ልደቱ አያሌው በኢትዮጵያ ታሪክ የ ማይረሳው ፖለቲከኛ ሆነ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby ጥልቁ1 » Mon Feb 13, 2006 8:18 am

ነቅንቄ:
ለመቀበል የተቸገርሀቸው ነጥቦችን እረዳቸዋለሁ:: ለማባርራት ያህልም :-

'መላው ኢትዮጵያዊ' የሚለውን ቃል የተጠቀምሁት ; ከማጋነን እና ከፕሮፖጋንዳ አንጻር አይደለም:: እንደፕሮፖጋንዳ የሚያቅለሸልሸኝ ነገር የለም:: ሰሞኑን አንዳንድ ተጋንነው የሚወጡ የድህረ-ገጽ ላይ ዜናዎችም ; እጅግ እያሳፈሩኝ እንዳሉ ልናገር እወዳለሁ:: ለእኔ "ኢትዮጵያ" የሚለውን የማንነቴን መግለጫ ; በጎሳ ሳይከልስ ; በበሰለ የፖለቲካ መዋቅር ; ለምርጫ የተወዳደረ ብቸኛ ፓርቲ ቅንጅት ብቻ ነው የነበረ:: መላው ኢትዮጵያዊ ለማለት የምፈልገውም ; ኢትዮጵያዊነቱን ብቻ የሚያስቀድም እንጅ ; ጠላቱ በፈበረከለት የጎሳ ፖለቲካ እራሱን የቀፈደደውን አይደለም:: (እዚህ ላይ ያለመግባባት መብት አለህ ; ለእኔ ግን ሀቁ ; የኢትዮጵያዊነቴ አጀንዳ ተጠቅልሎ ያለው ; በቅንጅት የፖለቲካ ፕሮግራም ውስጥ ነው)

በዚህ መሰረት አሁን 1.ቅንጂት 2.ኢህ አፓ 3.ኢሀዴግ .4.ኢዴአፓ አሉን ማለት ነው . እነዚህ የሚያደርጉት የስልጣንም ይሁን የፖለቲካ ሽኩቻ እዚያው እርስ በርሳቸው ቢፈልጉ ይባሉ እንጂ ዜጋው በምን ሂሳብ ይጨፈጨፋል ?? አሁን እኮ የምንፈልገው ነገር ቢኖር ነጻ መዉጣት የምንፈልገው ከወያኔ ሳይሆን ከፖለቲካ ድርጂቶችም ጪምር እየሆነ ነው .
እነዚህ እርስ በርስ መስማማት የምይችሉ 7000000ህዝብ እንዴት ሊያስማሙ ይችላሉ ??በዚህ ሀሳብህ ; 100% እስማማለሁ:: የልደቱን ክህደትም ከማመሰግንበት አንዱ ; ለስልጣን ቢበቃ ከመንግስቱ ሀይለማሪያም በአላነሰ መልኩ ; አንድ ቀን የሚቃዎሙትን የካቢኒ አባላት በሙሉ ሊረሽናቸው እንደሚችል ስለታዘብሁ ነው:: ለዚህ ምስክሬም ; የአሳተመው (በተከሰሱት ላይ የምስክርነት ቃል ያለው መጽሀፉ ነው):: በተጭማሪም ; ከምርጫው በኋላ የቅንጅቱ አመራሮች ; የአዲስ አበባን እና ሌላውንም የኢትዮጵያ ህዝብ ; ፓርላማ ስለመግባት አለመግባት ማወያየት አልነበረበትም የሚል ቃል ተናግሯል:: ይህ የሚያሳየን እንግዲህ ; አንዴ በህዝቡ ትክሻ ላይ ተረማምዶ ለስልጣን ቢበቃ ; ከዛ በኋላ ህዝቡ ምንም የመቃዎምም ሆነ ሀሳብ የመስጠት መብት አይኖረውም ማለት ነበር::

የኢትዮጵያ ህዝብም ; ንቁ የፖለቲካ አገናዛቢ እንጅ ; የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርኮኛ ተከታይ መሆን የለበትም ከሚሉት አንዱ ነኝ:: ኢህአፓን ያነሳሁበት ምክንያት ; ከምርጫው በፊት ጀምሮ እስከ የቅንጅቱ አመራሮች እስር ቤት መግባት ድረስ ; የመርዝ ለሀጩን ሲዘረጋ የነበረው ; ከወያኔ ይልቅ በቅንጅቱ አመራሮች ላይ እና በድርጅቱም ላይ ነበር:: ለዛ ነው ; እጅግ እነሱን ማሰብ እራሱ የሚያቅለሸልሸኝ:: እንጅማ የፖለቲካ ፓርቲ ተከታዩ በበዛ ቁጥር ; ሁሌም አገሪቱ የህዝቡ መሆኗ ይቀርና ; የካድሬ መፈንጫ ትሆናለች ማለት ነው::

እዚህ ላይ ግን ; ቅንጅቱ ከሚያኮራኝ ስራው አንዱ ; ምርጫውን አሸንፎም ይሰብክ የነበረው ; እኔ መንግስት ልሁን ሳይሆን ; በገለልተኛ የምርጫ አካል አማካኝነት ; ሁሉም ፓርቲዎች በነጻነት ወደ አገራቸው በመመለስ ተወዳድረው ; ህዝቡ ያሻውን ይምረጥ ማለቱ ነው:: የትላንቶቹ እነኢህአፓ እና መኢሶን ግን ; ህዝብን አባልተው ደርግን በኢትዮጵያ ላይ ጭነው ; የድሀን ልጅ አስከሬን አስታቅፈው ; እነሱ ወደ ውጭ አገር ወጡ::

ዛግሪ ; እባቡን ከመጨፍጨፉ ላግዝህ? :)
:idea:
ጥልቁ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 767
Joined: Tue Jan 27, 2004 4:32 am
Location: bhutan

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests