ስለ ኢትዮጵያ ድንበሮች

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ስለ ኢትዮጵያ ድንበሮች

Postby ወርቅሰው1 » Sun Feb 12, 2006 1:08 pm

ስለ ሁመራ አካባቢና እንዲሁም በገለብና ሃመር ባኮ በኩል ወያኔው ቆርሶ ለሱዳን እጅ መንሻ ስለ አቀረባቸው አካባቢዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠይቆ ነበር ወይ?

በመሆኑም የነዚህን ድንበሮቻቺን ጉዳይ አጣርተን ለማወቅ ስለሚያስፈልገን ኢትዮጵያዊያን በሙሉ አስተያየታቺሁን እንድጸጡበት የተከፈተ የመወያያ ገጽ ነው::

ካክብሮትም ጋር

ወርቅሰው1
ከ(ሰሐሊን)
ወርቅሰው1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4075
Joined: Wed Nov 05, 2003 9:49 pm
Location: Sehalin

Postby ዛግሪ » Sun Feb 12, 2006 2:13 pm

ውድ ወርቅሰው 1
ወቅታዊ አርእስት ነው የከፈቱት::

ቅጥረኛው የወያኔ ቡድን ገና ሲጠነሰስ ዋና አላማውና(objective) ግቡ (goal) በሂደት ቀስ በቀስ ኢትዮጵያን መሸራረፍ:- መቆነጣጠር:- መሸርሸር:- መፈረካከስና መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ የሚለው ስም እንዲጠፋ ማድረግ ነው:: አስታውሳለሁ ባንድ ወቅት የሌቦች ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም ሳያፍር እንዲህ ብሎ ነበር:-'' ከጅቡቲ በስተቀር ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር የድምበር ማካለል ስራ ይጠብቀናል'' ብሏል:: በዚህም መሰረት የኢትዮጵያን ምድር ለኬንያ:- ለሱዳን:- ሱማሊያ:- ኤርትራ ጎረቤት አይደለችም እንጂ ለግብጽም ጭምር እንደዳቦ እየቆራረሱ በማደል የኢትዮጵያን ህዝብ ከሁሉም የጎረቤት ሀገራት ጋር በማጋጨት ወደማያባራ የዘላለም ጦርነት ውስጥ መክተትና እንደሱማልያ በጎሳ አለቃ የሚተዳደሩ ቁርጥራጭ ግዛቶች እንዲፈጠሩ ነው ህልማቸው:: ሥለሆነም ኢትዮጵያን እንወዳለን የምንል ሁሉ ስሟን ጠብቀን ለማቆየት የምንችለው የራሳችን የሆነ ድንበር :-አንድነት አስከባሪ ጦር ሰራዊት ያስፈልገናል:: ለዚህም ተግባራዊነት ቀን ተሌት መስራት ይጠበቅብናል::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
.....
ዛግሪ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 966
Joined: Sat Dec 17, 2005 11:31 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 10 guests