ልደቱ አያሌው በኢትዮጵያ ታሪክ የ ማይረሳው ፖለቲከኛ ሆነ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby ኩኒሹ » Sun Feb 12, 2006 12:42 am

I am tired of hearing this name again and again. ሰውየው 14 ዓመት በመሰለል ወያኔን አገለገለ:: አሁን ተነቃበት: ህዝቡ ሁሉ ተፋው:: አሽቀንጥሮ ጣለው:: ቢሞትም ቢኖርም የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ ያስታውሰዋል:: አሁን ልደቱ እንዲህ ሆነ : እንዲህ አደረገ : እንዲህ ያደርጋል ... ትርፉ ራስን ማድከም ነው:: I think everyone is tired of hearing this dumb name! :evil:
ኩኒሹ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Sat May 14, 2005 11:30 am
Location: ethiopia

Postby ፎንቃው » Sun Feb 12, 2006 4:56 am

''.... በሕወሐት/ኢህአዴግ ዘመን የተሰራን አንድ ነገር ሳት ብሎት የሚያደንቅና የኢህአዴግ አባል የሆነ ዘመድ ወይም ወዳጅ አለኝ ብሎ ያወራ ሰውማ እንደሱ የአገር ጠላት የለም:: ለእነዚህ ሰዎች ከጥቁርና ከነጭ ውጭ ግራጫ የሚባል ቀለም አይታወቅም:..""

አቶ ልደቱ አያሌው.. የአረም እርሻ ገጽ 40

አቶ ልደቱ በዚህ አባባሉ ዛሬ ዛሬ 'ተቃዋሚ' ነን የምትሉትን የህዝብና የሀገር ጠላቶች በሚገባ የገለጻችሁ ይመስለኛል:: ኢህአዴግ የሰራቸው ስህተቶች ቢኖሩም እንኩዋ(ታሪካዊ የህዝብ ጠላቶች እንዲደራጁና ተመልሰው ያንን ሰው በላ ስርአት እንዲቀሰቅሱበት መፍቀዱ ስህተት አንድ)... ላገሪቱ ፍትህና ዴሞክራሲ ያበረከተው አስተዋጾ እጅግ የበለጠ ነው:: ነገር ግን በናንተ/ቅንጅት አስተሳሰብ ቀድሞ ከ15 አመት በፊት የመሳደብ ቀርቶ ሀሳብን ድጋፍም ቢሆን የመግለጽ መብት (በጥናት ካልተሰጣችሁ በስተቀር) አትተነፍሱ የነበራችሁ (ኢሰፓም ሆናችሁ ጦርሰ) ሁላ ዛሬም በነገር ጉንጎናና... የሌላውን የመናገር ፍላጎት በስድብ ብዛት ልታስቀሩ ስትሞክሩ ትታያላችሁ:: ዋናው ነገር እንኩዋን የሳይበር ላይ ስድብ... እርስ በርሳችሁም የምታፍሩበት አሉባልታና ውሸት ቀርቶ ያኔም በቀን በሚሊየን ብር የከሰራችሁበት የጦር መሳርያችሁም ከትግልና ነጻነት አልበገርንም:: ይልቁንም ዛሬ ያወደሳችሁትን ነገ የምታዋርዱ.. ..ዛሬ የሰቀላችሁትን ነገ የምታወርዱ.. የዛሬ ማንዴላ የነገ ሙሶሎኒ/ግራዚያኒ ቂቂቂ...ባላችሁበት የማትቆዩ 'ወፍዘራሾች'... የበተናችሁትን የሚሰበስብ ጠንከር ያለ ሰው ፈልጉና እንደአዲስ ደግሞ ዘምሩ... ትግሬ ጠላትህ ነው/ተጠቃሚ ነው?...ይህ ካሴት አርጅቱዋል>>>>

እኔም ትግሬ ብሆን ኑሮ ከደመነፍስና ከስሜት አንጻር እንደዚሁም የወያኔን ኃይልና "የበላይነት " ተገን በማድረግ ከማገኘው ጥቅም አንጻር የሚኖረኝ አቋም ከአንተ የተለየ አይሆንም ::
ጥቅምና ጭፍን ጥላቻ የሸፈነው አእምሮ ደግሞ እውነትን ለማየትና ለመቀበል ፍላጎትም ሆነ ጊዜ አይኖረውም ::


ወዳጄ እንድሪያስ ለማንኛውም እንኩዋን ደህና መጣህ:: ሁሌም እንደምለው አሁን አሁን እንኩዋ ያንተ አነጋገር አያስከፋኝም ምክንያቱም እውነትህን ነው ወያኔን የምደግፈው ትግሬ በመሆኔ ይሆናል እንበልና ግን ከሁሉም ያቺ ደመነብስ ያልካት ቃል ተስማምታኛለች... እንዴት ብትል ዛሬ አንተን መሰል 'አብዮተኞች' እየታገላችሁ ያላችሁት በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ለመቀየር ሳይሆን ትግሬንና ከትግራይ የተዋለደ ማንኛውም አማራ.. ጉራጌ.. ኦሮሞ..ወዘተ ለማጥፋት በመሆኑ... የዚህ መንግስት መኖር ለሀገር ዴሞክራሲ ማበብ ከሚያስገኘው ጥቅም በላይ የኛ ህልውና ኢትዮጵያዊ ሆኖ መኖር... ጋር ተዛምዶ ስላለው አዎ እንደግፋለን ብቻ ሳይሆን ከሊቅ እስከ ደቂቅ እንከባከበዋለን:: እናንተ የምትገዙዋት ኢትዮጵያ ከእንግዲህ በህልምም አትታሰብም:: ኢትዮጵያ የወዳጅነት እንጂ የመከባበርና የመፈቃቀድ እንጂ........
ዛግሪ wrote:
ባንዳውን ቀጥቅጡት !! ውገሩት !! የወያኔ ተላላኪውን በሉት !!!
የኢትዮጵያን ህዝብ በገንዘብ የለወጠ :-በስልጣን የለወጠ ታሪካዊ ባንዳ !!

እንደማትሆን በደንብ አረጋግጥልሀለሁ::
Don't let yesterday use up too much of today.
ፎንቃው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 222
Joined: Thu Oct 20, 2005 6:44 pm
Location: jamaica

Postby ጥልቁ1 » Sun Feb 12, 2006 10:24 am

:lol:
እጅግ የፖለቲካ አዋቂው አቶ ልደቱ የተናገሩት ከታች ተጠቅሷል:: እስኪ ትርጉሙን ደጋግመን እናንብበው እና ; የዚህን ሰው የአመለካከት ብቃት በደንብ እንፈትነው :!: :?:

እኔ እንደገባኝ ከሆነ ; አንድ በውጭ አገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ; በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ የማይፈልግበት ምክንያት ; አገር ውስጥ የዴሞክራሲ ለውጥ ከተከሰተ ; ከአገሩ ውጭ የሚኖርበት ምንም አይነት ምክንያት የለውም ነው የሚሉን::

1ኛ) ኢትዮጵያዊያን በውጭ አገር ያላቸው የመኖሪያ ፈቃድ ; ኢትዮጵያ ነጻ እንደወጣች ይነጠቃሉ እንዴ? :lol:

2) የኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እና እድገት ከውጭ አገራት ቢበልጥ ; አንድ ሰው ወደ ኢትዮጵያ ያለመመለስ የአማራጭ መብቱን የሚያስገድድ አዋጅ ኢትዮጵያ ታጸድቃለች?

3) ከሌሎች የአደጉ አገሮች የመጡ በአደጉ አለማት የሚኖሩ የተለያዩ ዜጎች እንዳሉ አቶ ልደቱ ያውቃሉን?

አንድ ሀቅ እጋራቸዋለሁ:: ኢህአፓን አይነት የወደቁ ፓርቲዎች ; ኢትዮጵያን አስመልክቶ የሚደረግ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እነሱ ከሌሉበት ; ያንን የጸያፍ አንደበት ብእር እና ሬዲዮናቸውን ; የከረፋ ቃላት ያስተፉታል:: ነገር ግን ; በአሁኑ ሰአት አቶ ልደቱ (ክህደቱ)ን እየተቃዎሙ ያሉት ኢህአፓዎች ሳይሆኑ ; መላው ኢትዮጵያዊያን ናቸው:: ኢህአፓማ እንደ ቅንጅት አይነት አፉን የሚያዘጋን የኢትዮጵያ ተወካይ ለማጥፋት የሚሰራውን የክህደቱን አይነት ዜጋ ከልብ ያፈቅረዋል::

አየ ፈላስፋው ክህደቱ :!: :lol:

ፎንቃው wrote:
''...በፖለቲካ ትግሉ ዙሪያም ሲታይ በቁጥር ብዙ ናቸው ባይባልም ሁልጊዜ በጎ የሚሰራውን አካል እያጥላሉና እያራከሱ ቅራኔን ቁዋሚ የፖለቲካ አጀንዳቸው አድርገው የሚኖሩ ጥቂት ሰዎች አሉ:: እነዚህ ሰዎች የስደት ፖለቲካውን ስራቸው አድርገው ስለያዙ በአፋቸው ደፍረው አይናገሩት እንጂ የሚቃወሙት በአሁኑ ወቅት በአገራችን ያለውን አምባገነናዊ ስርአት ብቻ ሳይሆን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚደረገውን ትግል ጭምር ነው ለማለት ይቻላል:: ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች አገራቸውን ለቀው እድሜ ልካቸውን በስደት ለመኖር የወሰዱትን የግል መርጫ ሁልጊዜ ምክንያታዊ የሚያደርግላቸው መጥፎ ሥርአት ከኢትዮጵያ እንዳይለይ የሚፈልጉ ይመስላሉ: እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብለው ስለማያምኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄድ ህጋዊና ሰላማዊ ትግል ስለሀሳብ ክርክርና የምርጫ ውድድር መስማት አይፈልጉም:: ለእነዚህ ሰዎች ወደ አገሩ መጥቶ ማልማት የሚፈልግና መኖሪያ ቤት የሚሰራ ብቻ ሳይሆን እናት አባቱን ጠይቆ ለመመለስ የሚመጣ ሰው እንደ አገር ከሀዲና የወያኔ ባንዳ ይቆጠራል......''


ልደቱ አያሌው ''የአረም እርሻ"" ገጽ 40

ምንም እንኩዋን ኢህአዴግን አምባገነን ቢልም ለለውጥ ያለው ፍላጎት እንደነሀይሉ ሻውል '' የፍየል ወጠጤ''ን ከተቀበረበት ለማውጣት የሚሻ አይደለምና አደንቀዋለሁ::
በሉ እንግዲህ ወያኔ መሆኑ ተረጋገጠ በሉና ዝፈኑ!! እዚያ አሜሪካ ቁጭ ባላችሁ ከዶላራችሁ ጋር የጦርነት አጀንዳችሁን ለምትልኩም ማንነታችሁን ዘርዝሮ አስቀምጡዋልና አንብቡት!! የኢሀአዴግን 'አምባገነንነት.. ፍትህ አልባነትና ጸረ-አንድነት ወዘተ'' ሲጽፍ ዘመናዊ ታጋዮች የሆናችሁትን የውጭ አገሮቹን የበለጠ ገልጻችሁዋል:: መጽሀፉ ራሳችሁን ብቻ በማድመጥ በራሳችሁ ቅኝት ወደመቃብር ስለወረዳችሁቱ 'አብዮተኞች' መታሰቢያ አለመባሉ ግን ቆጭቶኛል:: የሞታችሁ ዋይታ... የለቅሶዋችሁ ቅኝት..የሙሿችሁ ዜማ ድርድር.. የመቃብራችሁ መታሰቢያ.. የድንጋይ ሀውልታችሁ ቃል.. ቢሆን ግን ማን ይከለክላል::
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

Postby ፎንቃው » Sun Feb 12, 2006 4:15 pm

ጥልቁ1 wrote::lol:
እጅግ የፖለቲካ አዋቂው አቶ ልደቱ የተናገሩት ከታች ተጠቅሷል:: እስኪ ትርጉሙን ደጋግመን እናንብበው እና ; የዚህን ሰው የአመለካከት ብቃት በደንብ እንፈትነው :!: :?:

እኔ እንደገባኝ ከሆነ ; አንድ በውጭ አገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ; በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ የማይፈልግበት ምክንያት ; አገር ውስጥ የዴሞክራሲ ለውጥ ከተከሰተ ; ከአገሩ ውጭ የሚኖርበት ምንም አይነት ምክንያት የለውም ነው የሚሉን::


አይመስለኝም... ነገር ግን የፖለቲካ ሰው ከሆንክና ስደትህ በፖለቲካ ተቃውሞ ከሆነ የምትታገለው/የምትሰደደው በሀገርህ መልካም አስተዳደር እስኪመሰረት ይሆናል::ያ ካልሆነና አንተ እንዲቁዋቁዋም ታገልኩለት የምትለው መንግስት ተመስርቶ አብሮ ለማገልገል ካልቻልክ ግን ትግሉም ስደቱም ዋጋ ቢስ ነው ለማለት ይመስለኛል::


1
ኛ) ኢትዮጵያዊያን በውጭ አገር ያላቸው የመኖሪያ ፈቃድ ; ኢትዮጵያ ነጻ እንደወጣች ይነጠቃሉ እንዴ?
:lol:

ጥቂት ሰዎች ሲል ገልጾታል'ኮ... እነዚያ ጥቂቶች ደግሞ ለውጥ ፈላጊ ይምሰሉ እንጂ እንቅፋቶች ናቸው... ኢትዮጵያ ከማን 'ነጻ' እንደምትወጣ ባይገባኝም አንድ ቀን ስደቱ የሰው ሐገር ኑሮው ድሎትም ካለው መሰልቸቱ አይቀርምና እነዚያ መልካም ኢትዮጵያውያን ሲፈልጉ ይመለሱ ዘንድ መልካም የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ተዚጋጅቶላቸዋል::

) የኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እና እድገት ከውጭ አገራት ቢበልጥ ; አንድ ሰው ወደ ኢትዮጵያ ያለመመለስ የአማራጭ መብቱን የሚያስገድድ አዋጅ ኢትዮጵያ ታጸድቃለች?


.. ለፍቶ ጥሮ ግሮ ያገኛትን ቤተሰቡን ከመደጎም ጋር ራሱን በትምህርት አሻሽሎ እየተዘጋጀ መኖሩ'ኮ አንድ ቀን አገሩ የመመለስ ፍላጎት ቅድመ ዝግጅት ነው::ታዲያ ያቺ አንድ ቀን እንዳልከው ሰላምዋ የተጠበቀ ከጥላቻና መኖቆር የጸዳች አንዱ ካንደኛው የተለየ በማሰቡ በሉት የማይባልባት 'የነዛግሪ አብዮት' ያልፈነዳባት ኢትዮጵያ መሆን አለባት::
ይቅርታ ወዳጄ ጥልቁ መስሎኝ የነበረው የመመለስ መብት ነበር አለመመለስማ ምን ችግር አለው ምንስ አዋጅ ያስፈልገዋል ወንድሜ ባለበት ይመቸው እንጂ::
3) ከሌሎች የአደጉ አገሮች የመጡ በአደጉ አለማት የሚኖሩ የተለያዩ ዜጎች እንዳሉ አቶ ልደቱ ያውቃሉን?


ሳያውቅ አይቀርም ምክንያቱም ለቅስቀሳ በተለያዩ የአለም ሀገራት መንቀሳቀሱን መጽሐፉ ላይ ጠቅሱዋልና:: የአረም እርሻ ገዝተህ አንብበው

አንድ ሀቅ እጋራቸዋለሁ:: ኢህአፓን አይነት የወደቁ ፓርቲዎች ; ኢትዮጵያን አስመልክቶ የሚደረግ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እነሱ ከሌሉበት ; ያንን የጸያፍ አንደበት ብእር እና ሬዲዮናቸውን ; የከረፋ ቃላት ያስተፉታል::
ነገር ግን ; በአሁኑ ሰአት አቶ ልደቱ (ክህደቱ)ን እየተቃዎሙ ያሉት ኢህአፓዎች ሳይሆኑ ; መላው ኢትዮጵያዊያን ናቸው:: ኢህአፓማ እንደ ቅንጅት አይነት አፉን የሚያዘጋን የኢትዮጵያ ተወካይ ለማጥፋት የሚሰራውን የክህደቱን አይነት ዜጋ ከልብ ያፈቅረዋል::

አየ ፈላስፋው ክህደቱ :!: :lol:በተረፈ ልደቱ ማንዴላም ይሁዳም የተባለው በናንተው ነው እኛን (ኢህአዴግን) አይመለከትም:: ዋናው ግን ልዩነቱን በመነጋገርና በሰከነ መንገድ መግለጽ የሚችል ወጣት መሆኑን እመለከታለሁ:: መቃወም መብት ነው: ሀሳብን በስራት መግለጽም ጨዋነት ነው::ጣቱን ቀስሮ የሰው አይን የማጥፋትን ተቃውሞ ግን አንሽከምም:: በተለይም ተቃውሞን እንደጌጥ በሚያየው ገዢው ፓርቲ ዘንድ ጠንካራ ተቃዋሚ እንዲፈጠርና ኢህአዴግም ስህተቱን እንዲያርም ሲያበረታታ ቆይቱዋል:: እነልደቱ በየመድረኩ የሚችሉትን ያህል እነሱ ለሚያምኑበት 'የመጮሀቸው' ውጤት ስርአቱ የተመሰረተበትን ዴሞክራሲያዊነት ያረጋግጣል:: ቅንጅት የትግራይ ህዝብን ከስርአቱ ጋር እያቀላቀለ መንግስት በሚያስተዳድረው ሚዲያ ሳይቀር መዝለፉ እንኩዋ እንደዴሞክራሲያዊ መብት ነበር የተቆጠረላቸው.. ስህተት መሆኑ ከጅምሩ ቢታወቅም:: ይህ ተቃዋሚን 'የመንከባከብ' የስርአቱ ችግር እነሆ እድጎ ተቃውሞ ሁሉ የህዝብና የመንግስት ንብረትን እስከማውደም 'የትግሬ' ቤት እየተባለ እስከማቃጠል ዘለቀ:: እስቲ ደግሞ ነገን እናያለን...

ፎንቃው wrote:
''...በፖለቲካ ትግሉ ዙሪያም ሲታይ በቁጥር ብዙ ናቸው ባይባልም ሁልጊዜ በጎ የሚሰራውን አካል እያጥላሉና እያራከሱ ቅራኔን ቁዋሚ የፖለቲካ አጀንዳቸው አድርገው የሚኖሩ ጥቂት ሰዎች አሉ:: እነዚህ ሰዎች የስደት ፖለቲካውን ስራቸው አድርገው ስለያዙ በአፋቸው ደፍረው አይናገሩት እንጂ የሚቃወሙት በአሁኑ ወቅት በአገራችን ያለውን አምባገነናዊ ስርአት ብቻ ሳይሆን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚደረገውን ትግል ጭምር ነው ለማለት ይቻላል:: ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች አገራቸውን ለቀው እድሜ ልካቸውን በስደት ለመኖር የወሰዱትን የግል መርጫ ሁልጊዜ ምክንያታዊ የሚያደርግላቸው መጥፎ ሥርአት ከኢትዮጵያ እንዳይለይ የሚፈልጉ ይመስላሉ: እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብለው ስለማያምኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄድ ህጋዊና ሰላማዊ ትግል ስለሀሳብ ክርክርና የምርጫ ውድድር መስማት አይፈልጉም:: ለእነዚህ ሰዎች ወደ አገሩ መጥቶ ማልማት የሚፈልግና መኖሪያ ቤት የሚሰራ ብቻ ሳይሆን እናት አባቱን ጠይቆ ለመመለስ የሚመጣ ሰው እንደ አገር ከሀዲና የወያኔ ባንዳ ይቆጠራል......''


ልደቱ አያሌው ''የአረም እርሻ"" ገጽ 40
Don't let yesterday use up too much of today.
ፎንቃው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 222
Joined: Thu Oct 20, 2005 6:44 pm
Location: jamaica

ልደቱ ይገባዋል !!!!!

Postby ቃይ » Sun Feb 12, 2006 6:04 pm

ስለ ልደቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ብዙ አውቃለውና እንደሌሎች ባሕር ማዶ ተቀምጠውና በአገር ውስጥ እየኖሩ በፍፁም ስለ ልደቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ቀርቶ ስለ አገራቸው የፖለቲካ ሁኔታ በቂ እውቀት ሳይኖራቸው ከሚመርቀው ጋር እየመረቁ: ከሚሳደበው ጋር እንደሚሳደቡት ተራ ቲፎዞዎች ልደቱ አያሌው ላይ አፌን ልከፍት አልደፍርም !! በጣም የሚገርመው ዛሬ ልደቱን የሚሳደቡት ስዎች የምርጫው ስሞን መስቀል አደባባይ ቅንጅቱ ባደረገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ልደቱን በትከሻቸው ተሸክመውት ""ማንዴላ!!""ማንዴላ!!""እያሉ ሲያወድሱት የነበሩ ናቸው በውቅቱ ያወደሱት ሌሎች ስላወደሱት እንጂ ስለ ልደቱ ጠንካራነትና ደካማነት አውቀው አልነበረም ያም ሆነ ይህ ልደቱ አንድ ግለሰብ ነው ጥሩ ሰውም ሆነ መጥፎ ሰው ለብቻውን ምንም የሚፈጥረው ታምር የለም ይልቅ እሱን እንተወውና ወንድሞቻችንንና ቤተሰቦቻችንን እየገደለና በየ እሥር ቤቱ እያጎረ እኛንም እያሳደደ የሚገኘውን አምባገነናዊ የወያኔ ሥርዓትን ለመገርሰስ ታጥቀን እንነሳ የጊዜውም አንገብጋቢ ችግር ይህ ነው ሌላውን ጊዜው ይፈታዋል አበቃው
ቃይ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Tue Dec 28, 2004 9:14 pm
Location: france

Postby ዛግሪ » Sun Feb 12, 2006 6:12 pm

ለባንዳ የሚከፈለው ዋጋ:-

ImageImage
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

Postby Fesame » Sun Feb 12, 2006 6:28 pm

ቆቁ

ዶክተር መራራ ድምጻቸው አልጠፋም የሚችሉትን በሀገር ውስጥ እየሰሩ ይገኛሉ ፕሮፊሰር በየነም ቢሆን ህብረቱን ለኢሕአፓዎች ትተውት በሀገር ውስጥ ከሚገኙ ለውጥ ፈላጊዎች ጋር አዲስ የትግል ስልት እየቀየሱ ናቸው ! አዎን ቆቁ ምን አልባት ስለሚሰሩት ስራ እኛ በግልጽ በትንተና መልክ ስለማናገኘው የሉም ሊያስብል ይችላል ግን እየሰሩ ነው......................ይገርምሀል በእስር ቤት ያሉትን ለማስፈታት ደፋቀና የሚሉት እኝህው ስዎች ናቸው::

ውጤቱን አይተህ እራስህ እንድትፈርድ እጋብዝሀለሁ..............በውጭ ሀገር የሚገኙት ተቃዋሚ ተብዪዎች ስም ማጥፋት ወሬ መፈትፈት ብቻ እንጂ ለስራ ለወሬ ግን ዋርካ በየዊብ ሳይቱ ላይ ለመለቅለቅ አንደኞች ናቸው::

ቆቁ አቶ ልደቱ አያሌው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ዘመድ ካለህ ምን እያደረገው ነው ብለህ ጠይቅ............ የታሰሩትን የቅንጅት መሬዎችን እና የሀገሪቷን አለመረጋጋት የወያኔ መንግስት ተጠያቂነት እንዳለበት በፓርላማ ውስጥ እያስገነዘበ ይገኛል.....በዲፕሎማሲውም መስክ ቢሆን ኤምባሲዎችና የተለያዪ መንግስቶችን ጋር በመነጋገር የመለስን መንግስት ለህዝብ መብት ምላሹን እንዲስጥ አየጠየቀ ይገኛል::

ብዙ ግዜ ስዎች የሌለባቸውን እየተሰጣቸው እኛም እውነቱን የሚታይበት መንገድ እየተዘጎ ትግሉ አቅጣጫውን እየቀያየረ በመምጣቱ ታክቲኮችን መቀየር የግድ ይላል::

ቆቁ ግዜ ይስጥህ እና ማን እውነት ይዞ እንደሚታገል እግዜር ያሳይህ እላለሁ በተረፈ ሁል ግዜ ነገሮችን አጥብቆ ጠይቆ እና የመጎርጎር በሀሪ ስላለህ መልሱን እራስህ ታገኛለህ ! በተረፈ በርታ

ወሬ ግን ስልችቶኛል....................ወደ ፓርላም እንዳይገቡ እያሉ ዋርካን ፓልቶክ እንዳላጣበቡ ዛሬ እረ ይፈቱ ብሎ የሚጮ ጠፋ ያው የፈረደበት የቅንጅት አብሎች እና ደጋፊዎች በውጭ ሀገርም በሀገር ውስጥ የሚገኙት ናቸው እየጮሁ ያሉ ሌላው የእራሱን መቀመጫ ለማስተካከል ደፈጣውን ይዛል ! ቆቁ በደንብ ጎርጎር እማ የሚገርም ነገር አታጣም ለራስህ ስትል !

ሞት ለወሬኞች
ሞት ለስልጣን ጥመኞች
ሞት ለአንባገነኖች
ሞት ለመለስ እና ለኢሳያስ
ሞት ለአድርባዮችና ለሆዳሞች


ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ድል ሀቅን ይዘው ለሚራመዱ
ድል ለእውነት ሲሉ የሚሞቱ
Fesame
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Fri Sep 03, 2004 11:15 pm
Location: united states

Postby ቆቁ » Sun Feb 12, 2006 6:40 pm

[/b]ፈሳሜ ለመልስህ አመሰግናለሁ

ወደፊት ስለዚህ ጉዳይ እንወያይበታለን

እኔ ነገሮችን ለማወቅ ነው እንጂ በማንኛውም ኢትዮጵያዊ ላይ ጥላቻ የለኘም የማንም ደጋፊ አይደለሁም::

ቆቁ ጎጎሪ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4235
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby Fesame » Sun Feb 12, 2006 8:35 pm

ቆቁ ምስጋናህን ተቀብያለሁ

በደንብ ጎርጎር ወንድሜ ጥሩ ይዘሀል :!:
Fesame
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Fri Sep 03, 2004 11:15 pm
Location: united states

Postby ጥልቁ1 » Sun Feb 12, 2006 10:24 pm

ፎንቃው:
የትግራይን ህዝብ ሲጨፈጭፍ የነበረው ብቸኛ የቅንጅቱ ተወካይ እራሱ ልደቱ አያሌው ብቻ ነው:: በሚከተለው ድህረገጽ ገብተህ , በስተቀኝ በኩል ስለፌደራል አስተዳደር የተደረገውን ክርክር ተመልከት >>> http://www.uedpmedhin.org/

በተረፈ; እስኪ አንድ ሌላ የቅንጅት ተወካይ ስለትግራይ ህዝብ መጥፎ የተነገረውን ቃል (ከልደቱ በቀር) ንገረን :?: :!: በነገራችን ላይ ; እንደድሮው የመሞዳሞድ ፖለቲካ ስለማይሰራ ; ከዚህ በኋላ ኢዮጵያዊያን ከሚከፍሉት መሰዋትነት በአድ ለሆኑት የትግራይ ተወላጆች የሚከራከር ፖለቲከኛ አታገኝም:: አሁን ሁሉም ነገር ለይቷል::

ልደቱም ስለትግራይ ህዝብ ያንን ሁሉ ሲናገር የነበረው ; ከወያኔ በተሰጠው ትእዛዝ ነው ብየ አምናለሁ:: ምክንያቱም ; ከዛሬው የክስ መስፈርት ላይ አንዱ ; "ከምርጫው በፊት በተደረገው ቅስቀሳ " የሚለው ይገኝበታል:: የዚህ አይን የአወጣ ሸፍጥ እውነታው የሚጋለጥ ; ልደቱ ለተናገረው ሌሎቹን የቅንጅቱን አመራሮች ; አንተን ጨምሮ መውቀሳችሁ ብቻ ሳይሆን ; ወያኔም ከክሱ ውስጥ ቀንደኛውን የትግራይ ህዝብ ተሟጋች ልደቱ ምንም አለማለቱ ነው ::


ፎንቃው ; ከአንተ ከወያኔው ጋር ምንም የሚያነጋግረኝ የፖለቲካ ጉዳይ የለኝም:: ምክንያቱም ; ከዚህ በኋላ ወያኔ እና ኢትዮጵያዊነት የሞት ሽረት ትግል የሚያደርጉት በፖለቲካ መድረክ ነው ብየ አላምንም:: ለምን ቢባል ; የወያኔ ፖለቲካ ሰው በመግደል ሲሆን ; ኢትዮጵያዊው ደግሞ ፖለቲካዊ ልዩነቱን በጠረጴዛ ዙሪያ እየፈታ ; በነጻነት በአገሩ መኖር ነው::

በተርፈ ; ሌላውን ልታጃጅል ተጠቀምበት ; ለእኔ ግን ; በኢትዮጵያ ምድር ኢህአዴግ የሚባል ግንባር ኖሮ አያውቅም ; ብቸኛው የኢትዮጵያ ገዳይ ; ከትግራይ የፈለቀው ; ሰው በላው ወያኔ ነው:: ሌላውማ ለርሀቡ ማስታገሻ ነው ; ወያኔ አድርግ ያለውን ወንድሙን የሚያርድ የሚገድል:: ወያኔ ግን ; ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳትኖር ; ከትግል የመጀመሪያ ምእራፉ ነግሮናል:: እያደረገም ነው:: ዛሬ ደግሞ ከግድያው ተከታይ ገዳይ ; በህዝብ ትግል ላይ የቀለደው ልደቱ ነው:: ወያኔ በጦር መሳሪያ ሲገድል ; ልደቱ ደግሞ ግድያውን በመላሱ እና በሚጽፈው መጸሀፍ ; የወያኔን የግድያ ሀጢያት ሊያራክስለት ጎንበስ ቀና ይላል:: ይሄው አንተ ወያኔው እራስህ የምትከራከርለትስ ; ኢትዮጵያዊነቱን ከድቶ ስለአገኘኸው አይደል :?: :!: ሌላው ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ ሁሉ ስለልደቱ የሚቃዠውም ; ወይም ፖለቲካውን በቅርቡ የተቀላቀለ መንገደኛ ነው አለበለዚያም አፉን ሞልቶ እንደአንተ በወያኔ መልክ ከመከራከር ይልቅ ; ኢትዮጵያዊ የመምሰል ታክቲክም ይመስለኛል::

ሁሉም ግን የእጁን አያጣም:: ኢትዮጵያዊነትም ለዘላለም ሲያብብ ይኖራል :!:

ቸር እንቆይ 8)
Last edited by ጥልቁ1 on Sun Feb 12, 2006 11:24 pm, edited 1 time in total.
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

Postby ጥልቁ1 » Sun Feb 12, 2006 11:21 pm

በስህተት
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

Postby ነቅንቄ » Sun Feb 12, 2006 11:38 pm

ሰላም ማንበብን የመሰለ መስተዋት በየትም አይገኝም.ሁሉንም ወለል አድርጎ ያሳያልና.


ጥልቁ1 wrote:........... ነገር ግን ; በአሁኑ ሰአት አቶ ልደቱ (ክህደቱ)ን እየተቃዎሙ ያሉት ኢህአፓዎች ሳይሆኑ ; መላው ኢትዮጵያዊያን ናቸው::...............
ይህ በጣም በጣም የተጋነነ እና መጠን የለለው ስህተት ነው.ቢያንስ ቢያንስ እኔን -ከቤተሰቦቼ አንዱን --ወይ ጎረቤቴን ወይም አንድ የማዉቀው ግለስብን እንኩዋን ማጠቃለል ያልቻለ ክፍል ይህን ያህል አግዝፎ መላው ኢትዮጵያዊ ብሎ ማለት በጣም ስህተት ነው. ቅንጂት የሚባል ድርጂት ነበር.አባላት እና ደጋፊዎች አሉት.ፒርየድ.

ኢህአፓማ እንደ ቅንጅት አይነት አፉን የሚያዘጋን የኢትዮጵያ ተወካይ ለማጥፋት የሚሰራውን የክህደቱን አይነት ዜጋ ከልብ ያፈቅረዋል::.................በዚህ መሰረት አሁን 1.ቅንጂት 2.ኢህ አፓ 3.ኢሀዴግ.4.ኢዴአፓ አሉን ማለት ነው. እነዚህ የሚያደርጉት የስልጣንም ይሁን የፖለቲካ ሽኩቻ እዚያው እርስ በርሳቸው ቢፈልጉ ይባሉ እንጂ ዜጋው በምን ሂሳብ ይጨፈጨፋል?? አሁን እኮ የምንፈልገው ነገር ቢኖር ነጻ መዉጣት የምንፈልገው ከወያኔ ሳይሆን ከፖለቲካ ድርጂቶችም ጪምር እየሆነ ነው.
እነዚህ እርስ በርስ መስማማት የምይችሉ 7000000ህዝብ እንዴት ሊያስማሙ ይችላሉ??

በፍጹም እምነት የለንም.

.........ፎንቃው ከአንተ ከወያኔው ጋር ምንም የሚያገናኝኝ የፖለቲካ ጉዳይ የለኝም......ለምን ቢባል የወያኔ ፖለቲካ ሰው በመግደል ሲሆን ኢትዮጵያዊውደግሞ ፖለቲካዊ ልዩነቱን በጠረጴዛ ዙርያ እየፈታ በነጻነት በአገሩ መኖር ነው.


ጥልቁ ይቺ ምኞትህ የኔም ምኞት ናት. ግን ላለፈው አስራምስት አመታት እና ምናልባትም ለሚቀጥለው 1000አመት በኢትዮጵያ ገቢራዊ ሆና የማያት አይመስለኝም. ዛሬ እና ትላንት ያየናቸው ሁኔታዎች በሙሉ ይህን የሚያበስሩ ሳይሆን ሀገሪቱን ለማንም ቅንዳሻም ካድሬ ሁሉ እያስረከብን የምንፈረጥጥ ይመስለኛል.


ለፎንቃው

.........በተረፈ ልደቱ ማንዴላም ይሁዳም የተባለው በናንተው ነው እኛን (ኢህአዴግን) አይመለከትም::


ምንም እንኩዋን ጸረ-ኢሀዴግ ብሆንም የፎንቃው መልስ አሰጣጥ አርኪ ስለሆነ አደንቀዋለሁ. የጠላት ጀግና እወዳለሁ.የኔን ክንድ እስኪቀምሱ ድረስ.

በይሉል

መርሳ-ተክላይ
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Postby ዛግሪ » Sun Feb 12, 2006 11:53 pm

ዛግሪ wrote:ለባንዳ የሚከፈለው ዋጋ:-

ImageImage
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

Re: ልደቱ ይገባዋል !!!!!

Postby ነቅንቄ » Sun Feb 12, 2006 11:53 pm

ቃይ wrote:......... በጣም የሚገርመው ዛሬ ልደቱን የሚሳደቡት ስዎች የምርጫው ስሞን መስቀል አደባባይ ቅንጅቱ ባደረገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ልደቱን በትከሻቸው ተሸክመውት ""ማንዴላ!!""ማንዴላ!!""እያሉ ሲያወድሱት የነበሩ ናቸው ...........ትልቅ ማገናዘቢያ ነው. ዛሬ ዛሬ በንጽጽር መማር ስለቻለን ፖለቲካዉን በሞኖፖል መያዝ ለሚፈልጉ ብርቱ ማስጠንቀቂያ ደወል ሆኖ ያገለግላቸዋል.

ነቅንቄ

ከበይሉል--የወሎ ጥንታዊ ወደብ
""STRIVE FOR EXCELLENCE, NOT PERFECTION."

By somebody
ነቅንቄ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 269
Joined: Tue Mar 01, 2005 10:57 pm
Location: bet-amhara

Postby ዛግሪ » Sun Feb 12, 2006 11:54 pm

ዛግሪ wrote:
ዛግሪ wrote:ለባንዳ የሚከፈለው ዋጋ:-

ImageImage
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests