የወያነ የመጨረሽአ ምሽግ እውን ትግራይ ነው?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የወያነ የመጨረሽአ ምሽግ እውን ትግራይ ነው?

Postby ሳተርን » Tue Feb 07, 2006 5:44 pm

ይህ አባባል ከቀን ወደ ቀን አነጋጋሪ እየሆነ መጥትዋል;;

የወያነ ውድቀት ይራቅም ይቅረብ የማይቀር ነው;; የሰሞኑ የመለስ ያውርፓ ሩጫ ያስከትለበት ቅሊት , የትግሉ በየአራት ማእዘናት መንበልበል, ከቁጥጥር ውጭ ሊከሰት የሚችል time bomb በማንኝአውም ሰአት እንደሚፈነዳ ነው;;
በዙ ጊዚ በዋርካና በሊሎችም ድህረ-ገጽ እንዳየነው ትግራይ ለውያነ የመጨረሽአ መሽሽጊያ ልትሆን እንደምትችል ሲተነበይ ወይም ሲሰላ አይተናል;; በርግጥ ይህ ትንበያ እውነት ሊሆን ይችል ይሆን? በውነት የትግራይ ህዝብ ለነዚህ የታሪክ አተላዎች መሽሽጊያ እጁን ይዘረጋ ይሆን ወይስ አሚኪላ ሆኖ ይቀበላቸዋል? ስለትግራይ ህዝብ የወቅቱ የውስጥ የፖለቲካ ይዘት በተጨባጭ ና በመረጃ የተደገፈ ስሊት እስካሁን አላየሁም;;ለዚህ መረጃና ኢንፎርሚሽን ቅርብ የሆናችሁ ሰዎች ካላችሁ እስቲ ጀባ በሉን;;
የህዝቡ ስሚት ምን ይመስላል? ውጥረት አለ ወይ?

ሊላው መታየት የሚገባው ነገር ቢኖር የወያኒው መሪ መለስ የማታ ማታ ወደ ውጭ አገር ይኮበልላል ወይ? የት አገር? በማን ሽምጋይነት? በአሚሪካ ወይስ በእንግሊዝ? የመንግስቱ አይነት ደርድር ውስጥ ሊያስገባው የሚችል ተጨባጭ ሁኒታ ይኖር ይሆን ወይ? ልብ አርጉ መንግስቱም ያንን ሁሉ ሰው ገድሎ ጨፍጭፎ deal አግኝትዋል;; መለስስ ተመሳሳይ ዲል የማያገኝበት ምን ምክንያት ይኖራል? ይህን ካሰብን ደግሞ እስካሁን ያስገደለው ተረስቶ አንዱ አገር ሂዶ በሰላም ሊኖር ነው;; ይህ አካሂድ ማለትም ወንጀለኝኦችን የማሽሽና በህዝብ ላይ ለሰሩት ጭካኒ ፍርድ ስያገኝኡ እንዲያመልጥኡ ማድረጉ አግባብ ነውን? ሲደጋገም ለሊላው አገርም ሆነ ለራሳችንም ቢሆን የሚፈጥረው precedence የምንቀበለው ነው?
እስቲ እንወያይበት
ሳተርን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 397
Joined: Wed Dec 28, 2005 6:12 pm

Postby ሳተርን » Wed Feb 08, 2006 6:19 pm

ጨካኝ መሪዎች እስከ መቸ ነው የህዝብ ፍርድ የሚዳስሳቸው;; በስልጥአን ላይ እያሉ የሚፈልጉትን አድርገው ሲያበቁ ህዝብና አገር እንዳይተላለቅ በሚል ፈሊጥ በሰላም ከህገር ወጥተው የሚፈልጉትን ዘርፈው ያግበሰበሱትን ይዘው ሊላ አገር በሰላም እንዲበሉ ሲደረግ እያየን ነው;; ይህ ሁኒታ በዚሁ እንዲቀጥል ከተደረገ የዛሪዎቹ ዲክታተሮች የቻሉትን ያህል ገድለው አተረማምሰው, ነገ በአደራዳሪዎች ሰላማዊ ኑሮዋቸው ሊቀጥሉ ነው;; ይህ ሁኒታ ይበልጥ ጨካኝ ሰዎችን በምንም ምንም ስልጥአን ላይ እንዲወጥኡ አይጋብዝም ወይ? እከሊ ምን ተደረገ? ይህው በሰላም ይኖር የለ የሚለውን precedence ይፈጥራል;; በአውርፓ ምድር ግን ይህ እንዲሆን አይፈቀድም;; አሳደው ይዘው ለፍርድ ያበቁታል;; የሰርቢያው መሪ የነበረውን መጥቀስ ይቻላል;; ታድያ ላፍሪካ ይህ ፎርሙላ ለምን አይሰራም?
ትናንት መንግስቱ በዚህ መልክ አምልጥኦል,, ነገ ደግሞ ተረኝአው መለስ ሊያመልጥ ይገባዋል ወይ? የፖለቲካው ሁኒታ ተባብሶ ይህ መንግስት የማያመልጥበት ደረጃ ላይ ቢደረስ አሚሪካና እንግሊዝ ይህን ህሳብ ቢያቀርቡ እንቀበለው ይሆን? ይህን ሁሉ ሰው ጨፍጭፎና አገሪቱን ምስቅልቅልዋን አውጥቶ ነገ በሰላም ልንሽኜው ይገባን ይሆን? ይህ ሁኒታ ዲክታትሮችን ለመፈልፈል ይበልጥ አይጋብዝም?
ሳተርን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 397
Joined: Wed Dec 28, 2005 6:12 pm

መለስ ወደ ትግራይ ይህዳል?

Postby AGOTIYE » Thu Feb 09, 2006 12:52 am

በምንም ተአምር መለስ ወደ ትግራይ አይሸሽም::ሰዎች የማይገባችሁ ነገር እኮ በወንጀለኛነት መለስ ከሚፈለግበት ቦታ ዋነኛው ትግራይ ነው::ይህ ሰውየ ይትግራይን ህዝብ ከለላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለማጋጨት የፈለገ: እንደ ለላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ትግራይንም ያለ ወደብ ያስቀረ:
በአድዋ ጎጠኝነት ተለክፎ ለላውን የትግራይ ህዝብ አንደ ሁለተኛ ዘጋ የቆጠረ: ሀቀኛ የትግራይ ኢትዮጵያዊ ጀግኖችን ያሰረና ያስገደለ (ስየ አብርሀና :ህየሎም አራያን ልብ ይልዋል)
ስለዚህ ወገኖቸ የትግራይ ልጆች ይህ ሰላቢ ለባ አምልጥዋችሁ ወደ አድዋ ሳይገባ ይዛችሁ ፍርዱን
እንድትሰጡት ነቅታችሁ ጠብቁ::
ለላ መሸሻ የለውምና ጠንቀቅ ብለን እንጠብቅ::ድል ለኢትዮጵያና ለሕዝብዋ!!!!! :lol: :lol:
AGOTIYE
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 33
Joined: Wed Jan 05, 2005 2:35 am
Location: united states

Postby መሰረት ተስፋየ » Sun Feb 12, 2006 5:44 pm

ወዳጀ ሳተርን ብትግራይ ህዝብ በኩል ስለሚታየው የፖለቲካ
ሁኔታ በጥያቄ መልክ ያቀረብከውን አንብቤዋለሁ:: በኔ በኩል የሚታየኝ በወያኔ ጭቆና አገዛዝ ከየትኛውም ክልል ከሚኖር ኢትዮጵያዊ በከፋ የአስተዳደር ስርአት ውስጥ የሚገኘው ይኸው የትግራይ ህዝብ ነው:: ቢከፋም ቢለማም በሌሎች ክልሎች ብልጭ ድርግም እያሉ የሚታዩት ነጻ የግል ጋዜጦች ተሰራጭተው የትግራይ ህዝብ እንዲያነባቸው አይፈቀድለትም:: እንዲሁም ህዝቡ በወያኔው ድርጅት የሚታተመውን ዘር ከዘር የሚያጋጨዉንና ጠበብተኝነትን የሚሰብከውን ወይን ጋዜጣ ብቻ በየጊዜዉ እየገዛ እንዲያነብ ይገደዳል:: ስለዚህም ይትግራይ ህዝብ የነጻ ፕሬሱን ጋዜጦች አግኝቶ የወያኔን ማንነትና አላማዉን እንዳያዉቅና ሌሎች አማራጮችን እንዳያገኝ እየታፈነ ይገኛል ::
በተጨማሪም ባለፈው ግንቦት 8 ቀን 1997 ዓ/ም በተደረገው 3ኛ አገር አቀፍ ምርጫ በየክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲወች አላማቸውን በተወሰነ ደረጃ ለህዝቡ እንዲያስተዋዉቁ የተደረገ ቢሆንም የትግራይ ህዝብ ግን ከወያኔው ድርጅት ውጭ የትኛውንም የተቃዋሚ ፓርቲ አላማ ሊረዳና በየትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ ስብሰባ ላይ እንዳዪገኝ በወያኔ ካድሬወች ጫና እስራትና እንግልት ሲደርስበት እንደነበረ ተረድተናል:: ከዚህ የምንረዳው የትግራይ ህዝብ የመምረጥ መብትን እንዴት በወያኔ አምባገነናዊ ስረአት ከሌላው ህዝብ ባልተናነሰ መንገድ እየተበደለ መሆኑ ይታወቃል::
እንዲሁም በአሁኑ ሰአት ቱባ የወያኔ አመራሮች በየመድረኩ ላይ እየተገኙና የትግራይን ህዝብ እየሰበሰቡ የተማጽኖ ቃላቶችን በለቅሶ እያጀቡ በማቅረብና ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይን ህዝብ ለመበቀል የተዘጋጀ እንደሆነ የሚያሳይ አፍራሽ የሆነ ፕሮፓጋንዳቸዉን በመንዛት ላይ ቢገኙም በየስብሰባው ላይ ያገኙት ምላሽ ግን እነዚህኑ አምባገነኖች በጣም የሚያስደነግጥ ምላሽ ነው:: ይትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ እንደሚኮራና ከህዝቡም ጋር ለረጅም ዘመን በፍቅርና በአብሮነት እየኖረ እንደሆነና ይህን ከፋፋይ የወያኔ አላማ በአስቸኳይ እንዲቆም አስጠንቅቀዋቸዋል::
በአጠቃላይ ወያኔ በሌሎች ክልሎች እያደረሰበት ካለው ጫና ባልተናነሰ ሁኔታ በትግራይ ህዝብ በኩልም እየደርስሰበት እንደሆነ ይታወቃል:: ስለሆነም የትግራይ ህዝብ በምንም መልኩ ለነዚህ አምባገነኖች መጠጊያና መሸሸጊያ ይሆናል ብየ አላምንም::
ስለአፍሪካ አምባገነን መሪወች እጣ ፈንታ በቀረበው ጽሁፍ ዙሪያ ስንወያይ ደግሞ የአፍሪካ አምባገነን መሪወች በአገራቸው ህዝብ ላይ ይህ ነው የማይባል በደል ከፈጸሙ በሁዋላ በአሜሪካና በእንግሊዝ አስመሳይ አደራዳሪነት ከሀገር በሰላም ወጥተው የዘረፉትን የሀገር ሀብት ተደላድለው ሲበሉ ይታያሉ:: የዚህ ጉዳይ አብይ ምክኒያት እነዚህ አምባገነን መሪወች በስልጣን ላይ በነበሩበት ሰአት ለህዝባቸው እሬትና ጨካኝ ይሁኑ እንጅ ለአሜሪካና ለሌላው መራብ አገራት ጥሩ ተላላኪወችና የነሱ ፍላጎት አስፈጻሚወች ናቸው:: ስለዚህም በምእራቡ አለም እና በአሜሪካ እንዚህ አምባገነን መሪወች እንደ ባለውለታና ጥሩ አጋር የሚቆጠሩ በመሆናቸው አሜሪካንም ሆነ የምእራቡ አለም እነዚህን ለህዝባቸው እሾህ ለነሱ ግን ተገዥ የሆኑትን ለፍርድ አሳልፈው እንደማይሰጡ ከብዙ ተሞክሮወች ተረድተናል:: የኛም አገር አምባገነን መሪ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ህዝብ የብብት ውስጥ ቁስል ቢሆንም የአሜሪካንን ፍላጎት ጠባቂና ተላላኪ ስለሆነ አሜሪካ ለፍርድ አሳልፋ እንደማትሰጠው የታወቀ ነው:: አሜሪካ መለስን ለፍርድ የማቅረብ ፍላጎት ቢኖራት ኖሮ ይህ ግለሰብ በአሁኑ ሰአት በሀገሪቱ ላይ እየፈጸመ ያለው በደልና በግንቦቱ አገር አቀፍ ምርጫ የካርተር ማእከልና የአውሮፓ ህብረት ተወካይ አና ጎሜዝ የወያኔን አሻጥር ማጋለጥ በቂ ነበር:: ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ እና ህዝቡዋን አምላክ ስለሚወዳቸው አምባገነኖች አለማዊ አጋር ቢኖራቸውም ሰማያዊዉ አምላክ ድባቅ እንደሚመታቸዉ እምነቴ ነው::
germany
መሰረት ተስፋየ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Fri Dec 09, 2005 4:53 pm

Postby እርም » Sun Feb 12, 2006 5:55 pm

null
Long Live Ethiopia !!!
እርም
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1254
Joined: Tue Oct 11, 2005 12:21 pm
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests