ለከፍተኛ ስልጠና ወደ ውጭ የተላኩ የወያኔ መኮንኖች ኮበለሉ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ለከፍተኛ ስልጠና ወደ ውጭ የተላኩ የወያኔ መኮንኖች ኮበለሉ

Postby ዛግሪ » Thu Feb 09, 2006 7:57 pm

ለከፍተኛ ስልጠና ውጭ የተላኩ የኢህአዴግ መኮንኖች ኮበለሉ
http://www.tensae.net/
በአዲስ አበባ ይደረጉ በነበሩ የኢህአዴግ ከፍተኛ እርከኖች ላይ ሲሰሩ የነበሩ ሁለት መኮንኖች የላካቸውን አምባገነን ፓርቲ በመቃወም በወጡበት ቀርተዋል። ሁለቱ መኮንኖች መኮንን ደመቀ ክንፈ እና ደምሳቸው ደለለኝ የሚባሉ ሲሆኑ፤ ባለፈው ሰኞ እጃቸው ፌብሩዋሪ 6፣ 2006 ዓ.ም ለጀርመን ፌደራል የስደተኛ መቀበያ ባለስልጣን መስሪያ ቤት እጃቸውን የሰጡ መሆናቸውን ሪፖርተራችን ገልጿል።

እነዚህ ሁለት የኢህአዴግ ባለስልጣናት ወደ ውጭ አገር በሚመጡበት ወቅት የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ተሰጥቷቸው የመጡ ነበሩ። ሆኖም ግን የኢህአዴግ አስተዳደር በየጊዜው፤ በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል በመቃወም ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በመኮብለል ላይ ናቸው።
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

Postby ዛግሪ » Thu Feb 09, 2006 8:46 pm

:twisted:
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

ቢያስ ቀ.ኃ.ሥ. የማደንቃቸው!

Postby ወርቅሰው1 » Thu Feb 09, 2006 9:22 pm

ልጅ ነበርኩ በሳቸው ጊዜ ከዚያም ወጣትነቱ ተጀምሮ ስለ ፖለቲካቸው ምን የማውቅላቸው ነገር የለኝም ነበር::

በትምህር ቤቶች መዝሙር ስለ ጠቅል ጊዜ የፈረሱ ስምን እያወራን እየተኩራራን ደስ ብሎን የምንቦርቅበት ጊዜ ቢኖር የ ቀ.ኃ.ሥ. ዘመነ መንግሥት ነበር ማለት ይቻላል::

በዚያን ጊዜ የሶማሊያ ጦርነት ነበር:: እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1956 ዓ.ም. ይመስለኛል:: በካይሮ አቶ: ወልደአብ ወልደማርያም:: በሞቃዲሾ ደግሞ አቶ ጌታቸው ጋረደው ብቻ ነበሩን ስደተኞች::

የነዚህ የ2 ቱ ስደተኞች ዘመዶቻቺን ካገራቸው ወተው በሰው አገር መሆናቸውን ስሰማ እጅግ አድሮጎ ይቆጨኝ ነበር:: እንዴት አድርገው አንዷን ዕለት እንኳን ከማያውቁቸዋ ህዝብ መሐል ሊኖሩ እንደሚቺሉ ሁሉ በወጣት እድሜዬ ከልቤ ውስጥ ዘወትር እየመጣ ያብሰለስለኝ ነበር::

ከዚያ እንግዲህ ያየ66 አብዮት ሲፈነዳ ይዞ የመጣውን ጉድና አስደናቂነት ለናንተ እንድነግር አይገባኝም ቢያንስ ሳትሰሙት አትቀሩም በሚል ለአዲሱ ትውልድ ጥያቄውን እተወዋለሁ::

ወያኔዋ ክንፍ ያላት ጥቁሯ አሞራና መሪያዋን መላጣዋን እያንጸባረቀች የመጣቺው "አንቺ ትብሽዋ" አያድርስ በህዝብ ከመጠላቷም አልፎ ህዝቡ እንዳለ አገሩን እየተወላት ወጣ ለመጀመሪያም ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ስደተኝነትን በዓለም ሁሉ ሥራዬ ብለው ተያያዙት:: አገሪቱ ግን አሁንም እዚያው ዱሮ የነበረው መከራና ኌላ ቀርነት ውስጥ ነች::

ዱሮም ሞጃዎች የሚባሉ ነበሩ:: እነሱ ግን ቢያንስ ደኃን ያበሉ እንደነበረ ይረዳኛል:: ያሁኖቹስ አበስ ገበርኩ ያሰኛሉ:: ህዝቡ አያት ቅድመ አያቶቹ ካሉበት ከኖሩበትና አጻማቸው ከተቀበረበት ቦታቸው በሌሊት በግሬደር ተኝተው ሳሉ በመምጣት ቤታቸውን አስፈርሰው እነሱ ካሜሪካና አውሮጳ አጠራቅመው ይዘው አጎብዳጅም ለወያኔ ሆነው መሬት በመጠየቅ የሠፊውን ሕዝብ ቦታ በማስለቀቅ ባንጎሎ ሰርተው እየኖሩ ነው:: ይባላል::

አሁን ይህን ሁሉ ያነሳሁት: የወያኔ ግዜ ባላሥልጣናት መሰደድ ደግሞ መጀመራቸው አስደንቆኝ ነው:: አንዱ ባንዱ ላይ ሲስቅ ጀምበር ጥልቅ ይላሉ ይህ ነው:: ለኢትዮጵያ ዕድገት ማሰብ ሳይሆን የራሳቸውን ነፍስ ለማውጣት የሚደረግ ፍርጠጣ ለመሆኑ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ከሆነ ተሳስተዋል::

ይህ ሁሉ ቺግር በአገሪቷና በህዝቦቿም ላይ ሲፈጸም አብረው ተባብረው የሠሩ ስለሆነ ጊዜው ይርዘም እንጂ ሁሉም ከተጠያቂነት አይድኑም ለማለት ነው::

የሚያሳዝነኝ ግን ዘለዓለም አገር ጥሎ ከመሰደድ ይሊቅ ለምን በዳዮቻቸውን ወይም ጨቋኞቻቸውን አያስወግዱና ከዚያም ታላቅና በተለይ ለመልማቷ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዲሁም ገንዘብ ያላቸው አገር ብቻ ሳትሆን:: ህግ የሚመራት በህግም ጥላ ስር ሁሉን የሚያጣቅስ የሚያካፍል መንግሥትና ሥርዓት አብሮ ከሌሎቹ ወንድሞቻቸው ጋር በሚስጢር በመስማማት የመለሰ ዜናዊን የገለማና የበሰበሰ አስተሳሰብን ገልብጠው ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያዊያን እንድትሆን ከማድረግ ፋንታ በየ ፈረንጆቹ አገር ሥደተኛ ለመሆን ለምን መረጡ?

ፈረንጆቹ በዚህ ኃይለኛ የአየር ጠባይና የመኖር ፈተናን እኮ ያለፉት ተሰደው ሳይሆን በመደማመጥ የሚጠቅማቸውን ስላወቁ ብቻ ይመስለኛል:: ያንን ካላደረጉ አንዷን ዊንተር እንኳን ለማለፍ እንደማይቺሉ ጥሩ አድርገው ያውቁ በመሆናቸው ለዚህ ለሚሸሽባቸው አኖሪ መሆናቸው ለኛ ለሸሺዎቹ ደግሞ ምንኛ ያቺን አገር ሁሉን ለመስጠት የማትታማ ቦታንና 13 ወራት ጸሐያማ ኢነርጂ ለመኖር የማያስፈልግባት የኑክሌርም ሆነ የውውኃ ኮረንቲ ከተወሰነው በላይ የማትፈልግ ተስማምተው ከሰሩባት በሚቀጥለው አመት የምታፈራውን በጥሩ አድርጋ የምጸጥን አገር ባለመስማማት ጥሎ በመውጣት መና ማስቀረት ተገቢ አልነበረም ለማለት ነው::

ባጠቃላይ ወያኔዋ "ጃርት" መሆኗንና እንደ ጃርትም እንደምታስብ ሳልገነዘብ አልቀረሁም ስለስደተኝነት ዘወትር መልኳን እየለዋወጠች ያስተማረቺው በተለይ ወያኔዋ መሆኗን እንድታውቁት በሚል ብቻ እንጂ::

ታክብሮታዊ ወንድምነት ሠላምታ ጋር

ወርቅሰው1
ከ(ሰሐሊን)
ወርቅሰው1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4075
Joined: Wed Nov 05, 2003 9:49 pm
Location: Sehalin

Postby ዛግሪ » Thu Feb 09, 2006 9:59 pm

:shock:
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

Postby ዛግሪ » Thu Feb 09, 2006 10:12 pm

:arrow:
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

Postby ዛግሪ » Thu Feb 09, 2006 10:29 pm

:shock:
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

Postby ዛግሪ » Thu Feb 09, 2006 11:27 pm

:roll:
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

Postby ዛግሪ » Fri Feb 10, 2006 9:07 am

:arrow:
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 2 guests

cron