የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች...

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Postby ክቡራን » Fri Nov 09, 2012 10:39 pm

እኔ ያልገባኝ ነገር (ስለገረመኝ ነው በነገራችን ላይ ) ይሄ ቪዲዮ በሚያስደንቅ ሁኔታ ቡዙ ሰው ኦንላይን ላይ ይመለከተዋል በኔ መረጃ ይሄ ቪዲዮ እስካሁን ወደ አስራ አምስት ሺ ጊዜ ተጎብኝቷል::ይሄ ለኔ አዲስ ነው.. እንዴት ነው ሰው ይሄን ቪዲዮ ከሌሎች ቪዲዮዎች ለይቶ ሊያፈቅረው የቻለው..? የሌሎች አርቲስቶች ቪዲዮዎች, የደራሲያን, የኪነ ጥበብ ሰዎች ቪዲዮዎች.. እንደ ሙሴ ነርሲሲ ናልባንዲያን ያህል አልተጎበኙም...ከገረመኝ ነገር አንዱ ስለሆነ ነው እዚህ ያመጣሁት...እስኪ እቺን ጠቅ አድርጉ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby የተሞናሞነው » Fri Nov 09, 2012 11:04 pm

ሰላም ክቡራን :lol:

ቆይማ ልንገርህ...ሲሪየስሊ አስተዳደጌ ይሁን ሀይማኖቴ ወይም አካባቢያዊ ባህሌ ሰው በተለይ ደግሞ ታላቆችን አባቶችና እናቶችን እንዲሁም እህቶቻችንን በጣም አክባሪ ነኝ:: ግን አንድ ችግር አለብኝ....የሆነ ሰው በለተለይም በእድሜውና ባለበት ሁኔታ መድረስ ካለበት መድረስ ባይችል እንኳን ማሰብ ያለበትን ማሰብ አለበት እላለሁ:. ከዚያ ወርዶ ሳገኘውም እንደ ባህሌ ማክበር ነበረብኝ....ግን ሊሆን አልቻለም.:: አንተን እዚህ ዋርካ ካወቅሁህ ጀምሮ (በእድሜ አርባዎቹ መጨረሻ ትመስለኛለህ) በእድሜህ ማክበር ሲገባኝ ግን ሊሆን አልቻለም እንቅሀለሁ :lol: ማርያምን እንቅሀለሁ (ሶሪ ብሮ :cry: ) አነጋገርህ...አስተሳሰብህ...ጨዋታህ...ሽሙጥህ....ፖለቲካህ....አጻጻፍህ....ሁሉም እጅ እጅ ያለ የሞተ ነው----እናም ደግሞ ከአጻጻፍህ ጀምሮ የሞትህ እንደሆንህ ሲነገርህ የበለጠ አይገባህምና የበለጠ ናቅሁህ :shock: ይህ ማለት ግን እጠላሀለሁ ማለት አይደለም....እውነቱንስ አልጠላህም:: ግን ያው ምን ታደርገዋለህ....ስለምንቅህ ዋርካ ገብቼ ገና ስምህን ሳነብ እንኳን ያ ክቡራን የተባለ አፈር ምን ጠፈጠፈ ይሆን እንጅ ጻፈ እንኳን ብዬ አላውቅም :lol: በእውነት እኮ ነው የምልህ.....ምን እንደነካኝ እኮ :lol: :lol: እና ስሜን በየጠፈጠፍከው ቦታ ሁሉ ብታነሳው ወደህ አይደለም....አፈርነትህን አውቄብህ እንደምንቅህ ስለተረዳህ ነውና ብሮ :D ኤኒዌይስ እግረ መንገዴን እችን ግጥም እየተቃጠልክ ታነባት ዘንድ ጋብዤሀለሁ....እንዲህ ጽፈን ነበር....ገናም እንጽፋለን :lol: የሆንህ አመድ :lol:

ሰላም ላንተ ይሁን :wink: ወንድም ነን አይዞህ :lol:

የመለስ ቅዠት


አንዴ ባህር አንዴ ገደል

ይጥለዋል ዥው አድርጎ

አጠገቡ ግዙፍ ሰዉም ያያል

ይደነግጣል በርግጎ

እድሜ ጠገብ የጽድ ዛፎችም

ይስቁበታል ያስካካሉ

እንደሰው አጉረጥርጠው

ጦር በሱ ላይ ይሰብቃሉ

በደስታ ይንጫጫሉ ይጮሃሉ

የጫካው ወፎች በሙሉ


ደግሞም አዬ

ያንበሳ ደቦል እያገሳ መጥቶ

ልቡን ፈልቅቆ ሲጥላት

ከደረቱ መሃል አዉጥቶ

ሚስቱንም አያት

ፊቷ ጠወላልጎ ከሳስቶ

በወርቅ በሀምራዊ አጊጣ ሳይሆን

አገልድማ ቡትቶ


ትንሽ በራ ራሱንም አያት

ካንገቱ ተገንጥላ

በዛፎች ቅርንጫፍ ላይ

እንደ ቅል ተንጠልጥላ

የህዝብ ፉከራ እልልታም ሰማ

በሀገሪቱ በሞላ


ብዙ ነገስታትንም አዬ

እስከ ጃንሆይ ሃይለስላሴ

በዙፋናቸው ተቀምጠው

ታጂበው በክብር በዉዳሴ

በጳጳሳት ተከብበው

በቀሳዉስት ዝማሜና ቅዳሴ


በዚያ ሁሉ መሃል ነበር

'ተነስ እንጂ ምነው '?

የአጋዚዉን አለቃ

ለስብሰባ ለምክክር የቀጠርነው

ዛሬ እኮ ነው '

የሚል የሴት ድምጽ ያባነነው

ከጩሀቱ ከመዓቱ

ከጣር ከጭንቀት የገላገለው


ነቅቶ ትንሽ ልቡ ድው ትር እያለች ተሸብራ

በላብ ተዘፍቆ

ሃፍረተ ስጋው እየታየች ቀስቃሹንም ሳይፈራ

እየተንደረደረ ሄዶ

ከፍቶ ማዬት ጀመረ አልጀዚራ ::
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Nov 09, 2012 11:58 pm

ሠላም ታላቁ ክቡራን

እንኳን ደስ አለህ ብዬ ደስታዬን ልገልፅልህ ነው የመጣሁት :!:

ትንንሽ ከብቶች 'እንንቅሀለን" ሲሉህ የሚያመለክተው ነገር ቢኖር የክብርህን ታላቅነት ነው :D "ለአህያ ማር አይጥማትም" ብሏል የሀገሬ ሰው :lol:

ከእናቴ ጋር ሰፈሩን ማማት ናፈቀኝ; አንዴ መሄዴ ነው ቻዎ...ከዛ ደግሞ መጣሁህ እያለ ኡኡ ቢልም ዞር ብሎ የሚያየው ያጣ ሰው ስለአስተሳሰብ ሲያወራ በሳቅ ያንፈራፍራል :lol: :lol: :lol:

በርካታ አንባቢዎች እንዳሉህ ዋርካ ራሱ ምስክር ነው...በፃፍክ ቁጥር እግር እግርህ ስር የሚከተሉህ አድናቂዎችህ ብዛት :D ለዛውም አንብቡኝ ብለህ ሳታስገድዳቸው; የፅሁፍህ ጥልቀትና እውነት ጎትቶ የሚያመጣቸው......ያው እንደፈረደባቸው ቤትህ ተሳልመው; ሳያስቡት አድናቆታቸውን ገልጸውልህ ይወጣሉ :D

አክባሪህ
ዳግማዊ ዋለልኝ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby የተሞናሞነው » Sat Nov 10, 2012 12:56 am

አሁን ቀጥየ ደግሞ በአባይ ጸሀየ ላይ ወይስ በስዩም መስፍን በየትኛው ላይ ልግጠምበት ይሆን :roll: :lol: ቆይ መንፈሳችን እንዳምጥና እንጽፋለን :roll: አለነ ለማለት ነው :lol:

ትንቢተ- ሞንሟናው ምዕ. 1 ቁ. 1'ን ግን ዴጋግማችሁ አንብቧት :roll: መለስ ከመሞቱ ከአንድ አመት በፊት የተነበይነውን በግጥም ያስቀመጥናት ትንቢታችን እንዴት እንደተፈጸመችም ቁርምድ ብላችሁ ስትፈልጉ በዜማ ካልሆነም እንዲሁ አንብቧት እንላችኍለን :lol: :lol: :lol: :lol:

የመለስ ቅዠት


አንዴ ባህር አንዴ ገደል

ይጥለዋል ዥው አድርጎ

አጠገቡ ግዙፍ ሰዉም ያያል

ይደነግጣል በርግጎ :cry:

እድሜ ጠገብ የጽድ ዛፎችም

ይስቁበታል ያስካካሉ

እንደሰው አጉረጥርጠው

ጦር በሱ ላይ ይሰብቃሉ

በደስታ ይንጫጫሉ ይጮሃሉ

የጫካው ወፎች በሙሉ


ደግሞም አዬ

ያንበሳ ደቦል እያገሳ መጥቶ

ልቡን ፈልቅቆ ሲጥላት

ከደረቱ መሃል አዉጥቶ :cry: :cry:

ሚስቱንም አያት

ፊቷ ጠወላልጎ ከሳስቶ

በወርቅ በሀምራዊ አጊጣ ሳይሆን

አገልድማ ቡትቶ :cry: :lol:


ትንሽ በራ ራሱንም አያት

ካንገቱ ተገንጥላ :cry:

በዛፎች ቅርንጫፍ ላይ

እንደ ቅል ተንጠልጥላ :cry: :lol:

የህዝብ ፉከራ እልልታም ሰማ

በሀገሪቱ በሞላ


ብዙ ነገስታትንም አዬ

እስከ ጃንሆይ ሃይለስላሴ

በዙፋናቸው ተቀምጠው

ታጂበው በክብር በዉዳሴ

በጳጳሳት ተከብበው

በቀሳዉስት ዝማሜና ቅዳሴ


በዚያ ሁሉ መሃል ነበር

'ተነስ እንጂ ምነው '?

የአጋዚዉን አለቃ

ለስብሰባ ለምክክር የቀጠርነው

ዛሬ እኮ ነው '

የሚል የሴት ድምጽ ያባነነው

ከጩሀቱ ከመዓቱ

ከጣር ከጭንቀት የገላገለው


ነቅቶ ትንሽ ልቡ ድው ትር እያለች ተሸብራ

በላብ ተዘፍቆ

ሃፍረተ ስጋው እየታየች ቀስቃሹንም ሳይፈራ :lol:

እየተንደረደረ ሄዶ

ከፍቶ ማዬት ጀመረ አልጀዚራ :::lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ክቡራን » Sat Nov 10, 2012 1:57 am

ታላቁ ዳግማዊ እንደምን አለህልኝ ወንድም አለም. 8) ይሄ በከቻ አሳስቦኝ መልስ እንድሰጠው ዳሌውን እየመጣ ሲያነጠር አየሀው ..? ይሄ የናቱ ልጅ.. :lol: ሌባን ሌባ አካፋን አካፋ ማለት ግድ እንደሚል አላወቀውም....ይሄ አብሲት ጠጪ!! :lol: እኔ የሚገርምህ ረስቼው ነበር..ባለፈው አንድ ቤት ውስጥ ስገባ አድሚን ለምኖኝ ተመለስኩ ሲል...በሳቅ ብዛት ልሞትልህ ነበር...! ! ተሰናብትኩ ብሎ ሄዶ ቂቅ በሚል ስም ለሀጩን ሲያዝረከርክ እንዳላየነው....ሁሉ!! ይሄ ለሀጫም:: እንደው ዳግማዊ በህይወትህ ሙሉ ምንጭርክን የሚል
የቦሌ ልጅ ሰምተህ ታውቃለህ...? ምናለ በማንነታችን ብንኮራ!! የማርቆስ ልጅ ነኝ የዳንግላ ልጅ ነኝ እያለ ቢጽፍ እኮ ባከብረነው ነበር....ይሄ በራሱ የሚያሳይህ ምን ያህል ኢንፍሬይተሪቲ ኮምፕሌክስ ውስጥ መሆኑን ነው:: ቂቅ ነኝ ከቦሌ...!!! እኔን ቦሌ ያድርገኝ ቡልቡላ ፊት!! :lol: ሰላም አምሽልኝ እስኪ ዳግማዊ:: 8) ቂቅና መንማናው አንድም ሁለትም ሆነው እስካሉልን ድረስ አንደበደርም. አብሽርልኝ :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Sat Nov 10, 2012 11:41 pm

ኢትዮጵያዊነት ምንድነው..? "ኢትዮጵያዊነት የቆዳ ቀለም አይደለም...ኢትዮጵያዊነት እምነት ነው..."" መራዊ ስጦት እኮ ነው..ስለ ሙሴ ነርሲስ ናልባንዲያን ምስክርነቱን ሲሰጥ..
ስለ አቶ መራዊ ስጦት ለማወቅ እቺን ጠቅ ያድርጉ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Wed Nov 14, 2012 10:17 pm

ባለፈው እኔ የምኖርበት ከተማ አንዲት የኢትዪጵያውያን ምችት ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነብር:: አንዲት ልጅ የ12 ወይም 13 አመት የምትሆን በቅርብ ኢትዮጵያን ከወላጆቹ ጋር ጎብኝታ ስለነበር ስላየችው ነገር አስተያየት እንድትሰጥ ፕሮግራሙን በሚመራው ትጠየቃለች::

ጠያቂው ጀመረ.."" ኢትዮጵያ እንዴት ናት ? "" እንግዲ ቃለ ምልልሱ ባማርኛ ነው..
እሷም ደስ በሚል አማርኛ ( ""ጥ"" ን ) ""ት"" እያለች ግን እያጣፈጠች ትመልሳለች:: እዚህ አገር ተወልዳ እንዳደገች ልብ ይሏል::

"" ትሩ ናት"" ደስ ይላል...

""ማለቴ ምግብ እንዴት ነው ምን ምን በላሽ..?"" ጠያቂው ቀጠለ::

"" ዶሮ ወት...ስጋ ወት... ከይ ወት....ሁሉም ትሩ ነው ይታፍታል.."" ተጨበጨበላት...ልጅት ደስ እያላት እየሞቃት መጣ... :D

"" ይሀውልሽ እዚህ አገር እንደምታውቂው ከምግብ በኌላ እንደ ዴዘርት ኬክ ወይም ሌላ ቀላል ነገር ይበላል...ኢትዮጵያ ከምግብ በኌላ የሚቀርብ ነገር አለ.."?"

ልጅት አላመነታችም.....መልስ ሰጠች
"" አዎ አለ...""

""ምን..? ""

""ገንፎ!!"" :D

ቤቱ በሳቅ ተሞላ :: እኔ አልሳኩም ብቻ ቀስ ብዬ ባይኔ የልጆቿን ወላጆች መፈለክ ጀመርኩ:: :D :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby የተሞናሞነው » Wed Nov 14, 2012 11:06 pm

ስማ እንጂ መሀይሙ ወዳጄ :roll: አሁን እኮ መላምትን በሆሄያት ግድፈት ልትተቸው ሞክረህ አንብቤ ከት ከት ብዬ ሳቅሁና ወደ እዚህ እበትህን እምትከምርበት ቤትህ መጣሁ...እናም እንዲህ በቀይ አንቆጠቆጥኩልህ :lol: መሀይም እኮ ደፋር ነው...ጭራሽ አንተ ሰውን በአማርኛ አጻጻፍ ልትተች :lol: እምዬ ማሪያም :roll: ቆይ እስኪ የተቸህበትን ጽሁፍ ልየው...ቸኩዬ ነበር ያነበብሁት.... እርግጠኛ ነኝ ስህተት እንደማላጣበት...ስትፈጠር እኮ አንተ ራስህ ስህተት ነህ :lol:

ክቡራን wrote:ባለፈው እኔ የምኖርበት ከተማ አንዲት የኢትዪጵያውያን ምችት ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነብር:: አንዲት ልጅ የ12 ወይም 13 አመት የምትሆን በቅርብ ኢትዮጵያን ከወላጆቹ ጋር ጎብኝታ ስለነበር ስላየችው ነገር አስተያየት እንድትሰጥ ፕሮግራሙን በሚመራው ትጠየቃለች::

ጠያቂው ጀመረ.."" ኢትዮጵያ እንዴት ናት ? "" እንግዲ ቃለ ምልልሱ ባማርኛ ነው..
እሷም ደስ በሚል አማርኛ ( ""ጥ"" ን ) ""ት"" እያለች ግን እያጣፈጠች ትመልሳለች:: እዚህ አገር ተወልዳ እንዳደገች ልብ ይሏል::

"" ትሩ ናት"" ደስ ይላል...

""ማለቴ ምግብ እንዴት ነው ምን ምን በላሽ..?"" ጠያቂው ቀጠለ::

"" ዶሮ ወት...ስጋ ወት... ከይ ወት....ሁሉም ትሩ ነው ይታፍታል.."" ተጨበጨበላት...ልጅት ደስ እያላት እየሞቃት መጣ... :D

"" ይሀውልሽ እዚህ አገር እንደምታውቂው ከምግብ በኌላ እንደ ዴዘርት ኬክ ወይም ሌላ ቀላል ነገር ይበላል...ኢትዮጵያ ከምግብ በኌላ የሚቀርብ ነገር አለ.."?"

ልጅት አላመነታችም.....መልስ ሰጠች
"" አዎ አለ...""

""ምን..? ""

""ገንፎ!!"" :D

ቤቱ በሳቅ ተሞላ :: እኔ አልሳኩም ብቻ ቀስ ብዬ ባይኔ የልጆቿን ወላጆች መፈለክ ጀመርኩ:: :D :D [/color]
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ክቡራን » Tue Nov 20, 2012 11:42 pm

አሁን ሬድዮ እያዳማጥኩ ነበር ሳልፈልግ የሪፐብሊካን ቻናል ገባሁ...የእስራኤልንናና የኅማስ ጉዳይ ተነሳና የፈረደበትን ኦባማ መውቀር ጀመሩ:: ግልጽ ድጋፍ ለስራኤሎች አልሰጠም ከመጋረጃ በስተጀርባ ነው ድጋፉን የሚያደርገው..ይሄ...ጠቌራ አሉ ( በውሽጣ ውሽጢ..) :D ..መልሰው ደሞ እሱን ተውትና ባለፈው ማኬይንን ከሱዛን ጋ ችግር ካለብህ , ዮ ጋት ኤ ፕሮብሌም ዊዝ ሚ!! የሚለው አባባሉ ሲቆይ...አባነናቸው መሰለኝ...""ምን ማለቱ ነው ..ምን አስቦ ነው ..??" ወ.ዘተ እያሉ ወሬ ማማንዠክ ጀመሩ......አንዱ የሬድዮ ሆስት ጔደኛቸው ደሞ አዲስ ነገር ልንገራቹ አለና ይሄን አለ...""አን ኢምፖሎይመንት ሓርት አታክን እንደሚጭምር ታውቁ ነበር..?" ሲል ጠየቀ:: ሌሎቹ ሰምተውት የማያቁት አዲስ ጝኝት እንደሆነ ሁሉ እንደማያቁ ተናገሩ..
ቀዳዳው ሰውዬ መቀደድ ጀመረ.."" ይሀውላቹ እንግዲ ዱክ ዪነቨርስቲ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያመልከተው አን ኢምፕሎይመውንት በከፍተኛ ደረጃ ሀርት አታክ( የልብ በሽታን ) ይጨምራል:: በስመ ጥሩ የዱክ ዪኑቨርስቲ የሚካሄደው ጥናት አሳቀኝ:: እርግጠኛ ነኝ ለዚህ ጥናት ግራንት ተጽፎ እነ ቻርልስ , ወከርና , ሮበርት እንዲሁም ሜገንና አልበርት ተጠራርተውና ተቦዳድነው ፖሮፖሳል በማስገባት ደህና ሺ ዶላር ልፈውበታል!! አን ኢምፕሎይመንት አይደለም የልብ በሽታ የሚጥል በሸታስ ቢያመጣ ምን ይደንቃል..? ላሜሪካ እኮ መስራት ለመኖር ነው...የሚኖረውም ለመስራት ነው...ኤዲያልኝ ኤዲያ.. ድንቄም ጥናት..:x
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Wed Dec 26, 2012 9:44 pm

ፒያሳን ከመሸ አየኌት....ቀን ከሀሩር ሌሊት ከቁር እንዲጠብቃት የከለለቻቸው ጣራዎቿ አርጅተውና ፋብሪካቸው የቀባቸው ቀለሞች ወይበው ቀዮቹ ቀዮ ሆነው አሉ:: ፒያሳ በምሽት ትጨልማለች አትደምቅም....የመንግድም ሆነ የቤት መብራት የላትም:: አንዳንዱ ካፌ ቦታዋ እንደውም እንግዶቿን በሻማ ታስተናግዳለች:: ትልቁ የመብራት ሀይል ኅንጻ ግን እዛው አፍንጫዋ ስር አሁንም. ሰልፉን አሳምሮ ተሰድሯል..የፓያሳን እርጅና ለማየት የፈለገ ሰው ከሸዋ የኅገር ባህል ምግብ ቤት ፎቅ ላ ይ ህኖ ወይም ቢያድግልኝ ካፌ ቤት ላይ ቀሽር ሻይ እየቀሸረ ጣራዎቹን ማየት ይችላል:: የዛፍ እድሜ በቀለበቶቹ እንደሚታወቅ የፒያሳ ጣራዎች የፒያሳን እርጅና ይመሰክራሉ...የቀድሞው የኖቼራ ልብስ መሸጫ መደብር እንደታጠፉ የምትገኘዋ የከተማን ቤት ግሮሰሪ ተከትሎ ወደ አርሾ ቤት ሲኬድ የሚታዩት ቤቶች ግራ ቀኝ ተያይዘው አንዱ ሌላውን ኪሲንግ እየሳሙ ተደጋግፈው ቆመዋል:: ጣሮቿቸው ገርጥተውና ሸብተው የጨለማ መንፈስ ውስጥ የገቡ ሲመስሉ የሚጥል በሽታ የያዛቸው ዲጎኔ የሚባሉ መናፈስታት ዲስኮ የሚደስኩበትም ይመስላሉ:: የሚገርመው በነዚህ አሮጌ ጣሮች ላይ ዲሾች አሉ:: ዲሽ በፒያሳ ርካሽ ነው:: እንኴን ሌባ ሳምባ የጠገበ ዱርዬ ድመት ቢዘልበት ጥርምስ የሚሉ ጣራዎች ዲሾችን ግን በላያቸው አዝለዋል:: እንኚህ እንደ ዩፎ የመሰሉ ዲሾች ለፒያሳ ጣራዎች ውበት ናቸው :: ያም ሆኖ ግን ፒያሳ አርጅታለች...እርጅናዋን ዲሾች አልደበቁላትም:: አይኖቿ መጭሙጨዋል ግን አልሞተችም:: አልሞተችም የምለው ሞታለች ተብሎ ጡርምባ ስላልተነፋለት ይሆን..? የማህሙድ ቤት ጋ ጠብቂኝ ጸሀፊ የፒያሳን የሞት መርዶ አይነገረን ም:: ፒያሳ ለሱ ውብ ደሴት ናት:: እሱ በፒያሳ የካፌዎች ብዛት ፈንዲሻ በፈንዲሻ ሆኗል....ክሪያዚስ ካፌ ቤት በላፈው ማኪያቶ መርቅኖ በኅዘን ያሸለበችውን ና ፈንግል እንደያያዛት ዶሮ ፍንግል ልትል ቀኗን እየጠበቀች ያለውችን ፒያሳ እዝነ ህሊናው ሊያሳየው አልቻለም:: ፒያሳ ደክማለች መጣሁ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Fri Jan 11, 2013 12:34 pm

ሰለ ፒያሳ ጀመርኩ እንጂ አልጭረስኩም:: እመለስበታለሁ:: ሌላ ነገር ልጻፍ!!
***እኛንና እኛን በተመለከተ ነው:: እኛ እኮ በወረት የምንኖር ሰዎች ነን ..ወረተኞች ነን...ያለፍንበትን እንረሳለን...ትናንት ያለፍንበት ኅይወትና ኑሮ እውን ሳይሆን ህልም ነው... የህልምዣትም ነው:: ተረስቷል... በኗል.... እንጦርጦስ.... ገብቷል...ዞረን እንኴን ልናየው ይቅርና ልናስበውም አንፈልግም:: ""ሰው በትናንት ማንነቱ ሳይሆን በዛሬው እሱነቱ ይለካል"" ብለን የሚጎንጠንን ህሊና ዝም ጸጥ እናሰኝዋለን:: በውነቱ ከሆነ እኛ እንሰሶች ነን:: አንዳንድ የሚባሉ ልዩነቶች አሉን... እንሰሶች ያሟዣካሉ እኛ እንበላለን...እንሰሶች አይጽፉም እኛ እንጽፋለን..አንዳንዶቹ ለምሳሌ እንደ ከርከሮ አጋዘን አይነቶቹ ቀንድ አላቸው እኛ ግን ቀንድ የለንም...ይኅው ነው ..ቡዙም ልዩነት የለውም...ውስጣችን የተደበቀውን አውሬ በዲፖላምሲያዊ መንገድ በለበስነው ልብስና በውሸት በፈገግታ ሸፍነንዋል..አዉዉዉ ብለን አለመጯሀችን እንጂ ጅብ ስላለምሆናችን ምንም ማረጋገጫ የለም:: {ህንዶች የሚሉት ሪእንካሪኔሽንን ላፍታ ያስቧል::} ትናንት ስብሰባ ላይ ነበርኩ:: ላምስት አመት ኮሌጃችንን ስታስተዳድረው የነበረችው ፕሬዝዳንት ቦርዱ ባንድ ምሽት ባድረግው ዝግ ስብሰባ አባረራት:: በዚህ አግር አገላልጽ ስሶት አይነት ቌንቌዎች አሉ ""ፋየር"" , ""ቮልንተሪሊ ሪዛይን"" እና ደሞ መለየት ወይንም ""ሴፓሬሽን.."" ይባላል የደረሰን ኢ ሜይል ባጭሩ የሚለው ሺ ኢዝ ሰፓሬትድ ፍሮም ዚ ኮሌጅ ነው:: ያ ማለት አሁን የለችም ማለት ነው:: ኦቨር ናይት በሆነው ነገር ስለሷ የሚያወራም ቀርቶም የሚያስብም እንኴን የለም:: አዲሷን ኢንተርም ፕሬዝዳንት ለመቀበል ግን ሽር ጉዱ ግን ጦፏል:: ያዲሷ ፕሬዝዳንት ቲፎዞዎችና ስታፍ ሜምበሮች በሽቶና በክራባት ታጅለው ወዲያ ወዲህ ይላሉ:: ሞር ሰው ለመምስለ ነው ልብስ የለበሱት እንጂ የዱር አውሬዎች ናቸው:: ብቻ አዘንኩ ያዘንኩት በርሷ መባረር እይደለም:: በሰዋዊ ባህሪያችን አዘንኩ:: እኛ ማለት እኮ የምናንገር የምንጽፍ አሳሞች እንጂ እግዚአብሄር መጀመሪያ አስቦ የፈጠረን ሰዎች አይደለንም:: ካላመናችሁኝ ዞር ዞር በሉና አካባቢያችሁን ቃኙ:: ሰላም ቀን::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Sat Jan 12, 2013 3:26 am

እረ ጉድ ነው ከላይ የጻፍኩትን አስተያየት መልሼ ሳነበው አንድ ነገር በውስጤ መጣ ..የትኛ ው ክፍል እንደሆነ ግን አትጠይቁኝ እንጂ መጽሀፍ ቅዱስ ላይ አንድ ጥቅስ አለ!! ( ዘፍጥረት ውስጥ ይመስለኛል ግን..!! "" እጊዚአብሄር ሰውን በመፍጠሩ ተጸጸተ "" የሚል ነገር አለ:: በስኅተት ይሆን እንዴ የተፈጠርነው?? ወይስ የተሰጠንን ዲምክራሲያዊ መብት ተጠቅመን ራሳችን ስህተቶች ሆንን..? ጉድ ነው እስኪ መጣሁ ... ??
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Sat Jan 12, 2013 11:08 pm

ለነገሩ "" እግዚአብሄር ሰውን በመፍጠሩ ተጸጸተ"" የሚለው አባባል ስህተቱ አይታየኝም:: ጥሩ ሰዎች ያሉትን ያህል ዲያቢሎስ እየነዳቸው ወይም የስጋ ፍቅር እየመራችው ብቻ ክፋትንና ሀኬትን ሸርንና ምቀኝነትን አመጸኛነትንና ዘረፋን ዘረኝነትና ጥላቻን በየሄዱት የሚዘሩ ቡዙ አሉ እኮ:: እንደ መጽናናትና ሎቲ አይነት ባህሪይ ያላቸውን ሰዎች በእጊዚአብሄር አንጻር ነው የተፈጠሩት ብንል የእግዚአብሄርን ክብርና ሀይል እንዲሁም ማንነት መፈታተን አይሆንም..? አሁን ያ ወንድሜ ዲጎኔ በእጊዚአብሄር አምሳል ተፈጠረ ብል ማን ሊያምነኝ ይችላል..?? እግዚአብሄር እኮ ሁሉ በሁሉ የሆነ ሁሉን የሚችል Omnificent and Omnipotent ነው:: በዚህ ጉዳይ ላይ እጸልይበትና መንፈሳዊ ጥልቀት ያለው ማብራሪያ ይዥ እመጣለሁ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Wed Mar 13, 2013 2:13 pm

እቺን ፈኒ ፒክቸር ልጋብዛቹ...ግብዣ መቼም እኔጋ በሽ እኮ ነው.. :D እጀ መንገዴንም የተረሳችዋን ቤቴን ወደ ሳሎን ጎተት ላደርጋት በማስብም ጭምር ነው...ይጻፍባታል..ሰሞኑን ደሞ.. :D እቺን ጠቅ
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Thu Apr 04, 2013 1:56 am

በቀደም አንድ ሬድዮ ሰሰማ አንዱ የሬድዮ ፊታውራሪ ያንን የፈረደበትን ወያኔ የምንጥለው ""በማዕቀብ"" ነው አለና ሲያበቃ የማእቀቡን ዝርዝር ሲገልጽ ሳቄ መጣ:: ስስቅ ግን ከኌላቸው እንደሚያመልጣቸው የዋርካ ጊደሮች ቁቅቅቅ አላልኩም:: እዚህ ዋርካ በተለይ ሁለት ጊደሮች አሉ;;; ቁቅቅቅቅቅቅ.... ቁቅቅቅቅ ..የሚሉ:: አንዱ ደህና ነበር..ምን ያደርጋል ግን ""ካህያ የዋለ ጊደር ፈስ ተምራ መጣች"" የሚባለው እዚህ ዋርካ ላይ ሲሰራ አየነ... ይህን ለጊዜው እናቆየውና ወደዚህ የሬድዮ ፊታውራሪ ልውሰዳቹ እሱ እንደሚለው ካገር ቤት የሚመጣ እንጀራን ባለመብላትና ወዳገር ቤት የስልክ ካርድ እየገዙ ባለመደወል ወያኔን ባፍጢሙ መድፋት እንደሚቻል አድማጮቹን እያስረገጠ ያስረዳቸው ነበር:: እሱም ያድማጮቹን ሞራል እያገኘ ሲጮህ አድማጮቹም እልል ሲሉ ቆዩና የመጨረሻዋ ፓርት ፕሮግራሙ ሲያልቅ አካባቢ ያለው ግን አሳቀኝ ""ቁቅቅቅ"" አላልኩም እንደ ጊደሮቹ:: ""ለምንደነው የማትረዱን??" ሲል ተቆጣ.. :D ""እዚህስ መከራቸውን እያዩ እንጀራ የሚጋገሩትን ወገኖችስ የማትረዱት ለምንድነው?"" ሲል አይኑን አጉረጠረጠ:: አሁን ጨዋታው ገባኝ:: ካገር ቤት የሚመጣው እንጀራ ኦርጋኒክ በመሆኑ እዚህ በዋሽንግተን ፍሎር የሚጋገረውን እንጀራ ከጨዋታ ሜዳ እያስወጣው መሆኑ ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም:: ሰው ደሞ ረጅም እድሜን መኖር ፈለገ:: ብሊች በተደረገና ፕሮሰስ በሆነ የፋፍሪካ ውጤት ሆዴን አልቀፈድደውም አለ:: እና ምን ይሻላል..? ንግዳችን መቀነሱን በወያኔ ከምናሳብብ እውነቱን ተናግረን ለምን የመሸበት አድረን አዉውውውው!! የሚለው ጅብ አይበላንም..? አይ አቶ ምርጫው:: ለነገሩ አጅሬ የራጉኡልን ቤተ ክርስቲያን ከፍቶ የሚቀድስለት ዲያቆን ሲያጣ ቅዳሴ በዲሲ ከመጋረጃ ጀርባ በየሰንበቱ የሚያስነካ ወንዳታ ነው:: :lol: :lol:
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8914
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests