የጸረ-ወያኔው የትግል ማእከል አዲስ አበባ ሳይሆን ክልሎች ናቸው

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የጸረ-ወያኔው የትግል ማእከል አዲስ አበባ ሳይሆን ክልሎች ናቸው

Postby ነቅንቄ » Wed Feb 08, 2006 12:56 am

የሸዋ እርምጥምጥ ዲሞክራት ነኝ ባይ ዉጪ ከሚገኙ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ጋር ሆነው ሁሉም አይነት እንቅስቃሴ አዲስ አበባ ላይ ተጀምሮ አዲስ አበባ ላይ እንዲጠናቀቅ አጥብቀው ይመኛሉ.ቅቅቅቅቅቅቅ ታላቁ ስህተታቸዉም የሚመነጨው ከዚህ ነው.

በነሱ ደካማ አስተሳሰብ ጸረ-ወያኔው ትግል የሚጠናቀቀዉም የተወረሱ ቤቶችን በማስመለስ እና አንዳንድ የንግድ ድርጂቶችን /ማከፋፈያዎች/ማምረቻወችን ደርግ ከአባቶቻቸው የወረሰባቸዉን ሁሉ መልሶ በመረከብ እንደሚሆን ማወቅ ይገባል. ሁሉም አይነት ትግል ይህን ድል ማረጋገጥ ካልቻለ ሀገሪቱ ብትበታተንም ግድ የላቸዉም. ሞራል ብቻ ሳይሆን ሀገርም ከመግደል አይመለሱም.

ትክክለኛው ጸረወያኔ ትግል እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ የአምቦ-የጎጃም-የጎንደር-የወሎ ህዝቦችን ወዘተ ማቀፍ ካልቻለ የወያኔን አምባገነንት ከማራዘም በስተቀር አንዳችም መፍትሄ አያመጣም. የትግሉ እምብርት ገጠሮች እና ወረዳዎች እንዲሁም ገዢ መሬቶች መሆን ሲገባቸው የሸዋው እርምጥምጥ ""ዲሞክራት ነኝ ባይ ሁሉ አፓርታማ ላይ ተሰቅሎ ቡናዉ-ዉስኪዉን እየጨለጠ በትግሉ ሲላግጥ ይዉላል.

የሚቀጥል
ነቅንቃቸው
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Postby ሳተርን » Wed Feb 08, 2006 4:04 pm

ዝጉት ፕሊስ
ሳተርን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 397
Joined: Wed Dec 28, 2005 6:12 pm

Postby እርም » Wed Feb 08, 2006 4:32 pm

ነቅንቄ ባለህ አንቲ ወያኔ አቃምህ እያደነቅሁ ነገር ገን ሀስብህ ትክክል ቢሆንም ማለት ትግል ከምሀል መጀመር ለውጤት ባያበቃን ትግሉን ልክ ወያኔያዊ ቃንቃ በመጠቀም በማውገዝህ ትክክል አይደለህም በህገር ፍቅር በመንደድ ከሆነ ርምቴን ተቀበል አሊያ አካሄድህ ብዙን የሚደግፉት ካልሆነ በፍቅር በጥበብ አስረዳ ወያኔ ለመጣል ዛሬ ህዝቡ ቅርጦ ተነስቷል በየትም ይሁን በየት እኛ የራሳችን እንወጣ እንጅ አመራር አንስጠው ግዜው ተቀይሯል መሪ የሆነው ህዝብ ነው ተመሪ የሚሆኑት ተቃዋሚዎች ናቸው
ስለዚህ በሚቀጥለው ላይራስህን አስተላክል የራስህን ድርሻ ተወጣ ባይ ነኝ
Long Live Ethiopia !!!
እርም
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1254
Joined: Tue Oct 11, 2005 12:21 pm
Location: ethiopia

Postby ነቅንቄ » Wed Feb 08, 2006 11:04 pm

ምንስ ችሎታ አላቻ ሁና ነው ለኔ መልስ የምትሰጡት??

ስለየትኛው ህብረተስብ መናገር ትችላላች ሁ??

ምንስ አቁዋም አላች ሁ እና ነው ለኔ መልስ የምጸጡት??

የማትችሉትን??የሌላች ሁን እዉቀት??

ማንበብ ከቻላች ሁም በጎ ነገር ነው.

ዘመዶች ህ አስራአምስት አመት ሙሉ ጸረውያኔዉን ትግል የእንፉቅቅ እያስኬዱት ምን አፍ አላቸው እና ነው ለኔ መልስ የሚሰጡት??

እንዲያዉም ከበከተው እና ከተንበርካኪው የሸዋ ፖለቲከኛ ይልቅ በደም የተጨማለቀው ወያኔ እየረገጠ ሲገዛን ቆይቶ በመራራ ትግላችን ባመንበት ሰአት እና ወቅት ብናስወግደው እንመርጣለን.

ይህንንም ለማድረግ የትግሉን ማእከል ከዉስኪ ጨላጩ የአዲስ አበባ ፖለቲከኛ እጂ አዉጥተን በየወረዳዎች እና ክፍለሀገራት እንዲሁም ቀበሌዎች አካባቢ ማድረግ አለብን.

ሁሉም ቀብሌዎች እና ወረዳዎች ራሳቸውን ቀስ ብቀስ ከወያኔ ነጻ እያወጡ ለጠቅላላው ድል ሁሉም እንዲነሳ እናዘጋጀዋለን. ከዚህ በፊት ግን የበከተዉን የሸዋ ፖለቲከኛ ማጋለጥ እና ማግለል የወቅቱ አጣዳፊ ተግባራችን ይሆናል.


ነቅንቃቸው
ከቡግና ወረዳ
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Postby ነቅንቄ » Fri Feb 10, 2006 3:32 am

ነቅንቄ wrote:ምንስ ችሎታ አላቻሁና ነው ለኔ መልስ የምትሰጡት??

ስለየትኛው ህብረተስብ መናገር ትችላላችሁ??

ምንስ አቁዋም አላችሁ እና ነው ለኔ መልስ የምትሰጡት??

የማትችሉትን??የሌላችሁን እዉቀት??የሌላችሁን ወኔ??

ማንበብ ከቻላችሁም በጎ ነገር ነው. ቅቅቅቅቅቅ

ዘመዶችህ አስራአምስት አመት ሙሉ ጸረወያኔዉን ትግል የእንፉቅቅ እያስኬዱት ምን አፍ አላቸው እና ነው ለኔ መልስ የሚሰጡት??

እንዲያዉም ከበከተው እና ከተንበርካኪው የሸዋ ፖለቲከኛ ይልቅ በደም የተጨማለቀው ወያኔ እየረገጠ ሲገዛን ቆይቶ በመራራ ትግላችን ባመንበት ሰአት እና ወቅት ብናስወግደው እንመርጣለን.

ይህንንም ለማድረግ የትግሉን ማእከል ከዉስኪ ጨላጩ የአዲስ አበባ ፖለቲከኛ እጂ አዉጥተን በየወረዳዎች እና ክፍለሀገራት እንዲሁም ቀበሌዎች አካባቢ ማድረግ አለብን.

ሁሉም ቀብሌዎች እና ወረዳዎች ራሳቸውን ቀስ ብቀስ ከወያኔ ነጻ እያወጡ ለጠቅላላው ድል ሁሉም እንዲነሳ እናዘጋጀዋለን. ከዚህ በፊት ግን የበከተዉን የሸዋ ፖለቲከኛ ማጋለጥ እና ማግለል የወቅቱ አጣዳፊ ተግባራችን ይሆናል.


ነቅንቃቸው
ከቡግና ወረዳ
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Postby ፎግር » Fri Feb 10, 2006 5:39 am

አትለኝም?[ :?: :?: :?: [ክቡርነትዎ, :lol: :lol: :lol:
love
ፎግር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Sun Feb 20, 2005 12:18 am
Location: united states

ለነቅንቃቸው!

Postby ልጁነኝ1 » Fri Feb 10, 2006 9:17 am

ነቅንቄ!
አንተ ሁሉን እየነቀነቅህ ነው:: ሀሳብህ ንቁ እንደማለት ነው:: አዎ መንቃት መናደድ ጥሩ ነው:: ለናት አገር ሲባል:: በተለይ ወጣቱ ትውልድ ተናዶ እና አስቦ ሲንቀሳቀስ ሲነቃ መመልከቱ እንዴት ደስ ይለኝ መሰለህ::

ግን ወንድሜን የምጠይቀው? ስም አትጥራ ሁሉም ተሰባጥረው እንዲለፉላት አድርግ ወቅቱ እጅግ አሳሳቢም ነው:: ያንን ተገንዝበህ አልሚ አደባላቂ ኃሣብ አምጣ?

ከወያኔው በኌላ የምትኖረዋ ኢትዮጵያን ልታስባት ይገባል:: ለመሆኑ አንዱ በሌላው ላይ ሲነሳ እርስበርስም ሲጠላለፉ ህዝባችን የዓለም ውራ እንደሆነ ያችኑ ትንሿም ህይወት አሳልፎ ወደ መሬትነቱ የመለስ ትላለህ ወይስ ጠእግቦ በልቶ ለብሶና ሰርቶ ተምሮ አስተምሮ አውቆ አሳውቆ ማንነቱንም ከህፍረት ዘወትር ለማኝነትን አስወግዶ ለሌሎች ለተቸገሩ ረድቶና ቢያንስ ትንሽ ደስተኛ ሁኖ ኖሮ ማለፍ እንዲችል::

ከዚያ ደግሞ አገራችን በ2025 ምድረ በዳ ትሆናለች ሠኃራ በረኃንም ትመስላለች:: በዚያ ምክንያት ለወደፊቱ "አረንጓዴው ፓርቲን " ወጣቱ ትውልድ መሥርቶ አገሩንና በውበቶቿ በአራዊቶቿና በህዝቦቿ ኑሮ ላይ የሚያተኩር አማራጭ ፓርቲ በፍጥነት መመስረት ይኖርበታል:: በዚህ ፓርቲ ውስጥ በተለይ ወጣቶች ከ1ኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርስቲው ድረስ:: ከዚያም ብልጫ እንዲኖራቸው እንዲሁም አመራሩን የሚይዙት ወጣት ልጅ አገረዶች ወይም ሴቶች ከወጣት የትምህርትና የልጅነት ጓደኛቸው ወንድ ጋር ተባብረው ቢንቀሳቀሱና ከዚያም ለህብረተ ሰቡ በመላዋ ኢትዮጵያ እያንዳንዱ ህዝብ በስሙና በቤተሰቦቹ ስም ዛፍ ተከላና ቺግኝ እያፈሉም በዚያ በመነገድ አንደኛው ክፍል ዘንባባ አብቃይ ከሆነ ጽድ እና ዝግባ ወይራ አብቃ ላልሆኑት አካባቢም እነኛ በማቅረብ ከፍተኛ ገቢም ሊያገኙ ይቺላሉ::

ይልናም በዚያ ከቀጠሉ ፎጋሪው ወያኔውን አሽቀንጥሮ በመወርወር በንጹሕ ልቦና የተመሰረተው አረንጓዴው ፓርቲ ያገሪቱን አስተዳደር መዋቅሮቺን የክፍለ ኃገሮችና ያውራጃ የወረዳ ወንበሮችን ይቆጣጠራል:: ቀጥሎም መንግሥት የሚባለውም በምርጫ ካሸነፉ በኌላ ኢትዮጵያን አረንጓዴዋ ደሴት አድርገው የምርጫቸውን ጊዜ በደስታና በፍቅር ይመራሉ:: ይህን የመሰለ ሁኔታን ከማሰብ ከማገናዘብ ከመደራጀት ይልቅ የሸዋ ሰዎች ላይ ክንፍህን ለምን እንደዘረጋህ አልተረዳሁም::

ብዙ ብዙ ምኞቶች ለኢትዮያ ማሰብ ይገባኃል:: ምክንያቱም በጭንቀት ተቆጪተህ የምትናገር ስለመሰለኝ ነው:: አንድነኛው በር በኃይለኞች ቢዘጋ ሌላኛውን በር ራስህ መስርተህ ብዙኃኑን ብታሰባስብ ለአገርህ በጠቀምካት ነበር::

አሁን ትላንትና በሌላኛው ገጽህ ላይ ወቅሰህ የጻፍክልኝን ጉዳይ ወንድሜ ወርቅሰው1 ተመልክቶ መልስ ሰቶኃል:: ጥሩ ኃሣብ ነበር:: አሁን ታዲያ የነገርኩህ የአረንጓዴው ፓርቲ የቱን ያህል ለኢትዮጵያ አስፈላጊዋ ነው:: ህዝባቺን ከእንጨት የሚጠቀመው ነገሮች ሁሉ መቀነስ አለበት:: የፕላስቲክ ፋብሪካዎች:: ወንበር ጠረጴዛና ዕቃዎች ይሆናሉ:: ቤተሰብ ለምግብ ማብሰያ እንጨት ለቀማ መቆም ይኖርበታል:: ከሰል አክሳዮች በሌላ ሥራ ሊሰማሩ ይገባል:: ምሰሶና አጣና እየተባለ የሚቆረጥ ዛፎች በህግ የተከለከሉ መሆን አለባቸው:: ጫካ ምንጠራ እሣት ልኮሳን የመሳሰሉና የሰደድ እሳትንም እንዲነሳ ሆን ብለው የሚያደርጉን ሰዎች የዕድሜ ልክ እስራት ሊበየንባቸው ይገባል::

ህዝባባችን 85% በግብርና ላይ ይኸን 3000 ዓመታት አሳልፏል:: አሁን ግን ገቢያ የሚያስገኝለት አበባዎች ማብቀል:: ሌላ የጎጆ ኢንዱስትሪዎችን በኢትዮጵያ ህብረተሰብ እንዲለመዱ ማድረግ:: እልም ባለው ገጠር ብዙኃኑ ሊሰሩት የሚቺሉ በቀላሉ ላብን የማያስፈሰስ የጎጆ ሥራዎችን ማድረግ አታክልቶቺን በብዛት ሠርቶ ለገባያ ኢትዮጵያን አልፎ ለአፍሪቃና ለዓለም ገበያ ማቅረብ:: እንዲሁም የሁዳድ እርሻዎችን በተወሰኑ ክፍሎች መመሥረት:: ለምሣሌ አርሲና ጎጃም ወሎና ጎንደርን ለዚያ ግብርናው ሥራ መተለም ገበሬውም በህብረት እንዲያርስና ሰፊ ምርት ለአገሩ እንዲያቀርብ ማንቃት:: በዚያው የቀሩት ክፍለ ሀገሮች በጫካና በቱሪስት በአዕዋፎች ሞልቶ ጎብኝዎችን ማስደሰት ከዚያ የሚገኘው ገንዘብ ቤሳዋ ሳንቲም ሳትቀር ገቢ ሆና የት እንደደረሰች መቆጣጠር ህዝብ ዕድገቱ ወደኍላው ሲሄድ ዝርፊያ መጀመሩን ማወቅና ወዲያው የመንግሥት ለውጥ ማድረግ በሕግ የምጽተዳደር አገር እንዲኖር የየአንዳንዱ ኢትዮጵያ የዘወትር ተግባሩ ሆኖ ማንኛውም ሲበድል ሲመለከቱ ነገ በነሱ ላይ እንደሆነ ገምተው ተው አይሆንም ብሎ ያንን በዳይ ባለሥልጣን ነኝ ባይ በፍርድ ቤት ባስቸኳይ ከሶ ማስቀጣት::

ስልጣን የሚይዙት ህዝቡን ለማገልገል እንጂ ሕዝቡ እነሱን ለማገልገል እንዳልሆነ በኮርሶች በተግባርና ጨዋነት እንዲነገራቸው ያንን ተላልፈው ጉቦ እና እጅ መንሻ የወሰዱ ልክ እንደ ነፍሰ ገዳይ ተቆጥረው ለመእላው ያገሪቱ ዜጎች እንዲጋለጡና ቅጣታቸውን እንዲቀበሉ::

በዚያን ጊዜ የግል ጋዜጦቺም ሆኑ የመንግሥት እና የህግ አስከባሪው ክፍል 3 ቱም ከፍተኛ ተል እኮ አላቸው::ህዝቡ በጋዜጠኞች የጉድጓዱ ሚስጢርን ፈልጎ በማግኘት በማጋለጥ አንዱ ሌላውን የሚጨቁንበት የሚዘርፍበትን ስልት አጋልጦ ህዝባቸውን እንዲነቃ ማድረግ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ለሥልጣንና ለማድረግ ሳይሆን በትክክለኛ ህዝብን ታላገለገሉ በነሱ ጊዜ ሕዝብ ሥራ አጥቶ ቢቸገር ከብቶች የሚጋጥ ጠፍቶ ቢያልቁ: ህዝብ በበሽታና በቺጋር ቢማቅቅ ያፖለቲካ ፓርቲ ሁለተኛ ለመመረጥ እንዳይችል ጋዜጣው ለህዝቡ በዕውነት ይገልጽለታል ማለት ነው::

ስነ መንግሥት ማለት አንድ አገር ሥርዓቷና የህዝቧም ህይወትን ቀጥሎም የተማረው ማሰብ የሚገባውን አስቦ በውል ለመስራት ሲረባረብ ከኔ ይልቅ ሌሎቹስ ምን ህይወት ይኖራሉ የሚል መሪና ቃፊሮቹን የሚያሳብ ምን ቀረ ብሎ የሚረዳው ያለ አግባብ በሥልጣኑ ተመክቶ በዜጎች ላይ ግፍ የማይፈጽም የአካባቢውን ጥበቃ ጥሩ አድርጎ የሚመራ:: እንዲሁም አፈሯን ያለአግባብ ቦምብ እየጣለ የማያቃጥል የአመራር ሥርዓት እንዲኖረን መጣር ይገባኃል አካባቢህን አጠገብህ የሚገኙ ወንድምና እህቶቺን በመጀመሪያ ልታነቃቸው ይገባል ቀስ እያለም ከምትኖርበት ሰፈርህ አልፈህ ከተማዋን ብሎም ጠቅላይ ግዛቷ ሳይቀር ያንተን ኃሣብ ይደግፉኃል:: ህዝብ ወደደህ እግዚአብሔር ወደደህ ነውና::

ታሊያ ግን አይጠ ሞገጡ መለሰ ዜናዊና ጓደኞቹ እይየፈጸሙ ያሉትን ዓይነት በቁጪት ተነስተህ ሸዋን በመስደብህ ብቻ ደስተኛ ሆነህ ነገ እንደ አጋጣሚ ሥልጣን ቢኖርህ አንተም ወደ ቂም በቀልነት እንዳጽተላልፍ በሚል ነው ከላይ ያስቀመጥኩልህ የተስፋ ኃሣቦቼን ልነግርህ የሞከርኩት::

አክባሪህ
ልጁነኝ1
ከ(ሰሐሊን)
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states

Postby ነቅንቄ » Fri Feb 10, 2006 11:31 pm

ሰላም ልጁነኝ

የሰጠህኝ አስተያየት እና ምክር ከመሬት ጠብ አይልም.ዉስጣዊ ስሜቴን ተረድተህልኛል.

ምክሩ ለሁሉም ይመስለኛል. ትምህርቱ ለሁሉም ነው.
ሁልጊዜ መመከር--መማር--መወቀስ ብቻ ሳይሆን እመርታዊ ለዉጥ ማሳየትም በጣም አንገብጋቢ ነው. ወቅታዊም ነው.

ስለበጎ አስተያየትህ ምስጋናየ የላቀ ነው.
አክባሪህ

ነቅንቃቸው

መካነ-ሰላም
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Postby ነቅንቄ » Mon Feb 13, 2006 12:15 am

ነቅንቄ wrote:ምንስ ችሎታ አላቻሁና ነው ለኔ መልስ የምትሰጡት??

ስለየትኛው ህብረተስብ መናገር ትችላላችሁ??

ምንስ አቁዋም አላችሁ እና ነው ለኔ መልስ የምትሰጡት??

የማትችሉትን??የሌላችሁን እዉቀት?? በሌለ ወኔ?

ማንበብ ከቻላችሁም በጎ ነገር ነው.

ዘመዶችህ አስራአምስት አመት ሙሉ ጸረወያኔዉን ትግል የእንፉቅቅ እያስኬዱት ምን አፍ አላቸው እና ነው ለኔ መልስ የሚሰጡት??

እንዲያዉም ከበከተው እና ከተንበርካኪው የሸዋ ፖለቲከኛ ይልቅ በደም የተጨማለቀው ወያኔ እየረገጠ ሲገዛን ቆይቶ በመራራ ትግላችን ባመንበት ሰአት እና ወቅት ብናስወግደው እንመርጣለን.

ይህንንም ለማድረግ የትግሉን ማእከል ከዉስኪ ጨላጩ የአዲስ አበባ ፖለቲከኛ እጂ አዉጥተን በየወረዳዎች እና ክፍለሀገራት እንዲሁም ቀበሌዎች አካባቢ ማድረግ አለብን.

ሁሉም ቀብሌዎች እና ወረዳዎች ራሳቸውን ቀስ ብቀስ ከወያኔ ነጻ እያወጡ ለጠቅላላው ድል ሁሉም እንዲነሳ እናዘጋጀዋለን. ከዚህ በፊት ግን የበከተዉን የሸዋ ፖለቲከኛ ማጋለጥ እና ማግለል የወቅቱ አጣዳፊ ተግባራችን ይሆናል.


ነቅንቃቸው
ከቡግና ወረዳ
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests