነገር ቢኖር, የኢትዮጵያ ህዝብ ተንኮላችሁን , ጭካኒያችሁን በሚገባ ተረድቶታል;; እስቲ አንድ ጥያቂ ልጥእይቅህ
በርግጥ ህዝቡን አንተ እንደምትለው የሽዋው ምሁር አማራና ጥቂት ነፍጥእኝኦች ሊከፋፍሉት ና አገሪቱን ሊገድልዋት ከተነሱ ለምን ህዝቡን አስተባብራችሁ ድባቅ አታስገብዋቸውም?
ህዝቡ ከጎናችን ነው ብላችሁ ካመናችሁ እስቲ ነገ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሩና ቅንጅትና ወይም እንዳንተ አባባል ""የሽዋ ምሁራንን"" አውግዙ በሉ;; በህዝብ ላይ እምነት ያለው ኮ ይህንን በድፍረት ያደርጋል;;
እስቲ ለአንድ ሳምንት ህዝቡ የሚፈልገውንና የሚፈቅደውን እንዲያደርግ እድሉን ስጥኡት;; የህዝብ ወገን በህዝብ ላይ እምነት ያለው ይህንን ነው የሚያደርገው;;
ለማንኝአውም ይህ የመጨረሽየ መልስ ነው የሚሆነው;; ስም ቀይረህ ደግሞ በሊላ አርስት እስከምንገናኝ
ሳተርን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 397
Joined: Wed Dec 28, 2005 6:12 pm

Re: የቅንጅት መንፈስ ወሎ እንደሰፈነ የደሴው ተጋድሎ ብቻ ይበቃል

Postby ነቅንቄ » Wed Jan 25, 2006 10:39 pm

ሰላም ድጎኔ

ያንተን አስተያየት ደግሜ ደጋግሜ አንብቤዋለሁ. ወንድማዊነት እና ትምህርታዊነት እንዳለው ስላረጋገጥኩ ትንሽ ምላሽ ልሰጥ እወዳለሁ.

ዲጎኔ wrote:ወዳጄ ልቤ ነቅንቄ

በአሉታዊ መልኩ ወሎ ሸዋ እያልክ የጋመውን የኢትዮጵያ የነጻነት ትግል ስታበላሽ ሌላ ግምት አጥቼልህ ልክፍት መሆኑን ለማጣራት እንጂ ልፈርድብህ አልነበረም:: ወገን ሲለከፍ ወደ ጠበል አሊያም ወደ ጸሎት ቤት ወይም ወደነ ሀጂ መሀመድ ሳኒ መስጂድ መውሰድም የወሎ ልማድ ነው::


ወዳጅ የሚወደዉን ወደጸበል መዉሰዱን የምንወደው ባህላዊ መፍትሄያችን መሆኑን አምንበታለሁ. እኔንም ወደዚህ ደረጃ ያዳረሰኝ እነዚህ ጸረ ወያኔ የሚል ካባ ደርበው በድል አጥቢያ አርበኝነት በለው ፍለጠው ቁረጠው የሚሉት የሚሰሩት ስራ ሁሉ ስለአላማረኝ ነው. እንዲያዉም ይህን አስተያየት ከመስጠቴ በፊት ምናልባት የወያኔ ካድሬዎች ቅንጂቱን ከህበረቱ--ሌላዉንም እርስ በርሱ ለማባላት የሚያደርጉት መስሎን ለረዢም ጊዜያት መታገሴን ለገልጽልህ እወዳለሁ.

እኔ ልደቱ አያሌዉ በአካል አላዉቀዉም አያዉቀኝም.... ጋሻ ጃግሬዉም አይደለሁም. ቅንጂት አካባቢም የለሁ. ንጹህ ሀገር መዉደድ ካልሆነ ስተቀር የለጠፍኩት ታርጋ የለኝም.

ልደቱ በግንባር የተሰለፈ በመሆኑ የሚያሳየው ድፍረት እና የማሰባሰብ ጥረት እንዲሁም ዝንተአለሙን ከሚጎሳቆለው ክፍለሀገራችን ስለወጣ ያለኝ አድናቆት እና አክብሮት ከፍተኛ ነው. ስለዚህ ሁሉም ባመነበት እና በተሰለፈበት ያቅሙን ካበረከተ ወያኔ አስራአምስት አመት አይገዛንም ከሚሉት አንዱ ነኝ.

ግንቦት ሰባት በአንዳንድ ወገኖች የፈጠረው የድል ስሜት ሳይሆን ቅዠት እና የስልጣን ሱስ በመሆኑ ያገኙትን መልከፍ--ሞራል መገደል አይነተኛ ስራቸው ስላደረጉት እንዚህ ሰዎች በእርግጥ የአንድነት ወገኖች ናቸዉን????ለሀገሪቱስ ተቆርቁዋሪ ናቸዉን ???የሀላፊነት ስሜት አላቸዉን???? ወይስ አገኘናት እንደተመኘናት የሚሉ የጨቀየ አስተሳሰብ ያላቸው የስልጣን ሱሰኞች???? የሚሉ በርካታ ጥያቄዎችን እንዳነሳ አስገድዶኛል.

በኔ እምነት ቅንጂት ማለት የሀገር ቤቱ እና የውጩ ትግል ይበልጥ ተቀራርቦ--ተስማምቶ--ተቀናጂቶ በመንፈስም በአካልም ተግባብቶ ወያኔን ማራወጥ የሚችል ሀይል እንጂ ዛሬ እንደምናየው አንዲት ድንጋይ ስለተወርወረች ዝናዉን እና ታሪኩን ለመቆጣጠር የሚካሄድ ትግል መሆን የለበትም. ወደዚህ ደረጃ ያዳረሳቸዉም የቆየ ንቀት እና ተእቢት ስለሆነ ከእንግዲህ እነሱ በመስራት ላይ ያሉት ለወያኔ እድሜ መራዘም እንጂ መወገድ ባለመሆኑ ልደቱን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ከመግደል እንደማይመለሱ አምኘበታለሁ.ገና ብዙ እናያለን.


አሁንም አረመኔው ወያኔ የኢትዮጵያዊያዊያን የጋራ ደመኛ ጠላት ህዝባችንን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲጨፈጭፍ የትግሉን መንፈስ ሸዋ ወሎ ጎጃም ጎንደር እያለ የሚለያይን ሁሉ ያለ አድልኦ እንደምፋለም አረጋግጥልሀለሁ::በተረፈ የተቀናጀው የአንድነት መንፈስ ወሎ የለም ብትለኝ ደሴ የቅንጅት ጀግና አባላትን ቆራጥ ፍልሚያ መጥቀሱ ይበቃል:


በአባባልህ እስማማለሁ. አሁን አሁን እንደምናየው ግን ያ መንፈስ ወደ ቅዠት እየተለወጠ ብዙዎቻችንን እያነጋገረ ነው. ቡግና ወረዳ ላይ ህዝቡ በተከታታይ ያሳየው ጸረወያኔ የትግል መንፈስ ዛሬ መዳከሙን ምናልባትም ድጋሚ ምርጫ ቢኖር መልሱን ለሁሉም እንደሚያሳዉቅ አትጠራጠር. የስነ-መንግስት አስተሳሰቡን እና እዉቀቱን ያገኘው ቅንጂት እና ዶሮ ከመጮሀቸው ስንት እና ስንት ዘመናት በፊት ነው.

የውጫሌ ውል ስውር ሸር ገላጭ የአድዋ ጀግና ጣይቱ ብጡልን ቀየ የጁን ለማወቄና ከወሎው ቅድመ አያቴ ለመወለዴ ጊዜና ቀኑ ሲገጥም ሁሉም ወደብርሀን ሲወጣ በነፋሪስ የልጅ ልጆች እማኝነት ቆቦ ወረኢመኑ ወልድያ ወይም ገራዶ ላይ በላሌ ጉማ እንጉርጉሮ ይፈተሻል::


የሚገርምክ ነገር ወሎ ማለት ብሄር--ቁዋንቁዋ--ዘር ሳይሆን አስተዳደራዊ ክልል ወይም ጅኦግራፊያዊ አካባቢ ማለት ነው. ወደስሜን ብቅ ካሉት የኦሮሞ ቤተሰቦች የአንዱ ወገን ስያሜ ሲሆን ላለፉት ሁለትእና ሶስት መቶ አመታት ለመለየት በሚያስቸግር ሁኔታ በጋብቻ--በሀይማኖት-በንግድ በሀዘን በደስታ -በጦርነት--በድል--በሁሉም መስክ ከአካባቢው ህዝብ ተስማምቶ እና ተቀላቅሎ የኖረ ነው. ስለዚህ እኛ ወሎየዎች ቢቸግረን እንኩዋን ወሎ መጀን ብለን እንጽናናለን እንጂ ዘረኝነት እና ጎጠኝነት አይነካካንም. ዘረኞች እና ጎጠኞች እኛ ጋር ቦታ የላቸዉም. ለአንድነት ሀይሎች ድጋፉን የሰጠዉም በዚህ ምክንያት ነው. ባለፉት ጥቂት ወራት አዲስ አበባ ላይ አንዲት ፋብሪካ እንኩዋን አልተዘጋችም. ላባደሩም ስራ እንኩዋን አላቆመም. ከደሴ ላባደሮች በስተቀር. ይህም ለአንድነት ሀይሎች ከፍተኛ ድል ነው. ዛሬ ዛሬ ግን ድንጋዩም ተወርወረ እና መስዋእትነቱም ተከፈለና-በሚዘገንን ሁኔታ የሞራል ግድያው ተጡዋጡፎዋል. ይህን ነው የምቃወመው. ይህ ትግሉን ገደለ እንጂ አልጠቀመም ባይ ነኝ.


አቶ ልደቱ የትግል ተሳትፎና መከራውን ከሸዋ ሮቢት ጀምሮ የማደንቅለት ቢሆንም አሁን ጸረ-ወያኔ ብሄራዊ ትግሉን የሚፈታተን አቁዋሙን እንዲያስተካከል ከመገሰጽ ወደሁዋላ የማልል ሲሆን የቅንጅቱ አባል ኢዴፓ-መድህን በቅርቡ ለሰጠው የቅንጅት አባል ድርጅቶች ውህደት ውሳኔ ተገዥ እንደሚሆንም ሙሉ ተስፋ አለኝ::

ዲጎኔ ሞረቴው መቅደላ ወሎ ከተዋበች አሊ የአንድነት ግንባር


ባገኝሁት መረጃ መስረት ቅንጂት ራሱን ጠልፎ የጣለ ድርጂት እንጂ ማንም አልገፋዉም.ምርጫ ቦርድ አልነካው--ወያኔ አልነካው. የማይቆጣጠሩትን እሳት እኮ ነው የለኮሱት. በቂ ድርጂታዊ መዋቅር የላቸውም. የስው ሀይል ቢኖራቸውም ለአንድ ድርጂት እጂግ ጠቃሚ የሆነዉን መዋቅር እና ድርጂታዊ ጉልበት አልገነቡም.
ለዚህ ችግር ተጠያቂ የሚያደርጉት ሀቀኞችን እንጂ በእርግጥ ቅንጂትን ብቁ እና ዝግጁ አድርገነው ነበር ወይ ብለው መጠየቅ አይፈልጉም. በራሱ ጊዜ ነው ያከተመለት. ፍርድ በራስ ነው. ለዚህ ማስረጃ ከፈለግህ
1.የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የመስከረም ወር ጽሁፍ አንብብ
2.ሰሞኑ በኢትዮፕያን ሪፖርተር ላይ ምርጫ ቦርድ የሰጠዉን ቃለምልልስን አንብብ.

ቅንጂት በቂ አቅም አልነበረዉም በፍጹም ሞራል እና ስሜት ካልሆነ ብስተቀር እንደአንድ ድርጂት በሁለት እግሩ የቆመ አልነበረም. እንኩዋን ወያኔን አይደለም ካሰባሰባቸው ድርጂቶች ካንዱ ጋር እንኩዋን መደራደር እና ማሳመን ያልቻለ ስብስብ ነው. በብዙዎቻችንም ላይ የተሳሳሳተ የድልድራጊነት ስሜት ፈጥረዋል. ስለዚህም ነው አባላቱ እና ደጋፊዎች ቅንጂት መንፈስ ነው ሲሉ ህልዉና የለለው ጂራት እና ቀንድ የሌለው ሊዳበስ -ሊጨበጥ ሊታይ የማይችል የባዶ-ቤት መንፈስ አድርገው የሚያቀርቡልን. አጃኢብ እንላለን እኛ ወሎየወች እንዲህ አይነት ክስተት ሲያጋጥመን.

ልደቱ ይህንን አስከፊ ሁኔታ እና የተበላሸ አካሄድ እንመርምረው እና እናስተካክለው ነው የሚለው. ለዚህ ማረጋገጫው ደግሞ እንግባ አንግባ በሚለው በቀሪዎቹ መካከል እስከአሁን ያልተፈታ የተዘበራረቀ አካሄድ ነው. ለታሰሩት ከፍተኛ ከበሬታ አለኝ. ዛሬ በነሱ ስም ከዚያች እስርቤት ግድግዳ ባሻገር ምን እየተሰራ እንደሆነ ቢያዉቁ እጂግ ደስ ይለኝ ነበረ.ይህም ጊዜ ይፈጃል.

ግን አንድ ሀቅ አለ. እናት ኢትዮጵያ ብዙ ቆፍጣና ልጆች አሉዋት. ይህ ሁኔታ ሞራላችንን ቅንጣት እንኩዋን አይጎዳዉም. በፍጹም. ወሎ መጀን//////

አክባሪህ
ነቅንቄ

ከደሴ ዙርያ
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests