መተዛዘብ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

መተዛዘብ

Postby negoageyo » Thu Feb 09, 2006 7:56 am

ዋርካ በሳይበር ብቻ ሳይሆን በዛፍነቱም ብዙ ቻይ ነው:: አባቶች ስለቄያቸው የሚመክሩበት; አዛውንቶች ሰው የሚሸመግሉበት; እናቶች የሚጠለሉበት; ወፎች የሚሰፍሩበት; አራዊት የሚሸሸግበት እንዲያም ሲል እረኞች የሚማግጡበት ሲሆን ሁሌም አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን የሚስጥር ባለአደራም ነው::

የሳይበሩ ዋርካም ምንም እንኳን ወፍ ባይሰፍርበትም የሰዎች መመካከሪያና የአራዊቶች መሸሸጊያ ግን ከመሆን ግን አልቦዘነም::

እንግዲህ አባባሌን መቋጫ ላበጅለትና ዛሬ በራሴ አባባል "አራዊት' ለማለት ያስገደደኝን ምክንያት ልዘርዝር:: የሳይበሩ ዋርካ አንደ አገርቤቱ ዋርካ የተፈጥሮ አራዊቶችን የማስተናገዱ አቅም ባይኖረውም በተፈጥሯቸው "ሰው" በባህሪያቸው ግን 'አራዊት' የሆኑትን ያስተናግዳል::

'አራዊት' ከሰው ልጅ የሚለይበት አንደኛው ባህርይ ከራሱ ተፈጥሮ ውጭ ሌላውን በጠላትነት መመልከቱ ነው:: በመሆኑም ደግሞ ከመጠቃቱ በፊት ማጥቃትን/መሸሽን ይመርጣል:: ተፈጥሮ ቢያደለው ኖሮ ግን ከሌላው ተፈጥሮ ጋር ተላምዶና ተከብሮ ለመኖር በቻለ ነበር::

የሳይበር ዋርካ ውስጥ ስማቸውን እየቀያየሩ ፍቅርን ቀብረው ጥላቻን የሚዘሩ; መደማመጥን ዘንግተው መጮህ የሚወዱ; መማርን ጠልተው ማስተማር የሚሹ ብዙ ዋልጌዎች እየበዙ ከመሄዳቸው አልፎ "ዋርካችን የአራዊት መናገሻ' እየሆነች ነው:: ስለዚህ አዛውንት በዋርካ ላይ ምከሩ!!! [/b]
negoageyo
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 110
Joined: Thu Feb 10, 2005 2:09 pm
Location: australia

Postby ራስ ንጉስ » Thu Feb 09, 2006 8:25 am

ልክ ብለሀል ውንድሜ

ግን ብታብራራው :?: ባንተ እሳቤ ማነው አውሬ ማነው ሰው :?: ያውሬ ባይርይ የተላበሱ የሉም ማለቴ አይደለም በብዙ ስም የሚመጡ የሰው በላው ወያኔ አሽከሮች ብዙ ናቸው:

ጽሁፍህ እገሌ ተገሌ አይልም ማንን ነው :?: ሾላ በድፍን ሆነብኝ

ካክብሮት ጋር
Etiopia Tikdem!
ራስ ንጉስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 376
Joined: Mon Dec 08, 2003 8:10 pm
Location: Jupiter

Postby ወዲ_ፍቃዳ » Thu Feb 09, 2006 4:52 pm

ራስ ንጉስ wrote:ልክ ብለሀል ውንድሜ

ግን ብታብራራው :?: ባንተ እሳቤ ማነው አውሬ ማነው ሰው :?: ያውሬ ባይርይ የተላበሱ የሉም ማለቴ አይደለም በብዙ ስም የሚመጡ የሰው በላው ወያኔ አሽከሮች ብዙ ናቸው:

ጽሁፍህ እገሌ ተገሌ አይልም ማንን ነው :?: ሾላ በድፍን ሆነብኝ

ካክብሮት ጋር

ምን አይነት ---- ነህ ? አሁን እቺን መመለስ ያቅተሀል ?
አዉሬዎቹ ቅንጅት, ኦነግ ነዉጠኞች በቃ የሄ ነው ሻቢያ
ባጠቃላይ ቢሄርን የሚሰድቡ
I love Ethiopia and alll ethiopian
I like to read, wright and chut with my beloved ppl
ወዲ_ፍቃዳ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 72
Joined: Wed Dec 07, 2005 3:23 pm

Postby ራሄላ » Thu Feb 09, 2006 5:36 pm

ወዲ_ፍቃዳ wrote:
ራስ ንጉስ wrote:ልክ ብለሀል ውንድሜ

ግን ብታብራራው :?: ባንተ እሳቤ ማነው አውሬ ማነው ሰው :?: ያውሬ ባይርይ የተላበሱ የሉም ማለቴ አይደለም በብዙ ስም የሚመጡ የሰው በላው ወያኔ አሽከሮች ብዙ ናቸው:

ጽሁፍህ እገሌ ተገሌ አይልም ማንን ነው :?: ሾላ በድፍን ሆነብኝ

ካክብሮት ጋር

ምን አይነት ---- ነህ ? አሁን እቺን መመለስ ያቅተሀል ?
አዉሬዎቹ ቅንጅት, ኦነግ ነዉጠኞች በቃ የሄ ነው ሻቢያ
ባጠቃላይ ቢሄርን የሚሰድቡ
ራሄላ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 22
Joined: Sat Jan 21, 2006 11:02 am

ለራስ ንጉስ

Postby negoageyo » Thu Feb 09, 2006 10:45 pm

ወንድም ራስ ንጉስ

የፅሁፌን የመጨረሻውን አንቀፅ ብተመለከት መልሱ በቂ ይሆናል:: በተረፈ ግን አዛውንት ይምከሩ ብዬ ሃሳቤን ስለደመድምኩ የዋርካችን አዛውንት ያቀረብኩትን መረጃ መሰረት በማድረግ የሚሰጡትን አስተያየት በመረዳት ግንዛቤ ለመጨበጥ ያስችለናል ብዬ እገምታለሁ::

ከሰላምታ ጋር
negoageyo
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 110
Joined: Thu Feb 10, 2005 2:09 pm
Location: australia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests